www.maledatimes.com ቅኝቱን ያልሳተው አዲሱ ሹመት ከተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን) 21/09/2012 - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቅኝቱን ያልሳተው አዲሱ ሹመት ከተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን) 21/09/2012

By   /   September 21, 2012  /   2 Comments

    Print       Email
0 0
Read Time:15 Minute, 15 Second

2004 ዓ.ም ሃገራችን ብርቅዬና በሞያቸው አንቱ የተባሉ እንዲሁም ለሃገራቸው ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉ እጅግ ውድ ልጆችዋን እንዳጣች ሁሉ በስተመጨረሻው አዲሱ አመት ከመጥባቱ በፊት እንደ
መጅገር ተጣብቀው የህዝብና የአገር ደም ሲመጡ፣ ሃብት ንብረትዋን ሲመዘብሩ የነበሩት እስከ እኩይ ምግባራቸው ላይነቁ እስከ ወዲያኛው ማሸለባቸው የታወሳል፡፡ በማለቂያው እነዚህን እኩይዎች ነቀለልን እንጂ በመለስና በሰርዓቱ ሃገርና ህዝብ ሲታመሱ ነው  አሮጌው ዘመን ያለቀው፡፡ ዘመኑን ሙሉ እሱና ጀሌዎቹ ያረቀቁትን የአገሪቱን ህገ-መንግስት  አክብሮ ማስከበር እርም ሆኖባቸው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን  ተጠቅመው የተደራጁ የድርጅት አመራሮችን እንዲሁም የመፃፍና የመናገር መብታቸውን ተጠቅመው ስለዴሞክራሲ፣ ስለፍትህ፣ ስለመልካም አስተዳደር እጦት የፃፉትንና ሌሎችንም ንፁሃን ዜጎች ሰብስቦ የተለመድው ማጎሪያ የወረወራቸው ዘረኛው መለስ ጀምሮ ባልጨረሰው 2004 ዓ.ም መጀመሪያ ነበር፡፡
ይህ አመት በኢትዮጲያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በርከት ያሉ ትህይንቶች የተስተናግዱብተ አመት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ’’ከሁሉም በፊት ነፃነትና ዴሞክራሲ ለዜጎች መልካም አስተዳደር፣ ፍትህና እኩልነት በሃገሪቱ ይስፈን፣ ህዝብ በተለይ ወጣቱ የአባቶቹን አደራ ይጠብቅ እያለ በመጨረሻም በቃኝ ፍትህ፣ እኩልነትና ነፃነት በሌለበት ሃገር አልኖርም ’’ ብሎ በራሱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን ያቃጠለው ሰመዓቱ የኔሰው ገብሬ በመለስ እና በጭፍሮቹ እንደ አእምሮ በሽተኛ የተቆጠረው በዚሁ በሸኘነው አመት ወርሀ ህዳር ነበር፡፡
ሌላው በዚህ ጉደኛ አመት ከተደረጉ ህዝባዊ እንቅሰቃሴዎች ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን ያነሱት የደሞዝ ጭማሪና ተዛማጅ ጥያቄ
በአትሌት ሃይሌና በአምባገነኑ መለስ በጥቂት ተፈርጆ ቢፌዝበትም የአንድ ስሞን አንኳር የሃገሪቱ መነጋግሪያ ጉዳይ ሆኖ አልፏል፡፡ ሌላው ምንም እንኳን በአፋኙ ስርዓት መልስ ባያገኝም የአምባገነኑን መንደር አስጨንቆና ፋታ ነስቶ እስካሁን ሲንከባለል ዘመን የተሻገረው የሙሰሊሙ ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ ለሟቹ ዘረኛው መለስም ሆነ ለቀሩት የስርዓቱ ጭፍሮች ትልቅ እራስ ምታት እንደሆነ እስካሁን ዘልቋል፡፡ በዚህም የሙስሊም ማህበረሰብ ባነሳው የመብት ጥያቄ ምክንያት ብዙ ወገኖቻችን በግፈኛው የመለስ ብድን በግፍ ተገለዋል፣ አካላቸውን አጠተዋል፣ ታሰረዋል፡፡ ከወራት በፊት በአርሲ አሳሳ የተካሄደው ጭፍጨፋ ፣ በደሴ የተደረገው የግፍ ብትር ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡
በዘመኑ መጨረሻ እንደ አበደ ውሻ ሁሉንም ይነክስ የነበረው መለስ ዜናዊ መጀመሪያ በጀግናው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ከዛም በመለአከ ሞት እስከተሸነፈ ጊዜ ደረስ የሚይዝ የሚጨብጠው
እስኪያጣ እጅግ በገዘፈ መልኩ የአውሬነት ባህሪ ይስተዋልበት ነበር፡፡ ለዚህም ነው ለዘመናት ተከብሮ የኖረውን የዋልድባ ታሪካዊ ገዳም በልማት ስም እንዲታረስና አለም በቃን ብለው የመነኑ መነኮሳትመጠጊያና መሸሸጊያ እስኪያጡ የሳደዳቸው፡፡ በመሰረቱ ይህ ገዳም የሁሉም ኢትዮጲያዊያን፣ የጳጳሳት፣ የመምህራን፣ የመነኮሳት፣ የዘማሪያን መሰረት ከመሆኑም ባሻገር የሃይማኖት መገለጫ፣
በማንነታችን መኩሪያና ማሳያ፣ የታሪካችን አሻራ ከመሆኑም ባሻገር የተለያዩ የቅዱሳን ገድል ያለባቸው በርካታ መፅሃፍትንና የተለያዩ የኢትዮጲያ ሃገራችን ቅርሶች ያሉበት ገዳም ፣ ከተውልድ ትውልድ
ሲወራረስ የመጣውንና የበቁ አባቶች ፀሎትና ምልጃ የማይለየውን ይህንን ቅዱስ ቦታ በልማት ስም የተተናኮለው በመጨረሻው የጣር ሰአቱ ነበር፡፡

ቅኝቱን ያልሳተው አዲሱ ሹመት
ከተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን) 21/09/2012

በተጨማሪም በዚሁ ባሳለፈነው አመት በደቡብ ኢትዮጲያ በጉራ ፈርዳ ለአመታት የኖሩ የአማራ ተወላጆች ከነቤተሰቦቻቸው በሃገራቸው የመኖር መብታቸው ተቀምተው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረው
ሃብት ንብረታቸውን ተነጥቀው እንደ ዘበት ’’አገራችሁ ሂዱ’’የተባሉት የዴሞክራሲ እና የፍትህ አባት እየተባለ የሚዘመርለት መለስ ዜናዊ አውቆ እና ፈቅዶ ነው ፡፡ ይህም ያሳለፍነው አመት አንድ ትእይንት
ሆኖ አልፏል ፡፡
በሌላም በኩል መለስና ግብራበሮቹ በቃኝን የማያውቁ በመሆናቸው የሃገርና የህዝብን ሃብት እንደ ግል ንብረታቸው ከመቀራመትም ባለፈ ደሃ በመሆናችን በኛው ስም ለምነው ካገኙት ገንዝብ ላይ
ሁሉ ይስረቃሉ፡፡ የዓለም የፋይናንስ ኢቴግሪቲ (Global financial integrity) ባደረገው ጥናት መሰረት እንደ እ.አ.አ ከ2000 እስከ 2009 ባለው 9 አመታት ውስጥ 11.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጲያ በህገወጥ መንገድ ተዘርፎ ከሃገር መውጣቱን ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ይህ ገንዘብ በኢትዮጲያ ሲመታ ምን ያህል ነው? ምንስ ሊሰራ ይችል ነበር በላችሁ በማሰብ አትታመሙ፡፡
በአጠቃላይ ወያኔ ላለፉት ሃያ አንድ አመታት ሰራሁ የሚለንን መንገድ፣ አነፅኩ የሚለንን ህንፃ ፣ ገነባሁ የሚላቸውን ማንኛውንም ግንባታዎች ከሶስት እጥፍ በላይ ሊከውን የሚችል ገንዘብ በሟቹ
መለስና በዙሪያው ባሉ የወያኔ ሰወች እንደተመዘበረ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡
ይህ ከላይ ለመጠቆም የሞከረኩት ሁሉ ለአንድ ሚሊዮን ጊዜ በተለያዩ ሁኔታዎች የተነገሩና ሁሉም ስው የሚያቀው እውነታ ነው፡፡ ታዲያ እነኚህንና የተቀሩትን የዘረኛው መለስ ገድሎች ከሞተም በሗላ
ሲሰርቅ አብረው በሰረቁት፣ ሲገድል ተማክረው በገደሉት፣ ፍትህ ሲያጎድል እና ንፁሃን ዜጎችን በግፍ፣ በሃይል ሲረግጥ ብርጭቆ እያጋጩ ደስታቸውን በገለፁ፣ የሴራው ተባባሪ በሆኑት ሁሉ ወይም በእሱ
ብልሹ አሰራር ተለጣፊ ሆነው ኑሮአቸውን ያደራጁ፣ የመለስን ጩኸት ሲያስተጋቡ የነበሩ በቀቀኖች ጌታቸውን የሚያንቆለጳጰሱበት ቃላት አጥሮአቸው ተቸግረዋል፡፡ስንት ንፁሃን ዜጎች በየእስር ቤቱ
ያጎረውን ሰውዬ…. የፍትህ እና የዴሞክራሲ ተሟጋች፣ ሃገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ የሸጠ እና እጅ መንሻ የሰጠውን…. ባለ ህራህይ፣ ለሃገር አሳቢ አርገው ሲስሉት እጀጉን የደንቃል፡፡ መለሰ የፍትህ እና
የዴሞክራሲ አባት ከሆነ አሁን በሚነገርለት መጠን የዜጎችን መብት ያከበረና ያስከበረ ከነበረ የሽብሬ እና የነበዩ መገደል ትክክል ነበር ማለት ነው?፣ እስክንድር እና አንዱአለም እንዲሁም ሌሎች ንፁሃን
ዜጎች በእስር መማቀቃቸውስ አግባብ ነው? መቼም ይህንን ለማወቅ ጠቢብ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ በመሰረቱ በአለም ላይ ከብዙሃኑ በተሻለ አስተሳሰብ ያለው ሰው ለመሆን ሁለት አማራጮች አሉ፡፡
የመጀመሪያው እና ከባዱ የተሻለ ከሚያሰቡ ሰወች የተሻለ ሆኖ መገኘት ሲሆን ሁለተኛው እና በጣም ቀላሉ ደግሞ ደደቦችን በዙሪያህ በመሰብሰብ የተሻለ ሆኖ መታየት ነው፡፡ እናም በኔ አመለካከት ሟች
መለስ ሁለተኛውን አማራጭ ተክኖበታል ለዚህ ነው ያልፈጠረበትን ያልሰራውን ገድል እየተረኩ በማህበር ተደራጅተው በደቦ አልቅሰው ሲያላቅሱ የከረሙት፡፡ ለዚህ ነው ሃገር ምድሩን ማቅ አሰለብሰው የለቅሶ ከተት አወጁት፡፡የመለስን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ የግፍና የአፈና ስርዓትን የሚያወድስ ወይም አርአያ አድርጎ የሚከተል ቅኝቱን ያልሳተ አዲሱ ሹመት የተሻለ ነገር ይዞ ይመጣል ማለት ከንቱ ቅዠት ነው፡፡ መለሰ በዘረጋው የዘረኝነትና የጥላቻ ሀዲድ ሊዘውሩን እንሆ አቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝ ነግሰውብናል፡፡ በቃን ካላልን አሁንም ሊገዙን ሽርጉድ የሚሉት ያው የሟቹ መለስ ቅጥቅጦች ናቸው፡ ጉልቻ ቢለወጥ ነው ነገሩ . . . . . . . . .
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ ሞት ለወያኔ ለአሰተያየቶ፣-ftih_lewegen@yahoo.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 21, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 21, 2012 @ 8:59 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

2 thoughts on “ቅኝቱን ያልሳተው አዲሱ ሹመት ከተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን) 21/09/2012

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar