Read Time:11 Minute, 6 Second
በግደይ ገብኪዳን
መነሻ
የመስከረም 11 የዓለም ንግድ ማእከል ጥቃትን (9/11፡ የሽብራዊ አገዛዝውሎ ይመልከቱ) ተከትሎ አሜሪካ ሰራዊቷን በምድረ ዓረብ አሰማርታ የምታሳድዳቸውና የምትገላቸው ጽንፈኞች ወሬ አውራ ሚዲያዎች ዋና ዘገባቸው ማድረጋቸው ተለምዷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በምስራቅ፣ በምእራብና በሰሜን አፍሪካ ሃገራት የዓረብ ዓለምን ወደ ጨለማ ዘመን እየመለሱ ያሉት ሰዎች አሉ ተብሎ የዓረቡን ክስተት በአፍሪካ ለመድገም የአሜሪካና አውሮፓ ሰራዊቶች ሽር ጉድ እያሉ ነው።
በዚህ ዓመት በኬንያ ርእሰ ከተማ ናይሮቢ በዌስት ጌት ሕንጻ በተከሰተው “የአሸባሪዎች ጥቃት” ተከትሎ የአሜሪካ ሰራዊት የአፍሪካ እዝ (አፍሪኮም) መሪ ጄነራል ዱቪድ ሮድሪጌዝ እና በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ቢሮ የአፍሪካ ጉዳይ ረዳ ሃላፊዋ ጥቁርዋ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ሁለቱም ይህ ጥቃት አሜሪካ በአፍሪካ የምትከተለው ፖሊሲ ልክ መሆኑን የሚያሳይ ነው ለማለት አልዘገዩም ነበር፡፡
ጂኦ-ፖለቲካዊ ተንታኙ ቶኒ ካርታሉቺ እነዚህ የሽብር ሸማቾች እንዴትበምእራባውያን እንደሚደገፉ ያሳየናል፡
“መጀመርያ የሊቢያን መንግስትን ለመገልበጥ በኔቶወደ ወደ ሊብያ ቀጥሎ ከሊብያ ወደ ሶርያ የጎረፈው ገንዘብና መሳርያ በኤ.ኪው.አይ.ኤም (አልቃይዳ በማግረብ)፣ ቦኮ ሃራም እና አል ሸባብ መሃከል ያለው ትብብር በግልጽ እንዲጨምር አድርጓል፡፡ በሰሜን አፍሪካ የአል ቃይዳ አድማስ እንዲስፋፋ ኔቶ የሚያደርገው ድጋፍ ከኬኒያ የዌስትጌት ጥቃት ጀርባ ያሉ አሸባሪዎች እንዲህ ያለ ድንበር ተሻጋሪ ጥቃት ማድረስ እንዲችሉ ማስቻል ነው፡፡”
በሊብያ መንግስት ለመገልበጥ የተዋጉት አሸባሪዎች በቀጥታ ወደ ሶርያ ተዛውረው እዛም እየተዋጉ ነው፡፡ የሙአማር ጋዳፊ መገልበጥ ለሽብርተኞች መጠናከርና ከጀርባ ስልጣን መቆጣጠር ከፋተኛ እድል ሰጥቷቸዋል፡፡
አዲሱ ቅኝ አገዛዝ
ላለፉት 150 ዓመታት አፍሪካ በግጭትና ክፍፍል ባርነት ታስራ ተፈጥሯዊ ሃብቷ በምዕራባውያን ሲበዘበዝ ኑሯል፡፡ ዛሬም ቢሆን በአፍሪካ የተለያዩ “ሰብአዊ” ፍላጎቶችን በመከለል ምዕራባውያን አፍሪካን ከሰንሰለታቸው እንዳትወጣ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በአፍሪኮም ተልእኮዎች ክፍለ አህጉሪቱን በቁጥጥር ስር ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡ ይህ አዲሱ ቅኝ አገዛዝ ነው፡፡
በ2011 ዓ.ም ሂላሪ ክሊንተን እርዳታ በሶማልያ ማከፋፈል እንዲቻል እዛ ባለው የአል ሸባብ ጋር ስምምነት እንዳደረጉ ተናግራ ነበር፡፡ የውጭ ንብረት ተቆጣጣሪ ቢሮ ለውጭ እርዳታ የሚያቀርቡ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ከጸረ-ሽብር ሕጎች ከለላ የሚሰጠው ፈቃድ አሜሪካ እንዲራዘም አድርጋለች፡፡ የሚደብቁት ነገር ባይኖር ለምን ሕጉን ይቀይሩታል? አል ሸባብ እርዳታ ማስተላለፍ ስለረዳ በተራው ከአሜሪካ ምንድን ነው የተቀበለው?
እንደ ፈረንሳይ ዓይን ያወጣ ቅኝ አገዛዝ ግን የሚያራምድ የለም፡፡ በ2010 ዓ.ም ፈረንሳይ ባቀነባበረችው መፈንቅለ መንግስት የአይቮሪ ኮስት ፕሬዚደንት ሎረን ባግቦን ከፈረንሳይ ጭቆና ሃገሩን ነጻ ሊያወጣ ስለሞከረ ከስልጣን እንዲወገድ አድርጋለች፡፡ ባግቦ አይቮሪ ኮስትን ከፈረንሳዩ (UMEOA) ማእቀፍ ሌሎቹን 14 የቀድሞ (የቀድሞ መባል ለበትም ነበር) የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት አባላትን ይዞ ለመውጣት ሲንቀሳቀስ ነበር፡፡ ስልጣን እንደጨበጠ የመጀመርያ ስራው የነበረው ከፈረንሳይ ኢምባሲ ወደ አይቮሪ ኮስት ቤተ መንግስት በመሬት ስር በተቆፈረ ዋሻ የሚያገናኘውን የመሬት ስር ቦይ በኮንክሪት ግምብ መዝጋት ነበር፡፡ ፈረንሳይም ከስልጣን ያባረረችው ይህ ኮንክሪትን አፍርሰው ቤተ መንግስቱን ካጠቁ በኋላ ነው፡፡ ፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛቶቿን “ነጻ ስትለቅ” ጊዜ ናዚ ጀርመኖች ፈረንሳይን በተቆጣጠሩ ግዜ ዘርግተውት የነበረውን የፋይናንስ ቅኝ አገዛዝ ስልት በመኮረጅ አፍሪካውያኑ ላይ ተገበረችው፡፡ ይህ የብዝበዛ ስልቷ “ነጻ የለቀቀቻቸውን” ሃገሮች ውል በማስፈረም ነበር ያሰረቻቸው፡፡ ስርአቱ እንደሚከተለው ነው፡
· ፈረንሳይ በቀጠናው ሦስት ማእከላዊ ባንኮች ድምጽን በድም መሻር መብት ያላቸው ኮሚሳሮች አስቀምጣለች፡፡ ኮሚሳሮቹ በቀጠናው የትኛውንም ዓይነት ፊስካል፣ ሞኒታሪ እና ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎችን ማገት ይችላሉ፡፡
· ፈረንሳይ የቀጠናውን ገንዘብ ፍራንክ ሲኤፍኤ ታትማለች፣ ታወጣለች ዋጋውን ትተምናለች፡፡
· UMEOA አባሎች 65 መቶኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸውን ያለምንም ወለድ የግድ በፈረንሳይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
· በዚህ ተቀማጭ ምንዛሪ ፈረንሳይ 3 መቶኛ የወለድ ገቢ ታገኛለች፣ ይህን ትርፍ ገንዘብ ደግሞ መልሳ ከ5 – 6 መቶኛ ወለድ መጠን ቸድርጋ “ልማታዊ ድጋፍ” ብላ ታበድራለች፡፡
· UMEOA አባሎች የወርቅ ክምችታቸውን በሙሉ የግድ ፈረንሳይ ውስጥ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ ይህ በፈረንሳይ የተቀመጠው ወርቅ ኦዲት ተደርጎ አያውቅም፡፡
· ይህን ለመቀየር የሚሞክር የትኛውም መሪ እንደ ሎረን ባግቦ መፈንቅለ መንግስትና የጦር ወንጀለኛ ክስ በዓለም አቀፍ ወንጀል ችሎት ይጠብቀዋል፡፡
እኚህን ከላይ የተቀመጡትን እውነቶች ያስታወሰን ጸሐፊ አሁን በናይጄሪያ ልጆቻችንን መልሱ የሚለው እንቅስቃሴ እና የአሜሪካ መንግስት ለልጆቹ ደህንነት የተቆረቆረ መምሰልና ይባስ ብሎ የሚያምነው መኖሩ እጅግ አስገርሞታል፡፡ ዛሬ በአለም ላይ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር በነገሰበትና ሴቶች ኢ-ሰብአዊ በሆኑ ስራዎች እንዲሰማሩ በወንጀለኞች እየተጠለፉ በመላው አውሮፓ እንዲዘዋወሩ የሚደረጉትና “ስራው” በራሳቸው ለመስራት ሲሉ በሚያወጡት ሕጎች “የጠባቂዎች” ባሮች ሁነው እንዲቀሩ በሚያደርግ ዓለም እየኖርን ስለነዚህ ሴቶች ይህን ሁሉማለታቸው እውነትም ይገርማል፡፡
ቦኮ ሃራም በናይጄሪያ
እራሱን ቦኮ ሃራም እያለ የሚጠራ በናይጄርያ የሚንቀሳቀስና ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው ተቋም ናይጄሪያን እያመሰ ይገኛል። (ከአልቃይዳ ወይም አክራሪ ዋሃቢ / ታክፊሪ / ሳላፊስቶች ጀርባ የቆሙት ሲአይኤና ኔቶ መሆናቸው ጸሐይ የሞቀው እውነት ነው።)
ከዚህ በፊት ዊኪሊክስ ባወጣው መረጃ መሰረት በናይጄሪያ የአሜሪካ ኢምባሲ የጸረ ናይጄሪያ እንቅስቃሴዎች ማእከል መሆኑን አጋልጧል። ከዚህ ስራዎች ውስጥ የናይጄሪያ መንግስት መልእቶችን መሰለል፣ በናይጄርያ ቁልፍ ሰዎች ፋይናንስ መሰለል፣ አማጽያንን መደገፍና መደጎም፣ የከፋቸው ናይጄሪያውያን ላይ ቀስቃሽ ፕሮፖጋንዳ መንዛት፣ ከፍተኛ ቦታ ላይ ያሉ ናይጄሪያውያንን ቪዛ ተጠቅሞ የአሜሪካ ፍላጎትን እንዲያገለግሉ መጠምዘዝ ይገኙበታል። [በነገራችን ላይ የዊኪሊክስ መረጃዎች ሁሉ ትክክል ናቸው ማለት አይደለም፣ እንዲሁ ተጨባጭ ማስረጃ የሌላቸው ግምቶች ሁሉ ያካተተ ስለሆነ በጥንቃቄ መታየት አለበት። ዊኪሊክስ እራሱ ግጭት ለመፍጠር የተደረገ የሲአይኤ ስራ ነው የሚሉት አሉ።] አሁን የዊኪሊክስን መረጃ የምናየው ከተጨባጭ መረጃ ጋር ነው።
ይህ የአሜሪካ ተግባር ናይጄሪያ በአፍሪካ ያላትን ተጽእኖ ለማዳከም ያለመ የረዥም ጊዜ እቅድ አካል ነው።
በአሜሪካ መራሹ አክሪ – ACRI (Africa Crises Response Initiative) ላይ የዊኪሊክስ ዘገባ እንደሚያሳየው አክሪ በአሜሪካ የተቋቋመው ናይጄሪያ መራሹ ኢኮሞግ – ECOMOG (ECOWAS Monitoring Group on the Liberian Civil War) ወይም በላይቤሪያ ግጭት በናይጄሪያ መሪነት የኢኮዋስ አገሮች ያቋቋሙት ተቆጣጣሪ ቡድን ባጭሩ ኢኮሞግን ለመቀናቀን ነበር። በናይጄሪያ የሚመራ ጸረ-አሜሪካ እንቅስቃሴ መጀመርያ የታየው በቡሽ አስተዳደር ጊዜ ናይጄሪያ ያለተ.መ.ድ ድጋፍ በወቅቱ በነበረው ወታደራዊ መሪ ጀነራል ኢብራሂም ባዳሞሲ ባባጊዳ መሪነት የመጀመርያውን የአፍሪካ መራሽ ጣልቃ ገቢ ሃይል ወደ ላይቤሪያ ማስገባቷ ነበር።
በዚህ መስኩ ዘገባው በተጨማሪም ወደኋላ በመመለስ አሜሪካና ምስራባዊ ወዳጆቿን ፍላጎት በሚጻረርና ከታዛዥነት ውጪ በሆነ መልኩ በ70ዎቹ እና 80ዎቹ የደቡብ አፍሪካ አገሮች ነጻ እንዲወጡ በመደገፍ በወቅቱ ምእራባውያን በአፍሪካ ለነበራቸው እንቅስቃሴ እንቅፋት ሁና ነበር ሲል ይናገራል።
የዘገባዎቹ መደምደሚያ የነበረው በአካባቢው እየጨመረ የመጣውን የናይጄሪያን ተጽእኖ ባጭር ለመቅጨት ከኢኮሞግ ትይዩ ሌላ ተቋም መመስረት የሚል ነበር። ሆኖም ግን አሁንም ተጽእኖ ያላትን ናይጄሪያን እንዳያስደነግጥ የአሜሪካ መንግስት ዲፕሎማሲ እና የሐሰት ፕሮፖጋንዳ እንዲጠቀም ይመክራል።
ከዓመታት በኋላ ሲአይኤ በናይጄሪያ እየጨመረ የመጣውን የሃይማኖት ቅራኔ በመጠቀም ስራ አጥ ሙስሊሞችን በሙስሊምና ሌሎች ያገር ሽማግሌዎች ተጠቅሞ በመመልመል በተዘዋዋሪ መንገድ የውጭ የሽብር ሃይሎችን ተጠቅሞ ስልጠና እንዲያገኙ ያደርግ ጀመረ። ዝርዝሩን እንመለከተዋለን።
የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ በሏቸው፦
· በታህሳስ 2011 በአልጄሪያ ተቀማጭነቱን ያደረገ የሲአይኤ ክንፍ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ከቦኮ ሃራም ጋር እንደታቀደው 40 ሚሊዮን ናይራ ሰጥቶታል፣ ሌላም ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን ሳይዘነጋ።
· በሰኔ 29፣ 2009 ዊኪሊክስ ይፋ ያደረገው የአሜሪካ መልእክት እንደሚያሳየው ሲአይኤ ቦኮ ሃራም አደገኛ ሽብራዊ ጥቃት ያደርሳል ሲል ተናግሯል ይህ ቦኮ ሃራም ምንም ዓይነት ሽብራዊ ጥቃት ማድረስ ሳይጀምር ከሁለት ወር በፊት መሆኑ ነው።
· የሙያተኞች ምክርን ወደ ጎን በማለት አሜሪካ ሳውዲ ዓረቢያን አስታጥቃለች፣ ሳውዲም በተራዋ የሊብያ አማጽያንን አስታጥቃለች፣ እነዚህም በተራቸው የማሊ አማጽያንንና ቦኮ ሃራምን አስታጥቀዋል፤ ይህ የማስታጠቅ ሰንሰለት ቀድሞውኑ በሲአይኤ ተተንብዮ የነበረ ነው። አሜሪካ=>ሳውዲ ዓረቢያ=>ሊቢያ=>ቦኮ ሃራም።
· የዊኪሊክስ የስለላ ሰነዶች እንደሚያሳዩት በአሜሪካ የስለላ ተቋም የሆነው ኤስኤስ8 (SS8) የግለሰብ ኮምፒተሮችን እና ስልኮችን (አይፎን፣ ብላክቤሪ፣ አንድሮይድ ወዘተ.) ጠልፎ እያንዳንዱ ስራውን፣ እንቅስቃሴውን፣ ጂፒኤስ መረጃ እና በተጨማሪም ባለበት አካባቢ ያለ ምስልና ድምጽ ማግኘት የሚያስችል ቫይረሶች (ትሮያንስ) ይሰራ ነበር። ይህ ሶፍትዌር ታድያ በሲአይኤ ተገዝቶ የናይጄሪያ ፖለቲከኞችን ለመሰለልና ሕጋዊ ያልሆኑ ተግባሮችን ይመዘግቡባቸው ነበር። እነዚህ ፖለቲከኞች የአሜሪካ ጥቅምን የማያስጠብቁ ከሆነ መረጃውን እንለቃለን በማለት ይጠመዘዛሉ።
· በዚህ አጋጣሚም የናይጄሪያ ደህንነቶች ከሲአይኤ ጋር በመተባበር በቦኮ ሃራም ላይ መረጃ በማሰባሰብ ስራ እየሰሩ እያለ የግል መረጃቸው፣ አድራሻ፣ የባንክ መረጃ፣ የስልክ ቁጥር ወዘተ ተጠልፎ በመረጃ መረብ መለቀቁና የደህንነት ሰራተኞቹን ከጨዋታ ውጪ ማድረጉ የሚገርም አጋጣሚ ነው።
· በተጨማሪም ካቢሩ ሶኮቶ ከጥብቅ ሚስጥራዊ እስርቤት በተአምር ማምለጡንም ማተወስ ይገባል፣ የዚህን እስርቤት ቦታ ሲአይኤ ያውቀዋል።
የአሜሪካ ሴራ በናይጄሪያ የጀርባ ታሪክ፡ ከአክሪ ወደ አፍሪኮም
አክሪ በቡሽ አስተዳደር ጊዜ ነበር ናይጄሪያ መር የሆነውን ኢኮሞግን ለመቀናቀን የተመሰረተው። አክሪ የተገኘው ሲአይኤ ባሰራው የአፍሪካ-አሜሪካ ኢንስቲቱትና ብሩኪንግስ ሪፖርቶች መሰረት ነው። ሁለቱም ሪፖርቶች በኢኮሞግ ውስጥ ናይጄሪያ የነበራትን መሪ ሚናና ያለ ምንም የምእራባውያን ጣልቃ ገብነት የላይቤሪያ ቀውስን ማረጋጋት መቻሏን ልብ ብለውታል። የሪፖርቱ መደምደሚያም የኢኮሞግ ስራ ፍጻሜውን እስኪያገኝ እንዲሄድ ከተደረገ ዋና ተጠቃሚዋ ናይጄሪያ እንደምትሆንና በምእራብ አፍሪካም የቀድሞ ቅኝ ገዢዎችን፣ የብሪታንያ እና ፈረንሳይ ተጽእኖን ልትጋርድ እንደምትችል ይጠቁማል። ሪፖርቱ በተጨማሪም ላይቤሪያ ወደ ናይጄሪያ ተጽእኖ እንድትወድቅ አሜሪካ በጸጥታ መመልከት እንደሌለባት ይጠቁማል።
ናይጄሪያ በላይቤሪያ ተጽእኖ ሲኖራት ዝም ተብሎ ከታየ ለወደፊቱ የአሜሪካንና የምእራባውያንን ጥቅም ለመቀናቀን ድፍረት እንደሚሆናት ሪፖርቶቹ ያስቀምጣሉ። በዚህ መስክ በ70ዎቹ እና 80ዎቹ በግልጽ አሜሪካንና ምእራባውያ ወዳጆቿን ፍላጎት በሚቃረን መልኩ የደቡብ አፍሪካ አገሮች ከቅኝ አገዛዝ ነጻ እንዲወጡ ያደረገችውን አስተዋጽኦ ይዘክራል።
ከሲአይኤ፣ ፔንታጎን (መከላከያ ሚኒስቴር) እና ስቴት ዲፓርትመንት (ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር) የተወከሉት አካላት ሁለቱም ተቋማት በናይጄሪያ የኢኮሞግ ሚናዋ ላይ ያቀረቧቸውን ሪፖርቶች ለመመልከት የተቋቋመው የምክርቤት ሚስጥራዊ ኮሚቴ የሪፖርቶቹን ጥቆማ እንዲቀበል ሲገፋፉት ነበር። በዚም መሰረት ለላይቤሪያ የሚሆነው አማራጫቸው ላይ ናይጄሪያ እንድትገለል አስተያየት ሰጥተዋል። የዚህ ማሳኪያ መንገዱም ቁልፍ የአፍሪካ አገሮች በኢኮሞግ እንዳይሳተፉ ማድረግ ነበር። የዚህም ማጓጓያ ወይም መሳብያ ዘዴያቸው ወታደራዊና ሰብአዊ ድጋፍ እናደርግላችኋለን ብሎ ቃል መግባት ነበር።
በወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ዋና ጸሐፊ (ሚኒስትር) የነበረው ዋረን ክሪስቶፈር የአክሪ ሃሳቡን ለመሸጥ ወደ አፍሪካ ሲመጣ የተከተለው መስመር ይህን ነበር። ከዚህ በኋላ አንዳንድ አገሮች በኢኮሞግ የነበራቸውን አስተዋጽኦ በማጓተት እንቅስቃሴው ታገተ። በዲፕሎማሲያዊው መስክ ከወዳጆቿ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ጋር በመሆን አሜሪካ የተፈጠረውን (ያስፈጠረችውን) የኢኮሞግ መስተጓጎል ሰበብ አድርጋ ኢኮሞግ ዳግም እንዲፈተሽና አዲስ አቅጣጫ እንዲሰጠው ዘመቻ ጀመሩ። ከዚህ በኋላ አሜሪካና ወዳጆቿ ኢኮሞግን ለማስቀጠል የሚያስፈልገው የአሜሪካና ወዳጆቿ ጣልቃ መግባት መሆኑን መከራከር ጀመሩ። ሆኖም ግን ይህ የአፍሪካውያን እንቅስቃሴ በሆነው ውስጥ ጣልቃ በመግባት ዓለም አቀፍ ተቃውሞ እንዳይገጥማቸው በተባበሩት መንግስታት ጥላ ስር ለማድረግ ወሰኑ።
ከዚህ በኋላ ናይጄርያን የማግለል እቅድ ተፈጸመ። ከዚህ ጥንቃቄ ከሞላበት የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት በኋላ ነው የአሜሪካ ሰራዊት የአፍሪካ እዝ ወይም አፍሪኮም (AFRICOM – US Africa Command) የተመሰረተው። አፍሪኮም ከርሱ በፊት እንደነበረው በሰብአዊ ድጋፍ ስም የተሸፈነ ሳይሆን እየጨመረ በመጣው ዓለም አቀፍ ውድድር ውስጥ በአፍሪካ የአሜሪካን ፍላጎት ለማስጠበቅ የተቋቋመ የሰራዊት እዝ ነው።
አፍሪኮም ቁልፍ ቦታዎችን በመቆጣጠር በአሜሪካ ተጽእኖ ስር ማድረግ ነው ግቡ። ከዚህም ውስጥ በአህጉሪቱ እያደገ የመጣውን የቻይና ተጽእኖንም መቆጣጠር ያስችለዋል። ይህን ለማድረግ ግን በቅድሚያ ቁልፍ የአፍሪካ አገሮችን በውስጥ ግጭት በማዳከም የአሜሪካን “ድጋፍ” እና “ጥበቃ” እንዲሹ ማድረግ ያስፈልጋል። ያለዚያ እንዲበታተኑ ይደረጋሉ ከዛም አሜሪካ “እንድትጠብቀው” የምትቆጣጠረው ቀጠና ይሰጣታል። ይህን ሁኔታ የታላላቅ ሃይቆች አካባቢ በሚባለው ቦታ አሜሪካ እራሷ ከምትደጉማቸው አማጽያን ሃገራቱን ለመከላከል የአሜሪካ ልዩ ኃይሎች እንዲገቡ ሲደረጉ ከዚህ በፊት አይተናል።
በሱዳን የአልበሽር መንግስት የአሜሪካ ድርጅቶችን ችላ ብሎ ከቻይና ጋር የነዳጅ ስምምነት ለማድረግ በመድፈሩ በሃገሪቱ በዳርፉር በተፈጠረ ግጭት የአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ቀውስ የአዞ ዕንባቸውን እንዲራጩ ስትወተውት ነበር። በሊብያም ቢሆን በሊብያ የአልቃይዳ ክንፍ የሆኑ ታጣቂዎችን በምድርና በአየር በመደገፍ ንጹሐንን በመጨፍጨፍ ጋዳፊ እንዲወገድ ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል። የሊብያን ጉድ እመለስበታለው።
ከሁሉ በላይ ግን አሁን ቀጣይ እርምጃቸው የሆነውና በአፍሪካ የአሜሪካ የበላይነት የሚመጣው በናይጄሪያ እየተሰራ ያለው ሴራ ከተሳካላቸው ነው። በዚህ መልኩ ስናየው ነው ቦኮ ሃራም የተባለው ስብስብ ተግባራትና የአሜሪካ የደህንነት መማክርት ናይጄሪያ በ2015 ትበታተናለች ብሎ ያስቀመጠው ግምት መረዳት የምንችለው። ሕዝቡ ካልነቃ፣ የአሜሪካና የእውራን ጽንፈኞች ተላላኪዎቻቸው መጫወቻ ነው የሚሆነው።
ቦኮ ሃራም – የሲአይኤ ሽፍን ዘመቻ
የናይጄሪያመዲና የሆነች አቡጃን ያመሰው የጥቅምት 1፣ 2010 ዓ.ም ጥቃት በኋላ ሃገሪቱ እየጨመረ በመጣ ውጥረት ውስጥ ገብታለች። ከዚህኛው ጥቃት ውጪ ከዚህ ጥቃት በኋላ የደረሱ የአብዛኞቹን ጥቃቶች ሃላፊነቱን ቦኮ ሃራም ወስዷል። ማየት የማይቻ የሚመስለው የቦኮ ሃራም ተፈጥሮ ብዙ ናይጄሪያውያን ጥያቄ እንዲያነሱ እያደረጋቸው ነው። ለምንድን ነው ለውይይት እንዲቀርቡ የሚደረግላቸውን ጥያቄ የማይቀበሉት? እንዴት ነው ጥቃታቸውን በቀላሉ መፈጸም የሚችሉት? ጥቃት ባደረሱባቸው ቦታዎች ፍንጭ ማስረጃ የማይተርፈው ለምንድን ነው?
ናይጄሪያውያን ለሃይማታዊ ግጭት አዲስ አይደሉም። ሆኖም ግን የተለመዱት ልዩነቶች መንስኤዎችና አካሄዶች በባለስልጣናቱ የታወቁና ቀድመው ሊገመቱ የሚችሉ ናቸው፣ በዚህም ምክንያት በእንጭጩ መቆጣጠር የሚቻሉ ናቸው። አሁን ካለው ቀድሞ የነበረው የመሃመድ ዩሱፍ ቦኮ ሃራም እንዲህ ሊመደብ የሚችልና እንቅስቃሴዎቹ፣ አመራሮቹና መቀመጫቸው የታወቀ ነበር። አሁን ጥያቄው እንዲያ ያሉ ያልተማሩ፣ ባብዛኛው በኦካዳ አካባቢ ብቻ ይንቀሳቀስ የነበረ ከመቅጽበት እንዴት ነው ከሚሊዮን ናይራ በላይ ወጪ የሚያስወጣ ፈንጂ ንድፍ ማውጣት፣ መስራትና መጣልና በመላ ሃገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት መፈጸም የቻሉት?
ይህን ለማድረግ በቅጡ የተደራጀ የእዝ እና ቁጥጥር ስርአት ያስፈልጋቸዋል፣ እንዲህ አይነቱን ደግሞ ለመደበቅ ቢፈልጉም አይቻላቸውም። ስለዚህ ጥያቄው የሚሆነው እንዴት ሳይደረስባቸው ይህን ሁሉ ሊያደርጉ ይችላሉ?
የአንጓዴ-ነጭ ጥምረት (GREENWHITE Coalition) ይህ የቦኮ ሃራም ዘመቻ ሲአይኤ ያደራጀውና የሚቀናጀውም በናይጄሪያ የአሜሪካ ኢምባሲ ውስጥ መሆኑን ያሳየናል።
ሲአይኤ በኒጀር፣ ቻድ እና ካሜሮን አካባቢዎች ባሉ ክፍተትና ተጋላጭነት ባላቸው ድንበር ቦታዎች የሚስጥር የስልጠናና የመስበክያ ጣብያዎች አሉት። በነዚህ ጣብያዎች ከድሃ፣ የተጎሳቆሉና የተጣፋባቸው ወጣቶች መልምሎ በማሰልጠን ሰርጎ ገብ አጥቂዎች ያደርጋቸዋል። እነዚህን ወጣቶች የሚመለምሉ ወኪሎች ወጣቶቹን የተሻለ ሕይወትና ለአላህ ስራ ትሰራላችሁ በማለት ከወሰዷቸው በኋላ በተጨማሪ አሁን በናይጄሪያ ያለው ሃጥያተኛ መንግስትን በመቀየር እስላማዊ መንግስት ትመሰርታላችሁ ተብለው አእምሯቸው ይሞላል።
የሲአይኤ መርሃ ግብር አስፈጻሚ አሜሪካውያን ኢፊሰሮች በጥንቃቄ ከወደኋላ በመሸሸግ የእለት ተለት የመርሃግብሩ አስፈጻሚዎች ከመካከለኛው ምስራቅ ለዚሁ ሲባሉ የተመለመሉ ተቆጣጣሪዎች ያካሂዱታል። ከተወሰኑ ወራት ስብከትና የመሳርያ አያያዝ፣ በሕይወት የመቆየት ዘዴ፣ ቁጥጥር (ዳሰሳ) ዘዴ፣ የመሰወር (ያለመታየት) ዘዴ ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ ሰርጎ ገቦቹ ለቀጣዩ ዘመቻ በተጠንቀቅ ይጠብቃሉ።
በዚሀጅ መልኩ የጥቃት ዒላማ እስከመምረጥና እስከመጨረሻዋ የጥቃት ደቂቃ ድረስና ከዛ በኋላም ሃላፊነት የሚወስዱትን መልእክት እስከማሰራጨት ድረስ የሲአይኤ ድጋፍ አይቋረጥም። ለዚህም ነው ሊገኙ የማይችሉት።
አሜሪካ ለናይጄሪያ በ2015 ያዘጋጀችው …
የአሜሪካ መንግስት የብሔራዊ ደህንነት መማክርት ናይጄሪያ በ2015 ትበታተናለች ብሎ ያቀረበው ወረቀት ከግምት በላይ ነው። ሪፖርቱ በጠቅላላ አሜሪካ ናይጄሪያን ለመበታተን ያላት እቅድ ማሳያ ነው፡፡
ይህ የማበጣበጥ ዘመቻ ናይጄሪያን ከውስጥ አዳክሞ በ2015 ሃገር አቀፍ ምርጫ መቆጣጠር ከማይቻል ቀውስ ውስጥ እንድትገባ ማድረግ ነው፡፡ እስከዛ ድረስ በናይጄሪያውያን መሃከል ከፍጠኛ አለመተማመን ስለሚኖር ማንም የምርጫውን ውጤት ላይቀበል ይችላል፡፡ በስሌታቸው መሰረት ናይጄሪያ የዛኔ እጅግ የተከፋፈለች ስለምትሆን ጣልቃ ለመግባትና ለመከፋፈል አመቺ ትሆናለች፡፡ ይህን እቅድ እውን ለማድረግ ነው አሜሪካውያኑ የመተግበሪያ ባለ ሦስት ምእራፍ የእቅድ ትግበራ ያወጡት
ምዕራፍ 1፡ ናይጄሪያን ፓኪስታናዊነት ማላበስ፦ በመጪ ወራቶች የቦኮ ሃራም ጥቃቶች እየጨመሩ ይሄዳሉ፡፡ ሌሎች ቡድኖችም ዓመጻ ጥሪያቸውን ይጨምራሉ፡፡ ግቡ አለመተማመንና ውጥረት ማስፋፋት ነው፡፡ የጥቃት ስልቱን ሲአይኤ የፓኪስታን ልምዱን የሚደግምበት ነው፡፡
ምዕራፍ 2፡ ቀውሱን ዓለም አቀፋዊ ማድረግ፦ የግጭት መድረኩ በደንብ ከጀመረ በኋላ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ሕብረት እና የተባበሩት መንግስታት ቀውስን የማስቆም ጥሪ ያቀርባሉ፡፡ በዓለም ዙርያ በተለያዩ ከተሞች ሰላም የማውረድ ጉባኤዎች ይካሄዳሉ፡፡ ከጀርባ ቀውሱን ያቀጣጠለችው አሜሪካ ለግል ቅልፍ (ስትራቴጂክ) እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቿ እንዲመች አድርጋ ናይጄሪያን ትሸነሽናለች፡፡
ምዕራፍ 3፡ በተባበሩት መንግስታት ቁጥጥር ስር መከፋፈሉ ይፈጸማል፦ ከዚህ መከፋፈል ተጠቃሚው ያስጀመረችው አሜሪካ ትሆናለች፡፡
መጠየቅ ያለበት ጥያቄ
አሜሪካ ለምንድን ነው ጥቂት ፖሊሲ አውጪዎች ብቻ እንዲያዩት የሚገባ ሚስጥራዊ የደህንነት መረጃ ተብዬውን ለሚዲያዎች ይፋ እንዲሆንና ለበቂ ጊዚያት መገጃው በተነጣጠረበት አገር ውስጥ በደንብ ስርጭት እንዲኖረው ያደረገችው?
ይህ በዚህ መስክ የታሰበበት ፍላጎት እንዳለ አያስይም?
በየትኛውም የተለመደ የወንጀል ማጣራት ሂደት ውስጥ ጥፋተኛ የተባለው ድርጊቱን ከመፈጸሙ በፊት አውቆም ይሁን ሳያውቅ የተናገረው ነገር እንደ ማስረጃ ይቀርባል፣ በዚህ መልኩ የአሜሪካ የደህንነት መማክርት ሪፖርት ናይጄሪያ በ2015 ትበታተናለች ማለቱ ከዚህ የወንጀለኝነት ደረጃ አይቆጠርምን፣ በተለይም ደግሞ ይህ ቃል ከተለቀቀ በኋላ በናይጄሪያ ጥቃት መጨመሩና በዚህ መስክ በመላው ዓለም አሜሪካ ያደረገችውን ወደ ስሌቱ ስናመጣው?
የዓለም ሕዝቦች አሜሪካ በዓለም ዙርያ እየፈጸመች ያለችውን ቀውስ እስከ መቼ ነው በዝምታ የሚያዩት?
ከቪየትናም እስከ ዒራቅ እስከ አፍጋኒስታን እና ላቲን አሜሪካ ድረስ በዓለም ዙርያ የአሜሪካ መዝገብ ቆሻሻ ነው፡፡ በራሳቸው ቃል መሰረት አሜሪካ ቋሚ ፍላጎት እንጂ ቋሚ ወዳጅ የላትም፡፡ ፍላጎታቸውን ማወቅና የጨዋታቸው ሰለባ አለመሆን ሕልውናውን ማስቀጠል የሚፈልግ ሕዝብ ሃላፊነት ይሆናል፡፡
ዋና ምንጭ
ሌሎች ጽሑፎች
Average Rating