www.maledatimes.com ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ፡ የግብረ ሰዶም መረጃዎች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ፡ የግብረ ሰዶም መረጃዎች

By   /   July 27, 2014  /   Comments Off on ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ፡ የግብረ ሰዶም መረጃዎች

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 46 Second

 

ግደይ ገብረኪዳን

ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ – ሮሜ 1፡ 22
ዚህ በፊት አጠቃላይ የግብረ ሰዶማውያንን ሴራ የሚያሳይ ጽሑፍ “የግብረሰዶማውያን ነገር” በሚል ርእስ ተመልክተናል። ያላነበቡት ጽሑፉን እንዲመለከቱት እጠቁማለው። በቅርቡ በዚህ አንድ ሃገራዊ ድረ ገጽ ደቡብ አፍሪካ ተቀማጭነቱ ካደረገ ግብረ ሰዶም ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ አቅርቦ አደገኛ የማጭበርበር ሙከራ አድርጎ ነበር። በቃለ መጠይቁ በተለይ ግብረ ሰዶማውያን ሕጻናትን አያባልጉም የሚል ውሸት ተወርቷል። ሕጻናትን ማባለግ የግብረ ሰዶም መሰረት መሆኑን ግብረ ሰዶማውያኑ ራሳቸው ይናገራሉ።(22) በውነቱ ግብረ ሰዶም ድርጊት በሃገሪቱ ሕግ ክልክል ሁኖ ሳለ በማናለብኝነት እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት የሚፈጽም ሰው ቃለ መጠይቅ ማድረግ እንዴት እንደማያስጠይቅ ግራ ያጋባል። ይህ ድርጊቱን ከመደገፍ የሚለይ አይደለም። ሩስያ እንዳወጣችው የጸረ-ግብረ ሰዶም ፕሮፖጋዳ ሕግ አስፈላጊነቱ እዚህ ጋር ነው። የሆነ ሁኖ ግራ ዘመም፣ “ኢ-አማኝ” ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም የሚያራምዱ ሰዎች አወቁትም አላወቁትም የሰይጣን ፈረስ ናቸው። በዚህ ጉዳይ ተመልሼ እመጣበታለው።
በዋናነት አሁን ይህን መጻፍ ያስፈለገው ግን ለዚህ መልስ ለመስጠት ሳይሆን በማህበራዊ ድረ ገጾች አንዳንድ ሰዎች ግብረ ሰዶማዊነት ችግር የሌለው ጤነኛ ሌላ ተራ የሰው ልጅ ተግባር አድርገው የሚወስዱት ስላሉ በዚህ ድርጊት የተዘፈቀው ዓለም ምን እያስተናገደ እንዳለ ያውቁትና ያስቡበት ዘንዳ ነው።
ወደድንም ጠላንም ግብረ ሰዶም እንዲስፋፋ የሚወተውቱት ቁንጮዎች ሰይጣናዊ አጀንዳ እንዳላቸው የታወቀ ነው። ይህን አስከፊና ቆሻሻ ድርጊት እንድንደግፍ ጫና የሚፈጥሩት የሰብአዊ መብት ወዘተ. የሚቀባጣጥሩት ለሽፋን ሲሉ ብቻ ነው። እንጂ እውነተኛው መረጃ የሚናገረው ሌላ ነው። ቁጥሮችን አመሳክረን እስኪ ይህንና ሌላ የአእምሮ መሳት የሚያሳዩ ድርጊቶቻቸውንና ከራሳቸው አልፎ ለሌላው የሚተርፍ ጥፋት በማውረድ የሚያመጡትን ኪሳራ እንመለከታለን። ይህ ጽሑፍ በዋቢነት የተጠቀመው የ Frank Joseph, M.D., Everyone Should Know These Statistics on Homosexuals ነው።
በአለም ዙርያ ሰዶማዊ አጀንዳ ሕዝቡ ላይ አስገድዶ ለመጫን ሙከራው ተጀምሯል። አሁን እዚህ ከስር ባጭሩ ዋና መረጃዎችን ዝርዝር እንመለከታለን።

የግብረ ሰዶማውያን የኑሮ ዘይቤ

70 መቶኛ ግብረ ሰዶማውያን ከሚገናኟቸው ሰዋች ከ 50 መቶኛ በላይ የሚሆኑት ጋር አንድ ግዜ ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ።(3)
በአመት ውስጥ በመካከለኛው ስሌት አንድ ግብረሰዶማዊ ከ20 እስከ 106 ሰዎች ጋር ይወጣል።(6) ግብረ ሰዶም ያልሆኑ ሰዎች መካከለኛ ስሌት በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ (ልብ በሉ በዓመት አይደለም) 8 ነው።
አብዛኞቹ የግብረሰዶም ግንኙነቶች የሚፈጸሙት በአደንዛዥ እጽ፣ በአልኮል መጠጥ፣ ወይም ቅጥ ያጣ ዝግጅት ተጽእኖ ስር ነው።(7)
አብዛኞቹ ግብረ ሰዶማውያን ስለ ሕይወታቸው ዘይቤ የሚሰጣቸውን ማስጠንቀቅያ አይሰሙም፡ “ስለ ጤና መመርያ ያላቸው እውቀት ከፍተኛ ነው፣ ሆኖም ግን ይህ እውቀት ከጠባያቸው ጋር አብሮ አይሄድም።”(16)
በአሜሪካ ግብረ ሰዶማውያን በ1970ዎቹ መጀመርያ ላይ ነበር ግብረ ሰዶማዊነትን ከአእምሮ ሕመም ዝርዝር ውስጥ ያስወጡት፣ እንዲህ ያደረጉት አመታዊ የአሜሪካ ሳይኪያትሪክ ማህበር – ኤፒኤ (American Psychiatric Association – APA) በተከታታይ ሲያውኩ ከከረሙ በኋላ ነበር። “ሽምቅ ረብሻ ዘዴዎች (Guerrilla theater tactics) እና ይበልጥ ቀጥተኛ እየጮሁ መረበሽ (shouting matches) ስልት በተገኙበት መለያቸው ነበር።”(2) ኤፒኤ ግብረ ሰዶማዊነትን ከአእምሮ ሕመም ዝርዝር ውስጥ ከሰረዘው በኋላ ሕጻናትን ማባለግ (pedophilia) ቢሆንም ተሰርዟል (አዋቂው ሰው “ኅሊናዊ ጭንቀት” እስካልተሰማው ድረስ / except when the adult feels “subjective distress”)።(27)
በአሜሪካ ጨብጥ ከሚያዙት ሰዎች 3 – 4 መቶኛ፣ ቂጥኝ ከሚያዙት 60 መቶኛ፣ እና በግብረ ስጋ ከሚተላለፉ ሕመሞች ውጪ ወደ ሆስፒታል ለመታከም ከሚመጡ ጠቅላላ ሰዎች 17 መቶኛ የሚሆኑት ግብረ ሰዶም ናቸው።(5) እንዲህ በሚሆንበት ግዜ ከህዝቡ አጠቃላይ ቁጥራቸው 1 – 2 መቶኛ ሁነው ነው።
የግብረ ሰዶማውያን የሕይወት ዘይቤ ጤና ያጣ ነው፣ በቂጥኝ፣ በጨብጥ፣ የጉበት በሽታ፣ “ግብረ ሰዶም ሆድ መታወክ” (አንጀት የሚያጠቃ በሽታ)፣ የሳምባ ነቀርሳ እና ሕዋሳትን የሚያጠቃውና ተዋልዶ ሊያዛባ የሚችለው ሳይቶሜጋሎቫይረስ በሽታዎች ያንበሳውን ድርሻ ግብረ ሰዶማውያን ይይዛሉ።(27)
 73 መቶኛ የስነ ልቦና አማካሪዎች ወይም ሳይኪያትሪስቶች ግብረ ሰዶማውያን ከተራው ሰው ያነሰ ደስተኞች ናቸው ይላሉ፤ ከነዚህ ሳይኪያትሪስቶች ውስጥ ደግሞ 70 መቶኛዎቹ ደስታ ማጣታቸው በማህበራዊ መገለላቸው ምክንያት አይደለም ይላሉ።(13)
25 – 33 መቶኛ የሚሆኑት ግብረ ሰዶማውያን ሴቶችንም ጨምሮ አልኮል ሱሰኞች ናቸው።(11)
በአንድ ጥናት ዘገባ ላይ ከተጠየቁት ግብ ሰዶማውያን 43 መቶኛዎቹ  በሕይወት ዘመናቸው እስከ 500 እና ከዛ በላይ ሰዎች ጋር እንደተገናኙ አምነዋል፤ 28 መቶኛዎቹ በሕይወት ዘመናው ከ 1000 በላይ ጋር ሂደዋል፣ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 79 መቶኛዎቹ የሄዷቸው ሰዎች ግማሽ የሚሆኑት ምንም የማያውቋቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።(3)
78 መቶኛ ግብረ ሰዶማውያን በግብረ ስጋ የሚተላለፍ በሽታ አለባቸው።(20)
የኒውዮርክ ከተማ 1ኛ ደረጃ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛ የሆኑት ጆን ማርተፍ እንደሚሉት “በትላልቅ ከተሞች ከሚፈጸሙት የግድያ ወንጀሎች ውስጥ ግማሾቹ የሚፈጸሙት በግብረ ሰዶማውያን ነው።”(10)
የሎስ አንጀለስ ፖሊስ ካፕተይን ዊልያም ሪድል እንደተናገረው “በሎስ አንጀለስ የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ህጻናት የግብረ ሰዶማውያን ሰለቦች ነበሩ።”(10)
ከአጠቃላይ እራን ማጥፋት ቁጥር ውስጥ 50 መቶኛው የግብረ ሰዶማውያን ድርሻ ነው።(10)
ሳይኪያትሪስቱ ዶ/ር ዳንኤል ካፕሮን እንዳለው “ግብረሰዶማዊነት ጤናማም ሙሉእም አይደለም። ግብረ ሰዶማዊ ሰው ጤናማ ወሲብ ሕይወት ካለው ሰው በላይ ደስታ ያጣ እና ጎዶሎነት የሚሰማው ይሆናል።”(10) ግብረ ሰዶማዊነት ስህተት ነው ብለው የሚያምኑ ሌሎች ሳይኪያትሪስቶችን ለማየት National Association for Research and Therapy of Homosexuality ይመልከቱ።
ግብረ ሰዶማውያን ኤድስን በማሰራጨት ሰፊ ሚና ተጫውተዋል፣ እንዲህ ሁኖም ሁኔታውን ለመቃወም ማህበር አቋቁመው ይንቀሳቀሳሉ። ዛሬ ላይም ቢሆን በአሜሪካ ግብረ ሰዶማውያን በኤድስ ከተያዙ ሰዎች 50 መቶኛዎቹን ይሸፍናሉ፣ ይህ ቁጥር አጠቃላይ ቁጥራቸው 1 – 2 መቶኛ ብቻ መሆኑን ሲታሰብ ግዙፍነቱ ይታያል።
ግብረ ሰዶማውያን በጉበት በሽታ ትልቅ ድርሻ ይወስዳሉ፡ 70 – 80 መቶኛ በሳን ፍራንሲስኮ፣ 29 መቶኛ በዴንቨር፣ 66 መቶኛ በኒው ዮርክ ከተማ፣ 56 መቶኛ በቶሮንቶ፣ 42 መቶኛ በሞንትሬል፣ እና 26 መቶኛ በሜልበርን።(8)
37 መቶኛ ግብረ ሰዶማውያን ሳዲዝም (በሰው ስቃይ መደሰት) እና ማሶቺዝም (በራስ ስቃይ መደሰት) ቅልቅል የሆነው ሳዶማሶቺዝም ተግባር ይፈጽማሉ። በሳን ፍራንሲስኮ ግብረ ሰዶማውያን አጋራቸው ጋር በሳዶማሶቺዝም በሚተገብሩበት ግዜ እንዳይገዳደሉ ትምህርት ሲሰጣጨው ነበር።(8)
