www.maledatimes.com አሳዛኝ ዜና ከሚስቴ አንደበት!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አሳዛኝ ዜና ከሚስቴ አንደበት!!

By   /   August 29, 2014  /   Comments Off on አሳዛኝ ዜና ከሚስቴ አንደበት!!

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 57 Second
ሙንትሃ ሸረፋ 
አሳዛኝ ዜና ከሚስቴ አንደበት!!
(ሁላችሁም ልታነቡት የሚገባ)
_____________________

ሩቂያን እወዳታለሁ!! የልጅነት ፍቅረኛዬ ነች። ሳቋን መስማቴ ብቻ እድሜዬን ይጨምርልኛል። ነብሴን ያለመልምልኛል። የፊቷን ገፅታ ስመለከት ድህነቴን እረሳለሁ። በለስላሳ እጇ ስትዳብሰኝ ክፉ ህመሜ ይፈወስልኛል። ጫወታዋ ኑሮን ያደምቃል። ቀልዷ አመት ያስቃል።

ትዳር መስርተናል። ትዳር ከመሰረትን የሚቀጥለው ወር ድፍን አንድ አመታችን ነው። “በህይወትህ ስንቴ እድለኛ ሆነሃል?” ተብዬ ብጠየቅ “አንድ ጊዜ ብቻ። አሱም ሩቂያ የምትባል ፍቅር የሆነች ሴት ከእኔ ጋር በመሆኗ” እላለሁ።

ለሳምንት ያህል ለስራ ጉዳይ ወደ አፋር ሄጄ ነበር። ናፍቆቱ እያንገበገበኝ ነው። ለስራ ወደአፋር ከሄድኩ ጀምሮ ሩቂያን ማታ በህልሜ ያላየኋት ቀን የለም። ቀን ደግሞ በአይኔ ውልብ ሳትል ውላ አታውቅም። ዛሬ ግን ስራዬን ጨርሼ ወደ አዲስ አበባ እየተመለስኩ ነው። ውዷ ባለቤቴን አገኛታለሁ። የሳምንት ናፍቆቴን አበርዳለሁ።(መኪናው ቶሎ ቶሎ አይሄድም እንዴ?።ቀርፋፋ!!)

ደረስኩ!! እቤቴ ደረስኩ!! ውዴን ሩቂያን ሳያት ድካሜ ሁሉ ብ…ን ብሎ ጠፋ። ፊቴ ፈ…ካ!! በቃ የሩቂያን ጠረን ስምግ እያጠረ ካለው እድሜዬ ላይ አስር አመት የጨመረ ይመስለኛል።

ተንደርድሬ ልስማትና ላቅፋት ሁለት እጄን ዘርግቼ ስቀርባት “ቁም!” ብላ ጮኸችብኝ። ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ። ወደ እኔ ቀረብ ብላ በዚያ በለስላሳ እጇ መዳፍ ጉንጬን ቀስ ብላ አሸቺው። ደስ አለኝ!! አይኔን ጨፍኜ ከዚህ ቀጥሎ ልንሰራው የምንችለውን የፍቅር ጫወታ በአይነ ልቦናዬ ሳልኩት። አ…ቤ…ት ተንገበገብኩ።

በዚህ ምናባዊ ደስታ ውስጥ እያለሁ ሳላስበው በድንገት የባለቤቴ ለስላሳ እጆች ጉንጬን ከማሸት ወደ አካፋነት ተለውጠው ፍፁም የማይረሳና ከልብ የማይጠፋ ጥፊ አላሰቺኝ። (በጥፊ የመታኝ የባለቤቴ የሩቂያ እጅ ብቻ ነው ወይስ የታይሰን እጅም ተጨምሮበታል!? ያጠራጥራል። እኔ የባለቤቴን እጅ ልስላሴ አውቀዋለዋ!!)። በጥፊ የተቃጠለውን ጉንጬን እያሸሁ ባለቤቴን አስቆጥቶ በጥፊ ያስመታኝን ምክንያት ምን ይሆን ብዬ ብዙ ሐሳብ ማሰብ ጀመርኩ።

ምናልባት ሐሰን “ከሌላ ሴት ጋር ሲማግጥ አየሁት” ብሎ ነግሯት ይሆን?(ይወዳት ነበር። ቀድሜው ነው እንጂ!)

ምናልባትስ ለሳምንት ያህል ብቻዋን ጥያት ስለሄድኩ ተናዳብኝ ይሆን?

በዚህ መሐል “ፍቅሬ!” የሚለው የሩቂያ ተስረቅራቂ ድምፅ ከትካዜዬ አባነነኝ።”ለምን በጥፊ እንደመታሁ ገብቶሃል” አለቺኝ ፊቷ ላይ ፍፁም የሆነ ደስታ እየታየ።

“ለምንድነው የመታሺኝ” አልኳት (በስጨት እያልኩ ነው።)

“ደስ ብሎኝ እኮ ነው!”

“አረገዝሽ እንዴ” (በጉጉት)

“አይ እርግዝና አይደለም”

“እና ምንድነው ያስደሰተሽና እኔን ልትደበድቢ የተነሳሽበት የደስታ ምክንያት”(አሁን አይኔ ሁላ የሰው ሳይሆን የአውሬ ሆኗል)

“ምን እንደሆነ ታውቃለህ!? አንተ ከዚህ ቤት እግርህን ካወጣህ ጀምሮ መብራት ሄዶ ቤታችን ጨለማ ነበር። ልክ አንተ አሁን የጊቢውን ደጅ ስትረግጥ መብራቱ ለሳምንት ከሄደበት መጣ። እና መብራት ስለመጣ በደስታ ሰክሬ ነው በጥፊ የመታሁ።” ብላ የታፈነ ሳቋን እስከጣራ ድረስ አፈነዳችው።

ሙታንን የሚቀሰቅስ ሳቋን ስሰማ የጥፊው ህመምና ሰንበር ሁሉ ጠፋ፣ መከፋቴ ተነነ፣ ይበልጥ ውዴን አፈቀርኳት፣ አቀፍኳት፣ሳምኳት በሳቅ እየተፍነከነክን ወደ አልጋችን ሄደን የአምፖሉን ብርሃን ለማጥፋት እጄን ስዘረጋ ኤልፓ ቀድሞኝ መብራቱን አጠፋው።

ኤልፖ የስራህን ይስጥህ!! የሞቀው ፍቅሬ ላይ በረዶ ቸልሰህ አቀዘቀዝከው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on August 29, 2014
  • By:
  • Last Modified: August 29, 2014 @ 11:35 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar