ኢትዮጵያውያን በያዝነው አምባገነንነትን የማውደም ትግል ውስጥ እያንዳንዱ ዜጋ የራሱ ድርሻ እንዳለው የማይካድ ሃቅ ነው ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በእኛ ሰዎች ዘንድ አንድ ችግር አለ ፡ አንድ ሰው በራሱ አስተሳሰብ የሚሄድ ከሆነ እውነታን ይዞ አንገቱን ሰብሮ የሚታገል ከሆነ አንዱ ለአንዱ ለምን አላጎበደደም እንደኛ ለምን አላሰበም ለምን አስተሳሰቡን ጻፈ በሚል በከፍተኛ ፍጥነት ጥላቻ ይንጸባረቅበታል ይፈረጃል። እያንዳንዳችን ሰዎች የራሳችን አስተሳሰቦች እና አመለካከቶች አሉን፡፤ አስተሳሰቦቻችንን እና አመለካከቶቻችንን ደሞ የማንጸባረቅ መብት አለን፡፤ የግዴታ ለማንም ተገዢ አንሆንም አሁን እየታገልን ያለነው በ እምቢተኝነት ጭቆናን ነው። ሌላ ጭቆና በነጻው የማህበራዊ ድህረገጽ ላይ እንዲግውጥመን አንፈልግም፡፤ ሌላው ደም ሰዎች ከኛ በመረጃም ይሁን በአጻጻፍ ዘይቤ በልጠውን ሲገኙ አይናችን ደም የሚለብስበት ምክንያት አይገባኝም ። መከባበር ሲገባን የሰውን አስተሳሰብ ማክበር እና መተራረም ሲገባን ብድግ እያልን ሰውም መጠራጠር መፈረጅ መሳደብ መዝለፍ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት አሊያም የትግል ስልት አይደለም።
በየድህረገጹ የሚጽፉ ሰዎችን ቃላት እየሰነጠቁ ነገር እየፈለፈሉ ለማሳጣት መሞከር እና መታገል ለየቅል የሆነ እና የማይገናኝ ነገር ሆኖ ሳለ የፖለቲካ እውቀቱ እና ብስለቱ የሚያጥራቸው ጥቂት ሰዎች የማይታወቅ ጅራፋቸውን ታግለው በሚያታግሉ ሰዎች ላይ ሊሰነዝሩ ሲንደፋደፉ ይታያሉ። ሰዎች ሁሉ እንደ ተቃዋሚ ድርጅት አሊያም እንደ ተቃውሚ ግለሰብ ሆነን ስንሽከረከር እንደና ካላሰበ እኛን ካልተከተለ የኛን ካለጠፈ እሱ ተቀብሮ እኛ ካልታየን የሚሉ ከሆነ ይህ ትግል ለሃገር እና ለህዝብ ሳሆን ለስም እና ለዝና የሚደረግ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። ሰዎች የራሳቸውን መረጃም ይሁን ጽሁፍ ይዘው ሲመጡ ልናከብርላቸው ሲገባ ባንቀበለውን ባንስማማበትም መፈረጅ እና ማሳጣት አሊያም ትግሉን ሽፋን በማድረግ መዝለፍ አያዛልቅም። በአሁን ሰአት የሚደረጉ ዝባዝብንኪ የዘለፋ እና የትችት ተግባራት የትም የማያደርሱ እና ጭራሽ ትግሉን የሚገሉ መሆኑን ልናውቅ ይገባል። በተጨማሪም ሰዎች በጃቸው ያለውን የፖለቲካ መረጃ ደራርበው የሚያወጡት ከሆነ ትግሉን እንደሚገል እና እንደሚያጠፋ በግልጽ ለመመስከር የምንገደድበት ወቅት ላይ መድረሳችን በማይረቡ ሰዎች ትግሉን የማኮላሸት ሂደትን መጋበዝ አንዱ ስህተት ሆኖ ይሰማኛል። ፖለቲካ ማለት ጥንቃቄ የሚፈልግ እና የትግል ስልትን የማያዳከም ታላቅ ድል የሚሻ ጉዳይ ነው።
ይህንን ከግንዛቤ የማያስገቡ ሰዎች የግለሰቦችን ዱካ እና አረፍተ ነገር እየተከተሉ በቃላት ስንጠራ ላይ ከተሰማሩ ትግሉን ማን ይታገል ? ዘለፋ ላይ ካተኮርን ትግሉን ማን ይታገል ? በቂ ማስረጃ እና መረጃ ሳንይዝ እከሌ ላይ እንዲህ ይሁን እከሌ እንዲህ ነው ምናምን እየተባለ በስም ማጥፋት ላይ የምንሰማራ ከሆነ ህዝቡ በነቃ ጊዜ መግቢያ ቀዳዳ እንድሚጠፋን ካሁኑ ማሰብ ያስፈልጋል። ተቃዋሚ ነን የሚሉ ሁሉ በአጋር ተቃዋሚዎች ላይ የከፈቱት ዘመቻ እስካሁን ምን ያህሉ እንደተሳካ በተቃዋሚ ግለሰቦች ላይ የከፈቱት ስም ማጥፋት ምን ያህሉ እውነት እንደሆነ በቂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እውነተኛ ሰው የለም። ያሌለ ነገር ከመዘባረቅ እና የግለሰብ ማንነትን በሃሰት ከመበከል እንዲሁም ባልበሰለ የፖለቲካ ግምት ሰዎችን ከማሳጣት ውጪ ለትግሉ ምንም አልፈየደም። ምንም እድገት አላመጣም።
ትግሉን እንዴን ማሳካት እንችላለን ? አሁን ካለበት እንዴት ልናሳድገው እንችላለን ? ምን መርዳት አለብን ? ምን መተባበር አለብን ወዘተ የሚሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ይዘን ህዝብን ማነቃቃት ህዝብን ማስተማር ለለውጥ ማነሳሳት ሲገባን የግለሰቦችን ዱካ እየተከተልን ስም ማጥፋት እና መነካከስ መፈራረጅ በህዝቡ ዘንድ ያለውን ተቃዋሚዎች አይረቡም ተነካካሾች ናቸው እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ እኛን እንዴት ይመሩናል የሚለውን አስተሳሰብ እያሰፋ እንጂ እያጠበብ አይሄድም። ስለዚህ የግለሰቦችን ስም ማጥፋት እና መዘርጠጥ የማይሆን ስም መስጠት ታፔላ መለጠፍ ለትግሉ ምንም አይፈይድም።የሚሰደቡት ሰዎች በጥንካሬ በርትተው እያየናቸው እንጂ እንድ ተስአድቢዎች ሲከስሙ አላየንም ፡፤ የሚሰደቡ ሰዎች መረጃዎቻቸው እውነት ሆነው ሲገኙ እንጂ ሲያፍሩ አላየንም። ስለዚህ ይህ መፈራረጅ እና መዘላለፍ ቆሞ በጋራ ለትግሉ አስታውጾ ማበርከት አለብን ። ሊታሰብበት የሚገባ አቢይ ጉዳይ ነው።

Average Rating