www.maledatimes.com የኤምባሲው ግርግር …. - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኤምባሲው ግርግር ….

By   /   October 1, 2014  /   Comments Off on የኤምባሲው ግርግር ….

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 3 Second

Abdi Seid

<<. . . በስውዲን የሚገኙት የኢትዮጵያ ተማሪዎች በስቶክሆልም የሚገኘውን የኢትዮጵያ መንግሥት ኤምባሲ ለ6 ሰዓት ያህል ከያዙ በኋላ፣ በውስጡ የነበረወን የፕሮፓጋንዳና የመፃደቂያ እቃ - ጽሑፍ፣ ስዕል፣ ፎቶግራፍ - አንድ በአንድ እየለቀሙ አውድመው ኤምባሲው ግድግዳ ላይ የተቃውሞ ድምፃቸውን የሚያሰሙ ጽሑፎችንና የኢትዮጵያን ትክክለኛ መልክ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ለጥፈዋል። ኢምባሲው ውስጥ እንደገቡ ለደረሱ ጋዜጠኞች ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ ችግር፣ የኢትዮጵያን አሰቃቂ ሁኔታ በዝርዝር ለማስረዳት ችለዋል። >>

ይህ ዛሬ የተከናወነ ጀብዱ እንዳይመስልህና እርስ በርስ መቧቀስህን እንዳትጀምር ደሞ… የዛሬ 45 ዓመት ገደማ ጥር 25 ቀን 1962 ዓ.ም የተፈፀመ ድርጊት ነው… ‘በአጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ’ ከሚል መጽሐፍ ነው የቀነጨብኩት…

እነሆኝ ዛሬም “የኢትዮጵያን ትክክለኛ መልክ” ለማሳየትና ‘የሕዝቦቿን ችግርና ስቃይ’ ለማስረዳት ስንዳክር አለን… እዛው የኃቻምናው ጎዳና ላይ… ተኩሱ – ውዥንብሩ – ትርምሱ – ሁሉ አንድ ዓይነት ነው… ልዩነቱ ይሄኛው የቀስተደመና ቀለም ስብጠራ… አንበሳና መስቀል ምርመራ… ጨረቃና ኮከብ ቆጠራ… ምናምን የሚሉ አጀባዎች ተጨምረውበታል… ኧረ መስቀልና ማውረድም አለ!… ያውርዳችሁ አቦ!

ለመሆኑ ትክክለኛ መልካችን የቱ ነው? ድህነታችን… ኋላቀርነታችን… ለማኝነታችን አይደሉምን? ስለሌላው መልክህ መጨነቁን ተውና ና በነዚህ ላይ አብረን እንስራ… ያኔ ከምትመኘውም በላይ ውብ መልካችን ይወጣል… ያኔ የሚያደንቁንም ይበዛሉ… ያኔ ብትፈልግ ‘የናቁን ሁሉ ከጫማችን ሥር ይሰግዳሉ’… ‘እስቲ ያርግልን!’ እንዳትለኝ ብቻ!… ማንም የሚያደርግልህ የለም!… ከፈለግክ አንተ ራስህ ታደርገዋለህ… ካልፈለክ ደግሞ ያው ባለህበት እንደረገጥክና በነገር እንደታመስክ ትሞታለህ!… ጉዞው ቀላል እንዳይመስልህ!…

ያው ነው!…

ሀምሳ ዓመት ሙሉ ባለህበት እርገጥ!… ገና ቀጣይ ብዙ አመታትም ባለንበት እንረግጣለን!… እውነት ነው!… አሳምረን እንጨመላለቃለን!… ለውጥ በእውቀትና በብቃት የመርታት ውጤትም ጭምር ሲመጣ እንጂ እንዲሁ በግርግር ሲመጣ ፋይዳው እምብዛም ነው… ምናልባትም ውጤቱ ከሌላ ግርግር አይዘልም ይሆናል… ከሌላ ድብድብ ፈቅ አይልም ይሆናል…. ከዚህ መሰሉ ለውጥስ ቢቀር ይሻላል አይባል ነገር እንዲቀር የሚፈለግ ነገርስ አለ እንዴ?… እንደው ግራ የገባ ነገር!… ግራ ይግባችሁ አቦ!

ግንብ ግንብ አትበለኝ እስቲ!…

ግንብ ቢገነባ እውነት እንዳይመስልህ!… ከህንፃ ጋር አብሮ ሰውም መገንባት አለበት… ሰው ሳትሰራ ድንጋይ ብትደራርብ ያው የድጋይ ክምር ብቻ ነው!… ድንጋይ ደግሞ ድንጋይ ነው – ሰው ነው ውበቱ… የሰው ሥልጣኔ ነው ድምቀቱ… የሰዎች የሀሳብ እድገት ነው ርቀቱ!… እነዚህን ጌጦች አብሮ ያልያዘ ግንብ ድንቁርና በተባለ ድማሚት አፈር ድሜ ሊግጥ ይችላል… ዋስትና የለም!… ዋስትናህ ሰዎችን በመስራት ኋላቀርነትን ማሸነፍ ብቻ ነው!…እሱ ደግሞ በምኞት ብቻ አይመጣም!… በትጋትም ጭምር እንጂ!… ለግንብም ለሰውም ትጋ!… ያኔ ጉዟችን መስመር ያዘ እንላለን …

መንገድም እንደዛው!…

መንገድ ብትሰራም እውነት እንዳይመስልህ!… ጎዳናው ላይ በስኬት ሊራመዱ የሚችሉ ሰዎችን ሳትፈጥር… “የራሴን የስኬት መረማመጃ እያበጀሁ ነው” ብሎ አብሮህ የሚለፋ ወገን ሳታሰልፍ… “የልጄን ጎዳና እያቀናሁ ነው” የሚል ወላጅን ሳታሳትፍ…. እንዲሁ ጥርጊያ መንገድ ብትሰራ አንተኑ እያሳሳቀ ዳር ድረስ ይጠርግህና ለቀጣህ መንገደኛ ያስተላልፍህ ይሆናል እንጂ የመንገዱን ትሩፋት አያቋድስህም!… ትሩፋትህ እኔ ነኝ! – እኔ “ይህ መንገድ የኔ ነው!” እንድል ማድረግ ነው ሽልማትህ… እሱን ማድረግ ከቻልክ በልቤ ውስጥ ለዘላለም ትታተማለህ… ልጆቼና የልጅ ልጆቼም ይወርሱሃል…. እሱን ማድረግ ካልቻልክ መንገድህን ውሃ በላው… መንገድህ አንተን በላህ… መንገድህ እኔን ቀርጥፎ በላኝ ማለት ነው – ይብላኝለት ለልጄ!

ቆይ ግን …

ለዘመናት አንድ ያልሰመረን ስልት የሙጢኝ ብሎ ችክክ ማለት ምን ይባላል?… እስቲ የተሻለው ይመጣ ዘንድ ስልት እንቀይር… ሀሳብ እንቀይር… ሰውም እንቀይር… በለውጥ የሚያምን እርስ በርስ በመቀያየርም ማመን አለበት…

እናም በቅታችሁናል ውረዱ…
እናንተም ታክታችሁናል አታወናብዱ…
እስቲ አንተም አንቺም ከበርጫውም ከጨብሲውም ላይ ተነሱና ተቀላቀሉ..
እውን ተስፋችን በራሳችን እጅ አይደለምን?!…

ከግርግር ሰላም !
ብጥስጣሽ ሃሳቦች (bT’sT’ash) . . .

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on October 1, 2014
  • By:
  • Last Modified: October 1, 2014 @ 9:34 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar