www.maledatimes.com ሐሳበ ሽውራሮች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሐሳበ ሽውራሮች

By   /   August 26, 2014  /   Comments Off on ሐሳበ ሽውራሮች

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 13 Second

  1. ሰሞኑን የቴዲ አፍሮ አዲሱ ነጠላ ዜማ ሀገሩን እያነቃነቀው ነው፡፡ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሐኑ፣የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪዎች፣ካፌና ሬስቶራንቶች……ወዘተ በዚህ ነጠላ ዜማ መደማመቅ ይዘዋል፡፡የቴዲ አፍሮ ነጠላ ዜማ ታድያ ከመደመጥም ባለፈ በዚሁ ፌስ ቡክን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ-ገጾች ጭምር ሀሳብ መለዋወጫ እየሆነ ነው፡፡ለኔ አንድ ስራ ተደምጦ መነጋገሪያ መሆን መቻሉ በራሱ ትልቅ ውጤት ይመስለኛል፡፡በየትኛውም ወገን ይሁን መነጋገር፣መወያየት መቻል ዋጋው ከፍ ይላል፡፡ለዚህ ሰበብ መሆን ደግሞ ከመታደልም ይብሳል፡፡
    ለዚህች ጽሑፌ መነሻ የሆነኝን የሐሳብ ትግል ከልቦናዬ ጓዳ ሳዳውር እንዲሰነብት በመሆኑም ነው ሐሳበ ሽውራራዎች ላይ ለመጻፍ የተገፋፋሁት፡፡ርዕሴ አንደሚናገረው ይህ ጽሁፍ በሀሳብ መንሸዋረር ውስጥ ያሉትን ብቻ የሚመለከት ነው፡፡ስለቴዲ አፍሮም ሆነ ስለማናቸውም ጉዳዮች ሰዎች እንደየ ፍላጎታቸው፤ልምዳቸው፣ዕውቀታቸውና ሌሎች የትመጤነታቸው አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ሀሳቦችን ይሰነዝራሉ፡፡ይህ የሰው ልጅ ጠባይ በመሆኑ ተለመደና ብዙም የሚያስደንቅ አይሆንም፡፡ነገርግን አንድ ሰው ሁልጊዜም በማድነቅ አልያም በማውገዝ ውስጥ ብቻ ሲገኝ ችግር ያለ ይመስለኛል፡፡እንዴት ሰው ተኩኖ ሁልጊዜም በመስማማት ወይም በመቃውም ብቻ ይኖራል?ለዛሬው አሉታዊነት የሚታይባቸውን ትዝብቶቼን ብቻ ልቀጥል፡፡
    በኔ ምልከታ እነዚህ ሰዎች በማናቸውም አስተያየታቸው ውስጥ አሉታዊነት ብቻ ይታይባቸዋል፡፡ማውገዝ….መቃወም….ትክክል ለማለት ያለመድፈር….አዎንታዊነትን ማጣትና መሰል ሐሳቦች ብቻ የሚታይባቸው ናቸው፡፡ማድነቅ፣ማበረታታት፣ማረም፣ማገዝ፣ማጨብጨብ……ወዘተ ከአንደበታቸውም ሆነ ከብዕራቸው ለማፍለቅ የማይችሉ ሆነው ይታያሉ፡፡የስነ-ልቦና ባለሙያዎች እነዚህን ሰዎች NO MEN.ይሏቸዋል፡፡ጣታቸውን ሲቀስሩ ለአሉታዊ ትችት የሚውል ምስጋናና አድናቆት የማይወጣቸው ሆነው ይገኛሉ፡ዕውቅናቸውን፣ዕውቀታቸውን ለዚህ እኩይ ሐሳባቸው ማራመጃ የሚጠቀሙ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችን ከቻሉም ከዚያ አልፈው በዚህ ሸውራራ ሐሳባቸው ማጥመቅ የሚቀናቸው ሆነው ይታያሉ፡፡እንደዚህ አይነት ሰዎችን ሁል ጊዜም ሳገኛቸው መራቅን፣መሸሽን እመርጣለሁ፡፡አንዴ ሳነጋግራቸው እንደዚህ አይነት ቫይረስ እንደተጠቁ ካወቅሁ ዳግመኛ ከጎናቸው መሆንን አልሻም፡፡ሚዛንን የማሳት አቅም አላቸውና፡፡ከዚህ በተጨማሪም ለመናገር እንጂ ለማድመጥና የተለየ ሀሳብን ለማስተናገድ የሚሆን ሐርድ ዲስክ የላቸውም፡፡ዲስካቸው ሁሌም ፉል ነው፡፡ የተለየ ሐሳብ ለመቀበል ከሞላው ዲስካቸው ላይ delete ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ለዚህ ደግሞ ጊዜም ሆነ ፍላጎት አይኖራቸውም፡፡እነርሱ ሁሌም ፍላጎታቸው የሚያጠምቋቸውን ተከታዮች አዕምሮና ልቦና Format አድርገው የራሳቸውን አዲስ softaware በመጫን ላይ የተጠመዱ ናቸው፡፡
    የሚያስገርመው ጉዳይ እንደነዚህ ያሉትን ሸውራራ ሐሳብ ብቻ የሚያራምዱ ታዋቂ ስዎች ከእነርሱ በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ ታዋቂ ሰው እንዲኖር አይሹም፡፡እነርሱ ብቻ ታዋቂ እነርሱ ብቻ አዋቂ እንደሆኑ ያስባሉ፡፡አዋቂነትና ተዋቂነት በራሱ ይምታታባቸዋል፡፡ሌላው ገለባ ብቻ ነው፡፡ስለዚህም ማንም ታዋቂ ሰው መድረካቸው ላይ እንዲቆም አይፈቅዱም፡፡ባገኙት አጋጣሚ፣በዙሪያቸው በሚሰበስቡአቸው ጀሌዎችና ሌሎች ዘዴዎች ከፊታቸው የሚቆም የሚመስላቸውን ሰው እንደ እባብ ጭንቅላቱን ይቀጠቅጡታል፡፡ያስቀጠቅጡታል፡፡
    ሌላኛው ወገን የሆነውና የሸውራራ ሀሳብ ደቀ-መዝሙር የሚሆኑብኝ ደግሞ አሉ፡፡ምንም ስራ የማይሰሩ፣የሚሰራም ማየት የማይፈልጉ፣የሰራ የሚመስላቸውን በሰባ አንደበታቸው ሲከትፉ የሚውሉ፣ለራሳቻው ካላቸው የተሳሳተ ከፍታ ላይ ራሳቸውን ሰቅለው የተቀመጡ፣ቢያንኩአኩአቸው ደግሞ ባዶ እንሰራ አይነት ናቸው፡፡የሚያደንቋቸው፣የሚያከብሩአቸው፣የሚወዱአቸው ታዋቂዎቻቸው ደቀ-መዝሙሮች በመሆናቸው ቫይረሳቸውን የሚወጋ ካገኙ ለመውጋት የተዘጋጁ ናቸው፡፡ነገርግን ረብ ያለው ስራ ሰርተው የማያውቁ፡፡
    እንግዲህ የሰውነት ጠባያትን የማጣባቸው ለዚህም ይመስለኛል፡፡የሰው ልጅ ለተንሸዋረረ ሐሳብ ብቻ ተገዝቶ እንዴትስ ይኖራል ስል ሁል ጊዜም ራሴን የምጠይቀው በእነዚህ ምክኒያቶች ነው፡፡ጎበዝ ከዚህ ወስጥ ራሳችሁን ፈልጉ፡፡ሚዛናዊነት ለዘላለም ትኑር፡፡የሀሳብ ልዩነት በልቦናችን ታብራ፡፡
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on August 26, 2014
  • By:
  • Last Modified: August 26, 2014 @ 11:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar