ጌታቸው ሺፈራውባለፉት አራት ወራት ብቻ 17 ጋዜጠኞች አገር ጥለው የተሰደዱ ሲሆን 12 ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ከአገር መውጣታቸው ይታወቃል፡፡ ባለፈው ሳምንትም ውስጥም ተጨማሪ ሶስት ያህል ጋዜጠኞች አገር ጥለው ተሰደዋል፡፡ በመሆኑም አገር ጥለው የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 20 ደርሷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ገዥው ፓርቲ ከሚወስደው አፈና፣ የማተሚያ ቤትና ሌሎችም ችግሮች ተዳምረው የስደተኛ ጋዜጠኞች ቁጥር ከዚህም እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል፡፡ በቅርብ የተሰደዱት ጋዜጠኞች የደህንነት ሁኔታ አንጻር ስማቸውን መጥቀስ አልፈለኩም፡፡
እስካሁን አገር ጥለው የተሰደዱ ጋዜጠኞች ስም ዝርዝር
1. ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ (የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ፕሬዝደንት፣ የኢቦኒ መጽሄት አምደኛ፣ የአሳማን መጽሄት ኮረስፖንዳንት፣ የዳይሊ ጆርናሊስት ቋሚ ጸሃፊ፣ የኢካድፍ ፎረም ጸሃፊ፣ የኢትዮጵያ ሆት ክለብ ብሎገር)
2. ጋዜጠኛተሰማ ደሳለኝ (የኢቦኒ መጽሄት ማኔጅንግ ኢዲተር)
3. ዘሪሁን ሙሉጌታ (የሰንደቅ ጋዜጣ ከፍተኛ ሪፖርተር፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ የህዝብ ግንኙነት)
4. መላኩ አማረ (የሊያ መጽሄት ማኔጅንግ ኢዲተርና ባለቤት)5. ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ (የሎሚ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
6. ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው (የአፍሮ ታይምስ ማኔጅንግ ዳይሬክተር)
7. ጋዜጠኛ ሰብለወርቅ መከተ (የሎሚ መጽሄት ከፍተኛ ሪፖርተር)
8. ጋዜጠኛ አቦነሽ አበራ (የሎሚ መጽሄት ከፍተኛ ሪፖርተር)
9. ጋዜጠኛ ሰናይ አባተ (የሎሚ መጽሄት ዋና አዘጋጅ)
10. ጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ (የጃኖ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
11. ጋዜጠኛ ሲሳይ ሳይሌ (የፒያሳ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ባለቤት)
12. ጋዜጠኛ እንዳልካቸው ተስፋዬ (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የሮዝ አሳታሚ ድርጅት ስራ አስኪያጅ)
13. ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ምክልት ዋና አዘጋጅ)
14. ጋዜጠኛ እንዳለ ተሺ (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ከፍተኛ አዘጋጅ)
15. ጋዜጠኛ ሀብታሙ ስዩም (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት አምደኛ፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ገንዘብ ያዥ)
16. ጋዜጠኛ ዳዊት ሶሎሞን (የፍኖተ ነጻነት አዘጋጅ፣ የላይፍ መጽሄት ዋና አዘጋጅ፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ አመቻች ኮሚቴ አባል)
17. ዳንኤል ድርሻ (የሎሚ መጽሄት ሚዲያ ዳይሬክተር)
18. በቅርቡ የተሰደዱት ሶስት ጋዜጠኞች
Average Rating