የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብሶታቸውን በከፍተኛ ቁጣ ገልጸዋል። Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
– ለወያኔ ባለስልጣናት የቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳየው ስልጠናው ምንም የስኬት ፍንጭ አላሳየም።…
– የሃምሳ አመት እቅድ ለምን አስፈለገ የስልጣን ጥመኝነትን ያሳያል።
– ለሶስተኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ እየተካሄደ ነው።
– በኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይሁኑ አባላቶቹ የአስተዳደር ብቃት የላቸውም።
– ኢትዮጵያውያን በህግ ፊት እኩል የሚሆኑት እና ፍትህ የሚነግሰው ቀን እንናፍቃለን።
– በቫት ስም መንግስት ዘረፋ ይዟል በህጉ ቫት አይከፈልበትም የተባለው የጤና ዘርፍ ሳይቀር ቫት እየቆረጠ ነው።
በየአከባቢው እየተካሂደ ያለው ልማታዊነትን ሽፋን አድርጎ የስልጣን ማስረዘሚያ ሰበካ (ስልጠና) እንደቀጠለ ቢሆንም በህዝቡ እና በአሰልጣኞች መካክል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ከመከሰቱም በላይ ህዝቡና ተማሪው በአገራችን ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር ልንግባባ አልቻልንም ስለዚህ አበል ይቅርብን እና ስልጠናውን አቋርጡልን በማለት እየጠይቀ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። ሰልጣኞች እንደሚሉት እየተካሄደ ያለው ስልጠና ሳይሆን የፖለቲካ ሰበካ ነው ይህ ደሞ የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸውን ህዝቦች ለማደናቆር ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ የያዛችሁን ስልት ቀይራችሁ ህዝብ መሃል ግቡና አናግሩን እንጂ በ አበል እና በቀበሌ ጥቅማጥቅም አታስገድዱን፡ አያዋጣችሁም ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአዲስ አበባ የኢሕአዲግ ጽ/ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደጠቆሙት እስከዛሬ በተሰጡ ስልጠናዎች የተሰብሰቡ ሪፖርቶች እንደሚይመለክቱት ሕዝቡም ይሁን ተማሪው በተጻራሪነት እንደቆሙ እና በድርጅቱ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እና ማንጓጠጥ ያሳዩ መሆኑን የጠቆመ ሲሆን ስልጠናው ምንም የስኬት ፍንጭ አላሳየም ብሏል።
በጎንደር ዩንቨርስቲ ለየት የሚያደርግው ተማሪው ብሶቱን በከፍተኛ ቁጣ መግለጹ ነው።
በጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪው በዩንቨርስቲው ትምህርት ላይየና በመምህራን ጉዳይ ከፍተና ቁጣ በማሰማት ላይ ሲሆን ዩንቨርስቲው በመልካም አስተዳደር እጦት እና በሙስና እየታመሰ መሆኑን ተነግሯል በአንድ ምት ጊዜ ውጽት ብቻ 3 ፕሮፌሰሮች 3 ዶክተሮች 14 ሁለተኛ ዲግሬ ያላቸው ምሁራን ልምድ ያላቸው መምህርን ጎንደር ዩንቨርስቲን ለቀዋል።ለዚህ ምክንያቱ ደሞ የዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መንገሻ አምባገነንነት እና ፈላጭ ቆራጭነት መሆኑን ተማሪዎቹ አስምረውበታል።
የዩንቨርስቲው አመራር እና ቦርዱ አምባገነን ናቸው ያሉት ተማሪዎች በሙስና እና በወገንተኝነት የተዘፈቁ ስለሆኑ በዩንቨርስቲው ከ20 አመት በላይ ያገለገሉ ምሁራን እንዲለቁ ምክንያት ህነዋል።በ2007 ይነሳሉ ተብለው የነበሩት እና በጣም አስቸጋሪ ባህሪ እንዳላቸው የሚነግርላቸው የዩንቨርስቲው ፕረዚደንት ፕሮ.መንገሻ በኢሕ አዴግ ብባለስታን ድ/ር ስንታየው ትእዛዝ እንዲቀጥሉ መደረጉን ተማሪውን አስቆጥቷል።
ህዝቡና ተማሪው ዛሬ በጠዋቱ እነዚህን ሲናገሩ አርፍደዋል።
1 ኢሕአዲግ የሃምሳ አመት እቅድ አውጥቷል መጀመሪያ ደረጃ የ50 አመት እቅድ በማን ማንዴት ነው የሚያውጣው ሃምሳ አመት ከህዝብ ፍቃድ ውጪ የመግዛት እቅድ ኢሕአዴግ አለው ማለት ነው ይህንን አንቀበልም ሃገሪቷን ሌላ አደጋ ውስጥ ለመክተት ካልሆነ በቀር ማንም መንግስት እንዲህ አያቅድም።
2 ኒኦሌቤራሊዝምን እና ሶሻሊዝምን እየጠላችሁ ልማታዊ ዲሞክራሲ ትሉናላችሁ ከየትኛው የትናው እንደሚሻል እንኳን ግንዛቤ የላችሁም በውቀት ያልጠገባ አመራር እና አባል ታቅፋችሁ ሃገር እንዲት እንደምትመሩ በፍጹም አቅቷቹሃል እና አስቡበት
3 የትምህርት ጥራት አውርዶ የዩንቨርስቲዎችን ቁጥር ማብዛቱ፡ተቀሜታው ምንድነው ? በጎንደር ዩንቨርስቲ ዋና ነጥብ የሆነው በዩንቨርስቲው ውስጥ ያለው ትምህርትን የመግደል አምባገነናዊ አስተዳደር በስፋት ተነስቶ እንደነበር ሰልጣኖች ጠቁመዋል።
4. የከተሞችን እድገት በተመለከተ አንጻራዊነት አይታይም የይስሙላ ልማት ፕሮፓጋንዳ እንጂ እድገት የለም መንግስት ባወጣው ህግ በጤናው መስክ ፋርማሲዎች ቫት አያስከፍሉም ይባላል በተዘዋዋሪ ግን የቫት ማሽን አስገብተው እያስከፈሉ ነው ይህ የመንግስትን በዝባዥነት ያሳያል ።ብነጻ ገበያ ሰበብ መንግስት እጁን በገብያ ውስጥ እየከተተ የህዝቡን ንሮ እያደፈረሰ ነው ።ጎን ለጎን የጉምሩክ ቀረጥ የሚጠየቀው ከ እቃው በላይ ነው ይህ ደሞ የከብያውን ትራንዛክሽን እየጎዳው ነው የሚሰራው ለህገር ነው ወይንስ ለዘረፋ ህዝቡ ተማሯል መፍትሄ እንጅ ስልጠና አንፈልግም።
5 መንግስት ሙስኛ ባለስልጣናት ተንሰራፍተዋል እያለ ነው ራሳችሁ ያመናችሁበትን እርምጃ ክመውሰድ ይልቅ እናንተ እርምጃ የምትወስዱባችው ከኢህአዲግ ፖለቲካ ጋር ሲኳረፉ ነው ይህ አግባብ አይደለም ሁሉም ስው በህግ ፊት እኩል መሆኑ ማረጋገጥ የተሳነው መንግስት እንዴት ስልጠና ይሰጣል።
Average Rating