www.maledatimes.com በዓሉይመጣልብዬአሁንምበርበሩንአያለሁ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በዓሉይመጣልብዬአሁንምበርበሩንአያለሁ

By   /   October 4, 2014  /   Comments Off on በዓሉይመጣልብዬአሁንምበርበሩንአያለሁ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 9 Second

 

 


የሰማዕቱደራሲበዓሉግርማባለቤት
     በዓሉይመጣልብዬአሁንምበርበሩንአያለሁ
                                                                                                    /አልማዝአበራ


                             ( በቁምነገርመፅሔትቅፅ 13 ቁጥር 187፣ መስከረም 24/2007  የቀረበ ቃለ መጠይቅ)


በኢትዮጵያሥነፅሐፍውስጥስማቸውጎልቶከሚጠሩትደራስያንመካከልአንዱየሆነውደራሲናጋዜጠኛበዓሉግርማኦሮማይበሚልርዕስባሳተመውመፅሐፉሳቢያመስዋዕትነትንየከፈለደራሲነው፡፡በአፃፃፍቴክኒኩ፤በአጫጭርአርፍተነገሮቹናበድርሰትመዋቅሩአዲስየአፃፃፍብልሃትንአምጠቷልተብሎየሚታመነውደራሲበዓሉግርማየካቲት 24 ቀን 1976 .ከቀኑ 11 ሰዓትላይከቤቱእንደወጣየደረሰበትያልታወቀደራሲነው፡፡የበዓሉመጨረሻከዓመትዓመትሲያነጋግርናየቆየናያውቃሉየሚባሉሰዎችንምስክርነትእንደሻተእነሆ 30 ዓመትሞላው፡፡ይህኑመሰረትበማድረግየሙያአጋሩደራሲናጋዜጠኛአበራለማባለፉትሁለትተከታታይእትሞችየማይጮሁትበዓሉንየበሉጅቦችየሚልመጣጥፉንበቁምነገርመፅሔትላይ አስነብቦናል፡፡ይህንኑመነሻበማድረግየበዓሉግርማንባለቤት/አልማዝአበራንየመፅሔቱአዘጋጅጋዜጠኛታምራትኃይሉበመኖሪያቤቷተገኝቶህይወትከበዓሉበፊትናበኋላምንይመስላል?› ብሏታል፡፡መጨረሻውንየሚያውቁሁሉለህሊናቸውሲሉቢናገሩጥሩነውየምትለው/አልማዝባዶቤትሶስትልጆቹንትቶእንደወጣየቀረባለቤቷንየዓላማፅናትተጋርታልጆቿንአስተምራለወግለማዕረግያበቃችጠንካራሴትናት፡፡በዓሉይመጣልብዬበርበሩንአሁንምአያለሁየምትለው/አልማዝበዓሉመፅሐፉንሲፅፍምንሊመጣበትእንደሚችልያውቅነበርትላለች፡፡

ቁምነገር፡/አልማዝበቅድሚያበመፅሔታችንላይእንግዳሆነሽስለባለቤትሽደራሲናጋዜጠኛበዓሉግርማናስላለፉት 30 ዓመታትህይወትለመነጋገርፍቃደኛስለሆንሽእጅግአድርጌአመሰግናለሁ?

/አልማዝ፡እኔምአመሰግናለሁ፡፡

ቁምነገር፡እስኪወደኋላልመልስሽናበዓሉበመፅሐፉሳቢያከስራከታገደበኋላ6 ወራትያህልቤትውስጥነበርየሚውለው፤እንዴትነበርጊዜውንየሚያሳልፈውየሚለውንንገሪኝ ?

/አልማዝ፡ምንምአይጨነቅምነበር፤ብዙጊዜውንቤትውስጥያሳልፍናከቤትወጥቶዞርዞርብሎይመጣል፤ቤትውስጥበነበረበትጊዜምንምአይጨነቀምመሳቅመጫወትነበር፡፡የትእንደወሰዱትአላውቅምእንጅአንዳንድነገሮችንይፅፍነበር፡፡ 6 ወርቤትውስጥሲቀመጥምንምአልተቸገርንምነበር፡፡እኔእንዲያውምበጣምነውደስያለኝ፡፡

ቁምነገር፡ለምን?

/አልማዝ፡ሥራላይበነበረበትጊዜየትአግኝተነውእናውቅናአሁንነውቤትመዋልሲጀምርበደንብቆምብለንማወራትልጆቹንምአንዳንድነገርማሳየትናማዝናናትየጀመረው፡፡ደሞዝየለንምግንየምንበላውአላጣንምነበር፡፡ሰውቤታችንመጥቶሲመለከትይገረመዋል፡፡ይህሁሉ ነገርሆኖአንቺምአታዝኚምእሱምአያዝንም”ይለናል፡፡እግዚአብሔርይመስገን”ነበርየምላቸው፡፡በዓልዬንተለይቼውአላውቅምነበርቤትውስጥሲቀመጥ፡፡እረፍትያለውሰውአልነበረም፤እሱእንደውምየኔንሁኔታእያየ ‹‹ደስአለሽአይደልአልሚቤትውስጥበመዋሌ›› ይለኝነበር፡፡እንደዚህምሆኖቀንቀንቤትአየዋለመሸትሸትሲልይወጣነበር፡፡ተውአትውጣስለውእሱምንምየሚፈራውነገርየለም፤እንደሚከታተሉትቢያውቅምአይፈራቸውምነበር፡፡ባዶእጁንነበርየሚወጣው፡፡ያኔስራላይበነበረበትጊዜእንኳሽጉጥእንኳየሚይዝሰውአልነበረም፤የኢሰፓደብተሩንምእኔጋርአስቀምጦነበር፣  የሚሄደው፡፡ከስራእንዳገዱትነውራሱሄዶየመለሰላቸው፤ ‹‹ምንምነውትንሽብትቆይ? ባትቸኩልሌላነገርእንዳያስቡብህ›› ስለውባክሽተያቸውበቅቶኛል”ይለኝነበር፡፡

ቁምነገር፡ፅሑፍላይግንእንዴትነበርየሚፅፈው፤ስለበዓሉከሰማኋቸውነገሮችመሀከልአንዱበዓሉማስታወሻሲይዝአይታይም፤ነገርግንአንድመፅሐፍፅፎለመጨረስጊዜአይወስድበትምነበርይባላል?

/አልማዝ፡ትክክልነው፤በዓሉፅሑፍየሚጀምረውምየሚጨርሰውምጭንቅላቱውስጥነው፡፡ብዙጊዜአንድቦታተቀምጦይመሰጣል፤አትኩሮአንድነገርካየተመዘገበማለትነው፡፡ያንጊዜበዓልዬእየፃፍክነውአይደል?አለዋለሁ፡፡ከዚህውጪወረቀትአያገላብጥምአንድጊዜለመፃፍከተቀመጠግንብዙገፅፅፎነውየሚነሳው፡፡

ቁምነገር፡ብዙጊዜየሚፀፈውመቼነውምንሰዓትላይነው?

/አልማዝ፡ከስራመልስነው፤ያውያለውጊዜብቻነው፡፡መስሪያቤትከባድየሥራውጥረትነውያለበት፡፡ከስራከተመለሰበኋላልጆችበጊዜራታቸውንከበሉበኋላነውለመፃፍቁጭየሚለውልጆቹሲተኙቤቱፀጥይላል፡፡

ቁምነገር፡በዓሉምንይወዳል?

/አልማዝ፡ፀጥታይፈልጋል፤ዝምተኛነው፡፡ሁልጊዜዝምነውየሚለው፤ንፅህናይወዳል፡፡ጥሩቤትመኖርይወዳል፤ለሰውያዝናል፤ሙዚቃያደምጣል፤ገንዘብአይዝም፡፡እንደእሱያለውንገንዘብላገኘውሰውሁሉየሚሰጥሰውየለም፡፡የመፅሐፉንሽያጭእንኳበአግባቡየሚቀበልሰውአልነበረም፡፡አንድጊዜእንደውምምንሆነ መሰለህ? አንድመፅሐፉንእንዲያሳትምለትከአንድሰውጋርይዋዋላል፡፡ሰውየውመፅሐፉንሽጦለማተሚያቤትምመክፈልአልቻለም፡፡በዓሉነበርዋስአድርጎያስመዘገበው፡፡ታዲያማተሚያቤቱሰውየውንይከስናቤተሰቦቹንየሚያስተዳድርበትዳቦቤትነገርነበረው፡፡እናዳቦቤትይሸጥናገንዘቡንይውሰድተባለ፤ሰውየውትንሽህመምተኛነበረ፡፡ሆዱእያበጠብዙጊዜታክሟል፡፡ከዛበዓሉጋርሰውየውይመጣናይኽውልህእንዲህሆንኩልህበዛላይታምሜያለሁ”ይለዋል፡፡በዛጊዜበዓሉቤቱይሄዳል፡፡ሲሄድሚስቱልጆቿንይዛምሳሲበሉይደርሳል፡፡እንዴትነው?” ብሎሲጠይቃትበቃቤታችንምሊሸጥነውመውደቂያየለንም”ትለዋለች፡፡በዛጊዜበቃሀራጁነገነውእኔእመልሰዋለሁ፤ሰውሲሰቃይማየትአልፈልግም፡፡ዝምብላችሁተቀመጡልጆችሽንአሳድጊ፡፡”ብሏትወጣሀራጁንምአስቆመው፡፡ያውእሱዋስስለነበርለስንትዓመትያህልስንትሺህብርስገፈግፍኖርኩ፡፡በዓሉእንደዚህአይነትሰውነበር፡፡የተቸገረሰውአይቶማለፍአይችልም፡፡ስብሃትእራሱተናግሮታልየቸገረበዓሉካየቦርሳውይቀድመዋል”ብሏል፡፡ማድረግየፈለገውንየሚያደርገውከራሱተማክሮነው፡፡

ቁምነገር፡የመጀመሪያልጃችሁመስከረምበዓሉ1991 .ገደማይመስለኛልአዲስአበባዩኒቨርሲቲበተዘጋጀፕሮግራምላይተገኝታአንድየተናገረችውነገርነበር፡፡አባቴከአድማስባሻገርአበራወርቁጋርይመሳሰልብኛል፤በመፅሐፉላይአበራ5 ዓመትዘጠኝየኪራይቤትቀያይሯልይላልእኛምያደግነውእንደዛነበር”ብላነበር?

/አልማዝ፡ልክነው፤ቤትእንቀያይራለን፤ዘጠኝቤትቀያይረናል፡፡እቃችንንይዘንመዞርነው፡፡አንዳንድጊዜደግሞእቃችንእዛውትተንለአዲሱቤትየሚሆንሌላዕቃገዝተንነውየምንገባው፡፡ሰፊቤትሲገኝየመጀመሪያስራችንቦታውንበሜትርመለካትነው፡፡ከዛጋርየሚሄድሶፋገዝተንእንገባለን፡፡

ቁምነገር፡ብዙጊዜየምትከራዩትቪላቤትነውወይስአፓርታማ?

/አልማዝ፡ቪላቤትነበርበፊትየምንኖረው፡፡በኋላላይነው፣ እኔወደአፓርታማእንድንገባያደረግሁት

ቁምነገር፡ለምን ?

/አልማዝ፡ቪላቤትየተከራየንጊዜግቢውሰፊነው፡፡ግቢውንየሚጠብቁዘበኛነበሩ፡፡ዘበኛውየተለያዩስራየሰሩሰውሲመጣበርቶሎአይከፍቱም፡፡እሱምበርላይብዙሰዓትይቆምነበር፡፡ከዛበቃአፓርታማእንግባብዬራሴፈልጌነውይህንንቤትያገኘሁት፡፡እሱምአፓርታማነውየሚወደውድሮስብዬአልነበረምብሎገባን፡፡

ቁምነገር፡በዓሉከስራከታገደበኋላቤትውስጥሲውልችግርሊገጥመውእንደሚችልናከሀገርስለመውጣትአያስብምነበር ?

/አልማዝ፡ከሀገርስለመውጣትፍፁምአያስብምነበር፤ችግርሊገጥመውእንደሚችልያውቅነበር፡፡ነገርግንከዚህችሀገርንቅንቅአልልም”ነበርየሚለው፡፡ስለልጆቹምቢሆንወደፊትሲያድጉእውነቱንብቻእንዲናገሩአድርጊያቸውነበርየሚለኝ፡፡ከሀገርስለመውጣትአያስብምነበር፡፡

ቁምነገር፡ግንኢምባሲአካባቢያሉሰዎችጠይቀውትነበርየሚባለውስ ?

/አልማዝ፡ተጠይቋል፤በሞስኮኤምባሲ፣በአሜሪካኤምባሲአንተንብቻሳይሆንመላቤተሰቦችህንእናውጣችሁተብሏል፡፡ግንእምቢነውመልሱ፡፡ህንድኤምባሲምይሄነገርአጉልነውብትወጣይሻልሃልብለውትነበር፡፡እሱግንምንችግርአለውአስቤያደረኩነገርነው፡፡ከሀገሬየትምአልወጣም!”ነበርመልሱ፡፡ወንድሜምውጭሀገርነበርሊያወጣውይችልነበር፤ግንሀገሩንለቆመውጣትአልፈለገም፤እዚሁመስዋዕትሆነ፡፡

ቁምነገር፡ብዙጊዜለአለማቸውፅኑየሆኑሰዎችእንደዚህአይነትጥያቄሲቀርብላቸውባለመቀበልእራሳቸውንብቻነውመስዋዕትየሚያደርጉት፡፡ለልጆቻቸውናለቤተሰቦቻቸውግንየተሻለየሚሉትንነገርአድርገውነውያንንመስዋዕትነትየሚቀበሉ፡፡በዓሉለእናንተለልጆቹላይስለሚደርሰውነገርምንነበርሀሳቡ?

/አልማዝ፡ልጆቹንበቃአንቺአሳድጊነበርየሚለው፤በመፅሐፉሳቢያየሚመጣውንችግርእዚህሀገርውስጥሆኖመቀበልስለሆነየወሰነውምንምነገርቢመጣልጆቹንእንደምንምብለሽአሳድጊነበርየሚለው፤እኔበሰራሁትስራከሀገርወጥቼልጆቼናሚስቴመቸገርመታሰርየለባቸውምነውየሚለው፡፡እዚምእዚያምተሯሩጬስራመስራትእንደምችልያውቃል፡፡በፊትማስታወቂያሚኒስቴርሰርቻለሁ፤ቴሌቪዥውስጥምሰርቻለሁ:: እኔባልኖርልጆቼንልታሳድጋቸውተትችላለችብሎይተማመንብኝእንደነበርነውየምረዳው፡፡ያለምንምጡረታያለምንምገንዘብባዶቤትነውትቶንበወጣበትየቀረው፡፡ግንእግዚአብሔርይመስገንልጆቼንእንደጓደኛአድርጌነውያሳደግኋቸው፡፡ያኔአንተመፅሐፍስትፅፍእኔእየዞርኩእሸጥልሃለሁ”እለውነበር፡፡ደግሞምአድርጌያለሁ፡፡ያኔማስታወቂያሚኒስቴርስሰራበቀን 80 እና 90 ከአድማስባሻገርመፅሐፍንየቢሮእያዞርኩእሸጥነበር፡፡ምሳሰዓትላይምሳለመብላትእንገናኛለን፡፡ዛሬይኸውልህይህንያህልመፅሐፍሸጫለሁ”እለውነበር፡፡

ቁምነገር፡በዓሉየቤትውስጥስራይሠራል ?

/አልማዝ፡ይሠራል፤እኔነፍሠጡርስሆንየቤትውስጥስራዎችንይሠራነበር፡፡ምግብያበስላል፣ቤትማፅዳት፣አልጋማንጠፍየልጆችልብስመተኮስይሠራል፤ከስራየወጣጊዜእነዚህንየቤትውስጥስራዎችንይሠራነበር፡፡

ቁምነገር፡ምግብየሚወደውምንድንነው?

/አልማዝ፡ምግብየሚወደውሩዝነው፤የተወሰነዶሮወጥይወዳል፤ሱፕስቴክይወዳል፤ግንቀንየበላውንምግብማታቢቀርብለትአይበላም፡፡

ቁምነገር፡መኪናይቀያይራልወይስ?

/አልማዝ፡በፊትፔጆመኪናነበረችን፣ከዛእሷንሸጥንናያቺንአዲስቮልስዋገንገዛን፤ለኔምሌላመኪናገዝተንነበር፤ሁለትመኪናአንድቤትምንያደርጋልብለንሸጥናት፡፡

ቁምነገር፡በዓሉማስታወቂያሚኒስቴርውስጥትልቅባለስልጣንነበር፤ቤታችሁአንዳንድትልልቅባለስልጣናትተጋብዘውይመጡነበር? እናንተስተጋብዛችሁትሄዱነበር?

/አልማዝ፡ብዙምአይደለም፤ ግብዣቦታእሱምእንደነገሩነው፤እኔምሲጠሩኝየደርግባለስልጣናትጋርአልሄድምነበር፤ብቻውንሲሄድሚስትህስሲሉትእሷእኮእንደዚህአይነትነገርአይመቻትምነበርየሚላቸው፡፡

ቁምነገር፡ኦሮማይመፅሐፍከወጣናበገበያላይተሰብስቦከተቃጠለበኋላኮለኔልመንግስቱቤተመንግስትድረስአስጠርተውትእንደተናገሩትለገነትአየለበሰጡትቃለምልልስላይተናግረዋል፤የዛንዕለትምንነበርየተነጋገሩት? ምንነግሮሽነበረበዓሉ ?

/አልማዝ፡በእርግጥጠርተውትአነጋግረውታል፤ነገርግንበመፅሐፉላይሰውየውእንደሚሉትአይደለምየተነጋገሩት፤ውሸትነውየሚናገሩት፡፡የዛንዕለትተጠርቶየሄደውብቻውንአልነበረም፤የሸዋረንየተባለውህንድሰውነበርአብሮት፡፡እንደገባሊቀመንበሩያሉት ‹‹ ምነውበዓሉከዚህበፊትበቀይኮከብጥሪአብዩቱንእንደዛአድርገህሳልከው፤አሁንደግሞበዚህመፅሐፍመንጋጋውስጥነውከተትከን፤አንተምሁርነህ፤አብዩቱንስወታደሩንስለምንእንደዚህትላለህ?” አሉት፡፡ ”ሲጋራቸውንይዘውወዲያናወዲህይሉነበር”ብሎኛል… ”ለምንአላሳየኸኝምከመውጣቱበፊት”ምብለውትነበር፡፡

ቁምነገር፡በዓሉምንአላቸው?

/አልማዝ፡ምንምአላለ፤እንደዛእየተቆጡሲናገሩዝምብሎሲያዳምጥቆይቶእኔዘመቻላይሆኜያየሁትንነውየፃፍኩት፤ወልደማርያምሀብተማርምብዬየተናገርኩትየጠቀስኩትሰውየለም፤እኔስለሀገሬነውየፃፍኩት፡፡እዛውስጥተጠቅስናልየሚሉሰዎችስራቸውንየሚያውቁትናቸው፡፡ኢትዮጵያየጋራሀገራችንናትብያለሁ፡፡እጅመሰንዘርምዋጋየለውም፤ከዚህውጭያልኩትነገርየለም”ሲላቸው ‹‹ይሄውነውአቋምህ?” አሉት፡፡ ‹‹አዎያሄውነው›› ሲላቸው ‹‹በቃሂድውጣ›› ብሎአስወጣው፡፡ከዛበኋላስራቸውንሰሩ፡፡ከስራየተሰናበተበትንደብዳቤእንኳሚኒስትሩሊሰጡትሲጨነቁግድየለምፈርሙበትናመጥቼእወስደዋለሁ”ብሎያላቸው ‹‹በዓሉይህነገርመጣእንዴትአድርጌጽፌልስጥህ?›› ብለውትስለነበር ነው፡፡

ቁምነገር፡በዓሉየመንግስትከፍተኛባለስልጣንከመሆኑአንጻርየዚህአይነትውሳኔ /እርምጃ/ ላይይደርሳሉየሚልግምትነበረሽ ?

/አልማዝ፡በዓሉባለስልጣንቢሆንምእኮፍልጎትአይደለምየሚያሰሩትስልጣንየማይፈልግየማይወድሰውመሆኑንያውቃሉ፤እሱየሚፈልገውመፃፍብቻነው፤ግንየተማረሰውአጣንብለውነውበግድያስገቡት፡፡ቢሮውእንኳሲያመሽቢሮውመስኮትስርታንካቸውንእያስጠጉነበርየሚያስጠብቁት፤እንደማይወዳቸውያውቁነበር፡፡አንድጊዜእንደውምውጪሀገርእንግሊዝሀገርንግስትኤልሳቤትጋርደርሶሲመለስሊቀመንበሩ ‹‹ምንአለችህ?›› ብለውትበተናገረውነገርተናደውነበር፡፡

ቁምነገር፡ምንድነው ?

/አልማዝ፡የዛንጊዜየንጉሳውያንቤተሰቦችታሰሩበትጊዜስለነበር፤በኢትዮጵያእስረኞችበዝተዋል፤የንጉሳውያንቤተሰቦችንምብትለቋቸውእዚህእኔ ዘንድመጥተውይኖራሉ”ንግስቲቱማለቷንእንደመጣለሊቀመንበሩ  ነግሯቸውተቆጥተውነበር፡፡እንዲያውምበዓሉየንግስቲቱንሀሳብደግፎይፍቀዱናሰዎቹንእንግሊዝሀገርአድርሻቸውልምጣ›› በማለቱእንዴትነውየምትደፍረን?” ብለውታል፡፡በእንዲህእንዲህአይነትአጋጣሚዎችአቋሙንያውቁታል፡፡

ቁምነገር፡በመፅሐፍድርሰትሥራቤተሰብንመምራትማኖርይቻላልየሚልእምነትነበረው?

/አልማዝ፡የለውም፤ለስሜትያህልነውየሚፅፈውእንጂየድርሰትገቢያንያህልአይደለም፤ገቢቢኖርምአሳታሚናማተሚያቤትነውየሚወስዱት፤ደራሲየሚያገኘውነገርየለም”ነውየሚለው፡፡

ቁምነገር፡ከስራከታገደበኋላበሌላ/ቤትሥራየመጀመርሀሳቡአልነበረውም ?

/አልማዝ፡ጀርመኖችጋርስራአግኝቶመንግስት/ቤትከሚያገኘውደሞዝበሁለትሶስትእጥፍሊቀጥሩትሲሉነውየወሰዱት፤ከዛምበኋላወረቀትአግኝተናልየሚሉትይህንንየጀርመኖችድርጅትጋርየተፃፃፈውንወረቀትነው፡፡

ቁምነገር፡ከቤትወጥቶከጠፋበኋላምንአደረግሽ ?

/አልማዝ፡ምንአደርጋለሁ? ያወቃሉየምላቸውሰዎችጋርሄድኩ፡፡ምንምነገርየለም፤እዚህቦታሲሉኝተነስቼእሄዳለሁ፡፡ሸሚዝከአንድቀንበላይየማያደርገውበዓሉእስርቤትነውያለውሲሉኝየሸሚዝመአትይዤእዞራለሁ፡፡ሁሉምመልሳቸውአንድነው፡፡ከንፈራቸውንመጠውየለምነውየሚሉኝ፡፡ክፉዘጠኝዓመትያለፈውበመከራነው፡፡በዛላይከቤቴወጥቼወደየትምብቻዬንመሄድአልችምነበር፡፡ 24 ሰዓትይከታተሉኛል፡፡ልጆቼን/ቤትሳደርስይከተሉኛል፤የሆነገበያስሄድይከተሉኛልወደበኋላላይግንለመድኳቸውናሰውእንደሚከተለኝእንኳረሳኋቸው፤እኔመፃፍስለማልችልነውእንጂያሳለፍኩትህይወትራሱመፅሐፍየሚወጣውነው፡፡

ቁምነገር፡የበዓሉግርማፋውንዴሽንያቋቋመውማነው?

/አልማዝ፡መስከረምናዘላለምናቸውእዛውአሜሪካያቋቋሙት፡፡መስከረምበዓሉሲጠፋ13 ዓመትልጅነበረች፡፡ግንአንዳንድነገሮችታውቅነበር፡፡ዘላለምትንሽልጅይሁንእንጂያውቃል፡፡እሷምእሱምማስተርስድግሪያቸውንከያዙበኋላነውፋውንዴሽኑንያቋቋሙት፡፡መስከረምበልጅነቷአንባቢልጅነበረችማስተርስድግሪዋንየሰራችውምበጋዜጠኝነትነው፡፡

ቁምነገር፡ፋውንዴሽኑምንምንስራዎችንይሰራል ?

/አልማዝ፡የተለያዩስራዎችንይሠራል፡፡ልጆቼእየተማሩስለነበረየፋውንዴሽኑስራየሚያንቀሳቅሱትእንደሚፈልጉትአልሠሩበትም፡፡ግንእስካሁንባለውጊዜበበዓሉስምየተለያዩደብተሮችንእስክርቢቶዎችንአሳትመውበሀገርውስጥለተለያዩችግረኛተማሪዎችአከፋፍለዋል:: ወደፊትደግሞቅርንጫፍ/ቤትእዚህየመክፈትሀሳብአላቸው፤የበዓሉየተለያዩሥራዎችናፎቶግራፎችአሰባስበውበሙዚየምመልክየማስቀመጥናቀጣዩትውልድእንዲማርበትየማድረግሀሳብመስኪአላት፡፡

ቁምነገር፡የትውልድሀገሩኢሊባቡርጎሬበስሙ/ቤትተሰይሟልአይደል ?

/አልማዝ፡የመንግስት/ቤትነውበስሙየተሰየመለት፤ተጠይቄበደብዳቤአስፈቅደውኝነውየሰየሙትናበትውልድቦታውብዙልጆችየሚማሩበት/ነው

ቁምነገር፡እናቱእዛነበርየሚኖሩት ?

/አልማዝ፡አዎቅርብጊዜ ነውያረፉት፡፡አንድወቅትላይአዲስአበባአስመጥቻቸውነበር፡፡የኔእናትምበጣምተወደውነበርእዬዬእያለችነውየሞተችው፤እናቱየባላባትልጅስለሆኑሀብታምነበሩ፤አርሻናወፍጮቤትነበራቸው፡፡የቡናመፈልፈያምነበራቸው፤ተወርሶባቸውነበርኢህአዴግከገባበኋላነውእኔጠይቄየመለሰላቸው፡፡

ቁምነገር፡– 30 ዓመታትረዥምጊዜነው፤ምንከፉናደግነገርታስታውሻለሽከበዓሉበኋላ ?

/አልማዝ፡ልጆቼንጥርሴንነክሼአሳድጌለወግማዕረግማብቃትበመቻሌእግዚአብሔርንአመሠግነዋለሁ፡፡ልጆቼአባታቸውከቤቱወጥቶእንደቀረባቸውሳይሳቀቁየሚፈልጉትንነገርእያሟላሁላቸውየሚፈልጉትቦታበዓሉበነበረጊዜየምንወስዳቸውቦታሶደሬላንጋኖእየወሰድኩሳይሰማቸውነውእንዲያድጉያደረግሁት፡፡ሁለቱአሁንአሜሪካሀገርተምረውተመርቀውትዳርይዘዋልትንሹክብረበዓሉአብሮኝአለ፡፡ለዚህምእግዚአብሔርንአመሠግነዋለሁ፡፡ነገርሆኗልከዛውጪያለውነገርየሚነሳአይደለምክፉጊዜነበር፡፡

ቁምነገር፡መንግስትሲቀየርምንታስቢነበር፤በዓሉታስሮምከሆነየሆነ ቦታይገኛልብለሽታስቢነበር?

/አልማዝ፡እጠብቅነበር፤ተስፋአደርግነበር፡፡ግንያውየዛንጊዜመንግስትእንደተቀየረበሬዲዮአንድነገርሲነገርሰማሁ፤አንድበወቅቱሹፌርነበርኩሊገረፍሲልአመላልሰውነበርያለሰውአውቃለሁየሚለውንሲናገርስሰማራሴንስቼወደቅሁ፡፡ከዛበኋላየማውቀውነገርየለም፡፡በኋላበቤታችንዙሪያእኔምንምሳላውቅ ‹‹ከቤቱእንደወጣየቀረውደራሲናጋዜጠኛበዓሉግርማ›› ብለውፎቶውንሁሉአባዝተውበየህንፃውላይለጥፈውተመለከትኩ፡፡በዓሉየሚወዳትንሚስቱንትቶ፤የሚወዳቸውንሶስትልጆቹንትቶከቤቱእንደወጣለሀቅየወደቀሰውነው›› ይላልየተለጠፈውበከተማውላይ፡፡ሰዎችይህንንከተማላይየተለጠፈውንአይተውእያለቀሱቤቴድረስመጡ፡፡ እኔግንአሁንምድረስበዓሉይመጣልብዬበርበሩንነውየማየው፤ግንአንዳንድጊዜደግሞበግሌበነፍስካለበእኛላይእንዴትሊጨክንናሊጠፋይችላል? እላለሁግንአሁንምድረስእንዲህነውየሚልሰውአላገኘሁም፡፡

ቁምነገር፡መንግስትእንደተቀየረየኢህአዴግባለስልጣናቱንአግኝተሸየበዓሉንግድያያውቃሉከሚባሉትሰዎችጠይቃችሁእባካችሁአሳውቁኝአላልሻቸውም ?

/አልማዝ፡ብያለሁ፤ወዲያውእኮነውባለስልጣናቱከታሰሩበኋላለተቋቋመውልዩአቃቤህግክስሲመስረትቃሌንሰጥቻለሁ፤ለፍ/ቤቱየሰጠሁትቃልለታሪክተመዝግቦይገኛል፡፡መላየኢትዮጵያህዝብሁሉስለበዓሉመጨረሻየሚያውቁትእንደነግሩኝጠይቄያቸዋለሁ፤ግንአቃቤህጉ፤ ‹‹በዓሉግርማያለ ፍርድየተገደለነው›› ብለውደብዳቤፅፈውሰጥተውናል፡፡ምንያደርጋልበዓሉግርማለህዝብብሎለሀቅብሎየተሰዋደራሲነው፡፡ግንአንዳንድሰዎችያልሆነነገርሲናገሩሲፅፉአያለሁ፡፡ለምሳሌበዓሉግርማገዳምውስጥነውያለውብለውበሬዲዮሁሉቅርብጊዜሲናገሩነበር፡፡እዚህታይቷል፤እዚያነውያለውየሚሉናየሚፅፉመፅሔቶችአሉ፡፡የበዓሉንማንነትተረድተውሀቅቢያወጡነበርየምፈልገው፡፡የቤተሰቡሀዘንከመጨመርውጪዋጋየላቸውም፡፡ስለበዓሉየተፃፉማናቸውምነገሮችአያመልጡኝም፤ግንእውነቱንየሚናገርየለም፡፡የወደቀበትንየሚናገርየለም፡፡

ቁምነገር፡ኦርማይመፅሐፉእንደወጣነበርየታገደውናከገበያላይየተሰበሰበውሰውእጅገብቶነበርለማለትይቻላል?

/አልማዝ፡የገዙሰዎችእያከራዩያስነብቡነበር፤ሽያጭም 600 ብርደርሶነበር፡፡

ቁምነገር፡መታገዱንያወቃችሁትእንዴትነበር ?

/አልማዝ፡እኔመርካቶለቅሶለመድረስስሄድሰዎችየበዓሉግርማመፅሐፍከገበያላይእየተሰበሰበነውሲሉሰማሁ፡፡ደንግጪቦርሳዬንከነገንዘቡየትቦታእንደጣልኩትአላውቅም፤ስበርቤትስደርስ ‹‹ዳዲመጥቶነበር፤መፅሐፉከገበያላይእየተሰበሰበስለሆነአታስቢ›› ብሎሻልአሉኝልጆቼ፤እሱለካቀድሞአወቋል፡፡

ቁምነገር፡በወጣበስንተኛውቀንመሆኑነው?

/አልማዝ፡የተሸጠው10 ቀናትብቻነው፡፡ልክ10ኛውቀንነውየሰበሰቡትናያቃጠሉት

ቁምነገር፡ቤትውስጥመፅሐፉንአምጥቶትነበር?

/አልማዝ፡ያውሁሌምእንደሚያደርገውለሰዎችበስጦታመልክየሚሰጠውንየተወሰኑመፅሐፍትአምጥቶነበር፤ልክያንንየሰማሁዕለትአንዷንመፅሐፍወስጄደብቄያትአሁንምድረስአለ፡፡

ቁምነገር፡በታተመውእናበቀድሞውመፅሐፍመሀከልልዩነትአለየሚሉወገኖችአሉ፤የተቀነስነገርአለእንዴ?

/አልማዝ፡ራሱነውየታተመው፤ያውኢህአዲግእንደገባየወቅቱየማስታወቂያውሚኒስትርአቶበረከትነውራሱጠርቶኝልክእንደወረደመፅሐፉይታተምለትብሎትዕዛዝየሰጠልኝ፡፡ያውድጋሚሲታተምለመታሰቢያይሁንብዬየሆነነገርማስታወሻፃፍኩለት፤አብሮ ታተመ፡፡

ቁምነገር፡ቤቱንልቀቂተብለሽነበር ?

/አልማዝ፡እነሱማበላዬላይሁሉሊያሽጉመጥተውነበር፡፡በርላይጠብቄዞር በሉአልኳቸው፤በማግስቱየኪቤአድዋናስራአስኪያጅጋርሄጄባለቤቴከቤትእንደወጣአልተመለሰም፡፡ሶስትልጆቼንይዤየትልወድቅነው?” ስለውባለቤትሽማነው?” አለኝ፤ ”አላውቅም”አልኩት፡፡ወታደርነው?” አለአይደለም፡፡ማነው?” ሲለኝአልናገርም”አልኩት፡፡እሺለጊዜውሰውእያነጋገርኩነውከቢሮውጪጠብቂኝአለኝ፤ከቢሮስወጣፀሐፊውአየችኝ፤አወቀችኝከዛገብታነገረችውመሰለኝእንግዶችንከሸኙበኋላ ‹‹የበዓሉግርማባለቤትመሆንሽንለምንአልነገርሽኝም?›› አለኝ፤ ”ለምንእነግርሃለሁ?” አልኩት፡፡የአንቺጉዳይበጣምከባድነው፡፡ለማናቸውምምንልርዳሽ?” ብሎ 100 ብርከኪሱአውጥቶሊሰጠኝእጁንዘረጋ፡፡እኔልመናአልመጣሁም፤ምፅዋትህንቤተክርስትያንሄደህስጥ”አልኩትና ‹‹ባሌወንድነውእኔምየወንድልጅነኝእስኪማነውመጥቶየሚያስወጣኝአያለሁ›› ብየውወጣሁ፡፡ከዛበኋላአልመጡም፤ክትትሉግንእንዳለነበር፡፡

ቁምነገር፡በመጨረሻያንክፉጊዜከነልጆቸሽስታሳልፊአይዞሽሲሉየነበሩአንቺንምበዓሉንምሳያውቁግንየሚቆረቆሩበብዕራቸውምየሚጠይቁሰዎችይኖራሉናየምታመሰግኚያቸውሰዎችአሉ ?

/አልማዝ፡በጣምብዙሰዎችአሉ፤ያንጊዜእኮመንገድላይሁሉሰዎችይሸሹኝነበር፤ፊታቸውንሁሉየሚያዞሩነበሩ፡፡ስንትነገርአብረንያሳለፍንሁሉለእግዚአብሔርሰላምታይፈሩነበር፤የሆነሆኖጊዜአለፈ፡፡በመጀመሪያየኢትዮጵያመፅሐፍትድርጅትባለቤትአቶተስፋዬዳባብዙመፅሐፉንያሳተሙለትባለውለታችንነው፤አቶአማረማሞ፣ደራሲአበራለማ፣አመሰግናቸዋለሁ፡፡/ሙለጌታበዛብህየቅርብጓደኛውነውይጠይቀኛል፤የልጆች/ቤትያግዘኝነበር፤አቶጌታቸውብናልፈውሳይፈራየሚጠይቀኝሰውነው፡፡አቶእስቂያስአገኘውቤተሰብነው፡፡ከኔያልተለየሰውነው፡፡እግዚአብሔርውለታቸውንይክፈላቸው፤ብድራቸውንይመልስላቸውነውየምለው፤ፕሮፊሰርመስፍንወልደማርያምቤተሰብነበር፤አሁንአሁንሲታሰርሁሌሄጄእጠይቀውነበር፤ከበዓሉጋርምይግባቡነበርየወንድሜምጓደኛነው፡፡

ቁምነገር፡በወቅቱከነበሩመንግስትባለስልጣናትመሀከልአንዳንዶቹበአሁኑወቅትከሎኔልመንግስቱንጨምሮመፅሐፍእየፃፉነው፤ስለበዓሉግርማመጨረሻየሚያውቁትንነገርእንዲናገሩምንመልእክትታስተላልፊያለሽ ?

/አልማዝ፡እኔየምላቸውነገርየለም፤የሚያውቁትንግንለኢትዮጵያህዝብቢናገሩእውነቱንቢያወጡጥሩነውለህሊናቸውቢሆንሀቁንቢያወጡደስይለኛል፡፡

ቁምነገር፡ደርግግንይወድቃልብለሽታስቢነበር ?

/አልማዝ፡ለምንአይወድቅም? ጃንሆይምወርደዋል፤ደግሞየእነሱግፍይበልጣል፣ግፉራሱይጥላቸዋልብዬነበርየማስበው፡፡

ቁምነገር፡በዓሉከቤትከወጣበኋላመኪናውቃሊትአካባቢቆማነበርተብሏልእንዴትአገኘሻት ?

/አልማዝ፡ያውበየዕለቱወዲያወዲህእያልኩበየእስርቤቱሁሉእጠይቅነበር፤10 ኛውቀንቃሊቲመንገድዳርቆማለችብለውነገሩኝ፤ሄጄጠይቄልወስድብዬአስፈቀድኩ፤መኪናተመድቦአጅበውኝመኪናዋንከቆመችበትአመጣናትናግቢውስጥአቋምኳት፡፡ጠዋትጠዋትባየኋትቁጥርመበሳጨትስላልፈለግሁሸጥኳት፡፡

ቁምነገር፡አመሠግናለሁ፤

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on October 4, 2014
  • By:
  • Last Modified: October 4, 2014 @ 1:57 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar