www.maledatimes.com 37ኛውን የችካጎ ማራቶን በቅዳሚነት ለማጠናቀቅ እድሉ የእኔ ነው ሲል ቀነኒሳ በቀለ ገለጸ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

37ኛውን የችካጎ ማራቶን በቅዳሚነት ለማጠናቀቅ እድሉ የእኔ ነው ሲል ቀነኒሳ በቀለ ገለጸ

By   /   October 10, 2014  /   Comments Off on 37ኛውን የችካጎ ማራቶን በቅዳሚነት ለማጠናቀቅ እድሉ የእኔ ነው ሲል ቀነኒሳ በቀለ ገለጸ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 57 Second

እሁድ ጠዋት ከማለዳው 7፡00 የሚጀመረውን የችካጎ ባንክ ኦፍ አሜሪካን ማራቶን ሩጫ ፕሮግራም በተሻለ ሁኔታ ለማጠናቀቅ እድሉ ይኖረኛል ሲል ሃሳቡን ለማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ገልጾአል ።ከባለፈው የፈረንሳዩ ሩጫ ቀጥሎ የችካጎ ማራቶን በታሪከኛነቱ ሊመዘገብ የሚችል ሲሆን በዚህኛው ሩጫ ግን ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ዝግጅቴን አትጠናቅቄአለሁ ሲል ጠቁሞአል ።

በተለይም ስፖንሰር አድርጎኝ በመጣሁበት የናይኪ ኩባንያ የተለያዩ የማጠናከሪያ ኑትሬሽን ሰፕልመንት በመጠቀም የነበረኝን ሃይል ለማጎልበት በቅቻለሁ በሳምን ውስጥ ከፍተኛ ልምምድ እያደረኩኝ ብዙ ጊዜያትን አሳልፌአልሁ ሲል ገልጾአል ።

በዘንድሮው አመት የችካጎ ማራቶን ላይ ውድድርህን ለማድረግ ለማድረግ እዚህ ትገናለህ ስለዚህ ያንተ ዝግጅት ምን ይመስላል ብለ ለጠየቅነው መልስ ሲመልስ …ከዚህ ቀደም ስለችካጎ ብዙ እሰማ ነበር አሁን ግን የተሻለ ነገር በአካል መጥቼ እያየሁት ነው መልካም ነገር ለማድርገ ጥንካሬ ይጠይቃል እሱንም ለማድርግ ካደረኩት ልምድ በመነሳት ብዙ ልሰራ እችላለሁ ሲል መልሶአል ።

kenenisa bekele

ከፔስ ሜከሮችህ ጋር ስንት በስን ለመሮጥ ታስባለህ ለሚለው ጥያቄ ሲመልስምፔስሜከሮችን የሚያዘጋጁት አዘግጁ ኮሚቴ ነው ከእነሱ ጋር በዚህን ያህል ሊስት መሮጥ እችላለሁ ብዬ አልመደኩትም ምክንያቱም ልምምድ የምናደርግው በተለያየ ጎራ ነው ሁለተኛ እኔም የእነሱን ፍጥነት ተከትዬ ነው ለማምለጥ የእራሴን ሃይል ላሰባሰብ የምችለው ሲል ገልጾአል ።

በፈረንሳይ ከነበረውስ ጋር ያለውን ሩጫህን ውጤት አይተህ ወደ ችካጎ ጥሩ ሊጠበቅ የሚችልበት በሰራሃው ልምድ ከሆነ ከአንተ ምን መጠበቅ ይገባናል?

እንደ ተለመደው ኢትዮጵያውያን ጥሩ ነገርን እንወዳለን እኛም ጥሩ ነገርን ይዘን ለመምጣት እንጥራለን ግን ካልሆነም አልተሳካም ሊባል ይገባዋል ምክንያቱም እኛ የምንሮጠው ሩጫ ቀላል አይደለም ከፍተና ፉክክር እልህ  አስጨራሽ የሆነ ሃይል ነው ይዘን የምንገባው ከእኔም በላይ የተሻለ ደግሞ ልምድ የዞ ሊመጣ የሚችል ሰው እንደሚኖር ደግሞ መጠበቅ አለብን ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በቤተሳባዊ አትሌቶች ተከቧል እንዴት ነው የዚህ ሁኔታ የአንተ ራእይ አለበት ብለህ ታስባለህ ? ለምሳሌ ታሪኩ በቀለ ከእናተ ቤት ወጥቶአል ፣ከእነ እጅጋየሁ ቤትም 3 ሴቶች አሉ እና እንዲ እንዲህ እየተባለ ወደ ቤተሰባዊ ስራ መግባቱ ምን ይመስልሃል ?

ገና ጥቂት ሰዎች ናቸው እንዲህ አይነቱ ላይ የገቡት ቢገቡም ሊገርም አይገባም አብዛኞቹ ጥሩ ውጤት እያመጡ ነው ታሩኩም ቢሆን የኔን ያህል እድሉ ባይደርስበትም ጥሩ እየሄደ ነው ሆኖም ሁላችንም የየራሳችንን ድርሻ እንወጣለን ሁሉም በሚችለው አቅሙ ሊያደርግ የሚገባውን ሊያደርግ ይገባዋል እንጂ በቤተሰባዊነት ስፖቱ ውስጥ ጠልቀን ልንገባ ፍላጎቱ የለንም ፍላጎቱ ያለው በሚፈልገው ሙያ ሊሰማራ ይችል ይሆን ዘንድ ነውና ሲል ገልጾአል።

በአሁን ሰአት ምን ያህል ካፒታል አለህ

kenenisa bekele with maleda times media group members

እሱ እባክህ መደመር መቀነስ ነው በሃገራችን ሁኔታ ይሄን አለኝ ማለት አትችልም ሆኖም ግን አለኝን አለኝ ከእኔም በላይም በጣም ያላቸው አሉ ስለዚህ ሁሉንም ወደ ፊት አፍሪካም ሆነ ኢትዮጵያ እድገቷ እንደ አሜሪካ ሲሆን ይህንን ጥያቄ ብታመጣውም ባታመጣውም በወቅቱ ያለውን የተጣራ ካፒታል ልታውቅ ትችላለህ ሲል ገልጾአል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on October 10, 2014
  • By:
  • Last Modified: October 10, 2014 @ 11:13 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar