www.maledatimes.com የመለስ ህመም ምን ነበር? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የመለስ ህመም ምን ነበር?

By   /   September 21, 2012  /   Comments Off on የመለስ ህመም ምን ነበር?

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 21 Second

          ይህ ጥያቄ ዛሬም ድረስ አልተመለሰም። ምላሽ ማግኘት ግን አለበት። ኢህአዴግ የመለስን በሽታ የመደበቅ ህጋዊ መብት የለውም። የህዝብ ህይወት እጁ ላይ የነበረ መሪ እንደመሆኑ፣ ህዝቡ ስለመሪው የማወቅ መብት አለው። መሪው ሲጠጣ ወፈፍ የሚያደርገው ከሆነ ህዝቡ ማወቅ አለበት። በሽታው ጭንቀት የሚለቅ አይነት ከሆነ፣ በህዝብ ህይወት ላይ አደጋ ሊያደርስ የሚችል ውሳኔ ሊወስን ስለሚችል የመሪውን ጤንነት ማወቅ ግዴታ ነው።

አውሮፕላን አብራሪዎች ኤች. አይ. ቪን ጨምሮ ሙሉ የጤና ምርመራ ያደርጉ ዘንድ ግዴታ ውስጥ እንዲገቡ የሚደረገው የብዙሃን ህይወት እጃቸው ላይ የሚገባበት አጋጣሚ በመኖሩ ነው።
“በባህላችን ሰው ሲሞት የህመሙ አይነት አይነገርም፣ በሽታን መንገር የፈረንጆች ባህል ነው” ብለው የሚከራከሩ አሉ። ይሄ እውነት አይደለም። ጥላሁን ገሰሰ ሲሞት በሽታው አይደለም፣ የወሰደው የመድሃኒት አይነት ጭምር ሲነገር ነበር። ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል። ባህላችን ባይሆን እንኳ፣ መሪዎችን የሚመለከት አይሆንም።
መለስን ለሞት ያበቃው ህመም ምንድነው?
ለምን በምስጢር ተያዘ?
በምስጢር በመያዙ ምን ጥቅም ተገኘ?
በእውነቱ ጉዳዩ በምስጢር በተያዘ ቁጥር መላምቶች እየበረከቱ ሄደዋል። ወሬው ሲጀምር ህመሙ የአንጀት ካንሰር መሆኑ ነበር የተነገረው። በመቀጠል ወሬው እድገት አሳይቶ ወደ ደም ካንሰር ተቀየረ። ብዙም ሳይቆይ የአንጎል እጢ ሆነ። ከዚያም የጉበት ካንሰር መሆኑ ተከተለ። በG8 ስብሰባ ላይ አሜሪካኖች ናቸው በጨረር የገደሉት የሚሉ ደግሞ ተነሱ። የአበበ ገላውን ድምፅ ለመለስ ሞት ምክንያት ያደረጉም አሳባቸውን ሰንዝረዋል። መላ ምቱ ቀጥሎአል። ኢህአዴግ ሊነግረን የቻለው በኢንፌክሽን ምክንያት ለሞት መብቃቱን ነው። ዋና የህመሙን ምክንያት በግልፅ እስካልተናገሩ ድረስ፣ መላ ምቱ ይቀጥላል። በቅርቡ ለንባብ የበቃ ፅሁፍ ደግሞ፣
“መለስ የሞተው በሆስፒታል ኢንፌክሽን ይሁን እንጂ HIV በደሙ ወስጥ ነበር” ሲል ያብራራል፣ “….ወደውጪ ለህክምና ከሄደ በሁዋላ ለህልፈት ያበቃውን ኢንፌክሽን ለመቆጣጠር ያልተቻለው በደሙ ውስጥ በነበረው HIV ምክንያት ነው።”
ይህን ዜና ለማመን ምንም አሳማኝ መረጃ የለም። ላለማመንም ያስቸግራል። HIV በደሙ ውስጥ ከነበረ በተለያየ ምክንያት ሊመጣበት ይችላልና የሚያስደንቅ አይሆንም። ወይም የመለስን ሰብእና ሊጎዳ አይችልም። ይህ ዜና እውነት ካልሆነም፣ መፍትሄው መለስ በምን ምክንያት እንደሞተ ለህዝብ መግለፅ ነው።
ስዬ አብርሃ በቅርቡ ሲያትል ላይ ባደረገው ንግግር፣ ይህንኑ አንስቶአል። አያይዞም፣ “መለስ በምን ምክንያት እንደሞተ ሊነገረን ይገባል” ሲል አጥብቆ ጠይቆአል። ባልተነገረ ቁጥር፣ ከግምቶች መካከል አንዱ እንደ እውነት እንዲቆጠር ያደርገዋል። ወደፊትም ታሪክ ፀሃፊዎች በቅርብ ያገኙትን ይዘው ስለሚፅፉ ጉዳቱ ያመዝናል። ታሪክ ይዛባል። መረጃዎችን ማጣመም ለሚፈልግም ሰፊ በር ይከፍታል። በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በማንኛውም አጀንዳ ላይ ኢህአዴግ መደባበቅን ብቻ መምረጡ፣ ይጎዳዋል እንጂ አይጠቅመውም። “ያስጨነቀኝ መዋሸትህ ሳይሆን፣ ዳግም ላምንህ አለመቻሌ ነው” እንዲሉ።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 21, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 21, 2012 @ 7:41 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar