www.maledatimes.com ወደ ውስጥ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ወደ ውስጥ

By   /   September 27, 2014  /   Comments Off on ወደ ውስጥ

    Print       Email
0 0
Read Time:52 Second
 
(አትክልት አሰፋ – ቫንኩቨር)
 
ዝናብይቀጥቅጠኝ፤በረዶውምይውረድ
ፀሀይምያቃጥለኝ፤ሰውነቴንያንድድ፣
ናፍቆትያስቃየኝ፤እድሜምይሩጥይለፍ፤
ሆዴንይቦርቡረው፤አንጀቴምይንሰፍሰፍ፣
በሩቅ ፍቅር ራብ፤ ልታረዝ ልጠማ፣
ይንከራተት ልቤ፤ በሃሳብ ቁዘማ።
 

           
ምስክርባልሆንም፤አጠገብሽሆኘ፣
           
በክፉበመጥፎ፤ስምሽእየናኘ
           
ሃዘንሽበርትቶ
           
ጣርሽተበራክቶ፣
           
የልጅያለህስትይ፤ጆሮየእየሰማ፣
           
ፍቅርሽሆዴቀርቷል፤ውስጤንእያደማ።
           
ከጉያሽባልሆንምመከራሽሲበዛ፤
           
ስቃዩውስጤአለተቅምጧልበዛ።
 
ጉዳትሽ፣ውርደትሽ፤ሀዘን ሆነ ደስታ
ይደርሳል፣ ይመጣል፤ ካለሁበት ቦታ።
     ሰዎች ተገደሉ፣ ልጆችሽ ተራቡ፣
     ወጣቶችሽ ሁሉ፤ በርቼሌ ገቡ፣
     ሙስናው በረታ፣ መብቶች ተጣሱ
     ጎሳ ተንሰራፋ፣
     ማንነትሽ ጠፋ፤
     አንችነትሽ ከፋ፤
     ፍቅር ረከሰ፣
     መተማመን ጠፍቶ፤ ፍራቻ ነገሰ።
 
ሁሉም ይዳረሳል፣ በወሬ ነጋሪ
ይመጣል ሰንጥቆ ባህርን ተሻግሮ
ነፋስንም ቀዝፎ፣ ባየር ተወርውሮ።
 
እጅግ ያሳቅቃል፤ ከርቀት ሲሰማ
ይቅርብኝ አይሉት ያንችን ነገርማ።
መዳኒት የሌለው፤ ፈውስ አይገኝለት፣
ተስፋ ብቻ ቋጥሮ አሻግሮ መመልከት።
የስቃይ ተካፋይ፣ የታሪክ መስካሪ
ሆኖ አለመገኘት፤ ያማል ውሰጥ ያደማል፣
ስቃይን ያበዛል፣ ወደ ውስጥ ይፈሳል።
 
          ግና
         
          ግና ከጎንሽ ነኝ የቅርብ ሩቅ ሆኜ
          ባህር ተሻግሬ ለመኖር ወስኜ
          ሲያምሽም ልታመም፤ ስት’ቆስይም ልቁሰል
          ላ’ይንሽ እስኪያበቃኝ ስቃዩ ይከመር
          ራብሽ ይሰማኝ፤ ጠግቤ ልታረዝ፣
          የሆንሽውን ሳልም ባሳብ ልጠማዘዝ።
ግና
 
ግና እነግርሻለሁ… ስትጮሂ እጮሃለሁ
የስቃይሽን ልክ ላ’ለም አሰማለሁ።
 
ዝናብይቀጥቅጠኝ፣በረዶውምይውረድ
ፀሀይምያቃጥለኝ፣ሰውነቴንያንድድ፤
ናፍቆትያስቃየኝ፣እድሜምይሩጥ፤ይለፍ
ሆዴንይቦርቡረው፣አንጀቴምይንሰፍሰፍ።…
 
ውስጤን በመሃላ ካንቺው አጣብቄ፤
ላልከዳሽ፣ ላልረሳሽ፤ ቃሌንም ጠብቄ
ልኖር ወስኛለሁ ከጉያሽ ርቄ።
 
ተጠናቀቀ ሴፕቴምበር 26/2014 8፡33 ማታ (ቫንኩቨር)
 
 
 
 
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on September 27, 2014
  • By:
  • Last Modified: September 27, 2014 @ 5:06 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar