ከላይ ሆነን ስናይ
በ ገለታውዘለቀ
በቅርቡየኣሜሪካፌደራልኣቪየሽንኣስተዳደር(FAA)በዓለምላይለበረራኣደገኛየሆኑትንመስመሮችበካርታውላይከቦኣስጠንቅቆየነበረሲሆንበሪፖርቱላይእንደሚታየውእነዚህንኣደገኛቦታዎችበሁለትከፍሏቸዋል።ኣንደኛውመስመርኣደገኛነትያለውክልል (potentially hostile region) ሲሆንሁለተኛውክልልግንበረራንጨርሶየከለከለ(Flight prohibited) ክልል ነው።ኣደገኛነትኣላቸውተብለውኣብራሪዎችከግምትእንዲያስገቡየተመከሩባቸውክልሎችኬንያ፣ኣፍጋኒስታን፣ኢራን፣ሶሪያ፣ማሊ፣የመን፣ኮንጎናግብጽ ሲናይናቸው።የበረራመስመርየተከለከለባቸውኣካባቢዎችደግሞዩክሬንውስጥድኒፕሮፐትሮቭስክ (ይህ ኣካባቢ በሶቪየት ዮኒየን ጊዜ የኒውክሌር ማምረቻ ተቋም የነበረበትና በኣሁኑ ሰዓት ደግሞ በራሽያ የሚደገፉ ገንጣዮች የሚንቀሳቀሱበት ክልል ነው)፣የክራይሚያ ክልል፣ሊቢያ፣ሶማሊያ፣ኢራቅ፣ሰሜንኮርያናሰሜናዊኢትዮጵያ (ትግራይ)ናቸው።
የፌደራልኣቪየሽንኣስተዳደርመግለጫውንካወጣበሁዋላበተለይለበረራየተከለከሉትንክልሎችስናይብዙምጥያቄያልፈጠረብንቢሆንምየሰሜኑየኢትዮጵያክፍልግንተለይቶከነዚህኣደገኛኣካባቢዎችጋርእንዴትሊመደብቻለ?የሚለውጉዳይበተለይለኛለኢትዮጵያዊያንትልቅየመወያያጉዳይየሆነይመስላል።የኣሜሪካመንግስትምንኣይቶነው?ምንመረጃኣገኘ?የሚሉትጥያቄዎችበጣምያጓጉንምይመስላል።ይህጉዳይመወያያከሆነወዲህብዙሰውመላየመታውየኢትዮጵያመንግስትከኤርትራጋርለመዋጋትእቅድስላለውናየኣሜሪካመንግስትምይህንንስለተረዳበኣካባቢውወታደራዊእንቅስቃሴስለሚታይ ቦታውንከኣደገኛኣካባቢሊያስመድበውችሎኣልየሚልነው።ሙያው ባይኖረኝምና ለዛሬ ጽሁፌ ዋና ጭብጥ ይህ ጉዳይ ባይሆንም በዚህ ላይ እኔም እንደ ግለሰብ የግል ኣስተያየቴን መስጠት እፈልጋለሁ።
በእኔግምት የፌደራልየበረራኣስተዳደርንወደዚህ ከፍተኛ ውሳኔ ያመጣው መረጃ ኤርትራና ኢትዮጵያወደፊትወይምበቅርቡ ለሁለተኛ ጊዜ ጦርነት ሊያደርጉ በዝግጅት ላይ ከመሆናቸው ጋር በጥብቅ የተያያዘ ኣይመስለኝም።የኢትዮጵያመንግስትከኤርትራጋርለመዋጋትማሰቡበራሱየትግራይንክልልኣደገኛሊያሰኘውኣይችልም።ከዚህምበላይኢትዮጵያናኤርትራጦርነትለማድረግዝግጅትካለምይህየመጀመሪያኣይደለም።ከ1998 እስከ 2000 ድረስሰባሽህሰውያለቀበትንውጊያባደረጉበትጊዜኣሜሪካይህየበረራመስመርእንዲህኣሳስቧትኣታውቅም።ከዚህምበላይጉዳዩየሁለቱወገኖችጦርነትየማስነሳትፍላጎትማሳየትለኣሜሪካበረራኣስጊነውከተባለየኤርትራየኣየርክልልኣብሮለምንኣልተዘጋም?ብለን እንጠይቃለን::ቢያንስ-ቢያንስ Potentially hostile region በሚለውማሳስቢያውስጥእንኳንኣልገባም።ይልቁንመረጃውየሚያስጠነቅቀውየኢትዮጵያሃይላትኣልፈውኬንያ ማንዴራ ኣየር ማረፊያ ላይ ሳይቀር ኣውሮፕላኖች ሲነሱም ሆነ ሲያርፉ ከኢትዮጵያ ሃይላት ሊተኮስባቸው ሊችል እንደሚችል ነው። በካርታውላይእንደሚታየውኤርትራበኣደገኛክልልእንኳንያልተፈረጀችሲሆንሌላውየኢትዮጵያክፍልምበሁለተኛደረጃኣደገኛእንኳንኣልተባለም።ኤርትራምሌላውምየኢትዮጵያክፍልንጹህየበረራክልልሆነውነውየሚታየው።ሌላውደግሞሌሎችሃገሮችማለትምየጦርነትቀጣናየሆኑሱዳኖችንጨምሮበኣስተዳደሩበኣደገኛነትያልተፈረጁመሆኑየሚያሳየውኢትዩጵያናኤርትራለመዋጋትኣቅደዋልናበረራእንሰርዛለንወደሚልከፍተኛውሳኔእንደማያመጣነው።
ከሁሉበላይግንኣስተዳደሩንያሰጋውየጦርነትቀጣናመሆንያለመሆንጋርየተያያዘሳይሆንከኣሸባሪነትጋርየተያያዘስጋትነው።ስጋቱልክዩክሬንውስጥእንደሆነውሲቪልተጓዦችንሳይቀር ሊያነጣጥርና ሊጎዳየሚችልየሽብርስራሊደረግባቸውየሚችልባቸውንቦታዎችነቅሶከማውጣትጋርየተያያዘነው።ታዲያየኣሜሪካመንግስትመደዚህከፍተኛርምጃሲመጣኣንዱየሃገራችንክፍልበዚህክብውስጥወድቆኣልናይህክፍልትኩረትውስጥመግባቱለእኔያሳየኝንእንደሚከተለውኣንድሁለትልበል።
- ትግራይውስጥየከፍተኛ ሮኬቶችና ሚሳየሎች ክምችት ኣለማለትነው።
2. መሳሪያመኖሩብቻሳይሆን ኣሜሪካእምነትያጣችበትኣደገኛቡድንበዚህክልልይንቀሳቀሳልማለትነው:: ያ ቡድን ማን ሊሆን ይችላል?
በቅርቡዪክሬንውስጥተመቶየወደቀውየማሌዢያኣውሮፕላንሲመታኣንዱየተፈጠረውጥያቄየዩክሬንገንጣይቡድንይህንኣውሮፕላንበዚያከፍታላይመቶሊጥልየሚችልሚሳየልከየትኣመጣው? የሚል ነበር። የብዙዎች መላ ምት የነበረው ራሺያቡድኑንስለምትደግፍከሱዋየተገኘድጋፍመሆንኣለበትየሚልነበር።
ታዲያበዚህየኢትዮጵያክልልበልዮስሙትግራይውስጥእንዲህከፍተኛሮኬትሊኖረውየሚችልለኣሜሪካኣውሮፕላንስጋትየሚሆን ቡድንማንሊኖርይችላል?ብለንእንድንጠይቅያደርጋል።ኣልፎኣልፎእንደምንሰማውበዚያ ኣካባቢ ኣለመረጋጋትካለያቺየውስጥኣለመረጋጋትከክላሽንኮፕበጣምከዘለለደግሞከላውንቸርየበለጠኣቅምያለውተቃዋሚቡድንኣይኖርም።በመሆኑምበዚህቀጣናከፍተኛሮኬቶችንናሚሳየሎችንሊያከማችየሚችለውብቸኛቡድንወያኔ (TPLF) ብቻስለሆነይህቡድንነውበኣሜሪካየበረራኣስተዳደርበኣደገኛነትየተፈረጀውለማለትይቻላል።ይህቡድንብቻነውኣቅምያለውና።ወያኔትግራይንለምንየከፍተኛሮኬቶችናሚሳየሎችመደበቂያኣደረጋትለሚለውምላሹከኤርትራጋርለምታደርገውጦርነትብቻ ተብሎሊወሰድኣይችልም።ኢትዮጵያበሶማሊያበኩልበሱዳንበኩልምስጋቶችኣሉባት።በከፍተኛሁኔታወያኔበሚስጥርትግራይውስጥመሳሪያዎችንመደበቁ ድሮም ቢሆንለብዙዎችሲሸትየነበረጉዳይነው።ወያኔህዝባዊኣመጽሲነሳየመጨረሻውመደበቂያየብሎየሚያምነውትግራይንበመሆኑመሳሪያሲደብቅመሰንበቱኣይገርምም።
ያለበትስጋትከፍተኛበመሆኑመሳሪያሰብስቦ ኣይጠግብም።ጥያቄው ታዲያ ይህን ከፍተኛ መሳሪያ ከየት ያመጣዋል? ካልን ምንጮቹ ኣሸባሪነትን ከሚደግፉ፣ ለዩክሬን ገንጣይ ቡድን ራሽያ ታግዛለች እንደሚባለው በሚስጥር ከደጋፊዎቹ የሚሰበስበው ነው። ባለፈው ጊዜ ደቡብ ኮርያ ውስጥ ጥገኝነት የጠየቁ የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ሰራተኞች እንደገለጹት የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ሰሜን ኮርያ ውስጥ በምስጢር ገብቶ የጦር መሳሪያ ጭኖ እንደተመለሰ ነው።ህወሃት ያልተረዳው ነገር ሚሳየል መሰብሰብ ከምንም ሊያድነው እንደማይችል ነው። ይልቁን ኣሁን ኣሜሪካ እንዳደረገችው ኣለም እየተረዳው መጥቶ ለኣለም ስጋትነቱ ስለሚጋለጥ መጥፊያው ይሆናል።
ከዚህበፊትየወያኔ መንግስት በኣፍሪካቀንድላይኣሸባሪመሆኑየተገለጸሲሆንኣሁንደግሞየኣሜሪካየበረራኣስተዳደርትግራይንለይቶበካርታውላይመክበቡበተለይየትግራይነጻኣውጪላይያለውንእምነትማጣትብቻሳይሆንወያኔለራሷለኣሜሪካስጋትነውወደሚልድምዳሜእንዳመጣቸውያሳያል።እውነትምነው።
ይህመረጃበተለይምየትጥቅትግልለሚያደርጉወገኖችጠቀሜታውከመጉላቱምበላይየሃገራችንንየትግልኣቅጣጫናሊመጡየሚችሉተለዋዋጮችንእንድናይይረዳናል።ወያኔበዚያክልልመሳሪያመሰብሰቡበኤርትራበኩልሊመጡየሚችሉትንሃይሎችለመቋቋምብቻሳይሆንከፍሲልእንዳልኩትሁኔታውከገፋናኣመጾችከበረቱትግራይውስጥመሽጌኣገርመበጥበጤንእገፋለሁየሚልበመሆኑይህንንባህርዩንከመቼውምበላይበመገንዝብ ተቃዋሚዎች በትግል ካልኩሌሽናቸው ኣንድ ደረጃና ሁለት ደረጃ ከፍ ብለው መገኘት ኣለባቸው። ይቺን ካልኩኝ በሁዋላ በኢትዮጵያ የነጻነት ትግል ኣሰላለፍ ዙሪያ ጥቂት ወንድማዊ ኣሳቤንና ስጋቴንም ጭምር እንደሚከተለው ልጻፍ።
በሃገራችንየነጻነትትግልእንዳያብብኣብቦምእንዳያፈራካደረጉትችግሮችመካከልኣንዱየነጻነትትግሉ ኣጠቃላይቅርጹወዲያናወዲህየተጠመደመሆኑነው።ኣንዱበብሄርላይየተመሰረተሌላውደግሞብሄራዊበሆነኣቋምላይየተመሰረተ ኣንዱ ደግሞ ለዘብተኛ ነኝ የሚል በመሆኑትግሉእንዳያሸንፍኣሸንፎስልጣንቢይዝምነጻነትእንዳያፈራያደርጋል።
የቅርብጊዜውንታሪክስናይእንኳንህወሃትየብሄርኣርማኣንግቦትጥቅትግልከጀመረበሁዋላሌሎችብሄራዊኣቋምያላቸውንቡድኖችንኣብረንእንታገልበማለትይቀሰቅስነበር።በተለይኢህዴን ኣንዱ ለህወሃት ከፍተኛ ኣስተዋጾ ያደረገ ድርጅት ነው።
እነዚህሁለትቡድኖችማለትምኢህዴንናህወሃት ከመርህኣንጻርከሳይንስኣንጻርየማይደባለቅምንነትይዘውደርግንመጣልታላቅግብበማድረግብቻተጣምረውታገሉ።ህወሃትትንሽብልጠትስላለውኢህኣዴግየሚባልየማንነትማደናገሪያለጠፍኣርጎቀጠለ። በትግሉምወቅትሆነከትግሉበሁዋላህወሃትወታደራዊየበላይነቱንእንደጠበቀየቆየሲሆንሁኔታዎችሲረጋጉ፣መንግስትተመስርቶኣገርየሚባለውንነገርየምርየማስተዳደሩጉዳይሲመጣህወሃትኢህዼንንእንደገናኣተኩሮያየውይመስላል።እኔየትግራይነጻኣውጪነኝ፣ኦህዴድምየኦሮሞሆኖተሰልፎኣል፣ኣንተምንድነህ?በሚልኣይነትኣፍጦካየውበሁዋላወደብሄርቡድንነትዝቅእንዲልስሙንምኣርማውንምእንዲያስተካክልተፈረደበት።ህወሃትወታደራዊየበላይነቱንይዞታልናኢህዼንምንምኣላለም።
ኢህዴንበኣማራተወላጆችብቻኣልነበረምየተሞላው።የተለያዩብሄሮችያሉበትኣገራዊኣሳብየነበረውድርጅትቢሆንምብዓዴንበመባልየኣማራድርጅትእንዲሆንተፈረደበት።ኣሁንየምናያቸውኣማራያልሆኑመሪዎች የኣማራስምለጥፈውብዓዴንየሚባልኣስገራሚድርጅትፈጥረውቁጭኣሉ።የሚገርመው ኣማራውም ደንታ ሳይሰጠው ዝም ብሏቸው ሰነበተ።
ይህየማንነትጥያቄናየመጣመድጥያቄቀድሞበትግሉ ጊዜቢመጣ ሚናቸውንበሚገባቀድመውቢረዱየተለየመልክሊኖረውየሚችልሲሆንከድልበሁዋላህወሃትወታደራዊውንናደህንነቱንበሙሉከተቆጣጠረበሁውላበመሆኑእነኢህዴንሃይልኣልነበራቸውምናየተሰጣቸውንስምተሸክመው፣ያልሞቱለትን፣የህወሃትንዓላማያራምዱዘንድቀጠሉ።ህወሃትከመነሻውደርግንለመጣልከሚገባውበላይየጓጓበመሆኑየማይጣመደውኣልነበረም።ከኤርትራነጻኣውጪጋርተስማምቶታግሏል፣ከሱዳንበኩልየሚነሳቢኖርኖሮምኣብሮይታገላል ብቻከማንምጋርታግሎደርግንመጣልየመጨረሻውኣላማውነበር።ኢህዼንምቢሆንደርግንመጣልእንደመጨረሻግብበማየቱናይህግብዋናውንየሃገሪቱንመሰረታዊየነጻነትናየኣስተዳደርጉዳዮችለማየትኣይኑንበመጋራዱከማይጣመደውየቡድንነጻኣውጪጋርተጣምዶእያረሰኣዲስኣበባገባ:: ህወሃትንለድልኣብቅቶሲጨርስምእንደህወሃትእንዲሆንየህወሃትንኣምሳልሆኖእንደገናእንዲፈጠርተደርጎቁጭኣለ።
በሃገራችንበተለይምበሰሜኑክፍልየገናበዓልሲመጣየገና ጨዋታይደረጋል።በእድሜገፋያሉሰዎችሳይቀሩይሳተፋሉ።ታዲያበዚህጨዋታጊዜከየቀበሌውወይምጎጡየመጡትሰዎችጥንጓን (ሩሯን) ሲቆረቁሱ “ሚናህንለይ!”የሚባልነገርኣለ።ሚናያለየበትየገናጨዋታየሚያስታውቀውሩሯርቃኣትሄድም።በሚገባሚናየለየለትጨዋታግንወደኣሸናፊውያደላናድልኣድራጊናተደራጊበጊዜ ይለያል።
የሃገራችንየነጻነትትግልከህወሃትናኢህዴንትግልጀምሮኣሁንድረስምበቡድነኝነትናበብሄራዊታጋይነትሚናውቅጡየጠፋበትነው። የዚህየብሄርየነጻነትጥያቄጉዳይበኢትዮጵያውስጥመስመሩንሁሉስቶግልጽነትየጎደለውእንዴውምኣደገኛኣሰላለፍሆኖእናያለን።በመጀመሪያደረጃበብሄርላይተመስርቶየሚደረግትግልየሚያስፈልገውለመገንጠልነው።ለምሳሌየኤርትራንትግልካየንእንደግፈውምኣንደግፈውምለመገንጠልታገሉእንዳሉትምተገነጠሉ።እንደህወሃትኣይነቱግንፍላጎቱምኣይታወቅም።የብሄርጥያቄይዞተነሳትግራይንኣልፎኣዲስኣበባገባ።ከገባምበሁዋላኢትዮጵያንማስተዳደርጀምሮሃያኣመትከቆየበሁዋላእንኳንተምሮኣቋሙንየማይቀይርኣስቸጋሪድርጅትነው።
በኣንድነትእያመኑበብሄርየፖለቲካጥላስሮመቆምፈጽሞኣብሮኣይሄድም።የሃገራችንየፖለቲካግጭትምይሄነው።በመሆኑምኣሁንምለነጻነትቆመናልየሚሉድርጅቶችጥያቄያቸውለመገንጠልካልሆነናየነጻነትጥያቄከሆነኣገራቸውንነጻለማውጣትከዚህግልጽነትከጎደለውየትግልመስመርወጥተውህብረብሄራዊመልክመያዝኣለባቸው።የለምእኛበኢትዮጵያኣንድነትላይጥያቄየለንምነገርግንበብሄርላይቆመናልየሚባልነገርሚናውያልለየበመሆኑየሃገራችንንየነጻነትትግልከማወሳሰቡምበላይማንንምነጻኣያወጣም።በብሄርላይየተደራጁወገኖቼሊረዱትየሚገባቸውጉዳይቢኖርበዚህየትግልስልትለማሸነፍኣይችሉምቢያሸንፉምቡድናቸውንምሆነሃገራችንንነጻሊያወጡኣይችሉም።ይህንንከነህወሃትመማርያስፈልጋል።ህወሃትኢትዮጵያንምነጻማውጣትኣልቻለምቆሜለታለሁላለውየትግራይህዝብምነጻነትንሊያመጣኣልቻለም።ኢትዮጵያብዙናትብሎያመነታጋይ፣ ብዙህነቱዋንያመነነጻኣውጪብዙነቱዋንየያዘየነጻነትሰራዊትነውነጻሊያወጣትየሚችለው ብሎ ያምናል።
በኣሁኑሰዓትበትጥቅትግሉኣካባቢየሚንቀሳቀሱወገኖችምቢሆኑይህንንሃቅመረዳትናበመርህላይየተመሰረተመቀናጀትሊያደርጉይገባቸዋል።እንደትግራይህዝቦችዴሞክራሲያዊንቅናቄ (TPDM)ያሉየህዝብብሶትኣስነስቶናልየሚሉታጋዮችምከወያኔመማርኣለባቸው።
እውነቱንንገረንካላችሁኝከመርህኣንጻር ለእኔህወሃትምሆነየትግራይህዝብዴሞክራሲያዊንቅናቄ (ዴምህት)ሁለቱምኣንድናቸው።ልዩነታቸው ህወሃትንስልጣንላይሆኖብዙበደልሲፈጽምያየሁትሲሆንዴምህትንኣላየሁትም።ህወሃት ወንጀለኛ ሲሆን ዴምህት እንደማንኛውም የጎሳ ድርጅት ነው የሚታየኝ። በቃ።መነሳትያለበትየመርህጥያቄእንጂየህወሃትኣመራሮችበግለሰብደረጃክፉዎችናቸውየዴምህት(TPDM)ኣመራሮችግንጥሩዴሞክራትይመስላሉየሚለውኣይሰራም።የመርህጥያቄመነሳትያለበትሲሆንእነዚህቡድኖችምሆኑሌሎችበብሄርላይየቆሙሁሉበመርህደረጃኣንድመሆናቸውንማስተዋልተገቢነው።በግለሰቦችጥሩነትከሆነየህወሃትሰዎችምበትግሉጊዜበጣምጥሩይመስሉነበር።ሌሎችህብረብሄራዊየሆኑድርጅቶችደግሞበብሄርላይከተመሰረቱጋርበመጣመድኣብረንእንታገላለንማለትየለባቸውም።በተለይምበትጥቅትግልጎራያሉከሆነይህመንግስትቢወድቅምበእንደዚህዓይነትየትግልስልትየተመራትግልኣንዱየብሄርቡድንእንደህወሃትወታደራዊየበላይነቱንይዞእንደህወሃትኣይነትስርዓትላለመቀጠሉዋስትናየለንም።በተለይበጣምስስየሆነውወታደሩናደህንነቱበኣንድየብሄርቡድንእጅሲወድቅነጻነትኣያፈራምናከእንዲህዓይነትየትግልመጣመድሚናመለየትያስፈልጋል።የጨከነ በመርህና በሃቅ ላይ የተመሰረተ ሚናውን የለየ የትግል ኣቅጣጫ ያስፈልጋል ማለቴ ነው።ራሱ ወያኔ እንደ መጨረሻ ኣማራጭ (worst case scenario) እንደሚሉት የተለያዩ ተቃዋሚ የሚመስሉ ድርጅቶችን በመፈልፈልና የሰለጠኑ ደህንነቶቹን በዚያ በመሰግሰግ ገዢነቱን(status quo) ለመጠበቅ ስለሚጥር ህብረ ብሄራዊ የትግል ስልት መኖሩ እንዲህ ዓይነቶቹን ኣስመሳዮች ለመዋጥ ይጠቅማል። ዋናው ግን ሁሉን ለመጠርጠር ሳይሆን ጥበብ የተሞላበት ሚና የመለየት ስራ መስራት ኣሰፈላጊነቱን ለማስመር ነው።
ዴምህት እንደዚህ ኣስቦ ሊሆን ይችላል።ምናልባትምህወሃትከትግራይየተነሳበመሆኑናኣሁንያለውየኣስተዳደርብልሹነትስላበሳጫቸውናስላሳፈራቸውእኛውያመጣነውንእኛውእንመልሳለንየሚልስሜትያየለበትቁጭትኣስነስቱዋቸውሊሆንይችላል።ለነዚህወገኖቼመልእክትኣለኝ።ኣይዞኣችሁህወሃትንያመጣችሁትእናንተብቻኣይደላችሁም።እነኢህዴን፣የጎንደርህዝብ፣የወሎህዝብ፣የኦሮሞህዝብ፣ የሰሜን ሸዋ ህዝብየኤርትራነጻኣውጪውተባብረውነውኣዲስኣበባያስገቡት።የትግራይህዝብለዚህመንግስትለብቻውተጠያቂኣይደለም።ሁላችንተጠያቂዎችነን።የደርግ ጭቆና ስላንገፈገፈንና የደርግ መውደቅ ጉዳይ ዋና ግብ መስሎ ስለታየን የህወሃትን ተፈጥሮ ሳንመረምር፣ ስምህ ህወሃት ሆኖ እንዴት ወደ ኣዲስ ኣበባ ትገሰግሳለህ ብለን ኣጥብቀን ሳንጠይቅ ሁላችን ገፍተን ነው ኣዲስ ኣበባ ያስገባነው።ኣበባይዘንየተቀበልነው።በብልጠትህወሃትለጠፍያደረጋትኢህኣዴግየምትባልስያሜንምኣልመረመርንም።ጥፋቱ የሁላችን ነው። የትግራይህዝብለብቻውተጠያቂኣይሆንም።በመሆኑም ሁላችንበጋራታግለንነውይህንንኣሳፋሪታሪክየምንቀለብሰው።የትግራይህዝብበታሪኩከሌሎችወንድምወገኖቹጋርእኩልኣስተዋጾሲያደርግየኖረ፣ክፉንናደጉንኣብሮያሳለፈለኢትዮጵያዊነቱምንምየማይወጣለትነው።በመሆኑምከኣሁንበሁዋላበዚህህዝብስምምንምኣይነትየትግልእንቅስቃሴኣይፈልግም። ህወሃት የጎዳው ይበቃዋል። ይህ ወንድማዊ ኣሳብ ነፍጥ ላነሱ ወገኖች ብቻ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ ለሚታገሉ በብሄር ላይ ለተመሰረቱ ወገኖች ሁሉ ነው። ኣረና ትግራይ፣ ኦሮሞ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የመሳሰሉት ድርጅቶችም ከማንነት ፖለቲካ ወጥተው ህብረ ብሄራዊ መልክ እስካልያዙ ድረስ ትግላችን ኣያፈራም። በቅርቡ ኣረና ትግራይ ለውህደት መነሳቱን በውህደት ላይ ኣዎንታዊ ኣቋም መያዙ የሚደነቅ ሲሆን ይህን ኣቋሙን ቶሎ ብሎ ወደ ተግባር ቢለውጥ ትልቅ የመንፈስ መፈታትን በትግራይ ኣካባቢና በሌሎች ወገኖች ዘንድ ያመጣልየትግራይህዝብየሚፈልገውከሌሎችቡድኖችጋርኣብሮታግሎሃገሩንነጻማውጣትነው።ሌላውየኢትዮጵያህዝብምየትጋራይነጻኣውጪየሚባልኣዲስቡድንነጻእንዲያወጣውኣይፈልግም።ሁላችንእኩልየተሳተፍንበትትግልናድልነውየሚያዛልቀን።የኦሮሞውወገናችንምጥያቄእንደዚሁነው።ያልበላውንለማከክከመሞከርይልቅተቃዋሚሃይላትተባብረውዴሞክራሲንመልካምኣስተዳደርንቢያሰፍኑለትያነውጥማቱ። የኣማራውምጥያቄይሄነው።ለብቻውየዓማራቡድንተቁዋቁሞእነንደህወሃትየዓማራየበላይነትእንዲመጣለትኣይደለም።የደቡቡምየምስራቁምህዝብየጋራችግርበውነቱይሄኣይደለም።
ሌሂቃንበዚህችግርተኛህዝብህይወትላይባይጫወቱጥሩነው።ዛሬየኢትዮጵያኣስርበመቶየሚሆነውህዝብበየኣመቱርዳታጠባቂነው።ሰባበመቶየሚሆነውህዝብድሃነው።በዚህችምድርላይከኒጀርቀጥለንየመጨረሻውንየድህነትኑሮየምንገፋህዝቦችነን።ይህድህነትየሚገለጸውበኢኮኖሚብቻሳይሆንበመላህይወታችንነው። ወደሰላሳበመቶየሚሆነውህዝብማንበብናመጻፍእንኳንኣይችልም።በሃያኣንደኛውክፍለዘመንሃያሰባትሚሊየንየሚሆንህዝብስሙንእንኳንመጻፍበማችልባትኣገርኣርባኣመትሙሉበማንነትጥያቄመደናቆርበሚሊየኖችህይወትመቀለድይባላል።
እንደዴምህትኣይነቱድርጅትህወሃትንያመጣነውእኛነንናእኛውእንዳመጣንእኛውእንመልሰውብለዋልጥሩሰዎችናቸውብሎወታደራዊውንየበላይነትማስረከብናበእንዲህኣይነትመርህበሌለውየትግልስልትመጣመድለብሄራዊታጋዮችተገቢኣይደለም ብቻ ሳይሆን መርህ የጎደለው ማስተዋል የጎደለው ኣካሄድ ነው።።በቆራጥነትበመርህላይየተመሰረተሚናውበደንብየለየለትየትግልመስመርያስፈልጋል። ህወሃት፣ ኢህዴን፣ የኤርትራ ነጻነት ግንባር ደርግን ማሸነፍ የመጨረሻ ግብ ኣድርገው ታግለው ሲያበቁ ኢትዮጵያ በኣንድ የብሄር ቡድን ወታደራዊ የበላይነት ስር ወደቀች:: ወታደራዊ ተቋም ደግሞ በቀላሉ ደህንነቱን ይቆጣጠርና የዚያች ኣገር የፍትህና የዴምክራሲ ጥያቄዎች ዳዋ እንዲበላው ያደርጋሉ። ከኣሁንበሁዋላኢትዮጵያንየኣንድብሄርየበላይነትያለውወታደራዊእንቅስቃሴነጻኣያወጣትምብቻሳይሆንኣደገኛመሆኑንምመገንዘብኣለብን።ለኦነግወገኖቼ፣ለኣማራነጻኣውጪወገኖቼ፣ለጋምቤላነጻኣውጪወገኖቼ፣ለኦብነግወገኖቼ፣ለሲዳማነጻኣውጪወገኖቼናለሌሎችምየምመክረውምክርኣጭርነው።ወንድሜኦባንግያለውነገርኣለ።
“ሁላችንምነጻካልወጣንማንምብቻውንነጻመሆንአይችልም!”
ኦባንግ ሜቶ
ታላቅኣባባልነው።የቡድንጥያቄይዘንቡድናችንንምሆነኣገራችንንነጻልናወጣኣንችልም።ሌላውስለሚናስናነሳየርእዮቱንጉዳይብቻሳይሆንራሳቸውተቃዋሚየመሰሉኢህዓዴግየመሰረታቸውወይምየሱመጫወቻየሆኑትንእነሱንምየመለየትስራንምይመለከታል::እነዚህንበይፋየመለየትናየማውገዝስራካልተሰራኣሁንም ኣይናፋር ታጋዮች ሆነንሚናውያለየለትትግልውስጥስለምንቆይትግላችንቶሎኣያፈራም።
በመሆኑምየነጻነትታጋዮችበኣንድበኩልውህደትንናህብረትንእያጠናከሩበሌላበኩልደግሞየሚናመለየቱንጉዳይበቆራጥነትሊመሩትይገባል። ኣንድሰውበኣንድኣስተዳደራዊጥያቄዙሪያኣርባኣመትመጨቃጨቅየለበትም።ኣለምጥሎትበመጣ፣በኣንድወቅትብልጭባለግልጽነትበጎደለውየማንነትጥያቄዙሪያተኮልኩለንድሃውንማሰቃየትየለብንም።በመሆኑምኢትዮጵያዊያንህብረብሄራዊየሆኑትንእንቅስቃሴዎችእንደግፍ።እናንተኢትዮጵያንበሙሉማንነቱዋየምታዩነጻኣውጪዎችደግሞሚናየመለየትስራእየሰራችሁወደህብረትኑናኣገራችንንታደጉ።ዛሬህዝቡእየጠየቀነው።ኧረእንደዚህኣድርጉበሉን፣ምሩን….ለመታገልዝግጁነን……የትናችሁ?የትደረሳችሁ?ኣየ…. የጨነቀውህዝብ….።የሚያሳዝነውግንበተግባርየሚታይነገርየለም።ይህመንግስትበኣመጽነውየሚወድቀው።ይህንንደግሞለመምራትሚናቸውንበሚገባየለዩነጥረውየወጡ የእውነተኛፓርቲዎችህብረትናኣመራርሰጪነትንይጠይቃል።በቃ!….ያለፈውይብቃንናወደፍጻሜእንምጣ።ለነዚህበብሄርላይለቆሙወገኖቼበመጨረሻምየምመክረውይህንንነው።ችግሮቻችንየሚፈቱትከላይሆነንስናይነው።ከላይከኣፍረካህብረት፣ከላይከግሎባላይዜሽን፣ከላይከኢትዮጵያኣንድነትላይሆነንስናይውስጥለውስጥየሚነሱየባህላዊቡድንማንነትጉዳዮችየትግላችንንመስመርኣያሰምሩልንም።ከላይኣሁንየሰውልጅከደረሰበትማህበራዊናየተፈጥሮሳይንስየግንዛቤደረጃላይሆነንስናይከማንነትፖለቲካጋርየተያያዙብንጥያቄዎችገዝፈውኣይታዩንም።ይልቁንከፍባለዴሞክራሲናመልካምኣስተዳደርላይኣይናችንኣርፎበዚያይህንየተቸገረህዝብለመርዳትመቆምይገባናል ለማለት ነው።
እግዚኣብሄርኢትዮጵያንይባርክ!
geletawzeleke@gmail.com
Average Rating