የአንድነት ፓርቲ አባል የሆነው የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ምክትል ፀሐፊ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ መሰደዱ የታወቀ ሲሆን በተያያዘ ሁኔታ የሚለዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል በተደረገው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የእስረኛ ቱታ በመልበስ የገዥው ፓርቲን አምባገነናዊነት ካሳዩ ወጣቶች መካከል ዳንኤል ፈይሳም በተመሳሳይ ሁኔታ ለስደት መዳረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ምክትል ፀሐፊ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ በተደጋጋሚ ግዜ የደህንነት መታወቂ በሚይዙ ግለሰቦች ደረሰበትን ዛቻ ማስፈራሪና ድብደባ ተቋቁሞ ቢቆይም በቅርብ ግዜ ወዲህ ግን ማስፈራሪና ዛቻው ቅርጹን በመቀየር ለ12 ቀናት ለእስር እንደተዳረገና 3 የክስ ፋሎች ተከፍተውበት ፍርድ ቤቱ የመከላያ ምስክሮቹን እንዲቀርብ ማዘዙን ተከትሎ ከሳሾቹ የምንሰጥህን ተግባር የማትፈጽም ከሆነና በተለይም በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ካሉ የኢህአዴግ ሰዎች ጋር በመሆን የሚሰጥህን ተልዕኮ የማትወጣ ከሆነና በነ ሀብታሙ ኤያሌው ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር መሆን የማትችል ከሆነ 4ኛው ክስ ግራዚያኒ ሀውልት መገንባትን ተከትሎ በታሰሩበት ወቅት የቀረበበት አመፅና ሁከት ለመፍጠር የሚለው ክስ እንደሚንቀሳቀስ እንዲሁም በተደጋጋሚ ከኢሳት ቴሌቢዝን ጋር ግንኙነት በመፍጠር በሚል የአሸባሪነት ክስ ሊመሰርቱበት እንደሚችና እስር ቤት እንደሚበሰብስ መግለፃቸውን ተከትሎ ከሀገር ለመሰደድ መገደዱ እንደቻለ ለማወቅ ተችሏል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating