www.maledatimes.com ዘረኝነት፦ ብዙሃንን በአንድ ቁና መስፈር - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዘረኝነት፦ ብዙሃንን በአንድ ቁና መስፈር

By   /   July 29, 2014  /   Comments Off on ዘረኝነት፦ ብዙሃንን በአንድ ቁና መስፈር

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 29 Second
 

 

Zerihun Tesfaye
ያለፉት ሦስት ቀናት ፌስቡክ አሳፋሪ ክስተት የታየበት፣ የዘረኝነት ስካር ናላቸውን ያዞረው አዳጊዎች የሕወሓት ባለስልጣናትን በአንቀልባ ካላዘልን ብለው የጮሁበት መድረክ ሆኖ ነበር። ድርጊቱ አዲስ ባይሆንም የአንድ ባለስልጣን ‘ክብር’ ተናካ ብለው ጉዳዩን ከብዙሃን ጋር ለማያያዝ መሞከራቸው የዛሬ የሕወሓት አጫፋሪዎች ነገ ምን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ አመልካች ነውና በጉዳዩ ላይ የራሴን አስተያየት ለመስጠት ተገድጃለሁ።
የነገሩ መነሾ፤ የዞን ዘጠኝ ባልደረባ የሆነው ጆማኔክስ ከዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር በትዊተር ገጽ ያደረገውን ምልልስ ተከትሎ የተፈጠረ ነው። የጆማኔክስ “ስድብ” ቀጥታ ከባለስልጣኑ ጋር ያደረገውና ባለጉዳዩም መብት ረጋጭ ዓይነት ባይሆኑ ኖሮ መልስ የሚሰጡበት ጉዳዩም እዛው ገጽ ላይ የሚጠናቀቅ በሆነ ነበር። ይሁንና ነገርን እንዳሻቸው የሚቀለብሱት ካድሬዎች የሁለቱን ምልልስ ከአጠቃላይ የትግራይ ሕዝብ ጋር በማያይዝ ያዙኝ ልቀቁኝ ነበር የመረጡት።
ጥላቻን መርጨት ዋነኛ መተዳደሪያቸው ያደረጉት ግለሰቦች ስድቡ የትግራይ ሕዝብን እንጂ ቴዎድሮስ ላይ ያነጣጠረ ብቻ አይደለም ወደሚል መደምደሚያ ሊያደርሳቸው የሚችል አንዳችም መንገድ አልነበረም። ምክንያቱም አንደኛ፤ የትግራይ ሕዝብ በስም አንዳችም በምልልሱ ላይ ስላልተጠቀሰ ሁለተኛ፤ ባለስልጣናትን መስደብ ሕዝብን መስደብ ነው የሚል ትርጓሜ ስለሌለ። ( ቢኖርም እንኳ ሰውየው የኢትዮጵያ እንጂ የትግራይ ባለስልጣን የሚል ቅጥያ ስለሌላቸው። ሕዝብ ተሰደበ ከተባለም የኢትዮጵያ ሕዝብን ሁሉ የሚመለከት ስለሚሆን) ሦስተኛ፤ ስድብ የተባለው ቃል ከስድብነት ይልቅ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ስታተስን የሚገልጽ በመሆኑ። ይህም ከአንድ ቡድን ወይም የአንድ አካባቢ ተወላጅ ይልቅ በታሪኩ ውስጥ ያለፈን ግለሰብን የሚመለከት በመሆኑ
እውነታው ይህ ቢሆንም ካድሬዎቹ እንደተለመወደው የዘር ከበሯቸውን አንስተው ማጮህን ነበር የመረጡት። የትግራይን ሕዝብ በአንድ ቁና ሰፍረው ማደናገርን፤ ያልተሰጠውን ስያሜ በመስጠት ከተቃዋሚዎችም ከተቀረው ሕዝብ ጋርም ማቃቃርን የስልጣን ማራዘሚያ ዋነኛ መንገድ አድርገውታል። በዘጠና ሰባት ምርጫ ግንቦት ሰባትን፤ ከዛም እነ እስክንድር ነጋ ላይ አሁን ደግሞ የዞን ላይን ልጆች ላይ ተመሳሳይ የዘር ጉዳይ መነሳቱ የጥላቻ ፖለቲካ የሥርዓቱ ዋነኛ መርሕ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
ከሁሉ የከፋው ጉዳይ ግን በተመሳሳይ መልክዓ-ምድር የሚኖረው ማህበረሰብ ከሚጋራቸው ከቋንቋ እና ባህል ጉዳዮች ውጭ እንደ ግለሰብ የራሱ የሆነ የፖለቲካ አመለካከት፤ የነገሮች አተያይ ወይም አጠቃላይ የሕይወት ፍልስፍና የሌለው ይመስል ሕወሓት በሰፋለት ጥብቆ እንዲታፈን መገደዱ ነው። ሰዳቢውም ተሰድባሃል ብሎ ጠበቃ የሚቆመውም ሕወሓት መሆኑ ደግሞ ይበልጥ አሳዛኝ ነው

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on July 29, 2014
  • By:
  • Last Modified: July 29, 2014 @ 3:20 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar