#Ethiopia #Amhara #Gojjam #AEUP #EPRDF #MinilikSalsawi
ከ80 እና 90 እድሜ ባለጸጋ ሴት መነኩሴ አዛውንቶች ሳይቀር እሰር ቤት ውስጥ በአሸባሪነት እየተሰቃዩ ነው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በአማራው ክልል ከፍተኛ የፍርሃት ውጥረት ውስጥ የሚገኘው ወያኔ በምስራቅ ጎጃም እነማይ ወርዳ ወይራ ቀበሌ 30 ሰዎች ወደ ወህኒ መውሰዱ ታውቋል፡፡ በዚሁ ዞን የእነማይ ወረዳ ነዋሪዎችን ድብቅ መሳርያ ደብቃችሃል በሚል በማንገላታት እና በማሰር ብወያኔ ሃይሎች በግፍ እየተሰቃዪ ነዉ፡፡ የመኢአድ የወይራ ቀበሌ ተጠሪ አቶ ይታያል ጋሻዉ እንደገለጡት በአሸባሪነት ታስረዉ ከሚስቃዪት መሃል የ80 እና የ90 ዓመት ኣዛዉንት የሆኑት እሙሃይ ጦቢያዉ ዘለቀ እና እሙሃይ እቴነሽ ባየ ይገኙበታል፡፡
ወያኔ በአዲስ መልክ የጀመረው የትጥቅ ማስፈታት እንቅስቃሲ አማራውን በከፍተኛ ደረጃ እያንገላታው ሲሆን ከምርጫው ቀድሞ ልድምጽ መታጣት ያስፈራሉ የሚባሉትን የአከባቢው የሃገር ሽማግሌዎች እና የተቃዋሚ አመራሮችን እያደነ በማሰር ላይ መሆኑ ይታውቃል።
=======================================================
ሃብታሙ አያሌው ፣የሺዋስ አሰፋ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃ ደስታ በጠበቆች እንዳይጎበኙ ተከለከለ።
#Ethiopia #Blueparty #UDJ #EPRDF #AEUP #Ginbot7 @SemayawiParty
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙት የሽዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ በጠበቃቸው እንዳይጎበኙ መከልከላቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የማዕከላዊ ምርመራ ታሳሪዎቹ በሳምንት ሁለት ቀን (ረዕቡና አርብ) በጠበቃቸው እንዲጎበኙ ፈቅዶ የነበር ቢሆንም ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ደንበኞቻቸውን ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደ ማዕከላዊ አቅንተው ሳያገኟቸው ቀርተዋል ተብሏል፡፡
ተማም አባ ቡልጉ ወደ ማዕከላዊ ባቀኑባቸው ቀናት ‹‹ሌላ ቀን ታገኛቸዋለህ፣ ስብሰባ ላይ ነን›› እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች እያቀረቡ ቀኑን ሙሉ ሲያስጠብቋቸው እንደነበርና በተለይ በዛሬው ቀን ነሃሴ 23 ደንበኞቻቸውን ለማግኘት እየጠበቁ ከዋሉ በኋላ ‹‹ከፈለክ ችሎት ላይ ታገኛቸዋለህ፡፡ ከዚህ ማግኘት አትችልም›› ተብለው እንደተመለሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹ታሳሪዎች በጠበቃቸው፣ በኃይማኖት አባታቸው፣ በጓደኛና በዘመድ የመጎብኘት መብት አላቸው፡፡ በሳምንት ይህን ቀን ተብሎ በህግ አልተወሰነም፡፡›› በሚል በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ ነው የሚጎበኙት መባሉም ስህተት ነበር ያሉት አቶ ይድነቃቸው ‹‹ጭራሹን እንዳይጎበኙ መደረጉ ደግሞ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ህገ ወጥ ድርጊት ነው›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
Average Rating