እግዚአብሄር ይመስገን አይደለም ደም እንባ ሳይፈስ አለፈ፡፡
በፍርሃት ያሳለፍናት አርብ
ፀሐይ በየነ
ሶስትና አራት አመታትን ያስቆጠረው የአረብ ሀገሩ ቀውስ ይኸው ዛሬም እንዳለ አለ፡፡ከቱኒዝያ ተነስቶ ሊቢያን፣ግብፅን፣ሶሪያን ብሎም በየመን የተነሳው የፖለቲካ ቀውስ የብዙ ሺህ ንፁሃን ዜጎቸን ህይወት የቀጠፈ፣ ያቆሰለ በብዙዎች መጥፎ የህሊና ጠባሳ የጣለ፣የአለም ፍፃሜ ቀርበ ተብሎ ህዝብ በህብረት ወደ ፈጣሪ እግዚኦታን ያሰማበት ወቅት ሆነ፡፡
አንዴ ጋብ አንዴ ደግሞ ናር የሚለው ይህ አረቡ ሀገሩ ጦርነት እሳቱ ጨርሶ የሚጠፋው መች እንደሆነ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ታድያ በዚሁ እኔ ባለሁበት የአረብ ሀገሯ የመንም የእሳቱን መጥፍያ በመጠበቅ በሰቀቀን አለን፡፡ በየመን የማይፈልጉት ወርዶ የሚፈልጉት ስልጣን ላይ ቢወጣም አልዋጥ ብሎ ከጎሮሮአቸው ተሰንቅሮ ይተነናቃ…ቸዋል፡፡
አልዋጥ ብሎ ከጎሮሮ ተሰንቅሮ ያለውን ባለስልጣን ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ ለማሳማት በሚወጡ ሰልፈኞች፣ ሰልፈኞቹ በሚያሰማቸው ድምፅና በከሴት በተቀዱ የተቃውሞ መዝሙሮች መንገዶቿ ዘውትር ደምቀው ይውላሉ፡፡
በእነዚህ ቀናት እኛም መንገድ ላይ ሰልፈኞቹ ከገጠሙን ስለማንቀላቀል መዝሙሩ ከጆሮ እሰኪር ይኮመኮምን በአይን የተወሰነ መንገድ እንሸኛለን ሰልፉ ምንም ችግር ስለሌለበት፡፡ የትላትናው አርብ ግን ትንሽ አስፈሪ ነበረች፡፡ ተቃውሞ አሰሚዎቹ የሚፈልጉትን ነገሮች በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ካላስተከለ ከፍተኛ የደም መፋሰስ እንደሚኖር ስለታገሩ በፍርሃት አኮራምታ አውላናለች፡፡
ግን እግዚአብሔር ይመስገን አይደለም ደም እንባ ሳይፈስ አለፈ፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating