www.maledatimes.com የማለዳ ወግ …ትኩረት የሚሻው የአረብ ሃገሩ ስደት ጉዳይ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ …ትኩረት የሚሻው የአረብ ሃገሩ ስደት ጉዳይ !

By   /   October 6, 2014  /   Comments Off on የማለዳ ወግ …ትኩረት የሚሻው የአረብ ሃገሩ ስደት ጉዳይ !

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 41 Second

መስከረም 25, ቀን 2007 ዓ.ም በምሽቱ የ EBC ዜና እወጃ የፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ የኢምሬት ጉብኝት ተከትሎ አንድ ቀልቤን የሳበ መረጃ ሰማሁ ። ፕሬዘደንት ዶር ሙላቲ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሜሬት ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር መመካከራቸውንና ስለ ተቋረጠው የኮንትራት ሰራተኞች ጉዞ ተጠይቀው የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለማስጠበቅ የሚችል ህግና ደንብ እየተሰራበት መሆኑን ጠቁመዋል። መልካም ነው! የ EBC ዘገባ የአምናው የሳውዲ ” ህገወጦች ውጡልኝ! ” እወጃ ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን በደል ተከትል ዜጎችን በአፋጣኝ ወደ ሃገር ለማስገባት በዘመቻ መልክ ከኢምሬት የጅዳን ቆንስል ለመርዳት መጥተው የነበሩትን የኢምሬትን አምባሳደር አብዱልቃድርን ማብራሪያም አሰምቶናል ። ይህም መልካም ነው !

አጽንኦት ሰጥቶ ላዳመጠው አምባሳደሩ በገደምዳሜ ሳይሆን በግልጽ ከዚህ በፊት በመንግስት ደረጃ የሰራተኛ ልውውጥ ስምምነት እንዳልነበርና አሁን በዚያ ዙሪያ እየተሰራበት እንደሆነ አስረድተዋል። በመንግስት ደረጃ ስምምነትም ሆነ ቅድመ ዝግጅት ሳይኖር ለደረሰው የዜጎች ጉዳት ተጠያቂ ማነው ? ብለን ስላለፈው ከፍ ያለ ጉዳት ባንሞግትም በቀጣይ ሌላ አደጋ እንዳይከሰት ስለ እውነት ሲባል መነጋገሩ ተገቢ ነው። የሳውዲን ጉዳይ ካነሳን ከምንም በላይ የኢምሬቱ አምባዳደር ለስደተኛው መከራ እያደር መክፋት ከሚረቀቀው ህግ ባለፈ በሙያው የተካነ ፣ ለዜጎች መብት የተጋ ተጠሪ እጥረት መኖሩን በቦታው ተገኝተው እንዳዩትና በብዙዎቻችን ተግልጾላቸው እንደነበር አስታውሳለሁ ።

መቸም ስደቱን ማቆም ቢገድ “እየተሰራ ነው” ከተባለው ህግና ደንብ ጎን ለጎን በእጅጉ ስለጎዳን የአረቡ ሃገር ስደት እንነጋገር ከተባለ የአረቡ ሃገር ስደተኛ ዜጎቻችን መብት ለማስከበር የተጉ ሃላፊዎች የሉንም ። ለችግሩ መፈታት የምንሻ ከሆነ ይህ የመብት አዴሰከባሪ እጦት መመለስ ያለበት ቁልፍ ጥያቄ መሆኑ ችላ ሊባል አይገባም ። ሌላው አሁንም በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ከዚህ በፊት ያለ ህግ ማዕቀፍና በቂ ዝግጅት የተላኩት ዜጎች በየአረብ ሃገራቱ መብታቸውን አስከባሪ አጥተው ሞልተው ተርፈዋል። አሁን ድረስ በአደጋ ተከበው ኑሮን እየገፉ ላሉት ዜጎች መብት ጥበቃ በቂ ምላሽና መፍትሔ ሳይገኝ ዜጎችን እንደገና ወደ አረብ ለመላክ የተያዘው ጅምር በግል የስደተኛውን መከራ በቅርብ እንደሚመለከት ዜጋ ያሳስበኛል። በማያውቁት ሃገር ፣ ባህልና የስራ ጸባይ ለስራ ባልደረሰ ለጋ እድሜያቸው በአፈ ጮሌ ደላላ አማካኝነት በአረብ ሃገራት እንደ ጨው የተበተኑት ዜጎች ጉዳይ በውል ሊጠና ይገባል። የወገናችን ጉዳይ ያገባናል ብለን መረጃ ጨብጠን የምናቀርበው የሰላ ሂስ የምናቀርበውን ፣ እኛ የምንለው ቀርቶ ያን አምና ሳውዲ በዘመቻ መጥተው የስደተኛውን አበሳ በአካል አይተው የሚያውቁት እንደ ኢምሬቱ አንባሳደር አብድልቃድር ያሉ የመንግስት ከፍተኛ ሃላፊዎች እውነቱን ገላልጠው ለበላይ አካላት በማሳወቅ መፍትሔ ሊያፈላልጉ ይገባል ባይ ነኝ ! ከልብ ካዘኑ እንባ አይገድምና …

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ

Again to send contract Ethiopian contract workers:

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on October 6, 2014
  • By:
  • Last Modified: October 6, 2014 @ 8:35 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar