www.maledatimes.com የወያኔኢሕአዴግ ተላላኪው የዳላሱ ወጣት ኢብራሂም ሲራጅ ማን ነው? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የወያኔኢሕአዴግ ተላላኪው የዳላሱ ወጣት ኢብራሂም ሲራጅ ማን ነው?

By   /   September 4, 2014  /   Comments Off on የወያኔኢሕአዴግ ተላላኪው የዳላሱ ወጣት ኢብራሂም ሲራጅ ማን ነው?

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 20 Second

“ጉድ በል ጎጃም አለ ያገሬ ሰው!”

በሚሊዮን ኢትዮጵያ(ከዳላስ)

ወያኔ/ኢሕአዴግ በውጭ ሃገር የሚኖሩት ኢትዮጵያውያንን ለማደራጀት የሚያስችላቸውን የጥፋት ውጥን በመወጠን ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል ተወልደውያደጉ ለሆዳቸው ያደሩ አደርባዮችን በመመልመል የቤት ስራውን እየሰራ ይገኛል። አያሌ ኢትዮጵያውያን የስርአቱን አስከፊነት በመገንዘብ ሳይወዱ በግድ የሚወዱት ሃደራቸውና ሕዝባቸውን ትተው ቢሰደዱም እንኳን እስካሉበት የስደት ሃገር በመከተል የከፋፍለህ ግዛ መሰሪ ፖሊሲያቸውን ለማስፈጸም በፖሊሲ ደረጃ በመንደፍ የጥፋት ተግባራቸውን ገፍተውበታል። በዚህም መሰረት ምንም እንኳን እዚህ ገቡ የሚባሉ ቁጥር ያላቸው አባላት ማፍራት ባይችሉም ጥቂት ርካሽ ተውዳጅነት ለማትረፍና የግል ንዋይ ፈላጎታቸውን ለማሟላት ከመራሹ መንግስት ጋር በመተባበር ህዝብን ለማወናበድና ለማታለል የሚተጉ ግን አልጠፉም። ኢብራሂም ሲራጅ ከእነዚህ በጥቅም ከተደለሉትና የመሰሪው የወያኔ መንግስት ተልእኮ ለመወጣት ሌት ተቀን ደፋ ቀና ከሚሉት አንዱ ነው።
ዳላስ በወያኔ መሰሪ ተባባሪዎች እጅ ወድቃለች ማለት ባይቻልም እነዚህ ጥቂት ርዝራዦት በኮሚኒቲ፣ በቤተክረስቲያንና በሌሎችም ኢትይጵያዊ በሆኑት ተቓማት እጃቸውን በማስገባት ቀላል የማይባል የጥፋት ተልዕኮአቸውን ለመወጣት ሌት ተቀን ደፋ ቀና እያሉ ለቱባ የወያኔ አለቆቻቸው ታማኝ ለመሆን ተግተው ይሰራሉ። ምንም እንኳን በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አላማቸውን ማሳካት ባይችሉም። የጥፋቱ ሰለባ ከሆኑት ኢትዮጵያዊ ተቓማት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያንና(http://www.stmichaeleoc.org/) በዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የጋራ መረዳጃ ማህበር(http://maaecdallas.org/) ዋና ተጠቃሽ ናቸው። በእነ አቶ ተፈራወርቅ(ጋሻው ኢንሹራንስ) የሚመራው የጥፋት ቡድን አማካኝነት ቤተክርቲያኒቷን ፍርድ ቤት ሶስት ጊዜ በመክሰስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮች ወጪ ዳርገዋል። ኮሚኒቲውም ምርጫ በመጣ ቁጥር የወያኔ ጀሌዎቻቸውን ለማስረጽ ህዝብን በማወናበድ ላይ ይገኛሉ። ከወራት በኳላ የሚደረገውን የመራዳጃው ማህበር የቦርድ አባላት ምርጫ ላይ የወያኔ አባላትን ለማስገባት ተጽዕኖ ለመፍጠር የቤት ስራቸውን እየሰሩ ናቸው። ይህ እውነታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሁሉም የኮሚኒቲው አባላት ኮሚኒቲው በወያኔ እጅ እንዳይወድቅ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ሊታደገው ይገባል።
እነዚህ የጥፋት ሃይሎች እራሳቸውን “ሰበቡ” የሚል ስያሜ በመስጠት በእነ ተኮላ፣ ደምመላሽ፣ ተፈራወርቅና ሌሎችም መሪ ተዋናይነት የሚመራ ሲሆን ሁሌም ምክንያት እየፈጠሩ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮ በተነጠቀ በወያኔ በተመደበላቸው ባጀት ስጋዊ ፍላጎታቸውን የሚያስደስቱ ለሌላው ግድ የሌላቸው ህሊናቸው የሸጡ አገርና ሕዝብን የካዱ የግል ጥቅማቸውን ብቻ የሚያዩ ስንስቦች ናቸው። የማህበሩ አባላት ለሚሰሩት የጥፋት ተልዕኮ ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በትውልድ ቀዬያቸው በህገ ወጥ መንገድ ከድሃው ምስኪን የሃገሬ ገበሬ መሬት እየተነጠቀ ለውለታቸው የመኖሪያና የንግድ ቦታ መስሪያ ይሰጣቸዋል። ኢብራሂም ሲራጅ የዚህ ማህበር ተላላኪ እንደመሆኑ መጠን የጽዋው ተቓዳሽ በመሆን በባህር ዳር ከተማ ሲኒማ ቤት መስሪያ ቦታ ለውለታው ተችሮታል። እነዚህ የጥፋት ሃይሎች ኢትዮጵያውያን በሚሳተፉበትና የገቢ ማሰባሰቢያ ቦታዎችን በመገኘት ወያኔኢሕአዴግ ለዚህ ተግባር በተመደበውብ ባጀት በመለገስ ሕዝብን ለማወናበድና የኮሚኒቲው ተቆርቓሪ ለመምሰል ይጥራሉ።
የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ፕላን(GTP) በተመለከተ የወያኔ/ኢሕአዴግ ቱባ ባለስልጣናት ወደ ሰሜን አሜሪካ በመጡበት ወቅት ምንም እንኳን ጥሪው ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚመለከት ቢሆንም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለመታደም ግን አልታደሉም። ስብሰባው ለመታደም የተዘጋጀበት ስፍራ ብሄድም ውይይቱን ለመካፈል ከተነፈጉት አንዱ ነኝ። የኢትዮጵያ ጉዳይ የሁሉም እንጂ የወያኔ አባላት ብቻ አለመሆኑን እይርታወቅ ስብሰባውን ለጥቂት አባሎቻቸው ብቻ በደብዳቤ በመጥራት ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደብዳቤ የላች ሁም በማለት ወደ ስብሰባ አዳራሹ እንዳይገቡ ተደርገው በፖሊስ እንዲባረሩ ተደርገዋል። በዚህ ወቅት እንዳይገቡ የተደረጉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሲያሰሙ ለወያኔ የደህንነት አባላት የሚላክ ቪዲዮ በመቅረጽና ተቃውሞ እያሰሙ በነበሩት በመሳለቅ ኢብራኢም ሲራጅ ለወያኔ ታማኝነቱን አሳይቷል። ይህ ደግሞ ከሃገርና ህዝብ ክህደት በተጨማሪ ለዲያፖራው ማህበራሰብ ያለው ንቀት ምን ያህል እንደ ሆነ ያሳያል።
ኢብራሂም ሲራጅ በሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌደሬሽን(ESFNA) ዳላስን ወክለው ከሚጫወቱት ሁለት የስፖርት ክለቦች አንዱ በሆነው ኢትዮ ዳላስ ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ላለፉት 11 አመታት ስጫወት ነበር ብሎ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጠው ቃለ መጠየቅ በፍጹም ከውነት የራቀ መሆኑን ቡድኑ ውስጥ ከሚጫወቱት አባላት ለመረዳት ችያለሁ። ለነገሩ መች ኢቲቪ እውነት አውርቶ ያውቅና። ወያኔ ማለት የውሸት ከረጢት መሆኑን ከታወቀ ውሎ ሰንብቷል። ነገር ግን ቡድኑ አባላት ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባት እጁን በማስገባት ከጀርባ በመሆን ለሁለት እንዲከፈሉና ልዩነታቸው በሰላም እንዳይፈቱ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል። ወጣቶቹ ችግራቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከማድረግ ይልቅ ከዋናው ቡድን እራሳቸውን ላገለሉት አባላት የቅርብ ጓደኞቹና ዘመዶቹ በመመልመል የጥፋት ሴራውን ሲሸርብ ነበር። ምንም እንኳን ያሰበው አላማ ባይሳካለትም የመጨረሻ ግቡ ግን ወጣቶቹን በጥቅም በመደለል የዛሬ ሁለት አመት ገደማ በአብነት ገመስቀል መሪ ተዋናይነትና በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ ለተቓቓመው የስፖርት ማህበር ለማስረከብ ነበር።
ኢብራሂም ሲራጅ በአሁን ሰአት ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ ቴሌቪሽን በእንግዳ ፓሮግራም በተደረገለት ቃለመጠየቅ ኢትዮጵያ ውስጥ የማይካድ ለውጥ አለ፣ በውጭ ኃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስለ ልማቱ የሚናገሩትን አልሰማም፣ ወያኔኢሕአዴግ በሚያደርጋቸው ሁሉም ስብሰባዎች መሪ ተዋናይ ነኝ፣ የፖንድ ሽያጭና በቅርብ የማውቃቸው አቅም ያላቸው ኌደኞቼን በማስተባበር ላይ ግንባር ቀደም ነኝ ይለናል። በዚህም አንባገኑ የወያኔ ስርአትን ቀንደኛ ደጋፊ መሆኑና መራሹ ወያኔ ልማታዊነት ምስክርነት ይሰጣል። ውሸታሙን ኢቲቪንና ወያኔን እውነትነት አስረግጦ በመናገር የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ውሸታም መሆኑን ይነግረናል። ይህ ደግሞ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ያለው ንቀት ያሳያል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንባገነኑ ስርአት ለእስራት፣ ለስደት፣ ለሞት፣ ለረሃብ፣ ለእንግልትና ለስቃይ እየተዳረገ ባለበት ሁኔታ ወያኔን ማሞካሸትና ልማታዊነት መመስከር የህሊና ዳኝነት የጎደለው ከመሆን ውጪ ምን ይሉታል። ለመሆኑ ወያኔ የሚለውን የሚያስተጋባለትን እንጂ መች ሕሊና ያለው ሰው ይፈልግና።
ጀግናው በላይ ዘለቀ ያፈለቀችው ጎጃም ኢብራሂም ሲራጅ አሳድጋለች የናት ሆድ ዥንጉርጉር ይሉታል ይህ ነው። አንዱ የባህርዳር አንድ ክለብ የሚያሰነጥለው አብሮ አደጉ ስለ ኢብራሂም ሲራጅ ሲናገር ይህ ትልቅ ሃብታችን ነው ልንጠቀምበት ይገባል ብሎናል። ጀግናው በላይ ዘለቀ በተወለደበት ሃገር ሃገሩን ሽጦ ለሆዱ ያደረውን እንደ ሃብት ሲቆጠር ጉድ በል ጎጃም ማለት ይሄኔ ነው።
ውድ የሐገሬ ልጆች ሆይ ኢትዮጵያ ሃገራችን አንድነቷና ዳርድንበሯ ጠብቃ ልትቆይ የቻለችው ብዙ የደም መስዋዕትነት ተከፍሎባት እንድሆነ ሁሉም ጠንቀቆ የሚያውቀው ስለሆነ እኔ ልነግራች ሁ አልሻም ለቀባሪ ማርዳት እንዳይሆንብኝ። ዛሬ ግን ወያኔና ግብራበሮቹ ይህን ታሪክ ለማጥፋት የዘር ፖለቲካ በመከተል ህዝቡን አንድነቱን እንዳይጠብቅ በማድረግ፣ የገዛ መሬታችን ለጎረቤት ሀገራት አሳለፎ በመስጠት፣ ምስኪን ገበሬ በማፈናቀል ለውጭ ባለሃብት በመሽጥና ሌሎችም አያሌ መሰሪ ተግባራቸውን ገፍተውበታል። ወያኔ/ኢሕአዴግ ያለ ሕዝብ መልካም ፍቃድ ስልጣን በአፈሙዝ በማስፈራራት ቢቆናጠጥም ሕዝብ ያለመረጠው መንድስት ዘላቂነት ሊኖረው ስለማይችል ሰርጎገብ ከሆኑት የወያኔ ተላላኪዎች ሰላባ እንዳንሆን ነቅተን በመጠበቅ ማጋለጥ ይኖርብናል። የዚህ ጽሁፍም ዋናው አላማም ይህ ነው።
ኢብራሂም ሲራጅ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግዳ ፕሮግራም ያደረገው ቃለመጠይቅ እዚህ በመጫን ይመልከቱ! http://www.diretube.com/engeda/ebrahim-serag
አንድ ሕዝብ!!!
አንድ ኢትዮጵያ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም አንድነቷን ጠብቃ ትኑር!!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on September 4, 2014
  • By:
  • Last Modified: September 4, 2014 @ 3:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar