1
ይድረስ ለኢትዮጵያዊ
በቅድሚያ እንኳን ለዛሬዋ ዕለት የአምላክ ፈቃድ ሆኖ መልእክቴን ለማንበብ አደረሳችሁ እላለሁ፡፡ ለዚህም የምሰጠው ምክንያት ማንም ሰው በራሱ ብቃት ቀኒቱን ሊያገኝ የሚችል የለምና፡፡ ሥልጣንም ቢሆን ከላይ ከአርያም ካልተሰጠ፣ ሰው በገዛ ኃይሉና በወገናዊነቱ ሊያገኘው አይቻለውም፡፡ በመሆኑም ዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው ህውሃት/ኢህአዴግ ምንም እንኳ በአሜሪካና በእንግሊዝ መንግሥታት (USA & UK) “አይዞህ እኛ አለንልህ” ብለው ለሥልጣን ቢያበቁትም፣ የእግዚአብሔር ፈቀድ መሆኑን አንባቢ ያውቀው ዘንድ እፈልጋለሁ፡፡ እንዲህም ስል የወያኔ ዘረኛ መንግሥት ደጋፊ ሆኜ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጨካኝ መንግሥት ተላልፎ የተሰጠው ያለ ምክንያት ሳይሆን በሃይማኖት አለቆች ማስተዋል ማጣት እንደሆነ በማስረጃ የተደገፈ መልዕክቴ የኢትዮጵያ ሕዝብ በያለበት አገር እውነትን አውቆ፣ መደረግ ያለበትን በአሽቸኳይ ተግባራዊ ያደርገው ዘንድ ለማሳሰብ ነው፡፡ ጽሁፉም ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው በመሆኑ፣ ሃይማኖት ከፖለቲካ፣ ከማህበረ ሰባዊ ኑሮና ከወታደር ስርዓት ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡ መልዕክቱ በእውነት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ እውቀት ይገኝበታል፣ ራሱንም ከጥፋት እንዲያወጣ መንገዱን ያሳያል፣ ወገንን ለመምከር፣ ለማስጠንቀቅም ይረዳል እስከ መጨረሻው ለአነበበ፡፡ “የተሸፈነ መገለጡ፣ የተደበቀ መውጣቱ አይቀርምና በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን አውሩት፣ በጆሮአችሁ የሰማችሁትን በአደባባይ እውጁት … ” በተባለው መሠረት የተጻፈ ነውና፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ማን በሰላም ውሎ ያድራል ቢባል፣ ከሕፃናት በቀር አንድም ሰው እንደሌለ ርግጠኛ ነኝ፡፡ ለሰላሙ መደፍረስ በዋናነት የሚጠቀሰው ህውሃት/ኢህአዴግ እንደሆነ ቢጠቀስም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም የራቀው ከ1966 ጀምሮ ነው ቢባል ስህተት አይሆንም፡፡ ይህም ከዘመኑ መጨረሻ ጋር የተገጣጠመ በመሆኑ በህውሃት/ኢህአዴግ ዘመን ግን ብሶበት ነው ያለው፡፡ ዲሞክራሲን ፍለጋ የተጀመረው አብዮት እስከ ዛሬ ግቡን ሳይመታ ለብዙ ኢትዮጵያዊያ ሕይወት መጥፋትና ስደትን አስከትሎም በአርባ ዓመት ውስጥ ዛሬም እንደ አዲስ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ የእውቀት ማነስ እንዳይባል፣ ብዙ ምሁራን በውጭ አገራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎችን በማስተማር ላይ ናቸው፡፡ በጎሳ ልዩነት እንዳይባል፣ ዛሬም በጎሳዎች መካከል ጋብቻ እየተካሄደ ነው፡፡ የሃይማኖት ልዩነትም እንዳይባል፣ በእስር የሚማቅቁት በተለያዩ የእምነት ተቋማት ያሉ እንደ ሙስሊም፣ ፕሮቴስታንት፣ ኦርቶዶክስ አማኞች ናቸው፡፡ ወገንተኝነት እንዳይባል የትግራይ ተወላጆች ከስቃዩ ተካፋዮች ናቸው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መብዛትም ከሆነ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ የጉዳያችን ውስብስብነት በሰው አዕምሮና በተደራጀ የጦር ኃይል ብቻም የሚፈታ አይደለም፡፡ እንዲያ ስል መፍትሄ የለውም ማለት አይደለም፡፡ ጊዜው ደግሞ ኢትዮጵያ በዲሞክረሲ እስክትመራ የሚጠብቅ ሳይሆን ወደ ፍፃሜ እየተቿከለ ነው፡፡
ይህን መልዕክት ለመጻፍ ምክንያት የሆነኝ ኢትዮጵያን በተመለከተ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ተስፋዎች ደጋግሜ ስለማነብና የእግዚአብሔርን ጉብኝት በናፍቆት ስለምጠባበቅ፣ የተስፋ ቃሉ መዘግየት ለብዙዎች መልካም መሆኑን በመረዳቴ አምላኬን አመስግኛለሁ፡፡ እንዲያም ለማለት ያስቻለኝ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ አጀንዳ፣ አሁን ላለንበት ለመጨረሻው ዘመን ሠራዊቱ ይሆኑለት ዘንድ በ630 ዓ.ም አካባቢ የነቢዩ ሙሐመድን (ሶ.ዐ.ወ) መልእክት ሰምተው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ቤተሰቦች የተወለዱ ኢትዮጵያዊያን፣ በሥልጣን ላይ ያለውን የህውሃት/ኢህአዴግን መንግሥት ለመጣል አምርረው መነሳታቸውን በማየቴ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ በማስጨነቅ ለ21 ዓመታት ገዝቶ በሞት የተለየውን ነፍሰ ገዳዩ መለስ ዜናዊን በተመለከተ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለበረከት የተሸመ ይመስል “መለስን ያበቀለች ምድር ሌላ መለስን አትሰጥም ማለት እንዴት ይቻላል?” የሚሉ የፕሮቴስታንት (የጴንጤቆስታል) ሰዎች ንስሃ ለመግባት ጊዜ ስለ አገኙ ነው፡፡ “በዐይናቸው አይተው፣ በጆሮአቸው ሰምተው በልባቸው አስተውለው በመመለስ ይፈወሳሉ”የሚል ቃል አለና፡፡
በነቢዩ ሕስቅኤል በምዕራፍ 34 እና በምዕራፍ 40 ውስጥ የግሳጼና የማጽናኛ ቃላት እንዲህ ይላሉ፡- 1. “አንተ የሰው ልጅ ሆይ ለአገርህ ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ እረኛ በማጣት ተበተኑ፥ ለምድርም አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ፥ ለተበተኑም በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፤ የሚፈልግም አልነበረም። እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፡፡ እነሆ፥ በእረኞች ላይ ነኝ፥ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፡፡ እረኛ በተበተኑት በጎች መካከል ባለ ጊዜ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ ከአሕዛብም ዘንድ አወጣቸዋለሁ ከአገሮችም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም አመጣቸዋለሁ፡፡ እኔ በወፈሩት በጎችና በከሱት በጎች መካከል እፈርዳለሁ።” 2. “የሰው ልጅ ሆይ፣ በዐይንህ እይ፣ በጆሮህ ስማ፣ የማሳይህንም ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፣ ወደዚህ የመጣሃው ለዚሁ ነውና፣ ያየህውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር::” በተባለው መሠረት የተጻፈ መልእክት በመሆኑ ለችግራችን መነሻው የቤተ ክርስቲያናት ሰዎችም ጭምር መሆናቸውን ለማሳወቅ ነው፡፡ እንዲያ ስል የወያኔ ባለሥልጣናትን ነፃ ማድረጌ አይደለም፣ ከወያኔ ሠራዊት ጀርባ ልዩ ኃይል መኖሩንና በወኔ ብቻ ማሸነፍም እንደማይቻለን ለማሳሰብም ነው፡፡
የሕዝቅኤል ትንቢታዊ መጽሐፍ ለእኛ ኢትዮጵያ መሆኑን በተመለከተ፡- የእስራኤል ሕዝብ በበግ አይመሰልም፣ በጎች የሚባሉት ወንጌል ሰምተው በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ብቻ ናቸው፡፡ በወንጌል ያመኑም ቢኖሩ በአሕዛብ ሥር ሆነው ነው፡፡ የእስራኤል መንግሥት በሕዝቡ መካከል ልዩነት አያደርግም፣ ሕዝቡም በረሃብ የታወቁ አይደሉም፡፡ በእስራኤል የፖለቲካ እስረኛ የለም፣ ጋዜጠኞች እውነትን በመጻፋቸው አይታሰሩም፡፡ ኢትዮጵያዊያን ግን በዓለም ሕዝቦች የምንታወቀው “ረሃብተኞች እና ስደተኞች” ተብለን ነው፡፡ በሥልጣን ላይ ያለው ህውሃት/ኢህአዴግ መንግሥት ሕዝቡን ከፋፍሎ እየገዛ ነው፡፡ ብዙዎችን በአደባባይ ረሽኖአል፣ አስሮአል፣ ከመኖሪያው አፈናቅሎአል፣ ብዞችም ስደተኞች ሆነናል፡፡ ኢትዮጵያ ፍትህ የሌለባት አገር ሆናለች፡፡ እስራኤላዊያን ከዓለም ሁሉ ወደ አገራቸው ገብተዋል፣ እየገቡም ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊውን ደግሞ በአርባ ዓመታት ውስጥ ዛሬም በስደት ላይ ነን፡፡ በልቡ ስደትን ያልተመኘም የለም፡፡ በአውሬ እየተበሉ ያሉት፣ በስደት ላይ ያሉ ብቻ ሳይሆን፣ አዲስ አበባ ውስጥ ስንቶች በጅብ መንጋ እንደተበሉ በጋዜጦች አንብበናል፡፡ የወፈሩ በጎች ዳግም አስመሳይ ክርስቲያኖች የህውሃት/ኢህአዴግ አፈ ቀላጤዎች ካህናት፣ ፓስተሮች እና ሼኾች መሆናቸው አይካድም፡፡ ሌላው ደግሞ በመዝሙር 74፡14 “አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።” የሚለው ቃል መጻፉም ያለ ምክንያት አይደለም፡፡
እግዚአብሔር፣ ለአይሁዱ ለክርስትያኑና ለሙስሊሙ ሁሉ አባት ለሆነው፣ ለአብርሃም በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት እስራኤል በአገር ደረጃ ከታወቀች ከ1948 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ጀምሮ በሰማዊው እሳት የታጠረች አገር ናት፡፡ በመሆንዋም እንደ ጠላቶቿ ብዛት ድንበር ጥሰው ሊገቡ አልቻሉም፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ ለዘመናት በእግዚአብሔር ጥበቃ ነፃነቷ ተጠብቂ ብትቆይም ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ ሰማያዊውና ምድራዊው ቅጥሯ ፈርሶአል፡፡ሊፈርስም የቻለው፣ የሚዋጉላት አርበኞች ሞተው አልቀዋል ማለት ሳይሆን፣ ጃንሆይ፣ የቀድሞ ንጉሥ፣ በእግዚአብሔር ታምኖ ከመቆም ይልቅ በሲ.አይ ኤ አቀነባባሪነት የዓረብ አገራትን ዛቻ በመፍራት የተከሰተ ነው፡፡ በመሆኑም ጠላቶቿም በአሻቸው ሰዓት መግባትና መውጣት ችለዋል፡፡ በልማት ስም የፈለጉትን ያህል መሬት ወስደው ባለመሬቱ ጭሰኛ ሆኖአል፡፡ በንጉሡ ዘመን በጭሰኝነቱ አንድ ሶስተኛ ያገኝ የነበረው፣ ዛሬ ያንተ ነው ከተባለው መሬት የተመረተውን ሊቀምሰው አልተቻለም፡፡ ምድሪቱ እንደ ሴተኛ አዳሪ በኢንቬስትመንት ስም ገንዘብ ይዞ ለመጣ ሁሉ አገልግሎት ሰጪ ሆናለች እንጂ ኢትዮጵያዊው የልማቱ ውጤት ከመስማት ባለፈ ተጠቃሚ ሊሆን አልቻለም፡፡ እንደ ቀድሞ እስራኤል፣ ኢትዮጵያ ተላልፋ ለባዕድ ያልተሰጠችው፣ እግዚአብሔር ኃያልነቱን ለዓለም የሚያሳይበት መድረክ በመሆንዋ፣ ለተቀደሰ ዓላማውም አገልጋዮቹ ጥቂቶች ቢሆኑም ከመድረኩ አልጠፉም፡፡ ዛሬ እኛ ኢትዮጵያዊያን ወያኔን እንደምንቃወም፣ ከአብዮቱ ጅማሬ በፊትም “ኢትዮጵያ ለአሜሪካ 53ተኛ ክፍከ አገር (ስቴት states) አትሆንም፣ ለአሜሪካና ለእንግሊዝ አንበረከክም”፣ “ኢምፕሪያሊስትን እንዋጋለን”እያሉ ድምጻቸውን የሚያሰሙ እንደነበሩ፣ ዛሬም ጥቁቶችም ብንሆን አለን፡፡ ልጆቼ! “ውሻ በቀደዳ ጅብ ይገባል” እንዳሉት በጅቦች ባህርይ የመጡብን ወያኔዎች በአካል፣ በስነ ልቦና እና በመንፈስ እየገደሉን ናቸው፡፡
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ኢትዮጵያ ከእስራኤል ይልቅ የእግዚአብሔር በኩር ልጅ ናት፡፡ ብኩርነታችን በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠበቀ ሆኖ ሳለ፣ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ግን እንደ ኤሳው ብኩርናቸውን ለተለያዩ ጊዜያዊ ጥቅሞች የሸጡ ጳጳሳትና ፓስተሮች “ለባለ ሥልጣን ተገዛ”በሚል መፈክር ሕዝቡ ከፈጣሪው እንዲርቅ በማድረጋቸው፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ላለው እልቂት ተጠያቂ ናቸው፡፡ ከፈጣሪም ዘንድም ሳይቀጡ አያመልጡም፡፡ እግዚአብሔር ከጅማሬው መጨረሻውን የሚያውቅ አምላክ በመሆኑ ዘላለማዊ አጀንዳውን ተግባራዊ ለማድረግ ያዘጋጃቸው ሙስሊም ወገኖች አምርረው በኢትዮጵያ ጠላት በህውሃት/ኢህአዴግ ላይ እንዲነሱ አድርጎአል፡፡ በ”ድምጻችን ይሰማ” የተጀመረው ትግል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ድልን እንደሚያጎናፅፍ እርግጠኛ ነኝ፡፡ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ግን ፖለቲከኛ እንዳይባሉ አባል እህቶችን የዲቦራ ምሳሌ፣ ወንድሞችን የዳዊት ምሳሌ ሆነው በአደባባይ ከጣይቱና ከሚኒልክ ልጆች ጋር ድምፃቸው እንዳይሰማ አድርገዋል፡፡
2
የኢትዮጵያ ጠላት በሥጋ የተገለጠው ህውሃት/ ኢህአዴግ ብቻም ሳይሆን የኔፊሊም መንፈስ ተላብሰው እንደ ጎልያድ ነጋ ጠባ በእጃቸው ባለው መገናኛ ብዙሃን ሕዝቡን እያስፈራሩ መሆናቸው እየታወቀ፣ እንደ ጵንጤዎች መንፈሳዊ መረዳት ኀይለማርያም ደሳለኝ ዳዊት ከሆነ፣ ጎልታድ ማን ሊሆን ነው? ሂትለር አይሁድን የፈጀው በካቲሊክና በፕሮቴስታንት ድጋፍ እንደነበር፣ ዛሬም የጣሊያን ባንዳ ልጆች የኢትዮጵያን ሕዝብ ከምደረ ገጽ ለማጥፋት ለተነሱት ለህውሃት/ኢህአዴግዎች ድጋፍ መስጠት በራሱ ከሃሰተኛው ክርስቶስ ጋር ሕብረት ማድረግ እንደሆነ ምነው ሕሊናችው ዘነጋው? “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፣ … መብራት አብርተው ከዕንቅብ ስር ያስቀምጡትም” መባሉ እኮ የጨለማውን ገዥና ካድሬዎቹን ማባረሪያ ሆኖ ሳለ፣ በጨለማው ገዥ መደናቀፉ ለምን ይሆን? ኢሳይያስ 52፡1 “ጽዮን ሆይ ተነሺ፣ ተነሺ ኃይልን ልበሺ፣ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ የክብር ልብስሽን ልበሺ፣ ያልተገረዘ የረከሰም ከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም፡፡” እንደ ተባለው ፕሮቴስታንቱ በህውሃት-ኢህአዴግ እና ተባባሪዎቹ ላይ ካልተነሳ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡ “አንተ የተኛህ ንቃ” መባሉ ለዚህ ጊዜ ካልሆነ ለመቼ ነው? ብሉይ ኪዳን ለአዲስ ኪዳን ጥላ እንደሆነ በወንጌል አማኞች ዘንድ የታመነ ነው፡፡ እስራኤላዊያን ከ430 ዓመታት የባርነት ዘመን በኋላ በሙሴ መሪነት ከግብፅ ወጥተው ወደ ከነዓን ለመግባት በአርባ አመታት ውስጥ ከኔፊሊሞችና ከየዔናቅ ሰዎች ጋር ተዋግተው ከነዓን መግባታቸው ቢነገርም፣ የእግዚአብሔር ሰዎች ማረፊያ ቦታ ከነዓን የዛሬዋ ኢስራኤል ሳትሆን ጽዮን መሆንዋ የምናውቀው ዕብራዊያን ምዕራፍ አራትን ስናነብ ነው፡፡ በምዕራፍ 4 ቁጥር 8 “ኢያሱ ዕረፍት ሰጥቷቸው ቢሆን ኖሮ፣ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረም ነበር፡፡ ስለዚህም የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ገና ቀርቶለታል::” የሚለውን ስለተጻፈ የወያኔ ሠራዊቶች፡- አግአዚ፣ ፌድራል ፖሊስና ደጋፊዎቻቸው አውቀውትም ሆነ አላወቁት የኢትዮጵያን ሕዝብ እየተዋጉ ያሉት እንደ የኔፊሊሞችና የዔናቅ ሰዎች ወደ ጽዮን አላስገባም እያሉ ናቸው፡፡ ይህም መንፈሳዊ ውጊያ ላይ መሆናችንን የሚያመላክት መሆኑ በእግዚአብሔር ቃል “እናንተ ግን ወደ ፅዮን ተራራ ወደ ሰማያዊ ኢየሩሳሌም ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ መጥታችኋል” እያለን ስለሆነ፣ ዉጊያችን በሥጋና በደም ብቻም ሳይሆን መንፈሳዊም በመሆኑ በክርስቶስ ቅዱስ ደም የተዋጀ መንፈሳዊ ሰውም ለጦርነት መነሳት እንዳለብን ነው፡፡ ከግብፅ ወጥተው ከነዓን ሳይገቡ እንደቀሩት፣ የህውሃት ደጋፊዎችም ለጽዮን የተገባላትን በረከት እንደ ወጡ የሚቀሩና በውስጥም ያሉ በሞትም ይሁን በስደት እንደማያዩ ነው፡፡ በዳዊት መዝሙር 87 ፅዮን “ኢትየጵያ የአሕዛብ እናት” ተብላለችና፡፡
እግዚአብሔር በዘላለም ዕቅዱ መሠረት፣ አዳም የተፈጠረው፣ ሔዋንን ከአዳም ግራ ጎን የወጣችው፣ በሰይጣን የተታለለችው እዚሁ በምድራችን ነው፡፡ ዛሬም ሰይጣን ሙጢኝ ብሎ የያዘውና የዓለም ገዥ ለመባል የቀረው ኢትዮጵያ ናት፡፡ በመሆኑም ትግላችን ሥጋዊ ብቻም ሳይሆን መንፈሳዊም ጭምር ነው ያስባለውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ የህውሃት/ኢህአዴግ መንግሥት ሲወድቅ፣ ለዘመናት ምሽግ ሠርቶ የተቀመጠው የዲያብሎስና በክርስቲያን ስም የተሰለፉን አገልጋዮቹም አብረው የሚወገዱ ናቸው፡፡ የሃይማኖት ልዩነትም አብሮ ይወገዳል፡፡ በርግማን የመጡብን ረሃብና ቸነፈርም በኢትዮጵያ ስፍራ አይኖራቸውም፡፡ “የዘንዶውን ራስ ቀጥቅጠህ ለኢትዮጵያ ምግባቸውን ሰጠህ” የተባለው ትንቢታዊ ቃል ተግባራዊ ይሆናልናም፡፡ ወቅቱን በተመለከተ ሐዋሪያው ጳውሎስም በሮሜ 6፡15 “የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ” እንዳለው፣ ነቢዩ ሙሐመድም በአልተውባህ 9፡20 “እነዚያ ያመኑት ከአገራቸውም የተሰደዱት፣ በገንዘባቸውም በነፍሳቸውም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ፣ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡” መባሉ ከወያኔ ውድቀት በኋላ መሆኑ መታወቅ ያለበት ጉዳይም ነው፡፡ በመሆኑም የምንታገለው፣ የተባበሩት መንግሥታትን፣ አሜሪካንን፣ የአውሮፓ ሕብረትን በመማጸን አይደለም፡፡ በቅዱሳን መላእክት፣ በጻድቃናት እና በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትም የማይሆነው ኢየሱስ አርሱ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 በቁጥር 23 “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፣ አባቴም ይወደዋል፣ ወደ እርሱም እንመጣለን ፣ ከእርሱም ጋር እንኖራለን፡፡“ ብሎአልና፡፡ የቅዱሳን መላዕክት ሥራ ስለ እወነት የቆሙትን የሚጠብቁ ናቸው፡፡ እኛ ስንዋጋ ስለ እኛ ይዋጋሉ፡፡
የኢየሱስ ማንነት ለዘነጉ ፓትሪያርክ፣ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ መነኩሳትና ምዕመናት፡- 1. ሰዎች በልበ ሥላሴ ሳይቆጠሩ የዚያን ጊዜ ፍጡር ያይደለሁ እኔ ይህን ዓለም እጎበኝ ዘንድ አስቤአለሁና ቀድሞ በነቢያት አድሬ ኋላ ሰው ሆኜ ሥጋ ለብሼ አስተምራለሁ አለኝ፡፡ መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱእል 4፡6 2. ልዑል እግዚአብሔር ከጊዜው አስቀድሞ እንደተናገረ እወቅ፡፡ በዚህ ዓለም እንደሆነው ሁሉ አስቀድሞ በነቢያት እንደተናገረ ኋላ ሰው ሆኖ ሥጋ ለብሶ እንደ ታየ፡፡ መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱእል 7፡5 3. ክርስቶስም በመጣ ጊዜ ሐዲስ በሚሆን በመንግሥተ ሰማይ እንደ ፀሐይ ያበራል፣ የማይገባ ፀሐይ የማይጠፋም ፋና እኔ ነኝ ብሎአልና፣ እሱ እግዚአብሔር ብርሃንዋ ነው፡፡ መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱእል 8፡21 ስለዚህ መጽሐፉንም ካልሰማኽው ፈጣሪህ እግዚአብሔርን አልሰማኻውም፣ ሕጉንም ካልጠበቅህ እሱን አልወደድኽውም፣ ትዕዛዙንም አላደረግህም፣ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ካላደረግህ ለዘለዓለም ወደ ገሃነም ትገባ ዘንድ አለህ፡፡ መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ 7፡10-11
አንዳንድ የክርስትና እምነት አባቶች፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኢሳይያስ የተነገረው ትንቢት ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ታዲያ መጽሐፉን ከሃምሳ ዓመት በፊት ላነበበው ኢትዮጵያዊ ትርጉም የለሽ የሚሆንበት ምክንያት ትንቢቱ በአብዛኛው ተግባራዊ አልነበሩምና፡፡ ዛሬ ላይ ሆኖ ለሚያነበው ግን በአብዛኛው ትንቢቱ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ መፈጸሙን ብዙ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡ የቤተ ክርስትያናት አገልጋዮች ሊክዱት አይቻላቸው፡፡ ለችግሮቻችን ምክንያት የአገሪቱ አንጋፋ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ለሕዝቡ ማሰማት ችላ ማለትዋ ተከትሎ የመጣ ርግማን እንደሆነ ነው፡፡ ይህም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ከወንጌል ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለን የሚያመለክቱ ማስረጃዎቹም፡- 1. “ታማኝ የነበረች ከተማ እንዴት አመንዝራ እንደ ሆነች ተመልከቱ፣ ቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፣ ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፣ አሁን ግን የነፍስ ገዳዮች መኖሪያ ሆነች፣ ብርሽ ዝሎአል፣ ምርጥ የወይን ጠጅሽ ዉሃ ገባው፣ ገዥዎችሽ ዐመጸኞችና የሌባ ግብረ አበሮች ናቸው፣ ሁሉም ግቦን ይወዳሉ፣ እጅ መንሻም በብርቱ ይፈልጋሉ፣ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፣ የመበለቶች አቤቱታ አይሰሙም፡፡ ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ኃያል በባላንጣዎቼ ላይ ቁጣዬን እገልጣለሁ፣ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፡፡” ኢሳይያስ 1፡21-24 2. “ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፣ ሀብታቸው ልክ የለውም፡፡ ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፣ የሠረገሎቻቸውም ብዛት ልክ የለውም፡፡ ምድራቸው በጣዖታት ተሞልታለች፣ ጣቶቻቸው ላበጇቸው፣ ለእጃቸውም ሥራ ይሰግዳሉ፡፡ የተኩራራውን በሙሉ ሰው ዝቅ ብሎአል፣ የሰው ልጅም ተዋርዶአል፡፡ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእብሪተኛውን ሰው ዐይን ይሰበራል፣ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፡፡” ኢሳይያስ 1፡21- 3. ዐይናቸው እያየ፣ መሬታቸው በባዕድ ይነጠቃል፣ ጠፍም ይሆናል፡፡ የጽዮን ሴት ልጅ በወይን አትክልት ውስጥ እንዳለ ዳስ፣ በዱባ ተክል ውስጥ እንደሚገኝ ጎጆ፣ እንደ ተከበበ ከተማ ተተወች፡፡ ኢሳይያስ 1፡7 4. “ፍትሕ የጎደለውን ሕግ ለሚያወጡ፣ ጭቆና የሞላበትን ሥርዓት ለሚደነግጉ ወዮላቸው፣ የድሆችን መብት ለሚገፉ፣ የተጨቆነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፣ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው፣ በምጎበኝበት ቀን ምን ይውጣቸዋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታስ ለማግኘት ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ? ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፣ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም፡፡”ኢሳይያስ 10፡1-4
ከላይ ከአንድ እስከ አራት የተጠቀሱት ማስረጃዎች ለእስራኤል ነው የሚል ካህን ካለም፡- እስራኤል በአገር ደረጃ እውቅና ያገኘችው 66 ተኛው ዓመት ላይ ነች፡፡ ብዙ ብርና ወርቅ ቢኖራት እስካሁን ለዓለም ገበያ ታቀርብ ነበር፡፡ ፈረሶች የሏትም፣ በሥልጣን ላይ የነበሩ መሪዎችዋ በወገናቸው ላይ ግፍ ሲፈጽሙ አልታዩም ወይም አልተሰሙም፡፡ ለአንድ እስራኤላዊ ነፍስ ብለው በአንድ አገር ላይ ጦርነት ሲያነሱ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ ለነፍሰ ገዳዮች፣ ለሌቦች፣ ለጉበኞች ቦታ የላቸውም፡፡ ሕገ መንግሥታቸውን ያከብራሉ፣ ያስከብራሉም፡፡ እስራኤላዊን እስረኞች የሏትም፡፡ እምነታቸውን በተመለከተ በአስርቱ ትዕዛዛትና የእምነት አባት በሆነወ በአብርሃም አምላክ የሚያምኑ ናቸው፡፡ እኛ ግን ለብዙ መላዕክት፣ ለፃድቃናትና ለቅዱሳን በስማቸው ታቦት ተቀርጾላቸው ይሰገድላቸዋል፣ በአማላጅነታቸውም ቤተ ክርስቲያናት ተሰይሞላቸዋል፡፡ ፍትህ የለም፣ ኢህአዴግ አመጸኛ ነው፣ ግብረ አበሮቹ ግቦኞች ናቸው፡፡ ወላጅ የሌላቸው ልጆች በጉዲፈቻ ስም ተሽጠዋል፡፡ ስለ ወገኖች አቤት ያሉ ወገኖች ፍትህ በጎደለው ሕግ ዘብጥያ ወርደዋል፡፡
ከመጀመሪያው ሰው፣ ከአዳም ጀምሮ የሰው ልጅ ኑሮው የዱላ ቅብብሎሽ ሩጫን ይመስላል፡፡ አባትና እናት የያዙትን ንብረት ለልጆቻቸው አውርሰው እንደሚለዩ፣ መሪዎችም አገርን በመምራት በትረ መንግሥቱ (ሥልጣኑ) አፄ ኃይለ ሥላሴ ደርሶ በመጨረሻ የአገዛዝ ዘመናቸው ከዕድሜ መግፋት ይሁን በሌላ ምክንያት ተደናቅፈው የጣሉት በትረ መንግሥት ደርግ እጅ ገብቶ በኮነሬል መንግሥቱ ፈላጭ ቆራጭነት 17 ዓመት የኢትዮጵያ ሕዝብ በግፍ፣ በመከራ፣ በስደት ማለፍ ግዴታ ሆኖበታል፡፡ ከ17 ዓመት በኋላም ሥልጣኑ በህውሃት እጅ ገብቶ አቶ መለስም ግዳጁን አገባዶ ለቀጣዩ ሯጭ ለኃይለማርያም ደሳለኝ ተላልፎ ተሰጥቶአል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በሁለት ሐሳብ ያለ በመሆኑ አወዳደቁ ከሁሉ የከፋ እንደሚኖን አልጠራጠርም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ፣ “ለኢየሱስ ብቻ አድሬአለሁ፣ አገሬ በሰማይ ነው” የሚል ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ የሟች መለስ ዜናዊን ራዕይ በዓለም ደረጃ ለማስመዝገብ በመለስ ጫማ እየሮጠ ነው፡፡ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮችም “መለስን
3
ያበቀለች ምድር ሌላ መለስን አትሰጥም ማለት እንዴት ይቻላል?” በሚል መፈክር የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሹመት የጸሎት መልስ እንደሆነ ታምኖበት በጵንጤ አማኞች ዘንድ ሃሌሉያ አሰኝቶአል፡፡ በህውሃት/ኢህአዴግ ካድሬዎች ዘንድም ሙሉ ድጋፍ ተችሮታል፡፡ እስከ አሁን በተግባር እንደታየው በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የመሪነት ዘመን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአለፉት ዓመታት በበለጠ ስቃይ ውስጥ መሆኑ ማሳያው ብዙ ኢትዮጵያዊያን የተገደሉበት፣ ያለ ፍርድ የታሰሩበት፣ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉበት፣ የአገር ሀብት የወደመበት፣ ገንዘብ የተዘረፈበት፣ ቤተ ክርስቲያናትና ዩኒቨርስቲዎች የተቃጠሉበት፣ የአንድ አገር ሕዝብ በጎሳ ተለያይቶ እርስ በርስ እንዲገዳደሉ የተደረገበት፣ ዳር ድንበር ተቆርሶ ለሱዳን እና ለጅቡቲ እንደ ውለታ መላሽ ገጸ በረከት የተሰጠበት ነው፡፡ ደግሞም አሁን ካለው አስጨናቂ ጊዜ የከፋ መከራ በኢትዮጵያ እንደሚከሰት የትንቢተ ኢዮኤል መጽሐፍም ያስጠነቅቃል፡፡ ለእኛ ኢትዮጵያዊያንን መሆኑ የምንረዳው ሙሉውን መጽሐፍ ስናነብ ነው፡ ፡ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፤ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፣ ….፡፡ ኢዮኤል 2፡1-2 የዘመን ፍጻሜ ዋዜማ ላይ መድረሳችንን በተመለከተም፡- ኢዮኤል 2፡31 ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል። የሐዋሪያ ሥራ 2፡20 ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ። ራዕይ 6፡12 ማኅተሙን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፥ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠቆረች፣ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ቀላች፡፡ በቅዱስ ቁርኣን አል-ቂያማህ 75፡8 ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፣ ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፣ ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው? የሚለው እውን መሆኑን በሚያዝያ ወር ጨረቃ ደም መስላ መታየትዋ ተረጋግጦአል፡፡ ሂደቱም እስከ መስከረም 15 2015 (እኢአ) ድረስ በተለያዩ ጊዜያት አራት ጊዜ እንደሚደጋገም የጠፈር ምርመራ ጣቢያ NASA ባስተላለፈው ስዕላዊ መግለጫ ለማወቅ ተችሎአል፡፡ የጉዳዩ አሳሳቢነት የተረዱ በሰሜን አሜሪካ በወንጌል አማኞች የአሕዛብ ዘመን ማብቂያ መቃቡን በተመለከተ ምክሮችንና ማስጠንቀቂያዎችን ቀደም ብለው በመድረኮቻቸውና በድረ ገጾቻቸው አስታውቀዋል፡፡ አሕዛብን በተመለከተ ደግሞ ኢትዮጵያ የአሕዛብ እናት መሆንዋን በመጽሐፍ ቅዱስን ውስጥ በመዝሙር 87 ተጽፎልናል፡፡ መጨረሻ ዘመንም መዳረሳችን በተመለከተም እንደ ትንቢተ ዳንኤልም፣ ኢትዮጵያና ግብፅ በአባይ ወንዝ ምክንያት ንትርክ ገብተዋል፡፡ እንደተጻፈው ነገራት ሁሉ የሚሄዱ ከሆነ፣ የኢትዮጵያ ምሁር የታገሉለት ዲሞክራሲም በኢትዮጵያ ተግባራዊ ላይሆን ነው ማለት ነው፡፡ ደግሞስ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው እግዚአብሔር በመፍራት በፍትህ የሚያስተዳድረውን ሰው ነው እንጂ የኃያላንን ትዕዛዝ ተቀብሎ የሚያስፈጽም ሰውን ነው እንዴ? የሙሴ አማች ኢትዮጵያዊው ዮቶር ለሙሴ የመከረው አስተዳደር ሥርዓት ዲሞክረሲ ነውን? “የአሕዛብ ገዢዎች በሕዝባቸው ላይ ጌቶች እንደሚሆኑ፣ ባለ ሥልጣኖቻቸውም በኃይል እንደሚገዟቸው ታውቃላችሁ፣ በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም፡፡” ተብለናልና፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያውቀው የሚገባው ዲሞክራሲ ሥርዓት ለአሜሪካ መንግሥት ጥቅም ማስጠበቂያ መሆኑንና የዲሞክረሲ ምንጩ ከየት እንደሆነ ለማወቅ ይህን ድረ-ገጽ America Welcoming in Antichrist? Tom Horn on Sid Roth … መመልከት ነው፡፡
ለእኔ ለጸሃፊው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ለዘፍጥረት እስከ ራዕይ ያሉት ጽሁፎች በሙሉ ማለት በሚያስችል ደረጃ ትንቢታዊ ቃሎች ናቸው፡፡ ይህም እግዚአብሔር ሊሆኑ ያሉትን ነገሮች ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው ወደ መሆን የሚመጡ፣ እንደ ኮምፒዩተር ፕሮግራም (computer programme) የተጻፈ አድርጌ ነው የምመለከተው፡፡ አምላክም በኢሳይያስ 55፡11 ”ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።” እንዳለው ሰውም በኮምፒዩተር አንድን ሥራ ለመሥራት ወጥኖ በጻፈው ቅደም ተከተል ሥርዓት ውስጥ ሥራው ሳያጠናቀቅ በቃ endእንደማይል ነው፡፡ ኮምቲዩተር በቫይረስ እንደሚጠቃ ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስም “ጭማሪ፣ ማስተካከያ፣ በቀላል ቋንቋ” በሚል ቨይረስ መጠቃቱን የምናውቀው፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውስጥ ኢትዮጵያን በተመለከተ፣ “አንተ የዘንዶውን ራሶች ቀጥቅጠህ፣ ለኢትዮጵያ ሰዎች ምግባቸውን ሰጠሃቸው” የሚለው የተሰፋ ቃል በኦርቶዶክስ ሊቀ መንበርነት የሚመራው የመጽሐፍ ቅዱስ አዘጋጅ ማህበር መጠቃቱ ነው፡፡
በወንጌልም ሆነ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ የተጻፈው ማስጠንቀቂያም ይሁን ምክርና ማጽናኛ ሰውን ነው እንጂ ሃይማኖትን ወይም አገርን (ምድርን) አይደለም፡፡ አገርን በተመለከተ ለሁሉም ድንበር ሰርቶላቸዋል፡፡ ሰው ደግሞ የእግዚአብሔርን መልክና ዘላለማዊ ዕቅድ ይዞ ነው የተወለደው፡፡ አብርሃም የሰባ አምስት ኣዛውንት በነበረ ጊዜ ከአብራኩ የተወለደ አንድም ልጅ ሳይኖረው፣ “የእግዚአብሔር ቃል በራእይ አብራምን ወደ ሜዳ አውጥቶ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር፣ ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል። ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ፤ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።” ማለቱን ተከትሎ ትንቢታዊ ቃሉ ይስሐቅንና ያዕቆብን ተሻግሮ ዮሴፍን ወንድሞቹ ለኢስማኤላዊያን ሽጠው፣ ከዚያም ለግብፅ ባለሥልጣን ተሸጦ፣ በእስር ቤት ማቆ፣ በግብፅም ከንጉሡ ቀጥሎ ሁለተኛ ሰው ሆኖ ሳለ ምድሪቱ በጥጋብ ስትንበሸበሽ፣ በአንጻሩ በከነዓን የሚኖሩ የዮሴፍ ቤተሰብ በችግር ምክንያት እህል ፍለጋ ወደ ግብፅ መውረዱ ተከትሎ፣ የእግዚአብሔር ትንቢታዊ ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ አስጨናቂ መንግስት ተነስቶ ዕእብራዊያንን በማስጨነቁ ወደ አምላካችው በጮኹ ጊዜ በድንቅ በተአምር ከግብፅ ወጥተው ከነዓን እንደገቡ ተጽፎ አንብበናል፡፡ ኢትዮጵያዊ ወገኔ! ይህ መልዕክት ስለ እስራእል ያለፈ ታሪክ ለማውራት ሳይሆን፣ ስለ እኛ ኢትዮጵያዊያን መጪውን ዘመን በተመለከተ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወሰነውን (የተጻፈውን) ላስታውስህና ላስጠነቅቅ ነው፡፡ ዛሬ የሙስሊም ወንድሞቻችን “ፍትሕ አፈላላጊ ኮሚቴ” በእስር ቤት መሰቃየት፣ ዓርብ ዓርብ አደባባይ ወጥተው መጮኻቸው እንዲያው በዋዛ አይምሰልህ፡፡ በኃይለማርያም አገዛዝ ዘመን የህሊና እስረኞች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንደ ማናችንም ሰው ለህውሃት/ኢህአዴግ መንግሥትን “እንደ አሻህ ይሁንልህ” ብለው መኖር አቅቶአቸውም አይደለም፡፡ የወያኔ መንግሥት ለመጣል በጦር ሜዳ የተሰለፉን የሚያስተባብሩና የሚያሰለጥኑ እንደ አቶ አንዳልርጋቸው ጽጌና ሌሎች የጦር መኮንኖች፣ በልባቸው እውነት ተገቢውን ቦታ ስለያዘ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ አንተ አንባቢም በህሊና እስረኞች ላይ የሚደረግ ግፍና መከራ፣ ተጽኖ፣ በአንተ ላይ እንደተደረገ ካላየህው ምን ጊዜም ከህሊና ወቀሳ አታመልጥም፡፡ በህውሃት/ኢህአዴግ አባልነት ካርድ ይዘህ፣ “እኔ ከመንግሥት ወገን ነኝ፣ እኔ ክርስትያን ነኝ፣ መሣሪያ ታጥቄአለሁ፣ በጸጥታ ኃይል እጠበቃለሁ፣ በባዕድ አገር ነኝ” ማለት እንደማያወጣህ ላረጋግጥልህ ነው ይህን መልዕክት በአለህበት እንድታነበው የጻፍኩልህ፡፡ ከወያኔ ባለሥልጣናት መካከል ከአመት በፊት የጸጥታ ኃላፊ የነበረ ግለሰብ ዛሬ በእስር ቤት ውስጥ እንደሚገኝ አንብበሃል፡፡ አንተንስ ወያኔ ወደ እስር ቤት እንዳያስገባህ ማን ይከለክለዋል? ከኢህአደጎች መካከል እውነትን በልባቸው ይዘው፣ ውድቀቱን እያፋጠኑ መሆናቸውን በተመለከተ ወያኔ ተደጋጋሚ የፍርሃት መግለጫ እያወጣ መሆኑን አትዘንጋ፡፡ “ሁሉንም ነገር ጊዜ እንዳመጣው ጊዜ ይሽረዋል፡፡” ከፈጣሪ ጋር ግን ከተስማማህ፣ ቢጥሉህም አትጣልም፡፡ ግቦ ካልበላህ በምክንያት ትከሰሳለህ፡፡ ህውሃት ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ሊያጣላ የመጣ በአጋንንቶች ምሪት መሆኑን በተጨባጭ አረጋግጥልሃለሁ፡፡ አንተም ማስተዋል ያለህ ከሆነ ወደ አምላክህ በንስሃ ካልተመለስህ፣ ጎረቤትህንም ይቅርታ ካልጠየቅህ የሚቀርልህ አይምሰልህ፡፡ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው፡፡ ከጣለም ደግሞ ወደ ሲዖል ነው፡፡ ሲዖል የእሳት ባህር ሆኖ በአፋር ክልል የሚገኘው ኤርታሌ ምሳሌው ነው፡፡ እግዚአብሔር ተናገረ ማለትም አድረገ ማለት ስለሆነ የህውሃት/ኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎቹ ሊያስቡበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ሟች መለስ በድንገት በሞት እንደተወሰደ፣ አንተም በድንገት መለስን ከመቀላቀልህ በፊት ከእኩይ ተግባራትህ መበቆጠብ አለብህ የምለው በኢትየጵያ የሚከሰተው የለውጥ ማዕበል እንኳን ህውሃት/ኢህአዴግ የተባበሩት መንግሥታትም ማስቆም አይቻላቸውም፡፡ የሚቻልማ ቢሆን ኖሮ የቱኒዚያ፣ የሊቢያና የግብፅ መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው ባስቀሩ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የሚከሰተው የአስተዳደር ለውጥ በኢትዮጵያ ተወስኖ የሚቀር አይምሰልህ፡፡ ባለህበት አገር መጨረሻህ “ባልተፈጠርኩ“ የሚያሰኝ ነው፡፡ እኛም የኢትዮጵያ ልጆች ለውጡን የምናፋጥነው ወያኔን ለመጣል ከሚደረገው ትግልና ውጊያ በተጨማሪ በፀሎት ወደ እግዚአብሔር እጆቻችንን ስናነሳም ጭምር ነው፡፡ ያኔ ነው በመዝሙር 73 (74):14 “አንተ የዘንዶውን ራሶች ቀጥቅጠህ፣ ለኢትዮጵያ ሰዎች ምግባቸውን ሰጠሃቸው”የተባለው ትንቢታዊ ቃል ተግባራዊ የሚሆነው፡፡ ፍትህ ይሰፍናል፣ መዋደድ ይመጣል፣ ጥላቻ ከኢህአዴግ ሰዎች ጋር ይቀበራል፡፡ ፍቅር በመካከላችን ይነግሳል፡
እኛ ኢትዮጵያዊያን ለእግዚአብሔር ዘላለማዊ አጀንዳው ቀዳሚ ሆነን እንድንገኝለት ሆኖ ሳለ፣ በተለያዩ ምክንያቶች በቃሉ ላይ ማመፃችንን አውቆ በትንቢተ ሶፎንያስ በምዕራፍ 2: 12 “እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።” የሚለው ቃል ከኃይለ ሥላሴ ሥልጣን መውረድ ጋር የተጀመረ የሕዝብ አመጽ፣ “አብዮት ልጆቿን ትበላለች” የሚለው መፈክር የትንቢቱ አስፈጻሚ ኃይል ሆኖ ብዙ ወገኖቻችንን አጥተናል፡፡ በአመፃችንም ከቀጠልን እልቂቱም፣ ስደቱም፣ ንብረት መውደሙም እስከ ምጽዓቱ ይቀጥላል፡፡ እስራኤላዊያን ያለ አገር ለዘመናት የተንከራተቱት በአምላካቸው ላይ በማመጻቸው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቀሳውስት ዘንድም አማልክትና ጣዖታት በመመለካቸው ምክንያት እኛም በዘመኑ መጨረሻ በልባቸው ክፋትን የተሞሉ ጨካኞች መሪዎች፣ ኮነሬል መንግሥቱ ኃይል ማርያምን፣ አቶ መለሰ ዜናዊና አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን አስነስቶ እየተቀጣን ነው፡፡ ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝን በተመለከተ አንዳንድ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የሚያስቆጣ ቢሆንም ተግባሩ ግን ከቀደሙት መሪዎች እጅግ የከፋ ነው፡፡ ኢየሱስን በስም ያወቀ ሁሉ ጻድቅ ከተባለ፣ ሰይጣንም እንደሚያውቀው በሐዋሪያት ሥራ 19፡15 “… ርኩስ መንፈሱም፣ ኢየሱስን አውቀዋለሁ፣ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፣ እናንተ ግን እነማን ናችሁ?” በማለቱ ጸድቅ ሊባል ነው?
4
እነሆ በኢትዮጵያ ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ከተጀመረ አርባ ዓመት ሞላው፡፡ “ያለ ምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም” የተባለው መፈክር፣ ኢትዮጵያ መቅደምዋ ቀርቶ ፈራረሰች፣ ከልጆችዋም ብዙዎችን በወጣት እድሜአቸው ቀበረች፣ እናቶች የልጆቻቸውን ሬሳ እንዳያነሱ ተከለከሉ፣ ለተገደሉበት ጥይት ገንዘብ ከፈሉ፤ አዛውንቶች የትም ተጣሉ፣ ደካሞች በአውሬ ተበሉ፣ ጎልማሶች በባሕር ሰጠሙ፤ ለብዙዎች ስደት አማራጫቸው ሆነ፣ የቀረነውም ፍዳችንን እያየን ነው፡፡ ለስንዝር መሬት ፍርድ ቤት ይመላለስ የነበረው ንብረቱ በሙሉ ተወረሰ፡፡ ዳንድበር ፈርሶ ለባዕድ እንደ ገጸ በረከት ተላልፎ ተሰጠ፡፡ ያ ሁሉ መከራ እያለ አንድም ካህን፣ የእግዚአብሔር ቁጣ መሆኑን የነገረን የለም፡፡ ለምንድነው ይህ ሁሉ መከራ ብሎ አምላክንም የጠየቀ የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያናት እንዲያው በደፈናው ለአገራችን እንጸልይ ከማለት ባለፈ ችግራችን እየበረታ ባለበት በአሁኑ ወቅት “አምላክ ጸሎታችንን ሰምቶ ፕሮቴስታንት (ጴንጤ) መሪ ሰጠን” ብሎው እልልታ ያሰሙ አሉ፡፡ የሃገሪቱ መሪ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ከጨበጠ ጀምሮ የሟች መለሰ ዜናዊን ጅምር ሥራ ለማገባደድ ከመሮጥ ባለፈ ምን መልካም ሥራ ሠርቶአል? የጠ/ሚሩ ደጋፊዎች የሆናችሁ የፕሮቴስታንት አማኞች፣ እኩይ ሥራውን በሃሌሉያ መዝሙር ከመሸፈን ባለፈ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቁም ነገረ ሠርቶአል የምትሉት አለን? ፍትህ ተነፍጓቸው በየ እስር ቤቱ መከራና ስቃይ የሚያዩ ወገኖችን ችላ ያለ ግለሰብ፣ በእውነት የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ያለበት ደቀ መዝሙር ነው ያስብላልን? እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በልቡ ቢኖር ኖሮ ቀዳማዊ ተግባሩ የሕሊና እስረኞች ጉዳይ በሆነ ነበር፣ የሙስሊም ወንድሞች ጩኽት እልባት ባገኘ ነበር፣ አገር ተቆርሶ ለሱዳን ሲሰጥ በተቃወመ ነበር፡፡ ኢየሱስም “ʻመከስዋዕት ይልቅ ምህረትን እወዳለሁ’ እንዳለው፣ እውነት በኃይለማርያምና በግብረ አበሮቹ ቢኖር ኖሮ በንጹሃን ላይ ባልፈረዳችሁም ነበር፡፡ ተግባራችሁ ከአጋንንቶች የተማራችሁት መሆኑን አስቀድሞ የተጻፈልን፣ በማቴዎስ 7፡15 “በውስጣቸው ነጣቂ ተኩሎች ሆነው ሳለ የበግ ለምድ ለብሰው በመካከላችሁ በመግባት ከሚያሸምቁ ሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ፡፡ ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ፣ ከሾህ ቁጥቋጦ ወይን፣ ኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁም ጥሩ ዛፍ ሁሉ ጥሩ ፍሬ ፣ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል፡፡ ጥሩ ፍሬ የማያፈራ ሁሉ ይቆረጣል፣ ወደ እሳትም ይጣላል፡፡ ስለዚህ በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ” እንዳለው የጠ/ሚር ኃይለማርያምና የጸሎት ጓደኞቹ መንፈሳዊ ማንነት በተግባር እየታየ ነው፡፡
ዘመኑ በመንፈስ ሲመረመር የኢየሱስ ተቃዋሚ ስጋ ለብሶ በመገለጫው ዋዜማ ላይ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ያን መሰል እግዚአብሔር የማይወደውን ተግባራት ከፈጸመ፣ ሃሳዊ ክርስቶስን ሆኖ ስገዱልኝ ለማለት የሚከለክለው ማነው? የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ በኢትዮጵያ አይገለጥም ያለስ ማነው? ሰይጣንና ተከታዮቹ ከዐረብ አገራት ጋር ምን ጉዳይ አላቸው? አሁንስ በቁጥጥሩ አድርጎ እየሰገዱለት አይደለም እንዴ? የህውሃት/ኢህአዴግ ባለሥልጣናትና ካድሬዎቻቸውም ኢትዮጵያዊያንን ስቃይ የሚያሳዩት በመንፈሱ ተመርተው አይደለም እንዴ? ከጫካስ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ በየቤቱ እየገቡ ምታት ያደረጉ እንደነበርስ ይዘነጋል ወይ? ዛሬስ ቤተ መንግሥት ከአጋንንቶች የፀዳ ነውን? በመንግሥት እውቅና የተሰጠው የባህል መጽኃኒት ቀማሚዎች ህብረት፣ የአጋንንቶች ስብስብ አይደለምን? ዛሬም ሆነ ጥንት ምህታት፣ ርኩስ መንፈስ devil spirit፣ የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በሌላቸው ሰዎች ላይ ኃይል አለው፡፡ በመሆኑም ነው አስመራ ከተማ ውስጥ የሚቀለበው ዘንዶ (በዐይኔ ያየሁት) በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን አዳራሽ መግቢያ ላይ በወላድ ሴት ትከሻ ላይ ሆኖ ሃውልት ቆሞለት፣ ኢትዮጵያ በኤርትራ ተወላጆች ፈላጭ ቆራጭነት ስትገዛ፣ ኢትዮጵያዊያንም በአጋዚ ጦር ጭንቅላታቸው በጥይት መስዋዕት እየሆኑ ያሉት፡፡ አካለ ጎደሎና በእስር የሚማቅቁት፡፡ ኢትዮጵያ ያሉ ኡርትራዊ ስንቶች ሞቱ፣ የአካል ጉዳተኞችና እስረኞች ሆኑ?
ሰው ከእናቱ ማሕፀን ሲወጣ የራሱን የሥራ ድርሻ በልቡ ተጽፎ ነው የሚወለደው፡፡ ኢየሱስም ከመወለዱ አስቀድሞ በኢሳይያስ የትንቢት መጽሐፍ እንደተጻፈውና ኢየሱስም የሰው ልጅ እንደ ተጻፈው መሄድ እንዳለበት ተናግሮ በተግባርም የሐዋሪያቱን እግሮች በማጠብ ትህትናን አስተምሮ፣ ስለ ሰዎች ቤዛነት በመስቀል ላይ መሞቱን፣ በቀበሩን፣ መነሳቱን እንደተናገረው የመጀመሪያውን ዙር ተልኮ አጠናቆ ወደ አባቱ ተመልሶአል፡፡ ሟች ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናውም በመካከለኛ እድሜው እያለ የተሰጠውን የሥራ ድርሻ አጠናቆ ወደ ማይመለስበት አገር ሄዶአል፡፡ የመለስ መሞት በተመለከተ ለህውሃት/ ኢህአዴግ አባላት፣ ለደጋፊዎቻቸውና በከፊል ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስደንጋጭ ነበር፡፡ “ሕዝቡ ከመራራ ሃዘኑ የተነሳ ችግር ላይ ይወድቃል” ብለው ስጋት የነበራቸው እንደነበሩ ሁሉ፣ መታመሙን የሰሙም “አበቃለት” ያሉም ነበሩ፡፡ ሟች መለስ ዜናዊ ሐብታም ሆኖ ሳለ ገንዘቡ ሊያድነው እንዳልቻለ ዛሬ በስልጣን ላይ ያሉ ሁሉ የተረዱት ይመስላል፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ ህመም ያለባቸው ሰዎች ዘመኑ ባፈራው ሕክምና እድሜአቸውን ሲያስረዝሙ አይተናል፣ ሰምተናልም፡፡ ሟቹ መለስ ግን የተሰጠውን ተልዕኮ በጊዜው ስላገባደደ ለተቀጣዩ ሰው በራሱ ምርጫ አቶ ኃይለማርያምን ሾሞልናል፡፡ በጽሐፊው እምነት፣ አቶ መለስ ዜናዊ “ክርስቲያን ነኝ” የሚል ቃል ለኢትዮጵያ ሕዝብ አሰምቶ ቢሆን ኖሮ፣ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንኳን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር መሆን ቀርቶ ወደ አዲስ አበባ አይቀየርም ነበር፡፡ የወያኔ ባለሥልጣናትም ለ40 ዓመት የታገሉለት ስልጣን በጦር ሜዳ ላልነበረ ሰው ተላልፎ ሲሰጥ በመፈንቅለ መንግሥት ስም አመጽ አስነስተው ባወረዱት ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ነው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ለመሆን የበቃው፡፡ ይህም በዘመኑ መጨረሻ የሚፈለገው ሰው “ክርስቲያን ነኝ” የሚል በመሆን ስላለበት ነው፡፡
ሰው በሕይወት እያለ የሠራው ሥራ ለሌሎች ጎልቶ ባይታይም ልጅ ወልዶ፣ ባይወልዱም አሳድጎ፣ ደግና ከፉ ሥራዎች ሠርቶ ማለፍ ያለ ነው፡፡ በአምካክ ዘንድ ሰው ሁሉ መልካም እንዲሠራ የተፈጠረ ቢሆንም፣ ሰይጣንም የመላእክት አለቃ ሆኖ ሳለ በአመጽ ከሰማያት ከተጣለ ጀምሮ ለሰዎች ክፋትን እያስተማረ መሆኑን የማያውቅ የለም፡፡ የዘመኑ መገባደጃ መሆኑን አጋንንቶች በማወቃቸው፣ ከሕዝቦችም ብዙዎችን የራሳቸው በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ በሰው ውስጥ ሆነው በቤተ ክርስቲያናትና በመስጊዶች ገብተው ሕዝቡን እያጣሉ፣ ደም እያፋሰሱ ናቸው፡፡ በመካ መዲና ነቢዩ ሙሐመድን (ሶ.ዐ.ወ) ያሳድዱ የነበሩ ሰዎችም ተጠሪነታቸው እስከ ዛሬም ለአጋንንቶች መሆኑን የምናውቀው ቅዱስ ቁርኣንን በቀና መንፈስ ሲነበብ ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) አስተምሮ የኢስልምናን ሃይማኖት ለመመስረት ቢሆን ኖሮ፣ ለምንድነው የመካ መዲና ባለሥልጣናት ነቢዩን የተቃወሙት? እናንተስ ዛሬ ኢስላም ነን የምትሉ ኢትዮጵያዊያን የነቢዩን ትምህርት በዳግም ኽሊፋ ዑስማን በ25ኛው ዓመት የተቃጠሉትን ምዕራፎች አንብባችሁ ነው ወይስ ነቢዩ ሙሐመድ የአላህን ቃል ለሕዝባቸው ሲየሰሙ ከሐዲዎች “ድግምት ስለአለበት ይስባችኋልና አታዳምጡት” እያሉ ይንጫንጩ የነበሩትን ሰዎች አስተምሮ ተከትላችሁ ነው? ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ..ወ) የመካ መዲና ባለሥልጣናት ያመልኳቸው የነበሩትን ጣዖታት በማፈራረሳቸው ጦርነት እንደታወጀባቸው፣ በየሕይወት ታሪካቸው ተመዝግቦ ሳለ፣ ታዲያ በምን መንገድ ነው የሳውዲ እምነት ከነቢዩ እምነት ጋር አንድ ዓይነት የሆነው? ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አባቶቻችሁንና እናቶቻችሁን እንዲመልስ የኢትዮጵያን ንጉሥ ነጃሺን በወርቅና በብር ገጸ በረከቶች የተማጸኑትን ተከትላችሁ ነው? ዛሬም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በአልጂን 72፡23 “አላህንና መልዕክተኛውን የሚያምጽ ሰው ለርሱ የገሃነም እሳት አለው፡፡”, በአልሙእሚን 40፡41 “ወገኖቼ ሆይ ወደ መዳን የምጠራችሁ ስሆን ወደ እሳት የምትጠሩኝ ስትሆኑ ለእኔ ምን አለኝ፣ እኔም ወደ አሸናፊው መሓሪው እጠራችኋለሁ፡፡” በማለት ደጋግመው ያስተምሩ እንደ ነበር አላነበብክም? እንደ አሁኖቹ ክርስቲያኖች አስተምሮ፣ “መንግሥተ ሰማያት በአማላጅ ትገባላችሁ” አላሉም፡፡ ወንጌሉ የሚለው “እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው” ዮሐንስ 5፡24፡፡ በአል-አዕራፍ 7፡157 “የወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ የሚድኑ ናቸው፡፡”፣ ራዕይ 20፡15 “ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳት ባህር ተጣለ፡፡”፣ አል-ዒምራን 3፡53 “ጌታችን ሆይ! ባወረድከው አመንን፣ መልክተኘውንም አመንን፣ ከመስካሪዎችም ጋር መዝግበን፡፡” ማለታቸው ልዩነትን ነው ወይስ አንድነትን የሚያሳይ ነው? ይህ መልእክት በአልረሕማን መንፈስ መጸፉን እወቀህ በዲጃል መንፈስ የሚንቀሳቀሰው ከወያኔ ደጋፊዎች ጋር ከሆንክም፣ እድል ፈንታህ ከጂኒዎች ጋር ሲዖል ነው፡፡ ገነት ለመግባት ግን ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) እንዳስተማሩት በአላህና በመልክተኛው አልመሲህ ዒሳ አምነህ ከነፍሰ ገዳዩ ኢህአዴግ በመራቅ ነው፡፡
የሰይጣን እውቀትና ጥበብ የኢየሱስ መንፈስ ከሌላቸው ሰዎች ስለሚበልጥ፣ የማታለል ስልቶቹን እየቀያየረ የቤተ ክርስቲያናት ካህናትን፣ ፓስተሮችን፣ ሼኾችን ከእግዚአብሔር ሥርዓት አውጥቶ የራሱ አገልጋዮች እያደረጋቸው ነው፡፡ ለዚህም ማሳያውም በኢትዮጵያ የሃይማኖት እኩልነት ለሰላምና ለእድገት፣ “መቻቻል” ተስማምታችሁ ኑሩ የሚለው አዲስ የአስተዳደር ሥርዓት (NWO- New World Order) የእርሱ በሆኑ ሰዎች መመሪያ አርቅቆ ተግባራዊ ለማድረግ በማጣደፍ ላይ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናት ዘንድ የሚደመጥና የሚደገፍ በመሆኑ የጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሹመት ይህንኑ ለመተግበር ነው፡፡ አቶ መለሰ የህውሃትን አጀንዳ ለማስፈጸም አብረውት ጫካ የገቡ አንጋፋ ታጋዮች እያሉ ከደቡብ ኢትዮጵያ የኢየሱስ ብቻ ቤተ እምነት ተከታይ ተላልፎ መሰጠቱ በሁለቱ ሰዎች የመንፈስ አንድነት እንደነበረና አሁንም የመለስ መንፈስ ከጊዜው አንጻር በሰባት እጥፍ በውስጠኛው ሰውነቱ እየሠራ፣ በውጨኛው ስጋዊ አካሉ “ሃሌሉያ“ እያለና እያስባለው ነው፡፡ የሰይጣን ባህርይ መዝረፍ፣ መግደል ነሐሰት መናገር በመሆኑ፣ የህውሃት/ኢህአዴግ መንግሥትም ማታለልን፣ መዝረፍን፣ መግደልን፣ ንብረት ማውደምን የተማረው ከሰው ልጆች ጠላት ከሆነው ከሳጥናኤል ነው፡፡ ኃይለማርያምም ስድብ በቴሌቪዥን እየተደመጠ ነው፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎችም በጋዜጦችና በመጽሔቶች እያስነበቡ ናቸው፡፡ በራዕይ “ዙፋኑ ባለበት እንደምትኖር አውቃለሁ” የተባለው በእስራኤል ሳይሆን በምድራችን መሆኑን አንዱ ማሳያ ነው፡፡
ጥበበኛው ሰሎሞን “ለሁሉ ጊዜ አለው”እንዳለው የወንጌል ስብከት የሚያቆምበት ጊዜ መቃረቡ በተመለከተ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሊያውቁት የሚገባው ነው፡፡ ሰውም የተሰጠውን ድርሻ አጠናቆ ወደ መንግስተ ሰማያት ለመወጣትም ሆነ ወደ ሲዖል ለመውረድ የራሱ ፈቃድ ነው እንጂ በእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡ ውሳኔው ሕግጋትን በሙሉ 613 ቱን በመፈጸም ወይም ወንጌል ሰምቶ በማመን ነው እንጂ በአንዳንድ ወንጌላዊያን በፀጋው ድናችኋል እንደሚሉት አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ ለሁሉ የተሰጠ ነው፡፡ እንዲህ ማለቴ ከወንጌል ተጻራሪ መሆኔ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ፈልጉኝ ታገኙኛላችሁ ተብለናል፡፡ ሰውም እውነትን ያውቅ ዘንድ በልቡ መሻትን ስለአስቀመጠ፣ ወንጌልን ለመስማት የሚያስችለው ልዩ ኃይል ፀጋ ያስፈልገዋል፡፡ ድነትን ካገኘ በኋላ 613 ቱም ይሁኑ አስሩ የሙሴ ሕግ ተግባራዊ የሚያደገረገው በፀጋ በመሆኑ ኢየሱስም ከትዕዛዛጹ አንዷም መቅረት እንደሌለባት አስጠንቅቆናል፡፡ ስለዚህም በፀጋው ድነትን አግኝቻለሁ
5
ብለህ የወያኔዎች ሥርዓት ብታካሄድ፣ በሃሳብ ተባባሪ ብትሆን የእግዚአብሔርን ሕግ በመጣስህ ሲዖል መውረድህ አይቀርም፡፡ ከፀጋ ሥራዎች አንዱ በክርስቶስ የሆው ሰው በሞት ሲለይ ፀጋው ነው በኩሩቤልና ነበልባል ሰይፍ የሚጠበቀውን ቅጥር አልፎ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚያስገባው፡፡ ያለ ኢየሱስ መንፈስ የሆነውንም ሰው ወደ ሲዖል የሚያወርደው ለዚሁ የተመደቡ መላዕክት ናቸው፡፡ አሁን ወንጌልን ያጥላላ፣ ሲሞት መንፈሳዊ አካሉ አልወርድም ብሎ ስለሚያውክ፡፡ አንዴ ከገቡ ደግሞ መውጣት እንደሌለ ስለሚያውቁት ነው፡፡ በቅዱስ ቁርኣንም ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ነቢይ ከመባላቸው በፊት ወንጌልን በመስማታቸው ነው ለወንጌል አገልጋዮች የተሰጠውን መንፈሳዊ መጠሪያ “ነቢይ” የተባሉት፡፡ በሕይወት መጽሐፍ ስማቸው እንዲጻፍ የጸለዩት፡፡ ለምንድነው ከቁርኣን ተከታዮች መካከል እስከ ዛሬ “ነቢይ” ተብሎ የማይጠራው? ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ተከታዮቻቸው መንፈሳዊ መሪያቸውን “ነቢይ” ብለው ይጠሯቸው ስለነበር፣ አሳዳጆቻቸው የመካ መዲና ባለሥልጣናትም እውነተኛ ተከታዮቻቸውን ለማሳሳት ነቢዩ እያሏቸው ነው፡፡ የመዳን ወንጌል (ቁርኣን) ለዐረብ አገራት እንዲሰበክ የአላህ ፈቃድ ስለሆነ፣ የዐረብ መሪዎች ቢቃወሙም ወንጌልን ሰምተው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ እየተመዘገበ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እና ቅዱስ ቁርኣን የሚያስተምሩት “የዓለም ብርሃን ሆኖ የመጣውን፣ ከድንግል ማርያም ያለ አባት የተወለደው ኢየሱስን በአምላክነት ያመነ ሰው በልቡ ብርሃን ያለው በመሆኑ ወደ ጨለማ አይወርድም” የሚሉ ናቸው፡፡ ብርሃን በልቡ የሌለ ግለሰብ ግን ከጨለማ ገዥው ጋር ቢያንስ ለአንድ ሺህ ዓመት ወደ እሳት ባህር እንደሚጣል ያረጋግጣሉ፡፡
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የለውጥ ትግል በእግዚአብሔር መንፈስ ካልተቃኘ፣ ሳናውቀው ለሰይጣን አገልጋዮች ሆነን እንዳንገኝ የሚያመላክት መልእክት በመሆኑ በጥሞና ማንበቡ አስተዋጽዖ አለው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን፣ የወንጌልና የቁርኣን ተከታዮች አንድነትን ፈጥረን ህውሃት/ኢህአዴግን መንግሥትን ለመጣል መነሳታችን የዓለም መንግሥታትን በተለይም የዐረብ አገራት ሳያስገርም አልቀረም፡፡ አንድነታችን መንፈሳዊ መሆኑ ማሳያው፣ በቅዱስ ቁርኣን ጣሃ 20፡1-5 “ቁርኣን በአንተ ላይ እንድትቸገር አልላወረደም፡፡ ነገር ግን አላህን ለሚፈራ ሰው መገሰጫ ምድርንና የላይኛይቱን ሰማይ ከፈጠረ አምላክ በወረደው አልረሕማን ላይ ነው፡፡”፣ በአል- ኢስራእ 17፡110 “አላህን ጥሩ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፣ ከሁለቱ ማነኛውን ብትጠሩ መልካም ነው” ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ ከመሪየም የተወለደው ዒሳ እርሱ አልረሕማን ነው፡፡” በአል-ሙልክ 67፡29 “እርሱ እመኑበት የምላችሁ አልረሕማን ነው፡፡” በዮሐንስ ወንጌል 8 “… አባቴንም እኔንም አታውቁም፣ እኔን ብታውቁ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁ ነበር፣ እኔ እርሱ ነኝ ስላችሁ ካላመናችሁ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ፡፡” እኔ እርሱ ነኝ ማለቱ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ ነው፡፡ በቅዱስ ቁርኣንም አልመሲህ ዒሳ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ያለ ክርስቶስ፣ ክርስቶስም ያለ ኢየሱስ በምድር ላይ መኖር አይችሉም፡፡ ሰውም በሥጋ የሚታየውና የማይታየው ውስጣዊ መንፈሳዊ አካል ኖሮት ነው በምድር የሚንቀሳቀሰው፡፡ ካልተንቀሳቀሰ ሞቶአል ነው፡፡ ጳውሎስ በመልእክቱ “በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ የእግዚአብሔርን ቃል ተመኙ” እንዳለው፣ ኢየሱስም “ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም በእግዚአብሔር ቃል እንጂ” ብሎአልም፡፡ አይሁድ፣ ኢየሱስን ለመስቀል ሞት ያደረሱት ክርስቶስ መሆኑ ተሰውሮባቸው ነው፡፡ ኢየሱስ ብቻ ተከታዮችም ኢየሱስን እንጂ ክርስቶስን አናውቅም ማለታቸው ከየትኛው ወገን መሆናቸው አመላካቹ የጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግርና ተግባሩ ናቸው፡፡ በ1ኛ ዮሐንስ 2፡22 “ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ሃሰተኛ ማነው? ይህ አብንና ወለድን የሚክደው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡ ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ውስጥ ቢኖር፣ እናንተም በወልድና በአብ ትኖራላችሁ፡፡ ይህም የዘላለም ሕይወት ነው፡፡”
እንደ ቅዱስ ቁርኣን አስተምሮና የነቢዩ ሙሐመድ የሕይወት ታሪክ እንደሚነግረን፣ የኢስላም ሃይማኖት ፈጽሞ ወደ ኢትዮጵያ አልገባም፡፡ የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታይ የነበሩት ከሞት፣ ከእስራት አምልጠው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የደህንነት ወንጌል በነቢዩ አንደበት የሰሙና ያመኑ ናቸው፡፡ ኢስላም ተብሎ ስም የተሰጠው ነቢዩ ከሞሩ ከመቶ አመት በኋላ በመካ መዲና ባለስልጣናትና በወቅቱ እዚያ ይኖሩ በነበሩ በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክና በአይሁድ ቤተ እምነቶች ነው፡፡ ለነቢዩ ሙሐመድ ከአላህ የወረደላቸው ቅዱስ ቁርኣን ውስጥ የተበረዘና ከፊሉም መቃጠሉን በተመለከተ በአማርኛ የተጻፋን የቅዱስ ቁርኣን መቅድም ማነበብ ነው፡፡ “ክርስቲያን ገድሎ ገነት ይገባል” የሚል አባባል ከነቢዩ አንደበት አልወጣም፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ›ዐ.ወ) በመካ መዲና ባለሥልጣናት በመርዝ ይሁን በጥይት ከተገደሉ በኋላ ነፍሰ ገዳይነታቸው እንዳይታወቅ ለመሸፈን የተደረገ የታልሙድ ሴራ ነው፡፡ ክርስቲያንን ገድላችሁ ገነት ትገባላችሁም እያለ የሚያስተምረው ታልሙድ መሆኑን ድረ-ገጹን መመልከት ነው፡፡ ከነቢዩ ጋር ተከታዮቻቸው ከፊሎቹ ሲገደሉ፣ ጥቂቶቹ አምልጠው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ናቸው፡፡ የነቢዩ አሟሟት በተመለከተ www.alqatrah.net Sheikh Yaser al Habib. Youtube መመልከት ወይም who killed prophet Muhammad ብለህ ጻፍና ተጫን፣ ከዚያም በምን ምክንያት እንደገደሏቸው ማወቅ ትችላለህ፡፡ አል-ማኢዳህ 5፡32 “ … ነፍስህ የገደለ ሰው፣ ሰዎችን ሁሉ እንደ ገደለ ነው፣ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎችን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው፡፡” በአል-ተውባህ 9፡20 ያሉት “እነዚያ ያመኑት ከአገራቸውም የተሰደዱት፣ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት፣ አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው፡፡”
በየወንጌልና በቁርኣን ውስጥ ገነት መግባትን በተመለከተ ያላቸው አንድነት በጥቂቱ፡- ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፣ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለነበረ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ፡፡ ክፉ የሚያደርግ ብርሃንን ይጠላል፣ አድራጎቱም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም፡፡ በእውነት የሚመላለስ ግን ሥራው ከእግዚአብሔር የተሠራ መሆኑ በግልጽ ይታይ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል፡፡ ዮሐንስ 3፡19 አል-በቀራህ 2፡257 አላህ የነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ነው፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል፣ እነዚያም የካዱት ረዳቶቻቸው ጣዖታት ናቸው፣ ከብርሃን ወደ ጨለማዎች ያወጣቸዋል፡፡ ኢየሱስም እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፣ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ ከቶ በጨለማ አይመላለስም፡፡ ዮሐንስ 8፡12 በአል-ተጋቡን 64፡8 በአላህና በመልክተኛው በዚያ ባወረደው ብርሃን እመኑ፡፡ በእኔ የሚያምን በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፣ የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በዚህ ብርሃን እመኑ፡ አል-አዕራፍ 7፡?157 የወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡ ቃልም ሥጋ ሆነ፣ በመካከላችንም አደረ፡፡ ዮሐንስ 1፡14 የመርየም ልጅ ዒሳ ነው ያ በርሱ የሚጠራጠሩበት ውነተኛ ቃል ነው፡፡ መርየም 19፡34
በአንዳንድ መስሊሙ ሕብረተሰብ ተዘውትሮ የሚነገረው፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ንጉሥ ነጃሺ ሙስሊም እንደ ነበር ነው፡፡ ታዲያ ወደ መንግሥተ ሰማያት (ጀነትን) ለመግባት የወንጌል እና የቁርርኣን አንቀጾች ተመሳሳይ መልእክት ካላቸው የትኛው ወገን ነው የአላህን መልክተኛ አልቀበልም ብሎ ወደ ሲዖል የሚወርደው? ንጉሥ ነጃሺስ በየት በኩል ነው ሙስሊም ለመሆን የቻሉት፣ መካ ሄደው ነበር? ወይስ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አባቶቻችሁ የመካ መዲና ጣዖታትን አናመልክም በማለታቸው በደረሰባቸው ስቃይ አምልጠው ከመጡ ቤተሰብ ተሰብከው ነው? በዩኑስ 10፡94-95 “ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን፣ እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ፣ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፣ ከተጠራጣሪዎችም አትሁን፡፡ከነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና፡፡” መባሉት ተከትሎ፣ በአሊ-ኢምራን 3፡53 “ጌታችን ሆይ ባወረድከው አመንን፣ መልክተኛውን ተከተልን ከመስካሪዎችም ጋር መዝግበን” ያሉት እኮ ነቢዩ ሙሐመድና ወደ አቢሲኒያ የመጡት አባቶቻችሁ ናቸው፡፡ ታዲያ አንተስ፣ አንቺስ በምን መንገድ ነው ነቢዩ ሙሐመድን የገደሉ የመካ መዲና ሼኾችን ሰምታችሁ ኢስላም የሆናችሁት?
እስራኤላዊያን ግብፅ ሲወጡ አብረዋቸው ሌሎች ሰዎችም በመዉጣታቸው ምክንያት ብዙዎችን አሳስተው በሙሴ ላይ በማመጻቸው ከነዓን የገቡት ሁለት ብቻ እንደነበሩ፣ ዛሬም የሃይማኖት ካባ ለብሰው ብዞችን ወደ ፅዮን እንዳይገቡ እያደረጉ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ካህን በየነበረው አሮን በሲና ተራራ ስር የተቀረጸው ጣዖት ዛሬም ስሙ እና ቅርጹ ተቀይሮ በዓለም ሁሉ እየተመለከና እየተሰገደለት ነው፡፡ ሰይጣን የዓለም ገዥም የተባለው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ እንዲያም ሲባል የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ተገዝተውለታል ማለት አይደለም፡፡ ሆኖም በክርስትና ስም ዛሬም አገልጋዮችን አላጣም፣ ለነፍሰ ገዳዩ የወያኔ አገልጋዮች ካህናትና ፓስተሮች በኢህአዴግ ደጋፊዎች አድረጎ እያሰገዳቸው ነው፡፡ የሐሳዊ ክርስቶስ ዋና ምኞቱ የክርቶስ የሆኑትን ለራሱ አድረጎ ለማሰገድ የመጨረሻ የማታልል፣ የመስረቅ የመግደል፣ የሃሰት መናገር ባሕርዮቹን በወያኔ ላይ አድርጎ በኃያላን መንግሥታትና የዐረብ አገራት የገንዘብና የሞራል ድጋፍ ያልተለየውም፡፡ በዚያው አንጻር የእግዚአብሔር መንፈስ የራሱ የሆኑትን ኢትዮጵያዊያን አስነስቶ ከምድሪቱ እንዲጠፉ እያደረገ ነው፡፡
6
የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ መገለጫው ከዐረብ አገራት ሳይሆን፣ ከእኛው በኢትዮጵያዊያን መካከል በምድራችን ነው፡፡ በዐረቦች አገር የማይሆነው፣ ቀድሞዉኑ ወንጌል ሲሰበክ ወይም እውነተኛው ቁርኣን በነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሲበክ ተቃዋሚ ሆነው ጦርነት አስነስተው ነቢዩ ሙሐመድ ከተገደሉ በኋላ በቁጥጥሩ ስር ናቸው፡፡ ደግሞም ኢስላም ወደ ቤተ ክርስቲያን መቅረብ እንደ መርከስ ይቀጠራልና፡፡ ክርስቲያን ነኝ ከሚሉ፣ ከፕሮቴስታንትና ከኦርቶዶክስ፣ ጴንጤቆስታል አብያተ ክርስትያናት አማኞች መካከል ወያኔን ደግፈው፣ ወያኔም አይዞአችሁ እኔ አለሁ ከሚላቸው ሰዎች መካከል እንደሚሆን አልጠራጠርም፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ተፈታትኖ የነበረው ኢትዮጵያዊው የኩሽ ልጅ ናምሮድ እንደ ነበረ፣ ዛሬም ኢትዮጵያዊ ነው እንጂ የሌላ አገር ተወላጅ፣ ኢራቃዊ፣ ኢራናዊ፣ ሶሪያዊ፣ ቻይናዊ፣ ሳውድ አረቢያ ወይም ሩሲያዊ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ እነዚህ መንግሥታት ግን ድጋፍ አያድርጉም ማለት አይደለም፡፡ ኢህአዴግም በአሁን ጊዜ ከምዕራባዊያን ይልቅ በጠቀሱት አገራት እየተደገፈ መምጣቱ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ናምሩድ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንደሠራ፣ ዛሬም ወያኔ የሕዝቡን መኖሪያ እያፈረሰ፣ በማስተር ፕላን የመለስ ዜናዊ ራዕይ ለማስፈጸም ነው፡፡ እንደ ናምሮድ፣ የአባይም ግድብ ለስሙ መጠሪያ ማድረጉ ነው እንጂ ለአገር አስቦ አይደለም፡፡ ለአገር ቢሆንማ ኖሮ፣ ከሕዝቡ ጋር ተመካክሮ ያደርግ ነበር እንጂ በወታደር ኃይል ባልሆነም ነበር፡፡ በትዕቢት ተወጥሮ የሚሠራው በናምሩድ መንፈስ ሆኖ ነው፡፡ የናምሩድ ግንብ እንደፈረሰ፣ የኢአዴግም ሥራዎች ፈራሾች ናቸው፡፡ ለምን ቢባል፣ ከእዚያ የበለጠ በፍቅር ሆነን መሥራት ስለምንችል ነው፡፡ ደግሞም ሥራዎቹን እያየን አስታውሰን እንዳንታመም ነው፡፡
የዐረብ አገራት የህውሃት/ኢህደኤግን እየደገፉ በኢትዮጵያዊያን ላይ አምርረው የተነሱት፣ የዋሃቢስቶች እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ውጤት አልባ በመሆኑና ቀደም ብሎ በሼኾች የተነገረው ትንቢታዊ ቃል መፈጸሚያው በመቃረቡ ሳይቀድሙኝ ልቅደማቸው በሚል ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞችን በዐረብ አገራት በተለይም ሳውዲዎች እየገደሉና እያሰቃዩ ያሉት፡፡ ትንቢቱ የሚለው፡-
The Two Sahihs recorded that Abu Hurayrah said that the Messenger of Allah said,
«ﻳﺨﺮﺏ ﺍﻟﹾﻜﹶﻌﺒﺔﹶ ﺫﹸﻭ ﺍﻟﺴﻮﻳﻘﹶﺘﻴﻦِ ﻣِﻦ ﺍﻟﹾﺤﺒﺸﺔ»
(The Ka`bah will be destroyed by Dhus-Sawiqatayn (literally, a person with two lean legs) from Ethiopia.)
Also, Ibn `Abbas said that the Prophet said,
«ﻛﹶﺄﹶﻧﻲ ﺑِﻪِ ﺃﹶﺳﻮﺩ ﺃﹶﻓﹾﺤﺞ ﻳﻘﹾﻠﹶﻌﻬﺎ ﺣﺠﺮﺍ ﺣﺠﺮﺍ»
(As if I see him now: a black person with thin legs plucking the stones of the Ka`bah one after another.) Al-Bukhari recorded this Hadith.
Imam Ahmad bin Hanbal recorded in his Musnad that `Abdullah bin `Amr bin Al-`As said that he heard the Messenger of Allah say,
« ﻳﺨﺮﺏ ﺍﻟﹾﻜﹶﻌﺒﺔﹶ ﺫﹸﻭ ﺍﻟﺴﻮﻳﻘﹶﺘﻴﻦِ ﻣِﻦ ﺍﻟﹾﺤﺒﺸﺔِ ﻭﻳﺴﻠﹸﺒﻬﺎ ﺣِﻠﹾﻴﺘﻬﺎ ﻭﻳﺠﺮﺩﻫﺎ ﻣِﻦ ﻛِﺴﻮﺗِﻬﺎ، ﻭﻟﹶﻜﹶﺄﹶﻧﻲ ﺃﹶﻧﻈﹸﺮ ﺇِﻟﹶﻴﻪِ ﺃﹸﺻﻴﻠِﻊ ﻭ ﺃﹸﻓﹶﻴﺪِﻉ ﻳﻀﺮِﺏ ﻋﻠﹶﻴﻬﺎ ﺑِﻤِﺴﺤﺎﺗِﻪِ ﻭﻣِﻌﻮﻟِﻪ »
(Dhus-Sawiqatayn from Ethiopia will destroy the Ka`bah and will loot its adornments and cover. It is as if I see him now: bald, with thin legs striking the Ka`bah with his ax.)
This will occur after the appearance of Gog and Magog people. Al-Bukhari recorded that Abu Sa`id Al-Khudri said that the Messenger of Allah said,
«ﻟﹶﻴﺤﺠﻦ ﺍﻟﹾﺒﻴﺖ ﻭﻟﹶﻴﻌﺘﻤﺮﻥﱠ ﺑﻌﺪ ﺧﺮﻭﺝِ ﻳﺄﹾﺟﻮﺝ ﻭﻣﺄﹾﺟﻮﺝ»
(There will be Hajj and `Umrah to the House after the appearance of Gog and Magog people.)
አንተስ ክርስትያን ነኝ፣ ኢስላም ነኝ ብለህ የወያኔን ሰይጣናዊ የሥራ መመሪያ ተግባራዊ አድርገህ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጎሳ ተከፋፍለህ ያለህው መጨረሻህ ምን ይሆን? አማራ ነኝ ብሎ ትግሬውን መጥላት፣ ትግሬውስ ኦሮሞን መናቅ፣ ጉራጌን ማጥላላት፣ ሌላውን ማወረድ፣ ማስጨነቅ፣ ማሰር፣ መዝረፍ፣ መግደል ሰይጣናዊ ሥራ ስለሆነ መጨረሻህም ሲዖል ነው፡፡ “ወንድምህን እንደ ራስህ ውደድ” የምትለዋ ቃል ትፈርድብሃለች፡፡ ወገኔ በሩቅ ያለህውም፣ ከሚመጣው ቅጣት የምታመልጥ አይምሰልህ፡፡ እስራኤላዊያን ከግብፅ የወጡት ፈልገው አልነበረም፡፡ አራት መቶ ዓመት መገባደጃው ላይ እግዚአብሔር ጨካኝ መሪ አስነስቶ ወደ እርሱ እንዲጮኹ አስደረገ፡፡ ሙሴም ከግብፅ ቤተ መንግሥት ድሎት ይልቅ ከወገኑ ጋር መከራን የመረጠው ስለ ወገኖቹ ግድ ብሎት ነው፡፡ በዘመኑ መጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ አምላኩ ይመለስ ዘንድ በተለያዩ ጊዜአት መልክተኞች ቢልክም ሰሚ በማጣቱ ኮነሬል መንግሥቱንና አቶ መለስ ዜናዊን አስነስቶ ቢቀጣም፣ ሕዝቡ ባለመመለሱ፣ ከሁሉ የከፋውን ኃይለማርያምንና ጨካኞች ካድሬዎቹን የመጨረሻውን ቅጣት እየተቀጣ ባለበት በአሁኑ ጊዜም፣ ስለ ሕዝቡ ካህናት እግዞ ማለትን አልወደዱም፡፡ ዲያስፖራዎችም የሕዝቡን መደህየት አጋጣሚ የተፈጠረላቸው ይመስል በኢህአዴግን አባልነት ካርድ ኢትዮጵያዊ አርበኞችን እየዘለፉ ናቸው፡፡ የንብረቱን ተረካቢ፣ ኢንቬስተር ተብለዋል፡፡ የቤተ ሃይማኖት ሰዎችም ለአገር አፍራሹና ለጨቋኙ መንግሥት ረዥም ዕድሜ እየተመኙ ናቸው፡፡ ይህም ለሰይጣንም ረዥም እድሜ መለመን እንደሆነ መንፈሳቸው ካልመሰከረላቸው፣ ድነት የላቸውም ማለት ነው፡፡
በእምባቆም ምዕራፍ ሁለት “ከተማንም በኃጢአት ለሚመሠርት ወዮለት! እነሆ፥ አሕዛብ ስለ እሳት እንዲሠሩ፥ ወገኖችም ስለ ከንቱነት እንዲደክሙ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ አይደለምን?“ የሚለውን እናነባለን፡፡ እግዚአብሔር በዘላለም አጀንዳው ከአዘጋጃቸው ወገኖች መካከል የቁርኣን አማኞች ማህበረ ሰብ በኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለው መራራ ጽዋ አልዋጥ ያላቸው ናቸው፡፡ ከፊኒያኖች ዝርያ ያላቸው ከቃየን የዘር ሐረግ በሆኑት የሕውሃት/ኢአዴግ ነፍሰ ገዳይ ወታደሮች፣ ቀንና ሌሊት በሚያደርሱባቸው አረመኔያዊ ስቃይ ሳይፍረከረኩ፣ ለድርድርም አንቀርብም ማለታቸው በተመለከተ በአንዳንድ ወንጌል ሰባኪዎች ዘንድ ሞኝነት መስሎአል፡፡ ለእኔ ለጸሐፊው ግን እንደ ዳንኤል፣ እንደ ሲድራቅ፣ እንደ ሚሳቅ፣ እንደ አብድናጎ፣ እንደ መርዶክየስ ናቸው፡፡ ስለ ሕዝቡ ስቃይ፣ ስለ አገር መፍረስ፣ ፍትህ በመጥፋቱ ነው “የመፍትሄ አፋላላጊ” ብለው የሰየሙት፡፡ እየጮኽታቸው ለዋዛ አይምሰልህ እግዚአብሔር ያዘጋጀላቸውን ተመልክተው ነውና፡፡ ክርስቲያን ነን ባዮችንም ከአረመኔው መንግሥት ጋር እጅና ጓንት ያደረገው፣ የወያኔን ቅጣት ተካፋይ ለማድረግ ነው፡፡ ዛሬ “ማን አለብኝ” ባይነት ወገኖችን እያሰቃየ ያለው የህውሃት አባል ብትሆን እንኳ፣ በሃሰት ካልመሰከርክ፣ ጉቦ ካልተቀበልክ፣ ነገ በአንተ ላይ የማይነሳበት ምክንያት አይኖረውም፡፡ ግቦ ካልበሉ፣ በልተዋል ተብለው ይታሠራሉ፡፡ የአቶ መላኩ ፋንታና የአቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መወንጀል አንዱ መሳያ ነው፡፡ ፓስተሮች ኢህአዴግ አባል ካልሆኑ ቤተ ክርስትያም ዓመታዊ ፈቃድ አያገኝም በሚል ፓስተሮች የህውሃት ሥርዓት አራማጆች ሆነዋል፡፡ ይህም የኢትጵያን ሕዝብ በሙሉ አባል አድርጎ ለሃሰዊ ክርስቶስ ሰጋጅ ለማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ሙሴ ከሕዝቡ ጋር መከራ መካፈልን ያልመረጠ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ መጨረሻው ሲዖል ነው፡፡ የነፍሰ ገዳዩ የወያኔ ደጋፊዎች ሆናችሁ ገነት ከገባችሁ፣ አጋንንቶችም ይገባሉ ማለት ነው፡፡ የወያኔን ክፋት በጥልቀት የተረዱ ጳጳስ፡-
7
“ወያኔ/ኢህአዴግ እርቀ-ሰላሙን ከልብ ይቀበላል ማለት “ከእባብ እንቁላል የዶሮ ጫጩት እንደመጠበቅ ይቆጠራል፡፡ የእስልምና እምነት ተከታዮችን የሀባሽ አስተምሮን በግድ ለመጫን በፈጠረው ጣልቃ ገብነት በሺ የሚቆጠሩትን ለስደት፤ በርካቶችን ለእስራት እና ለሞት ሲዳርግ የቆየውና አሁንም ድረስ መቋጫ ያልተገኘለት ውዝግብ ውስጥ የገባው ወያኔ/ኢህአዴግ አሁን ደግሞ የጥፋት ቀስቱን በክርስትና እምነት ተከታዮች እና በቤተ-ክርስቲያን ላይ አነጣጥሯል፡፡”ብለዋል፡፡
“ሰዎች በአንድ ሃይማኖት ካልተዋቀሩ በአንድ አገር ውስጥ ሰላምና እድገት አይመጣም”ተብሎ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት ድርጅቶች በሙሉ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት (World Churches Counsel- WCC) በንዘብ ድጋፍ የተመሥርተው ለሰላምና ለእድገት በሃይማኖቶች መካከል (Interfaith Peace-building Initiative) “መቻቻል”፣ በፍርድ ሚኒስቴር በግብረ ሰናይ ድርጅት NGO ስም እውቅና አግኝቶ መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥሮአል፡፡ መቻቻል – ክርስኢስላም (Chislam) ለክርስቶስ ተቃዋሚ በር ከፋች፣ ማሕበርተኞቹም የሳጥናኤል ደቀ መዛምርት ናቸው፡፡ “መቻቻል” ፖለቲካዊና መንፈሰዊ ይዘት ያለው ሆኖ በማር የተለወሰ ሬት ነው፡፡ የተቋሙ አፈ ቀላጤዎቹ “በወንጌል አምነን ዳግም ልደት አግኝተኛል”በሚሉ በሐዋሪያት፣ በፓስተሮችና በስህተት አስተማሪዎች የተዋቀረ ነው፡፡ ሕዝቡ ወንጌልን ከመጠራጠር አልፎ፣ “እግዚአብሔር አለ ወይ? ካለስ ምን እየሠራ ነው?”እስከ ማለት አድርሰዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም የብዛታቸውን ያህል ዶክትሪናቸውም መጠን የለሽ በመሆኑ፣ እንደ አዋቂነታቸውም ለሕዝቡ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን ወንጌላዊ ምላሽ መሰጥት ተስኖአቸዋል፣ ራሳቸውም ጠያቄዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ደግሞም “በሕዝቦች መካከል ልዩነትን አታድርጉ፣ ግቦን አትቀበሉ፣ ዳር ድንበራችሁን አስጠብቁ፣ ለድሆች ደጀን ሁኑ፣ ቅን ፍርድን ፍረዱ” የሚለው አስተምሮ መንፈሳዊ መሆኑ ቀርቶ የፖለቲካ ቋንቋ ተደገረጎ በመታየቱ የወንጌል አማኞችን ከፖለቲካው መድረክ እንዲርቁ አድርጓቸዋል፡፡ “አገራችን በሰማይ ነው”የሚለው አባባል መጨረሻው ከኢህአዴግ ጋር መጥፋት እንደሚሆን ማረጋገጫው፡- 2ጴጥሮስ 2፡1 ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይነሳሉ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው ጥፋት የሚያስከትል የስህተት ትምህርት በስውር ያስገባሉ፣ ከዚያም ድንገተኛ ጥፋት በራሳቸው ላይ ይመጣል፡፡
የፀረ ክርስቶስ መንፈስ የተጸናወታቸው አንዳንድ ዳግም ልደት አግኝተናል፣ ድነት ከእኛ አይወሰድማ ባዮች በሮሜ 13፡1 “ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና”የምትለዋን በመውሰድ ወገኖችን ለሲዖል ሲያዘጋጁ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰማሉ፣ እንደ ሕይወት ሰጪ ስብከትም ተደርጎ በድረገጾችም ይደመጣሉ፡፡ በዚሁ ምዕራፍ በቁጥር 4 “ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።”የሚለውን አውቆ በመተውም፣ የድሃውን መኖሪያ ቤት እያወደመ፣ አምላክ የሚያመልክበትን ቤተ ክርስቲያን እያፈረሰ፣ ለእውነት የቆሙትን ጋዜጠኞችን እያሰረ፣ ሕዝቡ ከትውልድ ቀየው ለስሙ መጠሪያ በልማት ስም እያፈናቀለ፣ ዳር ድንበርን አፍርሶ ለሱዳን መስጠቱ እየተሰማ ባለበት ወቅት፣ ለወያኔ መንግሥት ድጋፍ መንስጠታቸው ከሰይጣናዊ መንፈስም ጋር አንድነት ያላቸው መሆኑ አመላካች ነው፡፡ የኢህአዴግ አገልጋይ ፓስተሮች፣ ጳጳሳት፣ ዲያቆናት በዳዊት መዝሙር 149፡2-9 “የጽዮንም ልጆች (ኢትዮጵያዊያን) በንጉሣቸው ሐሤትን ያድርጉ። ስሙን በዘፈን ያመስግኑ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት። እግዚአብሔር በሕዝቡ ተደስቶአልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ከፍ ከፍ ያደርጋልና። ቅዱሳን በክብሩ ይመካሉ፤ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ። የእግዚአብሔር ምስጋና በጕሮሮአቸው ነው፤ ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጃቸው ነው፥ በአሕዛብ ላይ በቀልን በሰዎችም መካከል ቅጣትን ያደርጉ ዘንድ፤ ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት፥ አለቆቻቸውንም በእግር ብረት ያስሩ ዘንድ፤ የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት።” የሚለው ምነው ተዘነጋ? ደግሞም እናደርገዋለን፡፡
በሐሳዊ ክርስቶስ መንፈስ የሚመራ ነው ተብሎ በሬዲዮና በቲቪ የተወራበት የሶሪያ ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ በጦርነት ውስጥ እያለ በአክራሪ ሙስሊሞች ክርሰቲያኑ እንዳይጠቃ በሠራዊቲ ሲያስጠብቅ፣ ክርስቲያኖችም መሪያቸውን በመደገፍ አመፀኞችን ሲዋጉ አይተናል፡፡ የሩሲያም ፕሬዚደንት በኦርቶዶክስነቱ ሰዶማዊያንን እንደሚቃወም በተግባር አስመስክሮአል፡፡ በአገራችን ግን በሥልጣን ላይ ያለው ባለሥልጣን አድባራትን እያስፈረሰና ቀሳውስትና ካህናት ከገዳም እያስወጣ፣ ቤተ ክርስቲያናትንና መስኪዶችን እያፈራረሰ መሆኑ እየታየና እየተሰማ “ጻድቅ የአገር መሪ” ከተባለ፣ የክርስቶስ ተቃማዊ መንፈስ ሲገለጽ ሥራው ምን ሊሆን ነው? “ከምርጫ በኋላ” የሚባል ነገር የለም፡፡ ጊዜው ወደ ፍጻሜ ደርሶአል፣ የቀረ ቢኖር፡ ዘረኞች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ገንዘብ ወዳዶች፣ አመንዝራዎች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ሃሰት መስካሪዎች፣ ከኢህአዴግ ጋር ከምድሪቱ በሕይወትም ይሁን በሞት ጠራርጎ አውጥቶ፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ቅዱሳንን በፅዮን አሰባስቦ ሬሳችሁን ማስጎብኘት ነው፡፡ ለዚህም ኢሳይያስ 66 መጨረሻውን ማንበብ ነው፡ በመጨረሻ ዘመን በተመለከተ በትንቢተ ሚክያስ ምዕራፍ አራት የተጻፈው ኢትዮጵያዊያን ጣዖታት አምላኪዎች መሆናቸውን አንብቦ መረዳትና በንስሃ ወደ እውነተኛው አምላክ ከመመለስ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም፡፡
የእግዚአብሔር የጣት አሻራ አለበት ተብሎ የሚነገርለት “ጽላተ ታቦት” የእግዚአብሔር ባርያ ሙሴ ተቀብሎ እስከ ዳዊት ልጅ ሰሎሞን ድረስ ከአይሁድ ጋር ቆይቶ፣ በኋላም በልጁ ቀዳዋሚ ሚኒሊክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ፣ በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ በጽዮን ትግራይ ለሺህ ዓመታት መቀመጡ ተነግሮናል፡፡ ታቦቱን በተመለከተ በ1 ሳሙኤል ከምዕራፍ አራት እስከ ምዕራፍ ሰባት ስንመለከት በዔሊ ልጆች አመጽ ምክንያት ታቦቱ በፍልስጤማዊያን ተማርኮ ከተወሰደ በኋላ በዳጎን ቤት ከጣዖት ጋር በመቀመጡ ጥፋት ማስከተሉን፣ ከፍልስጤም ከወጣ በኋላ የቤትላሚስ ሰዎችም ጉዳት እንደ ደረሰባቸው፣ በአሚናዳብ ቤት በመቀመጡ ግን እንደተባረኩ ተጽፎልናል፡፡ እስራኤላዊያንም በታቦቱ መማረክ አዝነው ሳለ ነቢዩ ሳሙኤል “በፍፁም ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትመለሱ ከሆነ፣ ሌሎች አማልክትንና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፣ ራሳችሁንም ለእግዚአብሔር አስገዙ፡፡”ባላቸው ጊዜ በንስሃ ወደ አምላካቸው ሲመለሱ በጠላቶቻቸው ላይ አስፈሪ ሆነው የተወሰደባቸውን ቦታዎች እንዳስመለሱ አንብበናል፡፡ ንግስት ሳባ የሰለሞንን ጥበብ ላማየት ወደ ኢየሩሳሌም ስትሄድ ለንጉሡ ሶሎሞን ያቀረበችለት ገጸ በረከት ሌሎች ከሰጡት እንደሚበልጥ በ1ኛ ነገሥት 10፡10 ተጽፎልናል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን በወሬ እንደሰማነው ከሆነ ከንጉሥ ሰሎሞን የተወለደው አጼ ሚኒሊክ አመጣው የተባለው ታቦት በእስራኤል ብልጽግና ካስገኘ፣ እንደ ኦርቶዶክስ ምእመናን አባባል በትግራይ ጽዮን ማርያም ውስጥ የሚገኘው ጽላተ ሙሴ ከሆነ እንደ አሚናዳብ ቤት መባረክ፣ እንደ እስራኤል ብልጸግና ሳይሆን ረሃብ፣ ስደትና ጦርነት ነው ያስገኘው፡፡ በ1967 ዓ.ም በቤተ ክርስቲያኒቱ መሪ ቡራኬ ሰጥቶ ወደ ጫካ የተሸኘው ወያኔም የአገርን ዳር ድንበር አፍርሶአል፣ ብዙ ኢትዮጵያዊያንን ገድሎአል፣ እየገደለም ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄዱ ጥፋቶች በሙሉ የርግማን ውጤቶች ናቸው የሚያሰኘው፣ በዚያው ታቦት አምሳያም ሌሎች ታቦታት ተቀርጸው በየአድባራቱ እየተመለኩ በመሆናቸው ነው፡፡ እግዚአብሔርም በኢሳይያስ 44፡14-18 “ዝግባ ይቆርጣል፣ ግማሹን እንጨት ያነደዋል፣ በቀረው እንጨት የጣዖት አምላክን ይሰራበታል፣ ወድቆ ይሰግድለታል፣ ያመልከዋል፣ ወደ እርሱም እየጸለየ አንተ አምላኬ ነህ አድነኝ ይላል፡”እያለን፣ በአዲስ ኪዳንም ሐዋሪያው ጳውሎስ “እኛ ከሰበክንላችሁ ወንጌል ሌላ ወንጌል የሚሰብክ የተረገመ ይሁን” ባለው መሠረት እነሆ በመጨረሻ የርግማኑ ውጤት በኢህአዴግ ዘመን በርትቶብናል፡፡ እስራኤላዊያን የሳሙኤልን ምክር ሰምተው በንስሃ እንደተመለሱ፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት፣ ባለሥልጣናትና ምዕመናን በአንድነት በንስሃ ካልተመለስን በመጨረሻ የሚያገኘን የምፍፈራው ነው፡፡ ይህም ጌታችንና መድኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አትፍሯቸው፣ የተሸፈነ መገለጡ፣ የተደበቀ መውጣቱ አይቀርምና፡፡ በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን አውሩት፣ በጆሯችሁ የሰማችሁትን፣ በአደባባይ አውጁት…” ባለው መሠረት በመታዘዝ የተጻፈ መልዕክት በመሆኑ፣ መልዕክቱን ይዘት መርምሮ ከጥፋት ማምለጥ የግለሰቡ ነው፡፡ “እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ የላኩትን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፣ እኔን የሚቀበልም የላከኝን ይቀበላል፡፡” ዮሐንስ 13፡20
በታቦትና በቅድስት ማርያም ስም አጋንንቶች በቤተ ክርስትያት ውስጥ የሚመለኩ በመሆናቸውን በተመለከተ፣ በመሪጌታ ሠረቀ ብርሃን ዘወንጌል መሳልቅ በተባለ መጽሐፋቸው፣ “አብዛኛው ጥንቆላዎችና ድግምቶች በሥጋ ወደሙ በተዘጋጀው ሕብስትና ወይን፣ በታቦት፣ በመስቀል፣ በጻድቃናት፣ በሰማዕታትና በቅዱሳን መላዕክት ስም የሚደረጉ በመሆናቸው ረጅም ዘመን ለማስቆጠር እድል ሰጥቶአቸዋል” ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት የሚሰበከው በአንደኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በኩል የገባው ወንጌል ሳይሆን፣ በአራተኛው ከፍለ ዘመን በግሪኩ (ሶሪያው) መነኩሴ የገባውን ሃይማኖት መሆኑን በተመለከተም፣ ዶ/ር ጳጳሳ አቡነ ገብርኤልም፣ “በጳጳሳት፣ በካህናትና በሰባኪዎች የሚሰበከውም፣ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን፣ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ እነ ቅዱስ ቂርሎስ የመሠረቱት ሃይማኖትን ትከተላለች፡፡ ቅዱሳን ሰማዕታት አያማልዱም፣ ንስሃ አባት አያስፈልግም የሚሉትን እንቃወማለን፣ ኦርቶዶክስን ማደስና መለወጥ ማለት ራስን ወደ ከንቱነት መለወጥ ነው፡፡” እያሉ ናቸው፡፡ የኦርቶዶክስን እምነት መመሪያን በመቃወምም ሐዋሪያው ጴጥሮስ በ2ኛ መልዕክቱ፣ “የነገርናችሁ እኮ የእርሱን ግርማ በዐይናችን አይተን እንጂ በሰዎች ጥበብ የተፈጠረውን ተረት ተከትለን አይደለም፣ ዕውቀት የጎደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደሚያጣምሙ እነዚህንም ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ፣ በአመጸኞች ስሕተት ተስባችሁ እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፡፡” ማለቱን ተከትሎ በሐዋርያት ሥራም 20:29-30 “ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጴስቆጳሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፣ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ፡፡ እኔ (ጳውሎስ) ከሄድሁ በኋላ ነጣቂ ተኩላዎች መጥተው በመካከላችሁ ሰርገው እንደሚገቡና ለመንጋውም እንደማይራሩ ዐውቃለሁ፡፡ ከእናንተው መካከል እንኳ የራሳቸውን ደቀ መዛምርት ለማፍራት እውነትን የሚያጣምሙ ይነሣሉ፡፡” ብሎአል፡፡ ታዲያ አንተስ ከየትኛው ወገን ነህ?
የክርስቶስ መንፈስ አለብን የሚሉም የፕሮቴስታንት ሰባኪዎችም “አንዴ ኢየሱስን የግል አዳኝህ አድርገህ ከተቀበልክ፣ ድነት ከአንተ አይወሰድም”እያሉ በሚያስተምሩ ፓስተሮች ምክንያት፣ ክርስትያኑ ከነፍሰ ገዳዩ መንግስት ጋር ህብረት እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ ወያኔን ለመጣል የተነሱትን አርበኞች ሲነቅፉና ሲገስጹ ይሰማሉ፡፡
8
ደግሞም በስብከታቸው “ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞችና የአመፀኞች ተባባሪዎች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።”, ማለቱን ተከትሎ “ማንም ሰው ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው የለምና …”ማለታቸው በራሳቸው ላይ እየፈረዱ መሆናቸውን ያለማወቃቸው፣ ምን ያህል ወያኔ ሕሊናቸውን እንደ ተቆጣጠረ የሚያሳይ ነው፡፡ አሁን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለው አማራጭ፡- የምድሪቱ ባለቤት ለመሆን ህውሃት/ኢህአዴግን መቃወም ወይም ከህውሃት/ኢህአዴግ ጋር ከምድሪቱ መወገድ ነው፡፡ ለኢየሱስ ሙሽራ ለፅዮን ሰማያዊ በረከት ከመለቀቁ በፊት መንፈስ ቅዱስ ቤቱን ስለሚያጠራ፣ አብሮ እንደ ጉድፍ ከመጣል በፊት የኢትዮጵያ ጠላቶችን ለመጣል ከተነሱ አርበኞች ጋር መነሳትና በጸሎትም ተባባሪ መሆን ነው፡፡ እግዚአብሔርም “ወደ እኔ ጩኽ እኔም እመለስልሃለው”እንዳለው፣ የኢያሪኮ ግንብ የወደቀው በጪኽት ነው፡፡ ሙሴ አማሌቃዊያንን ድል ያደረገው እጁን ወደ ፈጣሪ በማድረጉ ነው፡፡ ክርስትያኑስ ስለ ሕዝቡ መከራ እጁን ወደ አምላኩ አንስቶ እግዚኦ ማረነ ክርስቶስ ቢል የሚያሳፍር ነውን? በእግዞታ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ኃይል መሆኑ ታውቆም በሟች ፓትሪያርክ እንደ ተከለከለ ተሰምቶአል፡፡ ኢየሱስም ከመከራው ብዛት አስጨናቂዎቹ እየሰሙ ወደ አብ የጮኽው ምሳሌ እንዲሆነን ነው፡፡ እግዞታ ለአሁን ጊዜ ካልሆ ለመቼ ነው? አዲሲቱን ኢትዮጵያ የሚያዩት በጭንቋ ጊዜ በአደባባይ የጮኹላት፣ ለእውነት ሲሉ በእስር ቤቶች የታሠሩ ልጆችዋ፣ በበረሃ ወያኔን እየታገሉ ያሉ ናቸው እንጂ ነፍሰ ገዳዩንና፣ አገር አፍራሹን መንግሥት በመደገፍ ሃሌሉያ የሚሉ አይደሉም፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር በአሜሪካ፣ በእንግሊዝ መንግሥታት፣ በአውሮፓ ሕብረት፣ በተባበሩት መንግሥታት ኢኮኖሚ እቀባ አይፈታም፡፡ ዓለም በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው፣ በአየር መዛባትና በሃይማኖት ምክንያቶች እየተናወጠች ነው፡፡ አርባ ዓመት ሙሉ የታገሉለት ዲሞክራሲ ቢመጣም፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መፍትሄ አያመጣም፡፡ “ወደ እኔ ጩኽ ድንቅና ታምራትን አሳይሃለው፡፡” የተባለው ለኢትዮጵያዊ በመሆኑ፣ ዐይኖቻችንን የጋረደው መርገም ሲገፈፍ፣ በዓለም እንደተጠላን ሳይሆን ተወዳጅና ተፈላጊ እንሆናለን፣ በችግር የረዱንን አገሮች በእጥፍ ብድራትን መላሽ እንሆናለን፣ ማጌጫችን ወርቅና አልማዝ ሳይሆኑ ቶጳዝዮን (ኢዮብ 28፡19) ይሆናሉ፡፡ እንዲያም ሆኖ የኢትዮጵያ ሕዝብም አስታዋሽ አጥቶ በሜዳ የፈሰሰው ንፁህ ደሙ ከንቱ ይቀራልም ማለት አይደለም፡፡ “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይንዳል” እንዲሉ፣ ዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው የጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝም ካቢኔ፣ የህዋት/ኢእአድግም ባለሥጣናትና ደጋፊዎቻቸውም በኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው ሰቆቃ አሜሪካና እንግሊዝ ዐይኖቻቸው እያዩ እንዳላዩ፣ ጆሮቻቸው እየሰሙ እንዳልሰሙ በሆኑበት ነገሮች ተጠያቂ መኖናቸው አይቀርም፡፡ ጳጰሳት፣ ፓስተሮችና ሼኾችም ለኃይለማርያም መንግሥት ጽናትና ረዥም ዕድሜ መመኘት በራሱ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ መከራው ይራዘም ማለታቸው እንደሆነ ምነው ዘነጉት? በኃይለማርያም ዙሪያ ያሉ የፀሎት ጓዶች እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ያለባቸው ሰዎች ቢሆኑ ኖሮ ስልጣኑን እንዲለቅ በመከሩት ነበር፣ እኛም በሰማን ነበር፡፡ ከጊዜው አንጻር የኢየሱስ ክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ከአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን አልፎ የአስቆሮቱ ይሁዳን ገጸ ባህርይ እምነት በሌላቸው በህውሃት አባላት ላይ በዋና ተዋናኝነት አያርፍም፡፡ ኃይለማርያም ደሳለኝ ማስተዋል ያጣ፣ በል የሚሉትን የሚል የክርስቶስ መንፈስ የሌለው መሆኑን እየታወቀ፣ ሀሳዊ ክርስቶስ በእሱ ካልተገለጠ፣ በማን ሊገለጥ ነው? ኢሳት የወያኔን መንግሥት ለመጣል ቅስቀሳ እንደሚያደርግ፣ በአንድ ወቅት ኢራናዊያን መንግሥታቸውን ለመጣል በካሊፎርኒያ ግዛት የቲቪ ጣቢያ ከፍተው ቅስቀሳ በማድረጋቸው፣ የኢራን መንግሥት ወደ መውደቅ መቃረቡን ያልወደደው የአሜሪካ መንግሥት፣ “አንድ አገርን መጣል የአሜሪካ መንግሥት ሥራ ስለሆነ ከዚህ ሥራ እንድትቆጠቡ” ብሎ ጣቢያው መዘጋቱ ኢራናዊያን በቁጭት ይናገራሉ፡፡ ሲ አይ ኤ የኢሳትን ቅስቀሳ የትም እንደማያደርስ ያውቀዋል ለማለት የሚያስችለው፣ ወያኔን ለስልጣን ያደረሰው የአሜሪካ መንግሥት በመሆኑ ነው፡፡ በኢሳት ቅስቀሳ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉ ወገኖች የይሁዳ አንበሳ ያለበትን የኢትዮጵያ ባንዲራ ይዘው ለሰልፍ ከወጡ፣ ኢሳት በጥቂት ቀናት ወይም ወራት ውስጥ እንደሚዘጋ አልጠራጠርም፡፡ ሰበብ ፈልገው ኢትዮጵያዊውን ከአገራችን ይውጡ መባሉ የማይቀር ነው፡፡ የኃይለ ሥላሴ መንግሥት እንዲወድቅ የተፈለገው መንግሥታቸው በይሁዳ አንበሳ በመጠራቱ ነው እንጂ የሰማንያ አመት አዛውንት ተፈርተው አይደለም፡፡ እንዲያም ለማለት ያስቻለኝ፣ በራዕይ 5፡5 በይሁዳ አንበሳ የተሰየመው ኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑንና ሃሰተኛው ክርስቶስም በዚያ ውስጥ መስራት ስለማይቻለው ነው፡፡ ”መቻቻል” ሁሉን አቀፍ የሃይማኖት ድብልቅ ስለሆነ የፕሮቴስታንት አማኞችም ከሳጥናኤል ጋር በ”መቻቻል” አንድነት ፈጥረዋል፡፡ “አንበሳ ሲያገሳ የማይፈራ ማነው?” እንደተባለው ኢትዮጵያዊያን የአይሁዳ አንበሳን ሰንደዓላማ ይዘው ለተቃውሞ ቢወጡ፣ የዐረብ አገራት የሚፈሩት ዘመን መምጣቱ ምልክት ስለሚሆናቸው መደነገጠጣቸው አይቀርም፡፡ ለእስራኤሎችም የመሲሁ ዳግም መምጣት ለመቃረቡ ምልክት ነው፡፡ ደግሞም በወንጌልና በቁርኣን አማኘኞች ዘንድ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው የይሁዳ አንበሳው ኢየሱስ ክርስቶስ (አልመሲሕ ዒሳ) አይደለምን? ባንዲራው ቢውለበለብ የሚደነግጠው ኢህአዴግ ነው፡፡
አሁን በዓለም ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ ነገሮች ሁሉ ቀደም ብለው የተጻፉ በመሆናቸው ከመፈጸም የሚከለክለው አንዳችም ኃይል የለም፡፡ ጊዜውም አሁን መሆኑን የምናውቀው፣ የዐረብ አገራት አመጽ በተመለከተ በሕዝቅኤል 30፡4-5 “ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፤ የተገደሉትም በግብጽ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ ኢትዮጵያና ፉጥ ልድያና መላው ዐረብ ሊቢያና በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡” በኢሳይያስ 19፡2 “ግብጻውያንን በግብጻውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድምም ወንድሙን፥ ሰውም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል፡፡”ስለዚህም በኢሕአዴግ ላይ በተቃውሞ የተነሱ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ዝም እንኳ ቢሉ አመጹ በኢትዮጵያ መቀጣጠሉ የማይቀር ነው፡፡ የመንግሥት ለውጥም እንደሚመጣ ማሳያው በኢሳይያስ 66፡8 …ጽዮን ምጥ ሲጀምራት ልጆችዋን ወዲያውኑ ትወልዳለች፡፡ የልጆችዋም ዋና ተግባር በምዕራፍ 61 ተዘርዝሮአል፡፡ ስለዚህ የወያኔ ባለሥልጣናት ማስተዋል ካላቸው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የሕሊና እስረኞችን ፈትቶ ለሽግግር መንግሥት ሥልጣኑን አስረክበው የበደሉትን ሕዝብ በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ነው፡፡
አቶ ኃይለማርያም በፀረ ክርስቶስ መንፈስ የሚንቀሳቀስ መሆኑ አንዱ ማስረጃ፡- ሟች መለስ ዜናዊን “ዘላለማዊ ክብር ለጠ/ሚኒስትራችን”ማለቱ ብቻም ሳይሆን “እኔ ሀሳቤን በትክክል ይገልፃል የሚለውን አንኳሩን ክፍል ብቻ አይቼ ያቺን ቃል ሳላስተውል አመለጠችኝ፣ እናም ምንም አማራጭ የለኝም አልኳት:፡ እሳቸው (ሟች መለስን) ክርስቲያን አልነበሩም ማለት አይቻልም፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሄር ነበሩ በዚያ ላይ ቅን መሪ ስለነበሩ የብዙ መቶ ሺህ ቅዱሳን ፀሎት ደግሞ ስለደገፋቸው በሞገስ ሊመሩ ችለዋል፡፡” ማለቱ የተደመጠና ለታሪክም የተመዘገበ ነው፡፡ አሁንስ በፀረ ክርስቶስ መንፈስ ሆኖ በቤተ መቅደስ ውስጥ “እኔ ክርስቶስ ነኝ“ የምትለዋ ዐረፍተ ነገር ከልቡ እንዳይወጣ ከልካዩ ማነው? የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናትን “ስምምነቱን በፊርማችሁ ካላጸደቃችሁ ትታሰራላችሁ”ከአለ በኋላ “የቀልዴን ነው” ማለቱ በተመለከተ በወንጌል ሉቃስ 6፡45 “በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና መልካም ሰው ከልብ መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከልብ ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል።“ እንደ ተባለው ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚናገረውም ሆነ በተግባር እያሳየ ያለው የፀረ ክርስቶስን ባህርይ በመሆኑ፣ ራሱ የክርስቶስ ተቀዋሚ ሆኖ የሚገለጥ ሰው ነው፡፡ በማቴዎስ ወንጌል 15፡18 “ሰዎችን የሚሰናክል መምጣቱ አይቀርም፣ ነገር ግን ለመሰናክሉ መምጣት ምክንያት ለሚሆን ለዚያ ሰው ወዮለት፡፡ ይህ ሰው ከነዚህ ከታናናሾቹች አንዱን ከሚያሰናክል፣ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባህር ቢጣል ይሻለው ነበር፡፡”
በአንደኛ ጴጥሮስ 4፡17 ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ መድረሱን ካመለከተ፣ ደግሞም የአሕዛብ ዘመን መጠናቀቂያ ላይ በመሆናችን፣ ኢትዮጵያም የአሕዛብ እናት በመሆንዋ፣ ሰይጣንም መጨሻውን አወቆ በበቀል መንፈስ (የክርስቶስ ተቃዋሚን መንፈስ) በህውሃት/ኢህአዴግ ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያዊያንን ያለ ፍርድ እያስገደለ፣ እያሳሰረ፣ ንብረት እያስወደመ መሆኑ እየታወቀ፣ በአንዳንድ “የወንጌል አማኞች ነን”የሚሉ ሰዎች ከነፍሰ ገዳዩ ከወያኔ ጋር በመተባበር ሲዖል ዘላለማዊ ቤታቸው ማድረጋቸውን ያለማወቃቸው የሚያሳዝን ቢሆንም፣ እንደ ወንጌል ካልኖሩ ግን የማይቀር ጉዳይ መሆኑን የምናውቀው፡- “በክርስቶስ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን ስለ እርሱ መከራ እንድቀበሉም ነው፡፡”የተባልነው እውነትን በፍርሃት ለውጠው ለተገኙ ሁሉ ነው፡፡ በማቴዎስ 7፡21 የተጻፈው፣ “በዚያ ቀን ብዙዎች በሰማይ ያለውን ያባቴን ፈቃድ ሳይፈጽሙ ʻጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይʼበስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንት አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ታምራት አላደረግንምን? ይሉኛል፡፡ በዚያን ጊዜ፣ ʻከቶ አላውቃችሁም፣ እናንተ ክፉዎች፣ ከእኔ ራቁ ʼብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ፡፡”የተባለው ለወያኔ ደጋፊ ፓስተሮች ካልሆነ፣ ለማን ሊሆን ነው?
በብሉይ ኪዳን፣ በፍጥረት መጀመሪያ ከፀባዖት የተጣለው ሳጥናኤል በመጀመሪያ ያሳተው ሔዋንን እንደሆነ ሁሉ፣ በአዲስ ኪዳንም የአሕዛብ እናት (መዝሙር 87) ኢትዮጵያን የራሱ አድርጎ በቁጥጥሩ ካደረገ፣ በሉሰፈር አሸናፊነት ነገራት ሁሉ ፍጻሜ አገኙ ማለት ነው፡፡ የአርማጌድዮን ጦርነትም የለም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በዚህ በመጨረሻ ዘመን የራሱ የሆኑትን ልጆች በኢህአዴግ ላይ አስነስቶ በኢትዮጵያ ሥፍራ እንዳይኖራቸው እያደረገ ነው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የኢህአድ አወዳደቅ አስቀድሞ የታወቀ ነው፡፡ በመሆኑም፣ የወያኔ ደጋፊዎች በፀረ ክርስቶስ መንፈስ የተነሱ በመሆናቸው በኢትዮጵያ ምድር ለዘለዓለም ሥፍራ የላቸውም፡፡ አሁን በተግባር እየታየ ያለው ከዘመናት በፊት የነቢዩ ሙሐመድን (ሶ.ዐ.ወ) ስብከት ሰምተው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ቤተሰብ የተገኙ “ድምፃችን ይሰማ” ወንድሞችና አህቶች በድፍረት እየተጋፈጡ ያሉትና መስዋዕት የሆኑት በኢትዮጵያ ሰይጣናዊ የወያኔን መንግሥት ለመጣል መሆኑ በክርስቲያኖች ዘንድ ከታወቀ፣ በመጨረሻ ዘመን የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ አጀንዳ ለመተግበር መሆኑም ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ወያኔዎች ሰይጣን እንዳስተማራቸው ፣ እግዚአብሔርን ሳይፈሩ በፀነሱ ሴቶች ሆድ ያለውን ፅንስ በበረሃ እያሉ አውጥተዋል፣ በኢትዮጵያዊነቱ አማራ ነህ ተብሎ ተረሽኖአል፡፡ ወታደሩን መጽሐፍ ቅዱስ ለምን ያስክ ተብሎ ርምጃ
9
ወስደውበታል፡፡ በኢትዮጵያዊነቱ ስለ ወገኑ የተሟገታቸውን የትግራይ ተወላጅን ገድለዋል፣ አስረዋል፣ ንብረቱን ዘርፈዋል፡፡ ኦርሞነህ ተብሎ ከቀየው እንዲለቅ አድርገውታል፡፡ ስለዚህም አሁን እየተካሄደ ያለው ትግል በኢህአዴግያዊያን እና በኢትዮጵያዊያን መካከል፣ በአካል እና በመንፈስም ስለሆነ እያንዳዱ ሰው ከሁለት አንዱን መርጦ የትግሉ ተካፋይ መሆን እንጂ መሃል ሰፋሪነት የለም፡፡ የሳውዲ መንግስት ከወያኔ ጋር ለጥፋት ውህደት አድርገው ኢትዮጵያዊያንን እየገደሉ፣ እያሰቃየና እያሰሩ ያሉት ኢትዮጵያ የነቢዩ ሙሐመድን ተከታዮች በማስተናገድዋን ለመበቀል ነው፡፡ ስለዚህ ውጊያችን ከሥጋና ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ነው፡፡ አል-ሑጁራት 49፡14፣ 57፡27 የዐረብ ዘላኖች አምነናል አሉ፣ አላመናችሁም ግን ሰልመናል በሉ – እምነቱም በልቦቻችሁ ውስጥ ገና ጠልቆ አልገባም፣ አላህንና መልክተኛውን ብትታዘዙ ከሥራዎቻችሁም ምንንም አያጎድልባችሁም፣ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና በላቸው፡፡ የእንግሊዘኛው ቁርኣን chapters 49:14 and 57:27 “unbelievers in messenger of Allah, the Son of Miriam”
መጨረሻው ዘመን በተመለከተ በራዕይ 13፡11 “ … ሌላው አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፣ የበግ ቀንዶችም የሚመስሉ ሁለት ቀንዶች አሉት” ይላል፡፡ በኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ በግ መስሎ ይመጣል የተባለው አውሬ መንፈሳዊ መስሎ የመጣው ሐሳሰተኛው ኤልያስ መሆኑን በተለያዩ የድረ ገጾች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ጸሐፊዎች (Bolger’s) አስነብበውናል፡፡ ቀድሞ ስለመጣው አውሬ ግን ያሉት ነገር የለም፡፡ ራሳቸው ቅዱሳን እንደሆኑ ከመጻፍም ቸላ ያሉበምት ጊዜ የለም፡ ፡ ዛሬም ቅዱሳንን እየተዋጉ ያሉት የቀድሞው አውሬ ተከታዮች መሆናቸው ዘንግተውታልና፡፡ በዓመተ ምሕረት ዘመን (ዓ.ም) አውሬው ሰውን እያሳተ ያለው ወንጌል ሰምቶ እንዳይክደው ነው፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ እምነት እየተሰበከ ያለውም የጃንደረባው ወንጌል ሳይሆን በነፍሬሚናጦስ “መዳን በአማላጅ”የሚለውን በመሆኑ፣ የአውሬው ሁለቱ ቀንዶቹ ኦርቶዶክስ ተከታዮች እና የኤልየስ ተከታዮች ካልሆኑ ማን ሊሆን ነው? ጥንትም ሆነ ዛሬ የሰይጣን ዙፋን በእስራኤልም፣ በአሜሪካም፣ በአውሮፓም፣ ፣ በሩሲያም፣ በቻይናም አይደለም፡፡ ዓለምን እገዛለሁ ብሎ የዙፋኑ መቀመጫ ያደረገው በግብፅ ፓትሪያክ ውክልና በተሰጠው በሶሪያዊ ፍሬምናጦስ ጳጳስነት በተመሠረትው ጽዮን ማርያም ውስጥ ለሦስት ሺህ ዓመታት እየተመለከ ያለው ከአርያም የተጣለው አውሬን ነው፡፡ ህውሃትም ተልኮው እንዲሳካ በዚያው መንፈስ ሆኖ ነው መነኩሳትን በመጀመሪያ ካድሬ ያደረገው፡፡ ዛሬም የኦርቶዶክስን አማኞች በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ የቀረው ትቂቶችን መሆኑን “ፋክት” መጽሔት መከታተል ነው፡፡ እንዲያ ሲባል ፕሮቴስታንቱ አልተገዛለትም ማለትም አይደለም፡፡ ብዙዎች በእጁ መሆናቸው አመላካቹ፣ “መለስን ያበቀለች ምድር ሌላ መለስን አትሰጥም ማለት እንዴት ይቻላል?” እያሉ ናቸውና፡፡ ሰስለዚህ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ለውጥ ከሥሩ ካልሆነ መዘዙ የከፋ ነው፡፡ ኃያላን የተባሉ አገራት የሕዝቡን ስቃይ ሰምተው እንዳልሰሙ፣ ዐይተው እንዳላዩ የሆኑት ለራሳቸው ሰግተውም ነው ማለት የሚቻለው፣ በቁጥጥር አውለነዋል የተባለው የይሁዳ አንበሳ ልጆቹ በየአደባባዮቻቸው ጮኽታቸውን እያሰሙ በመሆናቸው ነው፡፡
ሁለቱን ቀንዶች በተመለከተ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የሆነውን እምነታቸውንና ተልዕኮአቸውን በተመለከተ፣ ራሳቸው ባወጧቸው ጽሑፎች የወንጌል ቀበኞችና ከጥልቁ ግብፅ የመጣው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ የተጸናወታቸው ስለመሆኑ ማረጋገጫው፡- 1. ክርስቶስ ሰምራ ዘብሔረ ቡልጋ በቀን ሦስት ሺህ ነፍሳት ከሲዖል ታወጣለች፡፡ ክርስቶስ ሰምራ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የታወቀች ቅድስት ናት፡፡ በየዓመቱ ግንቦት 12 መታሰቢያዋ ይከበራል፡፡ ወወሐባ ኪዳነ ከመ ታውጽእ ነፍሳተ አምሲኦል ሠለስተ እልፈ ነፍሳት በበዕለቱ፡፡ ትርጉም ጌታም በየቀኑ ከሲኦል ሦስት ሺህ ነፍሳት እንድታወጣ ሥልጣን ሰጣት ወይም ቃል ኪዳን ሰጣት፡፡ ገድለ ክርስቶስ ሠምረ ዘጥምቀት ቁ 61 www.abaselama.org/2007/07/bllog_post08.html 2. “የኦርቶዶክስ ስያሜ የተገኘው ከአውሬው (666) ነው፣ ትርጉሙም ጊዜ ያለፈበት አክራሪ ማለት ነው” በማለት ይቀጥልና “በትንቢት ተነግሮለት ታላቅ ኃይልና ሥልጣን ተሰጥቶት ከብሔረ ሕያዋን የወረደውን ቅዱስ ኤልስያን መቃወምም ይሁን ማስቆም አይቻላችሁም ያላችሁ ብቸኛ አማራጭ የዚህን አስፈሪ ቀናኢ ነቢይ የሚያዘውን የእግዚአብሔር ቃል መስማት ብቻ ነው፡፡ ይህን እሺ በጄ ብላችሁ ብትቀበሉ ባለፉት ዘመናት ሁሉ በኑፋቄ ሃይማኖታችሁ ተደናግረው ሲዖል የወደቁትን ወገኖቻችሁን ሁሉ ለማስተማር የምህረቱን በር ትከፍቱታላችሁ፡፡ እምቢ ብትሉ ግን የቅዱስ ኤልያስን ፈራጅነት መቋቋም አትችሉም፡፡ እንግዲህ ሁላችን በእመቤታችን ርህራሄ አንድ ሆነን፡ በንስኀ፡ ለኢትዮጵያ፡ ትንሳኤ እግዚአብሔር ያብቃን አሜን፡፡” ማኅበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አሐቲ የሰማይ ጉባኤ ዘቅድስት ቤተክርስቲያን ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ ወእመፍጥረተ ወላዲተ አምላክ፡፡ምንጭ MINILIK SALSAWI (ምንሊክ ሳልሳዊ): 2012-08-12
ሟቹ ፓትሪያርክም ለግብዕ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ “We Ethiopians were Christians for over a thousand years before Christ.” Patriarch of Ethiopia Orthodox Tewahedo Church, www.ethiopianreview.com April 16th 2007 ማለታቸው ነው፡፡ በዮሐንስ ወንጌል 10፡7-9 ኢየሱስ ያስተማረው፣ “እውነት እላችኋለሁ የበጎች በር እኔ ነኝ፡፡ ከእኔ በፊት የመጡት ሁሉ ሌቦችና ቀማኞች ነበሩ በጎቹ ግን አልሰሟቸውም፡፡ በሩ እኔ ነኝ፣ በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል፣ ይገባል፣ ይወጣልም፣ መሰማሪያ ያገኛል፡፡” በማቴዎስ 6፡24 “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ (ለዚህ ዓለም ገዥ ቅጥረኛ ወያኔ) መገዛት አትችሉም፡፡” እንደ ተባልነው፣ ዛሬ በዙሪያችን ካሉ ጠላቶቻችን የህውሃት/ኢህአዴግ መሣሪያ የሆኑ ለክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ መንገድ ጠራጊዎችን ሳንቃወም በኢትዮጵያዊነታችን በቅድስቲቱ ከተማ በፅዮን እኖራለሁ ማለት ጉምን እንደ መጨበጥ ነው፡፡
በሐዋሪያ ሥራ ሳውል በእስጢፋኖስ መገደል ተባባሪ እንደነበረና በኋላም ሐዋሪያ ከመባሉ በፊት ንስሃ መግባቱን ለትምህርት እንዲሆነን መጻፉን በተመለከተ፣ ዛሬም በእስጢፋኖስ መንፈስ ተነሳስተው እውነትን በመናገራቸው መስዋዕት የሆኑና በእስር የሚንገላቱ ብዙ ሆነው ሳለ፣ በመጨረሻ በወያኔ እጅ የወደቀው አንዳልካቸው ፅጌ ለኢህአዴግ መንግሥት ፍፃሜ መሆኑን የሚያመላክተው አማራ ትግሬ፣ ኦሮሞ ፣ሃዲያ ወላይታ፣ … ተብሎ በወያኔ እንዲከፋፈል የተደረገው ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ አንድ መሆኑን እያስመሰከረ በመምጣቱ ነው፡፡ ከእንግዲህ ትግሉ በኢትዮጵያዊያን እና በወያኔያዊያን መካከል ነው፡፡ ንስሃ ገብቶ ትግሉን መቀላቀል ነው እንጂ መሃል ሰፋሪነት ተቀባይነት የለውም፡፡
ሃሳዊ ክርስቶስ መነሻው በኢትዮጵያ ስለመሆኑ ማስረጃዎች ቢዘረዘር አንድ ትልቅ መጽሐፍ ይሆናል፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ሃይማኖታዊ በዐላት አንዱ መስቀል (ደመራ) ነው፡፡ መስቀልን በተመለከተ የሕይወት መመሪያ የሆነው ወንጌላችን በፊልጵስዩስ 3፡17 “… ብዙዎች የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነው ይነሳሉ፡፡ መጨረሻቸውም ጥፋት ነው፣ ሆዳቸውም አምላካቸው ነው፣ ክብራቸውም በነውራቸው ነው፣ ልባቸው ያረፈው በምድራዊ ነገር ላይ ነው” ብሎናል፡፡ የቤተ ክርስቲያን መለያ የሆነው መስቀል፣ በደመራ ተሰይሞ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት፣ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ መዘምራን የክብር ልብሳቸውን ለብሰው በከበሮ፣ በጸናጽልና በእልልታ ታጅበው ፓትሪያርኩ የኢየሱስ መስቀል በእሳት በማጋየት ይከበራል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስለ ሰው ልጆች በደል በመስቀል ላይ ሞቶ ከጨለማ ገዥው ሥርዓት ነፃ ያወጣበት የክርስቲያኖች ዓርማ ማቃጠሉ ማንን ለማስደሰት ነው? በዚያው ሳምንትስ በሰብረ ዘይት፣ በሆራ ሃይቅ የሚመለኩ አጋንንት፣ በየአውራጃውና በየወረዳው በባህል ስም ልዩ ክብር የተሰጠው አምልኮስ ለማነው? ፋሲካን በተመለከተ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገገራችንን የሚያበስረውን ዶሮ ማረዱ፣ ጨለማውን ከመውደድ የመነጨ ባህል አይደለምን? ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቀጥሎ የኢየሱስን መስቀል የሚያቃጥሉ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የሰይጣን ማህበርተኞች Ku Klux Klan ናቸው፡፡ ለማረጋገጥም ድረገጾቻቸውን መመልከት ነው፡፡ የኢየሱስን መስቀል በማቃጠል ወደ መንግሥቱ መግባት ይቻላል ተብሎ ይጠበቅ ይሆን? ሳጥናኤል በኢትዮጵያ መሆኑ ሌላው ማረጋገጫ የኢየሱስ ሐዋሪያት የነበሩ ማቴዎስና ማቴያስ በኢትዮጵያ መገደላቸው ማስረጃ አለ፡፡ ኢትዮጵያ ከክርስቶስ ልደት በፊትም የክርስቲያ አገር ነበረች የሚለው አነጋገር፣ ዛሬ ካልተኖረበት ፋይዳው ምንድነው?
ኦርቶዶክስ መስቀል በዓል Ku Klux Klan ኢሉሚናቲ የናዚ ዓርማ swastika
በክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እየተንቀሳቀሰ ያለው የሃይለማርያም ደሳለኝ መንግሥት መሆኑን በተመላክተ፣ ግለሰቡ ከአስቆሮቱ ይሁዳ ጋር የሚያመሳስለውም፡- የአስቆሮቱ ይሁዳ ከሐዋሪያቱ አንዱ ሆኖ በመጨረረሻ ዕራት Last Supper ከቂጣው የበላና ከጽዋው የተጎነጨ ግለሰብ ነበር፡፡ ኃይለማርያምም የኢየሱስ ብቻ ቤተ
10
እምነት ተከታይ ሆኖ በኢየሱስ ስም የተጠመቀ፣ ስጋ ደሙን የወሰደ፣ መጠሪያውም ክርስቲያን ቢባሉም፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን የካደ ነው፡፡ ሰይጣንም ኢየሱስን ቢያውቀውም እርሱ ክርስቶስ መሆኑ አላወቀውም ነበር፡፡ በሐሳዊ ክርስቶስ መንፈስ የሚነሳው ግለሰብ ይሁን ቡድን ከኦርቶዶክስ ቤተ ክህነት ሰዎች መካከል የማይሆነው፣ እንደ ወንጌል አስተምሮ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ድነት ከአማግኘት ይልቅ በቅድስት ማርያምና በቅዱሳን አማላጅነት ወደ እግዚአብሔር ዙፋን እንገባለን የሚሉ በመሆናቸው፡፡ ከሙስሊሙም ማህበረሰብ የማይሆነውም፣ ኢየሱስን ከነቢይነት ባለፈ አያውቁትም፡፡ አይሁድም ቢሆኑ በክርስቶስነቱ ሳይሆን የማርያም ልጅ እንደ ነበር ነው የሚያውቁት፡፡ አይሁድ ፋሲካን የሚያከብሩት ከግብፅ የወጡበትን ዕለት በማሰብ እንጂ የኢየሱስን ትንሣኤ በማስታወስ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ግን ፋሲካ የሚከበረው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሞቶ፣ ተቀብሮና በሦስተኛው ቀን መነሳቱን በተመለከተ ነው፡፡ ከጊዜው አንጻር በፀረ ክርስቶስም መንፈስ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ያሉት በኢትየጵያ ውስጥ በክርስትያኖች መካከል ነው፡፡ የኦርቶዶስ ቤተ ክርስቲያን ከወያኔ መንግሥት ጋር መንፈሳዊ ውህደት ፈጥረዋል የሚያሰኘው፣ ፓትሪያክ በወያኔ ምርጫ በመደረጉ ነው፡፡ ኢየሱስም በወንጌል “የኋለኞች ፊተኞች፣ የፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ” ባለው መሠረት ለወያኔ ትልቅ ራስ ምታት የሆኑት፣ እግዚአብሔር ለዓላማው ያስቀመጣቸው “ድምፃችን ይሰማ” ወገኖች በኢትዮጵያ እንዳይገለጥ እያደረጉ ናቸው፡፡ ይህም ሰውየው ከንጥቀት በፊት እንዳይገለጥ እያደረጉ ናቸው፡፡ ጊዜውም ቆሞ ስለማይጠብቅ፣ በአንድ ጀምበር ወያኔዎች አገር ጥለው እንዲወጡ ያደርጋቸዋል፡፡ኮነሬል መንግሥቱ እንደ ፈረጠጠው ማለት ነው፡፡ ከዚያም ከሌሎች ጋር ውህደት ፈጥረው ወደ ኢየሩሳሌም ኢትዮጵያ ለጦርነት እንደሚሄድ አስቀድሞ የተጻፈ በመሆኑ ተግባራዊ ያደርጉታል፡፡ በኢትዮጵያ ግን የሚመጣው መንግሥት ተቀዳሚ ተግባሩ እስረኞችን መፍታት፣ ያዘኑትን ማጽናናት፣ ቅጥቱን ማደስ፣ … ናቸው፡፡ ሕዝቡም ሃዘኑን ለማስታወስ የመይችልበት ይደርሳል፡፡
ወገኔ ኢትዮጵያዊ ይህን መልእክት ስጽፍ የራሴን እምነት እንድትከተል ወይም ያለኝን እውቀት ላሳይህ አይደለም፡፡ አምላክ በሰጠህ ማስተዋል እውነትን አንብበህ፣ በዐይንህም አይተህ፣ በጆሮህም ሰመታህ ከአጥፊዎች እንድትርቅ ነው፡፡ አውቆ ክፉ የሆነውን ሰው የፓስተሮች፣ የወንጌላዊያን፣ ጾምና ጸሎት ደግ ሰው አያደርገውም፡፡ በልቡ ያለውንም ከማድረግ አይመለስም፡፡ ህውሃት/ኢህአዴግ ፀረ ክርስቶስ አራማች ግብረ ሃይል መሆኑን ማሳያውና ነገ ለሚያውጀው ማንነቱ አመላካቹ በአዲስ አበባ በእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ዐናት ላይ ከመስቀሉ በላይ የራሱን ዓርማ የያዘ የኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲውለበለብ ማድረጉ ነው፡፡ በዚያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሰይጣናዊ ሥራዎች የታዩበት ሆኖ በመጨረሻ አርቆ ሃሳቢዎች መነኩሳት መከልከሉ ነው፡፡ ባንዲራውን ግን እንዲወርድ ያላደረጉት አንድም ሳያዩት ቀርተው ወይም ሚስጢሩ ተሰውሮባቸው ነው፡፡ በ2ኛ ተሰሎንቄ 2፡3 12 “አስቀድሞ ዐመጽ ሳይነሳ፣ ለጥፋትም የተመደበውም የአመፅ ሰው ሰይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና፡፡ እርሱም አምላክ ከተባለና ከሚመለከው ነገር ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው፣ እርሱም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተቀምጦ እኔ አምላክ ነኝ እያለ ዐዋጅ ያስነግራል፡፡ የዐመፀኛው አመጣጥ በሰይጣን አሠራር ላይ የተመሠረተ ሲሆን በሃሰተኛ ታምራት፣ በምልክቶችና በድንቅ ነገሮች ሁሉ ይሆናል፡፡ እንዲህም ይድኑ ዘንድ እውነትን ባለመውደድ የሚጠፉትን ሰዎች በሚያታልል በተለያየ የክፋት ሥራ ይመጣል፡፡ በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር በሐሰት እንዲያምኑ የስህተት አሠራር ይልክባቸዋል፣ ይህም የሚሆነው እውነትን ያላመኑት ነገር ግን በክፋት ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ እንዲፈረድባቸው ነው፡፡”
ወቅታዊ የእግዚአብሔርን እውነት ለማሳወቅ ድርሻዬን እንደ ተወጣሁ፣ አንተም አንቺም ለወገንህ በአመቸህ መንገድ መልእክቱን ለቤተ ክርስቲያንና ለመስኪድ ሃላፊዎች ብታስተላልፍ የወያኔን ኃይል ታዳክማለህ፣ የኢየሱስ ክርስቶስንም ዳግም መምጣት ታፋጥናለህ፡፡
እስከዛው የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ ይብዛልን፡፡
የ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር Disciple of Jesus Christ
ይድረስ ለኢትዮጵያዊ
Read Time:50 Minute, 18 Second
- Published: 10 years ago on July 26, 2014
- By: maleda times
- Last Modified: July 26, 2014 @ 9:51 pm
- Filed Under: Ethiopia
- Tagged With: news
Average Rating