መካከለኛው የግብረ ሰዶማውያን የእድሜ ጣርያ 42 ዓመት ነው፣ ከ65 ዓመት እድሜ በላይ የሚኖሩት 9 መቶኛዎቹ ብቻ ናቸው። በኤድስ ምክንያት የሚሞቱት ከተጨመረ ደግሞ መካከለኛ እድሜ ጣርያቸው ወደ 39 ዓመት ዝቅ ይላል። በትዳር ዓለም ያሉ ግብረ ሰዶም ያልሆኑ ሰዎች መካከለኛ የእድሜ ጣርያ 75 ዓመት ነው።(8)
የሴት ግብረ ሰዶማውያን መካከለኛ የእድሜ ጣርያ 45 ዓመት ነው፣ 24 መቶኛ የሚሆኑት ብቻ ደግሞ ከ 65 ዓመት በላይ ይኖራሉ። በትዳር ዓለም ያሉ ግብረ ሰዶም ያልሆኑ ሴቶች መካከለኛ የእድሜ ጣርያ 79 ዓመት ነው።(8)
ግብረ ሰዶማውያን ከተራው ሰው በላይ በ 100 (መቶ) እጥፍ የመገደል እድል አላቸው (ባብዛኛው በሌላ ግብረ ሰዶም ነው የሚገደሉት)፣ ከተራው ሰው በላይ 25 እጥፍ እራስን የማጥፋት እድል አላቸው፣ በተጨማሪም ከተራው ሰው በላይ 19 እጥፍ በመኪና አደጋ የመሞት እድል አላቸው።(8)
21 መቶኛ የሚሆኑት ሴት ግብረ ሰዶማውያን ተገድለው፣ እራሳቸውን አጥፍተው ወይ በትራፊክ አደጋ ይሞታሉ፤ ይህ በ25 – 44 እድሜ ክልል ውስጥ ካሉ ነጭ ግብረ ሰዶም ያልሆኑ አሜሪካውያን ጋር ሲነጻጸር 534 እጥፍ ይበልጣል።(8)
“የግብረ ሰዶም ጥቃት” ለማሳወቅ ከሚደረጉት የድረሱልኝ የስልክ ጥሪዎች 50 መቶኛዎቹ ግብረ ሰዶም ሌላ ግብረ ሰዶም ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ለማሳወቅ ነው።(18)
የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው መፈጸሙን ከሚጠባበቁት ሴቶች ውስጥ 50 መቶኛ የሚሆኑት ሴቶች ግብረ ሰዶማውያን ናቸው።(12) ግብረ ሰዶማውያን ሕጻናት ዋነኛ የወንጀል ሰለባዎቻቸው ናቸው።
33 መቶኛ የሚሆኑት ግብረ ሰዶማውያን አዋቂ ካልሆኑ ጋር ግንኙነት እንደፈጸሙ ገልጸዋል።(7)
በሺዎች የሚቆጠሩ አባሎች ያሉት North American Man and Boy Love Association ( NAMBLA) የተባለ የግብረ ሰዶማውያን ማህበር አለ። ይህ ሕጻናት የሚያባልግ ማህበር መፈክሩ “ወሲብ ከ 8 ዓመት በፊት፣ ከመርፈዱ በፊት” (“SEX BEFORE 8 BEFORE IT’S TOO LATE”) የሚል ነው። ይህ ማህበር በአሜሪካ በሚደረጉ ዋና ዋና የግብረ ሰዶማውያን ሰልፎች ላይ ሲሳተፍ መመልከት ይቻላል።
በአሜሪካ ተፈጽመው ሪፖርት ከተደረጉ ሕጻናትን የማባለግ ወንጀሎች ውስጥ 33 መቶኛዎቹ በግብረ ሰዶማውያን የሚፈጸሙ ናቸው። ግብረ ሰዶማውያን ከአጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር ውስጥ 2 መቶኛ ናቸው እንኳ ብንል፣ ከ20 ግብረ ሰዶማውያን አንዱ ሕጻናትን ያባልጋል ማለት ነው፣ ግብረ ሰዶም ካልሆኑት ደግሞ ከ 490 አንዱ ሕጻናትን ያባልጋል።(19)
73 መቶኛ የሚሆኑት ግብረ ሰዶማውያን ከ19 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ጋር ወሲብ ፈጽመዋል።(9)
ብዙዎቹ ግብረ ሰዶማውያን ሕጻናትን አባላጊዎች ወይም አጥቂዎች (ፔዶፍይል) መሆናቸውን ይቀበላሉ፡ “በአዋቂ ወንዶች እና በልጆች ወንዶች መሃከል ያለው ፍቅር የግብረ ሰዶማዊነት መሰረት ነው።”(22)
ግብረ ሰዶማውያን መዋለድ ስለማይችሉ ሕጻናትን ይመለምላሉ። ግብረ ሰዶማውያን በሰልፎቻቸው ግዜ “አስር መቶኛ በቂ አይደለም፣ መልምሉ፣ መልምሉ፣ መልምሉ” (“TEN PERCENT IS NOT ENOUGH, RECRUIT, RECRUIT, RECRUIT”) እያሉ ሲፎክሩ ይሰማሉ። ሴቶች ልጆችን መመልመል ስራው ያደረገ “ለዝቢያን አቬንጀርስ” የተባለ የሴት ግብረ ሰዶማውያን ማህበር ደግሞ አለ። በሕትመታቸው ውስጥ “እንመለምላለን” የሚል ጽሑፍ ያትማሉ። ሌሎች የግብረ ሰዶም ማህበሮች እንዲህ በግልጽ አይናገሩም፣ ማህበረ ሰቡን ውስጥ ውስጡን በመሰርሰር በቀላሉ የሚታለል ጭንቅላት ያላቸውን ወጣቶች ያጠምዳሉ። [በሃገራችንም በትምህርት ቤቶች፣ በቤት አስጠኚዎች ወዘተ. የተሰሩ የግብረ ሰዶም ማስፋፋት ስራዎችን ተመልክተናል።]

የግብረ ሰዶማውያን አጀንዳ

የግብረ ሰዶማውያን አጀንዳ በዋናነት ሰው ይህ ጠየናማ ያልሆነ፣ በወንጀልና በሽታዎች የተዘፈቀ የሞት መንገዳውን እንዲቀበል ማድረግ ነው፡ “የመጀመርያ ሥራ የአሜሪካን ሕዝብ እንዲላመድ ማድረግ ነው . . .። እንዲላመድ ማድረግ ያለምንም ልዩነት ግብረ ሰዶማዊነትን እንዲመለከት ማድረግ ነው። ሊሆን የሚችለው ምርጡ ነገር ግብረ ሰዶም ያልሆኑ ሰዎች ልክ የአይስ ክሬም ምርጫ ወይም የስፖርት ጨዋታ ምርጫን እንደሚያዩት ስለ ወሲባዊ ምርጫ ልዩነቶችንም እንዲያስመዘግቡ ማድረግ ቢቻል ነው።  … ቢያንስ መጀመርያ ላይ ሕዝቡ ግድ እንዳይሰጠው ማድረግ ነው፣ ከዚህ በላይ ሌላ አንፈልግም። ተራው አሜሪካዊ ግብረ ሰዶማዊነትን ሙሉ ለሙሉ “እንዲቀበል” ወይም “እንዲረዳ” ማድረግም አንችልም፣ አንጠብቅምም። ብዙሃኑን ግብረ ሰዶማዊነት ጥሩ ነገር ነው ብሎ ማሳመኑን መርሳት ይሻላል። የሆነ አንድ ሌላ ነገር ነው ብለው እንዲያስቡ ካደረግናቸው ለሕጋዊና ማህበራዊ መብት የምታደርጉት ትግል እንዳሸነፋችሁ መቁጠር ይቻላል።”(25)
አንዱ የግብረ ሰዶማውያን አጀንዳ ቆሻሻ የሕይወት ዘይቤያቸው ጤናማ ነው ብሎ ሕዝቡ እንዲቀበል ማድረግ ነው፣ በ 1987 ዓ.ም ሰልፋቸው ላይ አንድ ግብረ ሰዶማዊ እንዳለው አሁን እያደረጉት ያለው ጥበቃ እንዲሰጣቸው መጠየቅ ሳይሆን ልክ ግብረ ሰዶም ያልሆኑት ሁሉ እንዳላቸው መብቶች እንዲሰጣቸው ነው።(27) [አሁን ይህን አልፈው በባራክ ኦባማ አስተዳደር ሰፊ ርቀት የተጓዙ ሲሆን፣ ምዕራቡን ዓለም ተቆጣጥረው አፍሪካ ላይ እስከ ፖለቲካዊ ጫና መፍጠር ደርሰዋል። የተታለሉም፣ ግብረ አበሮችም አፈ ቀላጤዎች አላጡም።]
ሌላው የአጀንዳው ክፍል ሕዝቡን ከክርስትና ማስወጣት ነው፡ ክርስትና ግብረ ሰዶማዊ ድርጊት የሚከለክል በመሆኑ ግብረ ሰዶማውያን የክርስትና ሃይማኖትን ሊያወግዙ ይገባ ይላሉ።(1)
ግብረ ሰዶማውያን ሆን ብለው ስለ አጠቃላይ ቁጥራቸው 10 መቶኛ ነው እያሉ ይዋሻሉ። ቶም ስቶዳርድ እንዳለው እንደዛ የምንለው አውቀን ግብረ ሰዶማውያንን ለማበረታታትና የውሸት ብዝሃነት ለመፍጠር ነው ብሏል።(17)

የግብረ ሰዶማውያን ትክክለኛ ቁጥር

ቁጥራችን 10 መቶኛ ነው ለማለት ግብረ ሰዶማውያን ደጋግመው የሚጠሩት የኪንሰይ የ1948 ዓ.ም ጥናት ውሸት ነው፣ እንዲያውም የሚለው ከሕዝቡ ሙሉ ለሙሉ 4 መቶኛው ግብረ ሰዶም ነው ነው። የሆነው ሆኖ ግን ይህም ጥናት ቢሆን የተሳሳተ የምርምር ስልት የተጠቀመ ነበር፣ የተመራመረባቸው (ሳምፕሎቹ) በወሲብ ወንጀል የታሰሩ ላይ ነው፣ ይህ ሕዝቡን ሊወክል የሚችል መረጣ አይደለም። በተጨማሪም ኪንሰው ወጣት ልጆችና ሕጻናት አባላጊዎች (ፒዶፋይሎች) ላይ ያደረገው ጥናትን እያጣመመ ነበር ያቀረበው።
አሁን የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ከአጠቃላይ ሕዝቡ ውስጥ ግብረ ሰዶም የሆኑት 1 – 2 መቶኛ ናቸው። ይህ ቁጥር ምን ያህል ትንሽ መሆኑን አስቡትና እላይ ከጠቀሱት የድርሻ ቁጥሮቻቸው ጋር ያስተያዩት።
በአሜሪካ ግብረ ሰዶማውያን የሚደርስባቸው መገለል የለም። ልዩ ጥቅም የሚደረግለት መደብ እንዲሆኑ ለምን እንደሚጠይቁ አይገባም። የግብረ ሰዶማውያን መካከለኛ ዓመታዊ ገቢ 55,430.00 ዶላር ነው (የሚንከባከቡት ቤተሰብ ስለሌላቸው ይህ እንዳሻቸው የሚያጠፉት ነው)። የአጠቃላይ ሕዝቡ መካከለኛ ገቢ 32,144.00 ዶላር ነው። የጥቁሮች መካከለኛ ገቢ 12,166.00 ዶላር ነው።(24)
59.6 መቶኛ ግብረ ሰዶማውያን ከኮሌጆች የተመረቁ ናቸው። ከአጠቃላይ ሕዝቡ 18 መቶኛ ብቻ ነው ከኮሌጆች የተመረቁት ቁጥር።(24) “ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ” ሮሜ 1፡ 22።
49 መቶኛ ግብረ ሰዶማውያን ከፍተኛ/አስተዳደር ደረጃ የሥራ መደብ የያዙ ናቸው። ከአጠቃላይ ሕዝቡ እንዲህ ዓይነት መደብ የሚይዙት 15.9 መቶኛዎቹ ናቸው።(24)
ምንጮች
(1) Advocate, 1985.
(2) Bayer, R. Homosexuality and American Psychiatry.
(3) Bell, A. and Weinberg, M. Homosexualities: a Study of Diversity Among Men and Women. New York: Simon & Schuster, 1978.
(4) Cameron et. al. ISIS National Random Sexuality Survey. Nebraska Med. Journal, 1985, 70, pp. 292-299.
(5) “Changes in Sexual Behavior and Incidence of Gonorrhea.” Lancet, April 25, 1987.
(6) Corey, L. and Holmes, K. “Sexual Transmission of Hepatitis A in Homosexual Men.” New England J. Med., 1980, pp. 435-38.
(7) Family Research Institute, Lincoln, NE.
(8) Fields, Dr. E. “Is Homosexual Activity Normal?” Marietta, GA.
(9) Jay and Young. The Gay Report. Summit Books, 1979, p. 275.
(10) Kaifetz, J. “Homosexual Rights Are Concern for Some,” Post-Tribune, 18 December 1992.
(11) Kus, R. “Alcoholics Anonymous and Gay America.” Medical Journal of Homosexuality, 1987, 14(2), p. 254.
(12) Lesbian News, January 1994.
(13) Lief, H. Sexual Survey Number 4: Current Thinking on Homosexuality, Medical Aspects of Human Sexuality, 1977, pp. 110-11.
(14) Manlight, G. et. al. “Chronic Immune Stimulation By Sperm Alloantigens.” J. American Med. Assn., 1984, 251(2), pp. 237-438.
(15) Morton-Hunt Study for Playboy 
(16) MsKusick, L. et. al. “AIDS and Sexual Behavior Reported By Gay Men in San Francisco.” Am. J. Pub. Health, 1985, 75, pp. 493-96.
(17) Newsweek, February 1993.
(18) Newsweek, 4 October 1993.
(19) Psychological Reports, 1986, 58, pp. 327-37.
(20) Rueda, E. The Homosexual Network. Old Greenwich, Conn., The Devin Adair Company, 1982, p. 53.
(21) San Francisco AIDS Foundation, “Can We Talk.”
(22) San Francisco Sentinel, 27 March 1992.
(23) Science Magazine, 18 July 1993, p. 322.
(24) Statistical Abstract of the U.S., 1990.
(25) “The Overhauling of Straight America.” Guide Magazine. November, 1987.
(26) United States Census Bureau
(27) United States Congressional Record, June 29, 1989.
(28) University of Chicago’s Nation Research Corp.
(29) Diagnostic and Statistical Manual of Mental Disorders Fourth Edition, American Psychiatric Association, 1994.

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on July 27, 2014
  • By:
  • Last Modified: July 27, 2014 @ 4:16 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar