www.maledatimes.com ዩ ቲዩብ የጃኪ ጎሲን ፊያሜታ ዘፈን ድምጹ እንዳይሰማ አገደ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዩ ቲዩብ የጃኪ ጎሲን ፊያሜታ ዘፈን ድምጹ እንዳይሰማ አገደ

By   /   September 27, 2014  /   Comments Off on ዩ ቲዩብ የጃኪ ጎሲን ፊያሜታ ዘፈን ድምጹ እንዳይሰማ አገደ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 36 Second

ካለማንም ፈቃድ የድምፃዊ ተሾመ አሰግድን ‘የኔ አካል’ ዘፈን አቅርቦ የነበረውና በድምጻዊውም ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶበት የነበረው ጃኪ ጎሲ ፊያሜታ በሚል የሠራው ነጠላ ዜማ ዘፈኑ ከሌላ ድምጻዊ የተሰረቀ በመሆኑና ይህም አቤቱታ ስለደረሰው  የቲዩብ ምስሉ እንጂ የቪድዮ ድምፁ  እንዳይሰማ መታገዱ ታወቀ።

ከጃኪ ጎሲ ኦሺፌሻል ዩቲብ ገጽ ላይ ዘ-ሐበሻ ባገኘችው መረጃ መሠረት ፊያሜታ የሚለው ዘፈን ክሊፑ የሚታይ ሲሆን ድምጹ ግን ታግዷል። ዩቲዩብ ከቪድዮው ሥር በሰጠው መግለጫ “This video previously contained a copyrighted audio track. Due to a claim by a copyright holder, the audio track has been muted” ይላል።
jackey
ጃኪ ጎሲ ፊያሜታ የሚለውን ዘፈን ፍጹም ዮሐንስ የተባለ ኤርትራዊ ድምፃዊ ቀድሞ የተጫወተው ሲሆን፤ ጃኪ ይህን ዘፈን ከዚህ ድምጻዊ ወስዶ ሲሰራ አንዳችም ክሬዲት አለመስጠቱና የራሱ አስመስሎ ማቅረቡ ሲያስተቸው ቀይቷል። እንደውም ይህ ዘፈን የጃኪ የራሱ ፈጠራ የሚመስላቸው ሰዎች ያሉ ሲሆን እውነታው ግን ከፍጹም ዮሐንስ የተወሰደ መሆኑን የተረዱ የጃኪን የዘፈን ስርቆት በእጅጉ እያወገዙ ይገኛሉ።

ጃኪ በዩቲዩብ ዘፈኑ እንዳይሰማ ከታገደ በኋላ የራሴ ነው ብሎ ሲጠቅሰው የነበረውን ዘፈን ክሬዲት እንደሰጠ ለማስመሰል ከታገደው ቪድዮ በታች “I wanna say thank you to singer Fitsum Yohannes to his contribution on the chorus part of this song’s melody!!!” የሚል አስተያየት ለመጻፍና ሕዝብን ለማታለል መሞከሩ ብዙዎችን ያሳዘነ ሲሆን ይህም ከስህተቱ አለመማሩን የሚያሳይ ነው ሲሉ ይተቻሉ። ለድምጻዊው ቀድሞ ሳይታገድ በፊት እውቅና መስጠት እንዳለበት የሚተቹት አስተያየት ሰጪዎች ዘፈኑ ከታገደ በኋላ የሚያደርገው መፍጨርጨር ለትዝብት የሚጥለው ነው ይላሉ።

እነዚሁ የጃኪን የዘፈን ስርቆት የሚቃወሙ ወገኖች ወጣቱ ድምጻዊ መልካም ድምጽ ያለው እንደመሆኑ የራሱን ፈጠራ መጠቀም ይኖርበታል። ከዚህ ቀደም የተሾመን ሰርቆ በመሥራት እውቅናን ለመጎናጸፍ ሲበቃ፤ ቀጥሎ የፍጹም ዮሐንስን ዘፈን ወስዶ ገንዘብ አትርፎበታል። ተሾመ ምንም ሊያደርግ ባይችልም በፍጹም ፊያሜታ ዘፈን ግን ከዩቲዩብ በድምጽ መታገድ ሰለባ ሆኗል ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች። ጃኪ አሁን ደግሞ የሰማኸኝ በለውን ባላገር ዘፈን አንዳችም ክሬዲት ሳይሰጥ በየመድረኩ የራሱ በማስመሰል እየተጫወተ መሆኑን በመጥቀስ አስተያየት ሰጪዎች ድምጻዊው ከእድገት የውድቀትን መንገድ እየመረጠ መሆኑን ይጠቅሳሉ።

በተለይም ድምፃዊው አንጋፋውን ድምጻዊ ቴዎድሮስ ታደሰን ከመድረክ ጀርባ ማንጓጠጡን ተከትሎ አሁን ካለው የስርቆት እገዳ ጋር በተያያዘ ጃኪ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብቷል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

የጃኪ ጎሲን ፊያሜያታ ከዩቲዩብ መታገዱን ለማረጋገጥ ሊንኩ ይኸው፦http://youtu.be/MxCB354Druo

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on September 27, 2014
  • By:
  • Last Modified: September 27, 2014 @ 1:50 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar