የዒድ ተቃውሞ ተሰርዟል!
ዒድን አስመልክቶ የውስጥ አዋቂ መረጃዎች እየደረሱን ነው!
የመንግስት የሽብር ዕቅድ እንዲሳካ አንፈቅድም!
እሁድ ሐምሌ 20/2006
የኢድ አልፊጥር ክብረ በአል ላይ ቀድሞ የተሰላ ኹከትና ግርግር ለማስነሳት መንግስት ዝግጅቱን በማድረግ ላይ መሆኑን ከቅርብ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ድምጻችን ይሰማ!
የዒድ አል ፊጥር በዓልን አስመልክቶ የውስጥ አዋቂ መረጃዎች እየደረሱን ይገኛሉ፡፡ መንግስት የፊታችን ሰኞ ወይም ማክሰኞ በሚከበረው የዒድ አል-ፊጥር በዓል ላይ ኹከት ለማስነሳት ማቀዱም ታውቋል፡፡ በዚህ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታላቁ የረመዳን ወር የጾም ፍቺ በሚከበርበትና በአገራችንም በዋነኝነት በአዲስ አበባ ስታዲየም ከፍተኛ ሕዝብ በተሰበሰበበት በሚከበረው የኢድ አልፊጥር ክብረ በአል ላይ ቀድሞ የተሰላ ኹከትና ግርግር ለማስነሳት መንግስት ዝግጅቱን በማድረግ ላይ መሆኑን ከቅርብ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የግርግሩ ማእከል እንዲሆን በታሰበው አዲስ አበባ ስታዲየምና በአካባቢውም በካርታ በታገዘ ሁኔታ ዝግጅቱ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
እስካሁን በህዝበ ሙስሊሙ መካከል ሁከትና ረብሻ ለማስነሳት የታቀደ ስለመሆኑ የሚያሳዩ ተከታታይ የውስጥ መረጃዎች እየደረሱን ሲሆን መረጃዎቹን የማጣራት እና የመለየት ስራም በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ ይህንንም አስመልክቶ የሚደርሱ ተጨማሪ መረጃዎችን እና አስፈላጊ ማስታወሻዎችን የምንለቅ በመሆኑ ገጹን በቅርበት እንከታተል!
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
(በድምፃችን ይሰማ የሚወጡ ጽሁፎች እና መግለጫዎች መብዛታቸው ሳይሆን ተደራሽነታቸው እና ተፅእኖ መፍጠር መቻላቸው ነው ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው! እርሶዎም መረጃዎችን በሚፈለገው መልኩ መከታተል እና መልእክቱን ለሁሉም እንዲደርስ ማድረግ ይጠበቅብዎታል!)
የመንግስት የሽብር ዕቅድ እንዲሳካአንፈቅድም!
የዒድ ተቃውሞ ተሰርዟል!
እሁድ ሐምሌ 20/2006
በሃምሌ 11 ‹‹የጥቁር ሽብር›› ቀንየሙስሊሙ ማህበረሰብ ትግልፍጹም ሰላማዊነት ሰላም የነሳውመንግስት አሳፋሪና ታሪክየማይረሳው የሃይል እርምጃወስዷል፡፡ ይህንኑ እብሪቱንበመቀጠል አሁንም በተመሳሳይመልኩ የኢድ ቀን ተቃውሞ ላይከፍተኛ ብጥብጥና ሽብር አስነስቶየሰው ህይወት በማጥፋትእንቅስቃሴያችንን ለማጠልሽትበከፍተኛ ዝግጅት ላይ መሆኑታውቋል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ዒድበሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲኖር ታቅዶየነበረውን ተቃውሞ በሚከተሉትዋና ዋና ምክንያቶች መሰረዝአስፈላጊ ሆኗል፡፡
1. በመጀመርያ ደረጃእንቅስቃሴያችንን ምንጊዜምሰላማዊና የሰላም ወዳዱ ህዝባችንንባህልና ክብር የጠበቀ መሆኑ የታወቀነው፡፡ ስለዚህ ከህዝባችን ባህል እናክብር ተፃራሪ የሆነ ተግባርለመፈፀም እየተንቀሳቀሰ ካለውመንግስት ጋር በእኩል ደረጃመገመት ለህዝባችንምለእንቅስቃሴያችንም የማይመጥንበመሆኑና ለመንግስትም ያሰበውንእንዲያሳካ እድል መስጠት አስፈላጊባለመሆኑ፤
2. ‹‹ጥቂቶች›› እያለ ራሱንየሚያታልለው መንግስት በዒድየሚኖረውን ግዙፍ ህዝባዊተቃውሞ በከፍተኛ ሁኔታ በመስጋትዝግጅት እያደረገ እንደሆነ በጣምአስተማማኝ መረጃ በመገኘቱ፤በአሁኑ ወቅትም በመንግስት አካላትእየተካሄደ ያለው ውይይት‹‹የምንወስደው እርምጃ በዱላይሁን ወይንስ በጥይት?›› የሚለውእንጂ የሃይል እርምጃ መውሰዱአማራጭ የሌለው እንደሆነ ከውሳኔመድረሱን በማረጋገጣችን፤
3. በመቀጠልም መንግስት ለራሱየከሰረ የፖለቲካ ጥቅም ለመገብየትደፋ ቀና የሚልበትን እኩይ እቅዱንለማክሸፍና ይህንን ለማድረግያበቃውን ግዙፍ እንቅስቃሴበመንግስት እርምጃ እና ማዋከብተቻኩሎ ረጅሙን ጉዟችንንበአጭር ትንፋሽ እንድንጨርስየሚያደርጉ ማናቸውንም በሮችመዝጋት በማስፈለጉ፤
4. መንግስት በሙስሊሙ ላይከፍተኛ ግፍ የፈፀመ ቢሆንም ሃገርለማስተዳደር ኃላፊነት ወስጃለሁብሎ የሚያስብ ከሆነ ከተግባሩእንዲታቀብና አሁንምየሚመለከታቸው አካላት ቆምብለው እንዲያስቡበት ለማድረግ፤5. ላለፉት 3 አመታት ብዙ ችግሮችንተቋቁመን ሰላማዊነታችንንያስመሰከርን በመሆኑና አሁንምበዚሁ መርሃችን በመፅናት ሌሎችዘርፈ ብዙና እስካሁን ድረስያልተሞከሩ ስልቶችን ደረጃ በደረጃመተግበር የበለጠ ውጤታማያደርገናል ብለን በማመናችን፡፡
ስለሆነም ህብረተሰቡ የኢድ ቀንምንም ተቃውሞ እንደሌለበመገንዘብ ከዘመድ አዝማድ ጥየቃበተጨማሪ በ‹‹ጥቁሩ ሽብር››የተጎዱ ሰዎችን በመዘየርና እገዛየሚፈልጉትንም በመርዳትእንዲያሳልፈው ጥሪ እናቀርባለን፡፡ወደ ሰላት በምንሄድበትም ሆነበምንመለስበት ወቅት ከመንግስትአካላት ሊደርስ የሚችልንማንኛውም ትንኮሳ በትዕግስትበማሳለፍ ብስለታችንን እናሳይ፤የመንግስትን አላማም እናክሽፍ!በተጨማሪም እኛን መስለውበየአካባቢያችን ባሉ መስጊዶችበመግባት ሙስሊሙን ማህበረሰብለአደጋ ለማጋለጥና ለመከፋፈልከሚሞክሩ የመንግስት ሀይሎችራሳችንን እንጠብቅ!
በዒድ ቀን በጋራ አንድነታችንን፤ሰላም ወዳድነታችንን፤ለእንቅስቃሴው ያለንን ክብርናታዛዥነታችንን በማሳየት ለቀጣዩዘርፈ ብዙ ትግል እንዘጋጅ!
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድልደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
Average Rating