www.maledatimes.com 140 ሚሊዮን ብር ለቦረና አካባቢ ውሀ ስራ የተመደበው የት ገባና በውሃ ጥም ቦረና፣ ዲሎ መጋዶ… ከብቶቻቸው አለቁ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

140 ሚሊዮን ብር ለቦረና አካባቢ ውሀ ስራ የተመደበው የት ገባና በውሃ ጥም ቦረና፣ ዲሎ መጋዶ… ከብቶቻቸው አለቁ?

By   /   August 1, 2014  /   Comments Off on 140 ሚሊዮን ብር ለቦረና አካባቢ ውሀ ስራ የተመደበው የት ገባና በውሃ ጥም ቦረና፣ ዲሎ መጋዶ… ከብቶቻቸው አለቁ?

Print       Email
0 0
Read Time:0 Second

….140 ሚሊዮን ብር ለቦረና አካባቢ ውሀ ስራ የተመደበው የት ገባና በውሃ ጥም ቦረና፣ ዲሎ መጋዶ… ከብቶቻቸው አለቁ?

ግሩም ተ/ሀይማኖት

እዚሁ ፌስቡክ ላይ አንድ ነገረኛ ፎቶ አየሁ፡፡ ነገር አስነስቶ ነገር አሳስቦ ለምን በሚል ቁጭት የሚያርመጠምጥ ነው፡፡ የቦረና ከብቶች በውሃ ጥም አልቀው(ተረፍርፈው) ያሳያል፡፡ በወያኔ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለሆዳቸው ባደሩ የብሄሩ ተወላጆች የሚሰራው የበለጠ ህዝቡን በቁጭት ያርመጠምጣል፡፡ ከአቶ ተነስተው (ወታደር) ታጋይ፣ ከታጋይ የሚል ቅጽል ስም ዘለው ጀኔራል ከዛም ዘለው የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት ለመባል የበቁት አባዱላ ገመዳ ስልጣናቸው ላይ በነበሩ ጊዜ ኡታሎ፣ መጋዶ፣ ያቤሎ ከተማ የመጠጥ ውሃ ገባ ተብሎ በሌሎችም ቦረና ዙሪያ ቢርካ ሲመርቁ በቲቪ ታይተዋል፡፡ ከቴሌቪዥን እይታው ውጭ ከጀርባው ግን አስቂኝ ድራማ ነበረው፡፡ በሰዓቱ በኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ውስጥ ይሰራ የነበረ አንድ ወዳጄ እንደነገረኝ እና እንደ ሰጠኝ መረጃ የውሃ ቢርካው ለቲቪ እይታ እና ማስመሰል ብቻ የተደረገ የሙስና ድራማ ነበር፡፡

በፌደራል መንግስት አንደኛው ስራ ሲያልቅ ስለሆነ ሌላኛውን ኮንትራት መውሰድ የሚቻለው በሽፋን የቦረና ህዝብ ላይ የተጫወቱት አቶ ሽፈራው ጃርሶ እና አቶ አባዱላ ገመዳ ናቸው፡፡ በወቅቱ ከኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን የበላይ ቦርድ ሀላፊ አቶ ሽፈራው ጃርሶ ነበሩ፡፡ በሌላ በኩልም የዚህን ኮንስትራክሽን ስራ የሚቆጣጠረው የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ዲዛይን እና ቁጥጥር የቦርድ ሰብሳቢም ራሳቸው አቶ ሽፈራው ጃርሶ ነበሩ፡፡ ሁለቱንም በሞኖፖል ይዘው ስራው ቢበላሽ እንኳን የዲዛይን እና ቁጥጥር ቦርድ ሰብሳቢ በመሆናቸው ተቆጣጣሪና ተው(ሀይ) ባይ ስለሌለባቸው እንደፈለጋቸው ሆነው ባጀቱን አውድመውታል፡፡ አቶ ሽፈራው ጃርሶ እና አቶ አባዱላ የአንድ አካባቢ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ እንዲሸፋፈኑ አድርጓቸዋል፡፡

ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት የነበረው የቦረና አካባቢ የመጠጥ ውሃ ስራ እስካሁንም በእንጥልጥል ቀርቷል፡፡ በብሩ ሲጨፈርበት ተከርሞ እንደተሰራ በማስመሰል ድራማ ሰርተው ህዝቡን አታለሉት፡፡ አቶ ሽፈራው ጃርሶ ያቤሎ ብቅ ባሉ ቁጥር ያቤሎ ሞቴል አርፈው በቀን 800 የሚከፈልበታ አላጋ ተይዞላቸው ተንፈላሰው..ወስላ(የፍየል አሮስቶ) እየተሰራ እየበሉ ለእሳቸው አቀባበል በሚል ሰራተኛው ሁሉ በመጠጥ ተንበሻብሾ ይሰነብታል፡፡ ውሀው እስካሁንም ለያቤሎ ህዝብ የህልም እንጀራ ሆኖበታል፡፡

ያኔ በ2002 እና በ2003 ባለው ጊዜያት ከያቤሎ ከተማ ወጣ ብለው የሚገኙ ቦታዎች ላይ የኦሮሚያ የወቅቱ ፕሬዘዳንት የነበሩት አባዱላ ገመዳ አንዱ ፕሮጀክት አቀለ እያሉ ሲመርቁ በነበሩበት ወቅት የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር ተብሎ የሚሰራበት ቦታ ላይ በውሃ ቦቴ መኪና መጥቶ ይገለበጥበታል፡፡ ከውሀው መነሻ ዲሎ እና ኡታሎ እዚህ ድረስ ተገነባ ይባላል፡፡ ግን ከውሃ ታንከሩ ከ20 ሜትር የማይበልጥ ቧንቧ ውሃ ተዘርግቶ በመኪና የመጣውና ታንከሩ ውስጥ የተገለበጠውን የወቅቱ የኦሮሚያ ፕ/ት አባዱላ ገመዳ የሳቸውን ዝና ለመገንባት ቀን ከሌት ይሰራ የነበረውን ኦሮሚያ ቲቪ አስከትለው ከች ይላሉ፡፡ ሪባን ቆርጠው ቧንቧ ውሃው ረግመው ይሁን መርቀው ባልታወቀ መንገድ ለእይታ ይከፍታሉ፡፡ የተከፍተው ቧንቧ ውሃ ስር እጃቸውን አስነክተው ፊታቸውን ያብሳሉ፡፡ ባልሰሩበት የወርቅ ቦነስ ተቀብለው ይሄዳሉ፡፡

የወርቅ ቦነሷ ነገር አስገራሚ እና ብዙ የተባለላት ነች፡፡ የአቶ አባዱላ ገመዳ አጫፋሪዎች ህዝቡን ሰብስበው ለእኛ አስበው ይህን ያሰሩ ኩሩ የኦሮሞ ልጅ ናቸው፡፡ አዋጡና ደስ እንዳለን የሚገልጽ ስጦታ እንስጣቸው እየተባለ ከህዝቡ ይሰበሰብና ኪሱን አራቁተው ለእሳቸው ወርቅ ስጦታ ይሰጣቸዋል፡፡ እሳቸው ባላቸው ባካበቱት ሀብት ላይ ሲጨምሩ ምስኪኑ ገበሬ መሬት ገፍቶ ላቡን ደፍቶ ያገኘውን ከጉሮሮው ተነጥቆ ጦም ያድራል፡፡ ለህዝቡ ገባልህ፣ ሰራንልህ የተባለው ውሃ ታንከሩ ውስጥ የተገለበጠው ውሃ ሲያልቅ ይቆማል፡፡ ህዝብ መልሶ በውሃ ጥም ይቆላል፡፡ ከብቶቹ ይረግፋሉ፡፡ በዚህ ዙሪያ በርካታ ምስጢር ያካፈለኝ ወዳጄን ምስጋና ይድረሰውና በሰፊው እመለስበታለሁ….

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
Print       Email
• Published: 10 years ago on August 1, 2014
• By:
• Last Modified: August 1, 2014 @ 6:44 pm
• Filed Under: Ethiopia
• Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar