www.maledatimes.com ባንዲራ አይደለም አንገት ዝቅ አላለላቸውም:: - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ባንዲራ አይደለም አንገት ዝቅ አላለላቸውም::

By   /   August 27, 2014  /   Comments Off on ባንዲራ አይደለም አንገት ዝቅ አላለላቸውም::

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 32 Second
ፀሐይ በየነ
አንደበቶች ስለ ስደት መዓት ማውራት ከጀመሩ፣ ጆሮዎች የስደት መከራን ማዳመጥ ከሰለቻቸው አይኖች በስደት የሚደርሰውን እልቂት ማየት ከዘገነናቸው አመታትን እያስቆጠሩ ሄደዋል፡፡ዛሬ ዛሬ በሀገር ቤት መገናኛ ብዙሃን ብቻ ሳይሆን የአለም መገናኛ ብዙሃንም ሳይቀር ኢትዮጵያውያንን የስደት መከራ መዘገብ የዘውትር ተግባራቸው ሆኗል፡፡
በተፈጥሮም ሆነ ከጊዜ በሃሏ በሚደርስባቸው ችግር ምክንያት የመስማት፣ የመናገር፣ብሎም ሙሉ አካል የሌላቸውን ጨምሮ እናቶች አባቶች፣ አዛውንቶች፣ ዳዴ የሚሉና ገና በማህፀን ያሉ ጨቅላዎችን ጨምሮ ብዙዎች በተለያየ ምክንያት ሀገርን ጥለው እየተሰደዱ ነው፡፡
በህገ ወጥ መንገድ ሲወጡ የሚደርስባቸው መከራ ተቃቁመው ካሰቡት የሚደርሱት ጥቂት በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡አይደለም በህገ ወጥ መንገድ የወጡት ቀርቶ በህጋዊ መንገድ እንኳን የወጡት በየ ሰው ቤቱ ስንቱን መከራን የሚያስተናግዱ ብሎም እስከ ህይወት ማጣት የደረሱ እንዳሉ አለም የሚክደው አይደለም፡፡
በወር ሲበዛ በሁለት ወር ጀልባ በሱማሊያ አልያም በሊቢያ ባህር ይሰምጣል ብዙ እንጀራ ፈላጊ ወገኖችን ይዞ፡፡ታድያ ሁሌም ከከንፈር ምጥጫ የዘለለ አይደለም ሀዘን መግለጫን፡፡ይህንንማ ወገናችን ያልሆነው አረብም ሆነ ሌላው ማህረሰብ አልነፈጋቸውም፡፡
አንዳንዴ ምነው ፈጣሪ ጨከነብን እልና አስባለው፡፡ እራሴ ስመልሰው ምን አልባት መሰደዳችን ልክ ሳይሆን ቀርቶ ይሆን? መከራው በእኛ የበረታው ስል በመሰደዳችን ፈጣሪ ደስተኛ እንዳልሆነ መልስ አገኛለሁ፡፡ታድያ ያ ደግሞ አያፅናናኝም፡፡ በእርግጥ አንድ ሁሌም በአእምሮዬ ጥያቄ የሚሆንብኝ ነገር አለ፡፡

በየጊዜው ጀልባ ብዙዎችን ይዞ ሲሰምጥ የተለያየ ሀገር ስደተኛ በዛ ጀልባ ላይ ተሳፋሪ ቢሆኑና አደጋው እነርሱንም ቢያሳትፍ 70 ከመቶ የሚሆነው ግን ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ነው፡፡
ዋናው የዘውትር የህሊናዬ ጥያቄ ወደ ሆነው ቁምነገር ልምጣና ብዙ ጊዜ አውሮፕላን ሲከሰከስ በሀገሪቷ የሀዘን ቀናትና በንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ይደረጋል፡፡ ለዚህም የቅርብ ጊዜው ከቤሩት ሲነሳ ሚድትራንያን ባህር ላይ የተከሰከው አውሮጥላን በዋናነት መጥቀስ አስፈላጊ ነው፡፡ ታድያ የባንዲራው ዝቅ ብሎ መውለብለብና የሀዘን ቀን መታወጁ ለአውሮትላኑ ወይስ በውስጡ ለነበሩ እንጀራ ፍለጋ ተሰደው በአረብ እጅ ህይወታቸው ሳይጠፋ በአውሮፕላን መከስከስ ለሀገራቸው ምድር ሳይደርሱ ለቀሩ ወገኖች?
እውነት ለዜጎቹ ከሆነ የሀዘን እወጃው ዛሬስ በየ በህሩ ጀልባ በሰመጠ ቁጥር በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በሚያልቁበት ወቅት ለምን የሀዘን ቀን አልታወጀም? ነው ወይስ ጀልባው የኢትዮጵያ ንብረት መሆን ነበረበት የሀዘን ቀን ለማወጅ፡፡
ለምንስ አንዲት ደቂቃ አንገት ተደፍቶ የህሊና ፀሎትና የሻማ ማብራት ስነ ስርአት አልተደረገም ወገናዊነትን ለመግለፅ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on August 27, 2014
  • By:
  • Last Modified: August 27, 2014 @ 6:43 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar