_________________
በጣም ነው የምወዳት ከህይወቴ አስበልጬ!! የእኔ እስትንፋስ መኖሮና እንደሰው ቆሞ መንቀሳቀስ የእሷ ታላቅ አስተዋፅኦ አለበት። ያለሷ ህይወቴ ባዶ ነበር የሚሆነው ። የመኖርን ትርጉም ያወቅሁት በሷ ነው። አንድ ጊዜ በትንታ ከመሞት አድናኛለች። ስቆሽሽ አጥባ አፅዳታኛለች። የደረቀ ከንፈሬን አለስልሳልኛለች። ከፈጣሪ ቀጥሎ የእሷ መኖር ለእኔ ግድ ነው። ህይወቴ ላይ የመወሰን ሙሉ መብት አላት!!
አሁን ግን ከአጠገቤ ከተሰወረች ይኸው ወራቶች ተቆጠሩ። ብዙ ቦታ ፈለግኳት የለችም። የአዲስ አበባ ሰፈር፣ቅያስ፣መንደር፣ጉራንጉር፣ ሻይ ቤት፣ስጋ ቤት፣ትልልቅ ሆቴል፣በመንግስት መስሪያ ቤት፣በ…ግል መስሪያ ቤት………ያልፈለግኳት ቦታ የለም። ፈልጌ አስፈልጌ አጣኋት። ለብዙ “ቁልፍ” ለሚባሉ ሰዎች ራሱ ፈልገው ያመጡልኝ ዘንድ ጉቦ ሰጥቼ ነበር። ግን ይኸው የበላት ጅብ አልጮህ አለ።
አሁንስ በጣም ናፍቃኛለች። ምንም ነገር እንደዚህ ናፍቄ አላውቅም። እንድበላው የቀረበልኝን ምግብ ከጉሮሮዬ አልወርድ እያለ አንድም ጉርሻ ሳልጎርስ እመልሰዋለው። ይኸው እሷን ብቻ እያሰብኩኝ እራሴን ጥያለው። እሷ ከጠፋች ጀምሮ አካላቴን አንፅቼ አላውቅም። እሷ ከጠፋች ጀምሮ የለበስኩትን ልብስ ሰውነቴ ላይ እንደተሰፋ ሁሉ አልቀየርኩትም። ቆሻሻውና እድፉ ሰው በሩቁ እንዲሸሸኝና እንዲፀየፈኝ ያደርጋል።
ለወራት በመጥፋቷ ምክንያት ነው መሰለኝ እንደምወዳትና እንደምናፍቃት ታወቀኝ፣ተገለጠልኝ!! ማንንም በህይወቴ እንደሷ ናፍቄ አላውቅም። ማንንም!!
:
:
:
:
:
:
ውሃ!!
ኧረ! ባክሽ ልለምንሽ የኔ ውድ ውሃዬ ተመለሺ!!
ውሃ ሆይ ናፍቀሺኛል።
ውሃ ህይወቴ እኮ ነሽ!!
ውሃ የመኖሬ ምስጢር እኮ ነሽ!!
ውሃዬ ምግቡም ካላንቺ እኮ ከጉሮሮዬ አልወርድልህ አለኝ።
ውሃ ያለ አንቺ እንዴት መኖር ይቻለኛል? በፍፁም!!
ውሃዬ በእናትሽ
ውሃዬ በአባትሽ
ውሃዬ በምትወጂው ሁሉ ይሁንብሽ……ለወራት ከጠፋሽበት እስቲ ብቅ በይና “አለሁ…መጥቻለው …ሁሌም ካንተ ጋር ነኝ” በይኝ!!
ኦ! ውሃ
ኦ! ውሃ
ኦ! ውሃ
Average Rating