___________________
መገናሳ ጎረቤቴ ነው። የሀብታም ልጅና በእውቀት የታጨቀ አህምሮ ነበረው። የዚያ እውቀቱ የመጨረሻ ውጤት ግን አሳበደውና መገኛው አማኑኤል ሆስፒታል ሆነ።
መገናሳ አንድ ጊዜ ጥርሱን እስኪደክመው ጫት ቃመ። ሳንባው እስኪነካ ድረስ ሲጋራ አጨሰ ። አስካሪ መጠጥ ቂጡን ደፍኖ ጠጣ(ሞልቶ እንዳይፈስ)። ግን አንድ ቀን ሰክሮ ተወላግዶና ወድቆ አያውቅም።
መገናሳ ከቤተሰቡ ጋር ነው የሚኖረው። ታዲያ ሁል ጊዜ ቤቱ የሚደርሰው ለሊት ስለሆነ በር ከማንኳኳት ብሎ የግንቡን አጥር ዘሎ ነው ወደጊቢው የሚገባው። ታዲያ ዘወትር በግንቡ አጥር ወደቤቱ ዘሎ ከመግባቱ በፊት ያስለመደው አንድ ልም…ድ አለ። የመጨረሻውን የሚያጨሰውን ሲጋራ የግንቡ አጥር ጫፍ ላይ ሆኖ ያጨሰዋል። ከዚያም ተጭሳ ያለቀችውን ሲጋራ ወደ ውጪ ጥሎ እሱ ደግሞ ወደቤቱ ጊቢ ውስጥ ይወድቃል። ይቺ ልምዱን ሁልጊዜ ነው የሚተገብራት። ሲያደርገው እርካታ የሚያገኝበት ልምድ። ካላደረገው ቅር ቅር ይለዋል!!
አንድ ጊዜ ግን ቀኑን ሙሉ ኃይለኛ ጫት ሲቅም ነበር የዋለው። መጠጡንም ከልኩ በላይ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር። ከዚያም እንደምንም ብሎ የጊቢያቸው የግንብ አጥር ጫፍ ላይ ወጣ። እንደለመደውም የግንቡ ጫፍ ላይ ሆኖ የመጨረሻውን ሲጋራ አጣጥሞ አጨሰ። ሲጋራውን ካጨሰ በኋላ ግን ሁልጊዜ እንደሚያደርገው ያጨሳትን ሲጋራ ወደ ውጪ ጥሎ እሱ ደግሞ ወደ ግቢው አልገባም። የሆነው ነገር ፍፁም ተቃራኒ ነበር። መጨረሻ ያጨሳትን ሲጋራ ወደ ጊቢው ውስጥ ጥሎ እሱ ደግሞ ወደውጪ ወደቀ!!
እኔም ጧት ወደስራ ለመሄድ ከቤት ስወጣ መገናሳ ከአጥሩ አጠገብ ባለው ትቦ ስር ዘና ለጠጥ ብሎ ለሽሽሽ ብሏል።
እኔም “መገናሳ” ብዬ ልቀሰቅሰው ብል አይኑን እንደጨፈነ “ብርድ ልብስ ለምንድነው ያላለበሳችሁኝ? አንተ አሁን ወንድሜ ነህ!? ደመኛዬ ነህ!! የማትረባ ነህ እሺ!!” ይለኛል።እኔም በንግግሩ በሆዴ እየሳቅሁኝ “መገናሳ እኔ ወንድምህ አይደለሁም። ጎረቤትህ ነኝ። አሁን እኮ ያለኸው ቤት ውስጥ ሳይሆን ትቦ ውስጥ ነው” ብዬ ጉዶን አረዳሁት። እሱ ሆዬ ገና ስካሩ አለቀቀውም መሰለኝ በስካር ስሜት ውስጥ ሆኖ “በቃህ! አሁን ጆሮዬ ላይ አትለፍልፍብኝ። በጣም ነው የበረደኝ ስለዚህ የአባቢን ብርድልብስ ደርበህ አልብሰኝና የመኝታ ክፍሌን በር ዘግተህ ውጣልኝ!!!!” ብሎ ጮኸብኝ።
እኔም ለቤታቸው ሰራተኛ ትቦ ውስጥ ለተኛው መገናሳ ብርድ ልብስ እንድትደርብለት ነግሬያት ወደስራዬ ሄድኩኝ።
“ከመጠጥ ደስታ ይገኛል ብላችሁ
መጠን አትለፉ ትቃጠላላችሁ” lol
Average Rating