ስለ ቴዎድሮስ አፍሮ አንስተን ጥለን ብናወሳ ብዙ ነገሮችን መነጋገር አንችላለን:፡
ቲዲ አፍሮ በቅርቡ በሰባ ደረጃ የሚል አዲስ ነጠላ ዜማ በመልቀቁ ሁሉም ሰው ታራራም ታራራም እያለ ሃሳቡን በክራር ድምጽ መቃኘት ጀምሮአል ። በዚህ የቀድሞ ጽሁፍ ላይ አዳዲስ ሃሳቦቻችንን ጨምረን የቀድሞውን እንደነበረ አድርገን የቴዲ አፍሮን ስራዎች እና የጥበብ ሂደቶችን አብረን ማየትን ወደድን እና እስኪ እናንተም የበኩላችሁን ድርሻ ታደርጉ ዘንድ እኛ የራሳችንን እንበል። ቅኝት በሰባ ደረጃ በሰባ ደረጃ
በሰባ ደረጃ የሚለውን ሃሳብ ከምን ተነስቶ ምን ደረጃ ለመድረስ እንዳስቻለው ማሰብ እና መገመት የሚያቅተን አይመስለኝም ።ቴዲ አፍሮ እየዘመረለት ያለው ትልቅ ፍቅር ነው ።አንድ ሰው በፍቅር ልቡ ከታሰረ ብቻ ነው ማድረግ የማይችለውን ነገር ሊያደርግ ድፍረት የሚያገኘው የሚለው እውነታ ግልጽ እና ትክክለኛ ነገር ሲሆን በእነዚህ የዜማ እና ግጥም ውህደቶች ላይ ያነሳቸው የቀድሞ ታሪካዊ ቦታዎች ዛሬ ስማቸው እና ታሪካቸው ተረስቶ በአፍሪካ አገራት ስም ተሰይሞ የጥንትነት ታሪካቸው ደብዛው እንዲጠፋ ቢደረግም ቴዲ ግን በዝማሬው ታሪካቸውን አወድሶታል ። ፍቅረኛውንም በደረጃው በላይ አቁሞ የክራሩን ድምጽ ሊያስቃናት እንደሚሞክር እና እሷም የክራሩን መከርከር ስትሰማ ወደ እሱ ቀርባ ፍቅሩን እንድታጣጥም ይጋብዛታል ። እንዲህም እያለ ጥሪውን ያቀርባል »»»»»በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃዉ በፒያሳ አድርጌ
በፍቅር ማነቂያዉ ዶሮ እንዳይል በከንቱ እረ አንቺን ወዶ ..(ዶሮ ማነቂያ፣ ዕሪ በከንቱ)
ክራሩን ስትሰሚ ብቅ በይ ቆሞያለሁ ከበርሽ ማዶ ታዲያ እንዲህ እያለ የእለቱ ብርሃን ደብዘዝ ሲል በምሽቱ የዚያችን ውብ ድንቅ ዘበናይ ፍቅር የሚፈልገው ቴዲ ለምን ይሆን ? ልብኡ በፍቅር መራቡን የሚገልጽላት ወዘሪት የሰባ ደረጃን ደጋግሞ ቢወጣም ሊደክም እንደማይችል ይጠቁምላታል ታዲያ ይህን ወደ አልተፈለገ የፖለቲካዊ ፈለግ የሚወስዱ አንዳንድ ዜጎች ባይታጡም እውነታው ግን ፍቅርን በፍቅር ማግኘት የሚለው ሲሆን ስሜቱ የተወረሰው የፍቅር አውድማ ላይ ወድቆ መሸነፉን የሚያስይ ሲሆን ለዘመናይ ብቻ እጄን ሰጥቻለሁ ከዚህ በላይ ማንም አይደፍረኝም ባይ መሆኑን ያሳያል ። ለመሆኑ ለምን ዘበናይቱን እንደ አውራዶሮ ሊዞራት ፈለገ ?ለምንስ የክራር ድምጹን መረጠላት …የአርመን ዳቦስ የትኛው የአሁን ዘመን ልጅ ነው የሚያውቀው ?የሸዋ ዳቦን በልቶ ያደገ ልጅ የአርመን ዳቦ ምን እንደሆነ የሚያውቅ የለም ሆኖም ግን ምን ያህል ተወዳጅ እንደነበር እና የወቅቱ እንቡጥ እንደነበር ይገልጽበታል ።ሆኖም ግን ዜማዊ ቅላጼው ሁሉንም እውቀት እንዲያገኙ የሚያስዳሥሥ እንደሆነ ያሳያል ማንም ሰው ቢሆን ሰባ ደረጃን የሚያውቅም ሆነ ዶሮ ማነቂያን አለበለዚያም ተፈሪ መኮንን ድልድይን በእዝነ ህሊናው የማይቃኝ የለም ።ይህ ሙዚቃ ሰርጎ ገብ ሆኖ ፍቅርን በስሜት ውስጥ የሚዘራ ትልቅ መልእክት ያለው የዘፈን ግጥም ነው ። የዚህ ዜማ በእርግጥም አዲስ ባይሆንብንም ከተለያዩ የእራሱ እና የሌሎች ሰውችን ዜማ ቅንጥብጣቢ በማድረግ በአንድ ላይ በማዋቀር የሰራው ስራ ቢሆንም ይበልጥ እንዲወደድ አድርጎታል ።ምክንያቱም የተሰባበሩ ነገሮችን እንደ አዲስ ገጣጥሞ በአዲስ መልኩ ማሳየት የሚቻልበት ምእራፍ እንዳለ ያሳየናል ። እስኪ ግጥሙን ታነቡት ዘንድ እኛም ግብዣችን ይሁን ብለናል ።
ከመኮንን ድልድይ ከእንጨት ፎቁ በላይ
ሲመሽ እንገናኝ
መጣሁ አንቺን ብዬ ሳይከብደኝ እርምጃዉ
በሰባ ደረጃዉ
አዝማች፡
በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃዉ በፒያሳ አድርጌ
በፍቅር ማነቂያዉ ዶሮ እንዳይል በከንቱ እረ አንቺን ወዶ ..(ዶሮ ማነቂያ፣ ዕሪ በከንቱ)
ክራሩን ስትሰሚ ብቅ በይ ቆሞያለሁ ከበርሽ ማዶ
ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ
ማታ ማታ
ማታ ማታ
አምጣት ከጎኔ ትቀመጥ
እንጀራ አይቀርብም ካለወጥ
አቅፎ ገላዋን አልጠግብ ያለዉ
ማነዉ ካላችሁ ማነዉ ማነዉ?
ልቤ ልቤነዉ ልቤ እራብተኛዉ
እሏን ወዶ ሌት የማይተኛዉ
ይዉጣ ይዉጣ እግሬ ይዛል በእርምጃዉ
ከሏ አይብስም ሰባ ደረጃዉ
ዘበናይ ዘበናይ….
ሲመሽ ወደ ማታ ሁሉ ዘግቶ በሩን
ታም ታራም ሳረገዉ ብቅ በይ ክራሩን
ታም-ታራራም-ታራራም…..
ፀጉራን ተተኩሳዉ እንደ አርምዴ ሜሪ
ዘበናይ ናት ፍቅሯን በክራር ነጋሪ.
ታም-ታራራም-ታራራም…..
ሄዶ ከኮሪያ ዘማች ሲመለስ
ያወሳል ናፍቆቱን በክራሩ ድምጵ
ፍቅርሽ አስጨንቆ መላወስ አቃተኝ
ተደናበርኩልሽ ጥይት እንደሳተኝ
ሳተና ነበርኩኝ ተካሽ በመዉ ዘሬ
ለዘበናይ ብቻ እጄን ሰጠሁ ዛሬ
አዝማች
በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃዉ በፒያሳ አድርጌ
እንደ አውራ ዶሮ ክንፍ ኮቴን እየሳብኩት መሬት ለመሬት
በዞርኩት ገላሽን ሳትወጣብኝ ፀሀይ ሳይነጋብኝ ሌት
ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ
ማታ ማታ
ማታ ማታ
ሞልቶ በአራዳ የአርመን ዳቦ
ሳሳ አካላቴ ሰዉ ተርቦ
አቅፎ ገላዉን አልጠገብ ያለዉ
ማነዉ ካላችሁ ማነዉ ማነዉ?
ልቤ ልቤነዉ ልቤ እራብተኛዉ
እሏን ወዶ ሌት የማይተኛዉ
ይዉጣ ይዉጣ እግሬ ይዛል በእርምጃዉ
ከሏ አይብስም ሰባ ደረጃዉ
ዘበናይ ዘበናይ….
አይወጣም ደረጃ ቢፈጥን ሴሼንቶ
እንደኔ ካሌደ በፍቅር ተገፍቶ
ታም-ታራራም-ታራራም…..
መድፈሪያሽ ወርቅ ነዉ ብርም አይገዛሽ
ልብ የሌለዉ ሀብል ግድም አይሰጥሽ
ታም-ታራራም-ታራራም…..
ከአንገትሽ ላይ አርጊኝ እንደማርትሬዛ
ወደወዲያ እንዳልል አደብ እንድገዛ
ተከለከለ አሉ የንጉስ አዳራሽ
የክት ያለበሰ አይገባም በጭራሽ
መጣሁ ከኮሪያ ይዤልሽ ሰዓት
በፓሪ ሞድሽ ላይ አምርሽ ታዪበት
ዘበናይ ዘበናይ….
ግጥምና ዜማ፡ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
ሙዚቃ ቅንብር፣ ሚክሲንግ፣ ኪቦርድ እና ቤዝ ጊታር፡ ዳግማዊ ዓሊ
ናሙና ዝግጅት፡ አብርሃም ዘዉዴ
ክራር፡ ታመነ መኮንን
ድምጵ ቀረጳ፡ ክብረት ዘ/ኪዮስ
ፕሮዲዩስድ፡ በቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
ነገሩ ግን ወዲህ ነው በአንባብያን በኩል የአኔ የፅሁፍ ቁም ነገር አዘል ሃሳብ የታየው… አኔን ልክ አሱን በከፍተኛ ደረጃ አግዝፌ አንደማደንቀው ተቆጥሮ መታየቱ ብቻ ሲሆን ፍሬ ሃሳቡን ግን ከምን ደረጃ አና ምን ሰራ ለምን ቴዎድሮስ ስራዎቹ ሊወደዱለት እና በህዝብ ዘንድ ልብ ውስጥ ተቀብረው ቀሩ የሚሉትን ዳሰሳ በጥልቀት ለመመልከት አልቻሉም ፡፡
በእርግጥም ማንኛችንም ስህተቶችን ከመፈፀም አንርቅም እና አኔም ሆንኩ ሌሎች ሰዎች ከስህተት ከምንርቅበት የማንርቅበት ጊዜ ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል ሰለሆነም አኔም ካጠፋሁ ስህተቴን ልታርሙኝ ዝግጁ ነኝ አስተያየታችሁን በበጎም ሆነ በመጥፎ መልኩ ብላችሁ የምታሰቡት ነገር ለአኔ ግን ጥሩ ስለሚሆን ወደ ኍላ ባታስቀሩብኝ መልካም ነው አላለሁ ፡፡ የቀጣዩንም የቴዲ አፍሮ ጥራዝ አንዲህ አቅርቤዋለሁ መልካም ጊዜ……
ቴዎድሮስ ካሳሁን ዛሬ አንዲህ በቀላሉ ስሙን አንስተን የምናብጠለጥልበት ምክንያት ሁላችንም አንደምንረዳው ከሰራው ስራ አንፃር ስሙ በሃገራችን ከፍ ብሎ ሰለሚጠራ አና ስራዎቹ ከምንም በላይ ገነው በሰው ጆሮ እንዳይሰለቹ ተደርገው መሰራታቸው እና ለአያንዳንዳችን የተለያዩ ፋይዳ መስጠታቸው ሳይሆን እንዳልቀረ እገምታለሁ ፡፡ምክንያቱም የምንጠላው ሰው ቢሆን ኖሮ ስራዎቹንም አናደምጥም እሱንም ስሙንም አናንሰሳም ነበር ስለዚህ ክርክሩ ሊቀጥል ግድ ይላል ፡፡ አሁንም በተወሰነ መልኩ የስራዎቹን ዳሰሳ በማድረግ ወደ ህዝብ አስተያየት አና ጋዜጠኛ ግርማ ደገፋ ገዳ ወደ ሰጠኝ ምላሽ አቀናለሁ ፡፡
“ሞናሊዛ” በሚለው ሙዚቃው ላይ በሰራበት ወቅት ሁሉም ሰው በማድመጠ የተደመመበት እንደሆነ ትውስ ይለኛል እስካሁን ድረስ ያንን ዘፈን አድምጦ ስሜታዊነት መንፈሱን የማያድስ የለም ፡፡ ምክንያቱም አንደ ሌሎቹ አቀንቃኞች አርቲ ቡርቲ የበዛበት ፥አልያም እንደ ፈሊጣዊ ፍልስፍና ወደድኩሽ ጠላሁሽ አተካሮ ወይንም ውስጥ ገብቶ እራስንም ሆነ አድማጭን ከመበጥበት ይልቅ በትልቁ የጥበብ መንገድ ረጂም ጉዞ ተጉዞ ዘመናትን ተሻግሮ ከባህር ማዶ ርቆ በ1503–1519 እ.ኤ.አ በቀድሞው አዛውንት ሊዮናርዶ ዳቬንቺ በሸራ ተወጥራ በተሳለችው ላጆኮንዳ (ሞናሊዛ) ጥበባዊ ረቂቅ ምናባዊ ምትሃት ሲያቀነቅን የገበሬ ሚስት ስለነበረችው እና ለዚያ ምስል ሞዴል ስለሆነችው ማዶና ሊዝ ለምትባለው አንዲት ሴት ቁንጂና እና ዉበት ተስቦ ሊያንጎራጉርላት የሞከረ ሳይሆን ለሰኣሊው ጥበባዊ መናፍስት ካባውን የደረበላት መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ በእርግጥም የክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ካወረሰን ሞናሊዛዬ ነሽ ይለያል ፡፡
ሁለቱም የየራሳቸው የፍቅር ምትሃት ቢኖራቸውም ቴዎድሮስ ግን ማናባዊ ፍጥረት ከብራና ላይ ሰለሰፈረችው ከቡርሹጋር የነበራትን ጥምረት እና ውህደት የዉበት አሻራ መሆኑን ተገንዝበን ነበር ፡፡
ወይስ ሙዚቃውን በሰማንበት ወቅት በደፈናው ስሜታችን መርቶን ሃይላችን ከማንቆጣጠርበት መንደር ስንደርስ እንደ እንቦሳ በደስታ ስካር ፈንጥዘን የሙዚቃው ጩኸት ሲበርድ የእኛም ስሜት አብሮ ይከስማል ? እንደዚያ ከሆነ የማድመጥ ክህሎታችንን ማስፋት ያለብን ይመስለኛል ፡፡በአርግጥም ቴዲ አፍሮ ለዚህ ዘፈኑ ማለትም “ሞናሊዛ” እና “ገና እወድሻለሁ” ማጀቢያ የተጠቀመበት የሙዚቃ ስልት አይነት ስሎው ሮክ የሚባለውን የሙዚቃ ስልት ሲሆን የዚህ አይነቱ ስልት ደግሞ በብዙዎቹ ዘንድ ተወዳጅ እና ተደናቂነትን ብቻ ከማትረፍም በላይ በከፍተኛ ቁጥር ተደማጭነትንም አትርፎላቸዋል ፡፡ቴዲም ይህንን ስልት በመጠቀሙ ከወትሮው በበለጠ ሁኔታ አድማጮቹን አና የአድማጮቹን ቀልብ ሊገዛ ችሎአል ፡፡ በሌላም አይታ ብናየው አሱ ይህንን አይነት የሙዚቃ ስልት ካሳያቸው በሁዋላ በአሁን ወቅት በመውጣት ላይ የሚገኙት ወጣት ድምሳውያን የአሱን ፈለግ በመከተል ከአዘፋፈን ስታይል ጀምሮ አስከ ሙዚቃዊ ስልት ድረስ ሃሳቡን በመከተል ለመዝፈን የሚጥሩ አቀንቃኞች አልታጡም፡፡ብዙም ጥሩ ጥሩ ዘፈኖችን ልንሰማም ችለናል ማለት ነው፡፡
“ገብረስላሴ”
እያለ ያቀነቀነው በሃገራችን ታሪክ ውስጥ ለረጅም ዘመናት በተለያዩ የአልማችን ክፍለሃገራቶች በፈጣኖቹ አግሮቹ የተለያዩ ክብረ ወሰኖችን በመስበር ለሃገራችን ክብር ,ለባንዲራችን ደግሞ በኣለም ዙሪያ ከፍ ብሎ አንዲውለበለብ ላደረገው ፈጣኑ ሯጭ ሃይሌ ገብረ ስላሴ መሆኑ ማንም የማይክደው ትልቅ ስራ ነው ፡፡ በእውነቱ በሃገራችን ውስጥ በቁም ሳሉ ማወደስ ባለተለመደበት ሃገር ላይ የውስጥ ስሜቱን አና የአኛንም የደስታ ስሜት አጣምሮ በመግለፅ ለሁላችንም አንድ ቕንቕ ሆኖልናል ፡፡ ምክንያቱም ሃይሌን ስናነሳ በሃገራችን ዙሪያ ለሚያስጠራት ስፖርታዊ ስሜት ጎን ለጎን ከፍተኛ ሃገራዊ ፍቅራችንን ስሜታችንን ቀልባችንን ገዝቶን በደስታ ሲቃ እንባ አራጭቶናል፡፡ ቴዎድሮስም ለአንደነዚህ አይነት እዳዎች አኛን ባለ እዳ አድሮጎናል ማለት ነው ፡፡ ጆሮአችንን ኮርኩረን በጠራ ቅላፄ እንድናዸምጠው ገፋፍቶናል የሃይሌንም ባለውለታነት አሱው በአንደበቱ አስታውሶናል ስለዚህ በኪነጥበቡም ዘርፍ ሆነ በሩጫው ለሃይሌም ሆነ ለቴዲ ለገድላዊ ስራዎቻቸው ባለ አዳ ሆነናል ማለት ነው ፡፡
ሪጌ ስልት ስለሆነው ሻሸመኔ ብናወሳ ደግሞ አራሱን የቻለ አንድምታ ይኖረዋል ፥የሬጌ ፈጣሪ አና በስበናው አና በተርጋጋ መንፈሱ ሬጌን ሲያቀነቅን መንፈስንም ሆነ ህይወትን የሚያድሰው ቦብ ማርሌይ ለስራዎቹ ክብር ከመስጠቱም በላይ በከፍተኛ ደረጃ ፊቱን ወደ አለም ህዝብ አዙሮ ለሰላም ማንጎራጎሩ የማይካድ ታላቅ የሙዚቃ ሰው ነው ፡፡ አሱን ተከትለው ብዙ ዘፋኞች አሱው በፈጠረው ሬጌ ስልት ተለክፈው ዛሬ በከፍተኛ ደርጃ ተከታዮቹ በመሆን ሙዚቃዎቹን ሲሰሩ ቦብ እንደ መሲህ አነሱ ደግሞ እንደ ደቀ መዝሙር በመሆን ስራቸውን ሲያቀላጥፉ አና ለህዝብ ጆሮ ሲያሰሙ በተለያዩ አለማት ይደመጣሉ ፡፡ ይህም የሚሆነውም በአለማችን በሚገኙት በተለያዩ ቍንቍዎች ሁሉ መሆኑ ግርምትን ሳይፈጥር አይቀርም ታዲያ በዚህ መልኩ ከሆነ ቴዲ አፍሮ የቦብን ፈለግ በመከተል ዝማሬውን ቢያቀርብም ፥በተወሰነው አና በተገደበው አንደበቱ ለሃገሩ ብቻ የምትሆነውን ቃላት ቢያመነጭም እንደ ቦብ ማርሌ ለሰላም ቆሞ ጩኸቱን ለማሰማት ባይችልም በእርግጥ የሙዚቃውን ሃይል በመጠቀም ሞክሮታል ፡፡ በአጠቃላይ ቴዎድሮስ ስለሰዎች ሰበአዊ ክብር ለማቀንቀን ቢሞክርም በአጭሩ እንዲቀጭጭ ተደርጎአል ከዚያም በሁዋላ የውስጥ ድንጋጤ ከተፈጠረበት በሁዋላ በአራሱ አነሳሽነት ~ instigation ማድረግ አልሞከርም ለማለት አይቻልም ግን ስራዎቹን ሰርቶ ለማቅረብ መንገድ አላገኘም ፥ለምን ቢባል የህይወት ዋስትናው ምን አንደሆነ ስላላገኘው ነው ፡፡ማንም ያልሰማቸው ግን ቢሰሟቸው አይደለም አንዲት ሀገርን ሌሎችንም ሊያስደነግጥ ስራ በአጁ ቢኖርም ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር አራሱን ለማቆየት ሲል የስራውን ልፋት አና ጥረት ለህዝብ ልደብቀው በቅቶአል ፡፡ይህ ባይሆንማ ኖሮ ብሉስ የተሰኘው ስልት ከሁአለት መቶ አመታት በፊት በአሜሪካ የላይኛው ክፍል ማለትም ደቡቡን ጫፍ ይዞ ይደረግ በነበረው የባርነት ዘመን አና ሰቆቃ ፥ተንሰራፍቶ የነበረውን ባርነት ለማንፀባረቅ ሲባል እና ከዚያም አልፎ ተርፎ ምሬታቸውን ለመግለፅ ይጠቀሙበት የነበረውንም ብሉስ ሃይል ባለው ቃል ድምፅቱን ሰርቶት አስቀምጦታል ፡፡አዎ ብሉስ አመፅ ነው የአመፅ ማቀጣጠያ ሻማ ነው ልክ እንደ ቀረርቶ በአርሻው ውስጥ ፥በማእድን ማውጫ ስፍራ ፥ በጕዳው እና በጎድጕዳው እንደ እንሰሳ በማይቆጥሯቸው ጨካኝ አሳዳሪዎቻቸው ምሬታቸውን፥ ስሜታዊ ጉዳታቸውን የሚተነፍሱበት አንደበት ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ከዚያን የኤሉሄ ዘመን አልፎ የፍቅር መገለጫም እስከ ማንጎራጎሪያነት ሲጠቀሙበት አይተናል፡፡ እያየንም ነው፡፡ ስለዚህ ቴዎድሮስ በተፈጠረላት የሙዚቃ ብርሃን ውስጥ አሱም ባለው ሃይል ለሙዚቃዊቱም የብርሃን ጭላንጭል ለመሆን በቅቶአል ፡፡ ግርማዊነትዎ
እኔም ሆንኩ ቴዎድሮስ ባልተፈጠርንበት ዘመን በእርግጥም የታሪክ በዛግብቶች በሚያሳዩን አና በሚያስረዱን መሰረት አና አንዲሁም በአፈ ታሪክ ንግርት በተነገረን መሰረት ስለ ቀዳማዊ ኅይለ ስላሴ ለማውራት የሚያበቃን የተሟላ አንደበት ይኖረናል ማለት ዘበት ነው ይህ ሆኖ ሳለ ግን ይህ ወጣት ባልተጠበቀ ሁኔታ የዘውዳዊ አስተዳደሩን በግርማዊነታቸው ክብር ምን ይመስል አንደ ነበር የአፍሪካ የክብር አባትነታቸውን ያመላከተበት ትልቅ መልእክት ነበር ፡፡ ምክንያቱም በአስራ ዘጠኝ ስድሳዎቹ አጋማሽ የግርማዊነታቸው የዘውድ ንግስናዊ ግርሰሳን ተከትሎ አቅማቸው በማይፈቅደው አና በማይለካበት ሁኔታ አብሪተና የሆነ ወራሪ በመጣባቸው ወቅት አራስን ለማዳን ሽሽት ማይጨው ቀጥለውም ጄኔቭ ባደረጉበት ወቅት ትንቢት መሰል ንግግር ማድረጋቸውን እና ከዚያም ሊግ ኦፍ ኔሽን የተሰኘው ድርጅት መፍረስን የሚያመላክቱ ፅሁፎችን ማንበቤን አስታውሳለሁ ፡፡እኝህም ሰው ስለታሪካቸው ከአሰፈሩት መፀሃፍ My Life and Ethiopia’s Progress: The Autobiography of Emperor Haile Sellassie Iበተሰኘው መፅሃፍ በተወሰነ ደረጃ የሃይለስላሴን አንደበት እና የነበራቸውን የሃይል ብቃት ለማውቅ ችያለሁ የተጋፈጡትንም ችግር በተወሰነ መልኩ እንዳሰምርበት ኣድርጎኛል ቀልቤንም ገዝቶ ይዞኛል፡፡ ታዲያ ይህ ሆኖ ሳለ ዘንዳ ቴዲ ስልኝኽ ታላቅ ተብለው በወቅቱ ይጠሩ ለነበሩ ንጉስ ምንነታቸውን አና ማንነታቸውን ሳያውቅ የድምፅ ቅላጼውን አውጥቶ ማንጎራጎሩ ሳይደንቀን ቀርቶ ይሆን ወይስ ምንድን ነው? ወዪስ በራስ ተፈራያኖች ዘንድ ብቻ ሲነሱ ታሪኩ የእኛ ሰውየው የእኛ እያልን በተረት አጋንዱር ቡቡምቡር የምንል የዘመኑ ትውፊቶች ለመሆን የምንታገል ሰዎች ነን ?ወዪስ በታሪክ ታጅለን ማንነታችንን ራሳችንን ሳናውቅ ሰዎች ብቻ ሲነግሩን የምንነቃ የቤተክርስቲያን ደውል (ቃጭል) ሆነን ነው ፡፡ ራስተፈራውያኖች አንደ መለኮታዊ ባህርይ የሚያዩዋቸውን ሃይለስላሴን የአራሳቸው ልዩ ባህርይ ቢኖራቸውም አኛ ግን ለአፍሪካ አንዲሁም በተለይም ለኢትYኦጵያ ያደረጉትን ታላቅ አስተዋፅኦ የሚካድ አንዳልሆነ ስነ ልቦናችን ያውቀዋል ታዲያ አሁንም ቢሆን ቴዎድሮስ የአኝህን ሰው መለኮታዊ ባህርይ ሳይሆን ታልቅ ስራቸውን በአለም ዘንድ ስማቸው ያስጠራበትን ተግባር እና ተግዳሮት ለመዳሰስ ሞክሮአል ፡፡
በአስራ ሰባት መርፌ
ይህንን ዘፈን በሰማንበት ወቅት በሃገራችን የምናልመው አና ሁልጊዜም የምንመኘው ወደፊትም የምንፈልገው የሃገራችን ሰላም አና የግዞት ኑሮ ያበቃለታል ብለን የጠበቅንበት ጊዜ አንደሆነ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነበር ፡፡ አዎ በደርግ ጊዜ ብዙ ወገኖቻችን በግፍ ተግድለዋል በከፋም ኑሮ ኖረዋል ብዙ ወጣቶች ያለምንም ምክንያት ደማቸው መሬት ፈሶ ቀርቶአል ብዙዎቹ ደግሞ በዱር በገደሉ የአሞራ አና የአውሬ አራት እና ምሳ ሆነው የበላቸውም ጅብ ሳይጮህ ለቤተሰቦቻቸው የዘላለም ፀፀት ሆነው ቀርተዋል። ይህ ሁኔታ ደግሞ የሁላችንንም ቤት ያንኵኳ ነበር። ሆኖም ግን ዘመነ ለውጥ መጥቶ ሰላማዊ ህይወትን ናፋቂው ወገኔ ለሰላም አጁን እያጨበጨበ ፍትፍት ፈትፍቶ አያጎረስ ወደ ስልጣን እንዲወጣ ያደረገውን የወያኔን መንግስት በደስታ ቢቀበለውም አነ አጅሬ ግን ውስጣቸውን ለቄስ ሰጥተው በመምጣት ጭቁኑን የኢትዮጵያ ህዝብ መልሶ በግዞተኝነት የጭቆና ቀንበር እንዲርወድ ሲያደርጉት የተመለከተው ይህ ወጣት በጫካ የነበራቸውን ህይወት ፍንትው አድርጎ በሚያሳይ አንደበት እውነታውን ሊገልፅላቸው ችሏል ከዚያም ጊዜ በሁዋላ ንቃተ ህሊናቸው መስፋት ባይችልም አንደገና ሊብስባቸው በቅተዋል ፡፡ታዲያ ይህንን ጊዜ ነበር የህብረተሰባችንን ብሶት በተወሰነች የግጥም አንጕ አና የሙዚቃዊ ቃና በየሰው ግንባር ላይ የተነበበው ፡፡
አንዲህ አይነት ሳይታሰቡ የበሰሉ ግጥሞቹን በጣም በወረደ የኣመለካከት ሂደት በወዳጄ ግርማ ደገፋ በኩል የመጡትን አስተያየቶች ለመቀበል የሚዳዳኝ አይመስለኝም ፡፡ በእውነቱ የግጥሞቹን ይዘት አና አወራረድ አንመልከት ካለን ብዙ ማለት ይቻላል አና አንባቢያንን ላለመሰልቸት በሚል ለመቁረጥ ወስኜ ነው ወደ ጋዜጠና ግርማ ደገፋ የገባሁት አንጂ ሃሳብ አልቆብን አይደለም ሆኖም በተወሰኑት የዘፈን ረሶች ላይ ትኩረታችሁን አሁንም ታደርጉ ዘንድ አጠይቃችኍለሁ፡፡ ለአብነት ያህልም “በገና” (“ተውልጄ ወይንም ከሃሁ ታረቅ”) ለአባቱ ጋዜጠና አና የመድረክ መሪ ለነበረው ካሳሁን ገማሞ የዘፈነውን “አቡጊዳ” እንዲሁም ሊሎቹንም በጥልቀት ብንዳስሳቸው መልካም ይመስለኛል አንጂ በደፈናው ልጁ አልሰራም ብሎ ማለት የሚያዋጣ አይመስልም አንዲያውም በጣም ከባዱ አና ትልቁ ፈታኝ ስራ በእራስ ተገጥመው በእራሳቸው ዜማ አና የሙዚቃ ቅንብር ተሰርተው የሚቀርቡ ሙዚቃዎች ትልቁን ድርሻ ሲወጡ ትልቅም ልፋት ታይቶባቸው ሲሆን በአርግጥ በሰዎች ተገጥሞ እየተሰጣቸው ማይክ ጨብጠው ዘፈንን ከሚሉት ጋር ያለውን የስራ ልፋት ትግል ስናየው የእነዚህኞቹ ፋይዳ ቢስ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡
በሌላም በኩል በጋዜጠኛ ግርማ በኩል ስለ አስቴር አወቀ ሙዚቃ ስራ ላይ በተመለከተ ላነሳሁት ሃሳብ መልሹን ሲሰነዝር በስድስት አመትም አይነካካትም ብሎ ጠቅሶ ነበር እኔም አንግዲህ የምስራች ልበልህ እና አንደሸቀት ንግድ ተያያዘችው እንዴ ያልኵትን አስቴርን ጉዳይ ጠቆም ላድርግህ ..በባለፈው አመት አዲሱን አልብሟን ጨርሳ ጨጭሆ አያለች የሰው ጆሮ ስታጮህ እንደነበር የምታስታውሰው ይመስለኛል ፥አሁንም ሙሉ አልበሟን ጨርሳ ከናሆም ሪከርድስ ጋር ፣(ኤልያስን) ግዢ አንዲፈጽምላት በመወትወት ትገኛለች ይህ ማለት በከፍተና ደረጃ ለሙዚቃ ያላትን ክብር ማሳየቷ ይሆን ወይስ ንግድ ምጧጧፏ ?መልሱን ላንተው ልተወው..በአርግጥ አስቴርን ከአንተ በበለጠ አወዳት አና አደንቃት የነበረች አንጋፋ ድምፃዊት ናት ግን ይህንን እድል ያጣችው ከ”ሰውየው አለ ወይ” አያለች ካንጎራጎረችበት አልበም በሁዋላ እንደሆነ ሳልገልፅልህ አላለፈም ፡፡
ይህንን ያህል ሰለ እሷ ካነሳሁለህ ቀታዩ ተመልሼ የማወራህ በቴዎድሮስ ጉዳይ ይሆናል የገንዘብ መከማቸት ወዪንም በአንድ ጊዜ ተቆልሎ መምጣት የሰራን ስኬት ውጤት የሚያሳይ እንጂ ስንፍናን አጉልቶ የሚያወጣ አይደለም ያም ካልሆነደግሞ በአሜሪካን የሙዚቃ ስታንዳርድ አየተባለ በደረጃ በሚሰጠው ቶፕ ቴን ደርጃ ላይ በአድማጭ እና የአልበም ሽያጭ ውጤት የሚያመላክተው የስራህን ተወዳጅነት አንጂ ተወቃሽነት አይደለም ስለዚህ የዚህ ሰው ስራ ከምንም በልጦ እና ገዝፎ የወጣውም በዚሁ የብቃት ደረጃ መለኪያ ብቻ ነው ! መለኪያው መስፈርቱ ምንድን ነው ብለህ ለምትለው ተከታይ ጥያቄ ደግሞ ህዝቡ እና ህዝቡ ብቻ ነው …በየጊዜው የሚፈልቀው የአድማጩ ብዛት መወደድ አንደሆነ የምትረዳው ይመስላል፡፡ ቀጣዩ አስቴር ለቁጥር የሚታክት ጫማ ኣላት ላልከው በጣም በትልቁ ያሳቀኝ ነው `በአርግጥም ይኖራታል እንጂ በዲዛይነርም ቢሆን የተሰራ ልታጠልቅ ትችላለች ግን እውነት አድሜ ልኵን ስትዘፍን የኖረችበትን ያህል አንኵን ቢሆን ቴዎድሮስ ካሳሁን ባሳለፍነው ሁለት ወራት ብቻ ለ ሁለት ኮንሰርት የተከፈለውን ያህል ብር ይኖራታል ለማለት አያስችለንም ምክንያቱም አንደዚህ አይነቱ የክፍያ ጣሪያ የመጣው እና በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈለው ይህ ወጣት ብቻ ነው ፡፡ አንባብያን ይህንን ያህል ስለቴዎድሮስ ካሳሁን ያለውን ሃይል ካቀረብኩ በቀጣዩ ደግሞ ምን ድክመት አለበት ምን ሰራ የሚሉትን አና ሌሎችንም ነገሮች ጊዜ ካገኘሁ ለመዳሰስ አሞክራለሁ ….አስከዚያው መልካም ጊዜ ።
Average Rating