በዘላለም ገብሬ
ዛሬ ምንም ባልታሰበ እና ባልተጠበቀ ጊዜ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በቀረጥ ክፍያ በማጭበርበር ተከሰሰ የሚል አደናጋሪ ወሬ ሰማን እና ምን አለብቶት የሚል ሆኖብን ታዲያ ይህ የክስ መዝገብ እንዴት ዛሬ ሊታይ ቻለ የሚለውን ዙሪያ ጥምጥም ለማየት ለመዳሰስ ሞክረን ቀደም ካሉት አንዳንድ መጣጥፎች እና የቴዲን መዝገብ አስመልክቶ ምን ተካሂደው ነበር የሚለውን የመኪና አደጋውን ሂደት ምን ይመስል ሁኔታውም ሆነ የክስ ሂደቱ እንዴት አለፈ ?የሚለውንነና ሌሎቹንም ለመዳሰስ ያስችለን ዘንድ አንዳንድ ነጥቦች እናንሳ ።በ1999 አመተ ምህረት ጥቅምት ሃያ ሁለት ቀን በተፈጸመ የመኪና አደጋ ክስ በተጭበረበረ የክስ መዝገብ ሲከናወን እንደነበረ ይታወሳል።
ሆኖም ዛሬ ደግሞ ከስድስት አመታት ቆይታ በኋላ እንደገና አዲስ ክስ ተቀስቅሶ ይሄው አቤቱታውን ሊያሰሙን የቅድሚያ ምርመራ እንዲደረግ እና ክሱን በውጭ ሆኖ እንዲከላከል ሲሉ ዳኛው በመወሰናቸው የ30.000 ብር ዋስትና ተፈቅዶለት ከእስር መለቀቁ ሁሉንም አስደንግጦአል ።
የቴዲ አፍሮ ክስ መመስረት በአመክሮ ከተመለከትነው በትክክል የፍርድ ሂደትን እና የህግ ረቂቅ አዋጅን ተከትሎ የመጣ ሳይሆን የግላዊ ጥላቻን ለማንጸባረቅ ከሚጀመረው የሂደት ጉዞ ሲሆን ካለው የፖለቲካ ልዩነት አንጻር የግለሰቡን የፖለቲካ አመለካከት ካለመቀበል እና ልክ እንደ ጣኦት እኛን ካላመለከን አንተም አትመለክም የሚለውን አመጸኛ አመለካከታቸውን በጊዜያዊው ስልጣናቸው ፣የስልጣን በትራቸውን ለመቃጣት የሞከሩት የኢሃዴግ አጎብዳጆች መሆናቸው ይታወቃል ።ለዚህም እንደምክንያት ሊቀርቡ የሚችሉ የተለያዩ ዳሰሳዎችን ማቅረብ እችላለሁ ።
በመጀመሪያ ደረጃ ክሱ ከመጀመሩ በፊት መኪናዋ እንዴት ቴዲ አፍሮ ሊገዛት ቻለ ?የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል በዚህ ጥያቄ ላይ ብዙ ነገሮችን ሊያሳየን የሚችለው ጠቋሚ መንገድ ይኖራል አንደናው ያለ ቀረጥ ካስገባ ሰው ላይ ገዝቶ ከሆነ ፣ያለቀረጥ ያስገባው ሰው ያልከፈለበትን ቀረጥ የመክፈል ግዴታው እንደሆነ ግልጽ ነው ፣ሆኖም ግን በዚህም ሆነ በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ቴዲ አፍሮ ቀረጥም ሆነ የግብር ገቢ ታክስ ሊከፍልበት የሚችልበት ብዙ አማራጭ መንገዶች እንዳሉ ይታወቃል ከእነዚህም መካከል በኢንቨስትመንትም መልኩ መኪናዋን አስገብቶ ከሆነ ቦሎ እና የሰሌዳ ቁጥር ለማውጣት ሲያስመዘግብ የሚጠየቀውን ነገሮች ሁሉ በማሟላት ወደ ህጋዊ የሆነው የፈቃድ አገልግሎት ማግኘት የሚችልበት መንገድ የተዘረጋበት አስራር እንዳለው የሚታወቀው የትራንስፖርት እና መገናኛ ባለስልጣን ሁሉንም መረጃዎች አጣርቶ ፈቃዱን እንደሰጠው ግልጽ ነው ። በሌላም በኩል ቢሆን በግዥ አገር ውስጥ የተፈጸመ ከሆነ ደግሞ በውል እና ማስረጃ በኩል የሚከናወኑትን የስም ማዛወር ስራዎች በሙሉ ከነ ሙሉ መብቱ ክፍያውን ሊያጠናቅቅ እንደሚችል እና የባለቤትነቱን ሰርተፊኬት እንደሚያገኝ የሚታወቅ ነው ። ይህ አሰራር በወቅቱ የነበረውን ክፍለ ከተማ ስብጥር በሚል በተጀመረው አሰራር ሂደት የሚከተል እንደሆነ ይታወቃል ።
በቴዲ አፍሮ ጉዳይ ላይ ብዙ ነገሮችን እናንሳ ካልን የዚህች የቢ ኤም ደብሊው ጦስ እና መከራ ብዙ ነገሮችን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ይታወቃል ።ምክንያቱም መንግስት ከመሰረተው ክስ ጀምሮ መጣረስ እና ምስክር ነን ባዮች የሰጡት ቃል አለመገጣጠም ፣የቴዲ የመኪና አደጋ እና ሟች ደጉ ይበልጣል የተባሉት ግለሰብ ሞቱ የተባሉበት ቀን እና ቴዲ አፍሮ ወደ ሃገር ቤት የገባበት ቀን አለመገጣጠም ፣የፖሊሶች የይግባኝ ጥያቄ ጠይቀው እንደገና ክሱን በመከለስ ቴዲ በገባበት ቀን የክስ መዝገቡን ቀን እና እለቱን በመቀየር ክሱ በአዲስ መልኩ እንዲታይ ማስደረጋቸው ይሄ ሁሉ በተጨባጭ ንጹህ የሆነን ሰው ለመኮነን ከሚደረጉት ጥቂት የሆኑ ግን ጉልህ ስህተቶቻቸው እራሳቸውን ተወቃሽ ሲያደርጋቸው የሚኖር ሲሆን ዛሬም ለመሰረቱት ክስ የዚሁ አይነት እጣ ፈንታ እንዳለው ከመገመት አያዳግትም ።
ይህንን ለመን መገመት አስፈለገ ተብሎ ለሚጠየቀው ጥያቄ ከላይ ያለው መንደርደሪያ ሃሳብ መልሱን ሲሰጥ ለአሁኑ ክስም ሆነ ለቀድሞው ክስ መመስረት ምክንያት የሆኑት ዋነኛ ነገሮች
ጃ ያስተሰርያል …. አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ የሚለው እና እንዲሁም ባንዲራ ከሚለው ከ 9 አመታት በፊት በአውሮጳ የተዘፈነው ዘፈን ቀስተዳመናው ላይ አንበሳው ከሌለ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ትርጉሙ የታለ ! የሚሉት ሁለት ዜማዎች አስቆጥቶአቸው ክሱን ለመፈጸም ደፋ ቀና ሲሉ የከረሙት የወያኔ አዛውንቶች ዛሬ ሊሳካላቸው አገረቤት ሲገባ ጉሮሮውን ይዘው እስርቤት በማስገባት በጥያቄዎቻቸው ሊሞሉት ሞክረዋል።
ታዲያ ነገሩ እንዲህ ከሆነ ለምን የሚለው ጥያቄ ያስነሳል እስከዛሬስ የት ነበሩ ? ለሰባት እና ለስምንት አመታት ምርመራ እያደረጉ ነበርን ወይንስ የሚከሱበትን መንገድ እያውጠነጠኑ ?
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለምን ከዛሬ 6 ወይንም 7 አመታት በፊት የመኪና አደጋ ክሱ በነበረበት ወቅት ሊታይ አልቻለም ?
ለምንስ የጉሙሩክ ስራ አስፈጻሚ አካላቶች ይህንን መኪና ያስገባውን ሰው በዋነኛነት ሊጠይቁ አልቻሉም ?
ቴዎድሮስ ካሳሁን በሚል ስም የገባ ከነበረስ እንዴት እስከዛሬ ድረስ ሳይከፍል መረጃዎቹ ተጠናቀው ተሰጡት ፣ካልከፈለምየጉሙሩክ ቱባ ባለስልጣናት ለዚህ ስራቸው በከፍተኛ ደረጃ ተጠያቂ ሊያደርጋቸው ለምንስ አልቻለም?
ይህ በሙስና የተደራጀ ድርጅት እንደሆነ እና ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት የትግራይ ተወላጆች እና በህወሃት ጥላ ስር ያሉ ልጆች ብቻ እንደሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በቴዎድሮስ ላይ ያረፈው አለንጋ በእነርሱ ላይ ማረፍ ሲገባው ለምን ለሶስተኛ እና አራተኛ ወገን ላይ ህጉ ሊፈጸም ይችላል ?
በሃገራችን እየተዛባ ያለው የፍትህ ስርአት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ሊሆኑ የሚገባው በእራሳቸው አስተዳደር ላይ ያሉት ሰዎች የተሰጣቸውን ስራ፣ ስነ ምግባር በጎደለው መንፈስ ፣በቅንነት በሌለው ጎዳና እና በስነ ምግባር ካለማገልገላቸው የተነሳ የህብረተሰብንም ሆነ የሃገርን ገንዘብ በመዝረፍ ለከፍተኛ ኪሳራ እየዳረጉ ዛሬ ምንም ባለተጠበቀበት ወቅት የንጹሃንን ገንዘብ ለማጋበስ ያመቻቸው ዘንድ የሚጠቀሙበት አቋራጭ መንገድ ሆኖ ተገኝቶአል ።
ምናልባትስ የከፈለበትን ፋይል ከግምሩክ ውስጥ ደብዛውን አጥፍተውትስ ከሆነ እና ዛሬ ደግሞ በሌላ ሁኔታ ለማሰቃየት እና መቀጣጫ እናድርገው ብለው በሙስና የጎለበተውን ጉልበታቸውን ሊያሳዩት ይሆን ?
አለበለዚያም ከእስር ቤት በነበረበት ወቅ ላይ በሲ ኤም ሲ የነበረው መኖሪያ ቤቱ ሲፈተሽ አስፈላጊ ያሉአቸውን መረጃዎች ሰብስበው ሄደው እሱ በማያገኛቸው መልኩ ከናካቴው አጥፍተው እንደገና ፊታቸውን እና ጣታቸውን ወደ እሱ ቀስረውስ ቢሆን ማን ያውቃል ?
ለማንኛውም ቀድሞ የነበረውን የክስ ሂደት ምን ይመስላል የሚለውን ለመዳሰስ ያህል ከስር አስቀምጠነዋል ለመረጃ ያህል የተቀመጠ ሲሆን የምርመራው ሂደት ምን ይመስል እንደነበር እና ክሱንም አስመልክቶ የቀረቡትን ሁኔታውች የሚያሳይ ስለሆነ ትኩረት ቢሰጡበት መልካም ነው እንላለን ።
ለፍትህ ሚንስትርም ቢሆን አሁንም ልብ ይስጠን እያልን የተጀመረው የክስ ሂደት ክሱ ከመቅረቡ በፊት ጥናት ቢደረግበት መልካም ነው የሚለውን ሃሳባችንን እየሰጠን በዚሁ አጋጣሚ በጉምሩክም ሆነ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የደህንነት አባላት በትራዋይነታቸው ብቻ አትንኩኝ አትናገሩኝ እኛ ብቻ የንነግራችሁን ትፈጽሙ ዘንድ ቃላችን ነው ይህንን ካላደረጋችሁ ግን አገር ትቃጠላለች የሚሉትን በስርአቱ ብታስተነፍሷቸው የሚቀል ይሆናል እንጂ በዘር ተለይቶ የምትከፋፈል አገር ልትኖረን እንደማይገባ እና የነገውን ትውልድ ሌላ ጠባሳ ጥላችሁበት የምታልፉበት እንዳይሆን ጊዜው ዛሬ ነው እና ትውልዶቻችንን የማዳኑን ስራ በትክክለኛ የፍትህ ስራ በመታገዝ እናሳይ ። ከላይ የተጻፈው አጭር ጽሁፍ የሚያሳየው በሃገራቸን ያለውን የፍትህ መጓደል እና የቴዲ አፍሮ የሰቆቃ ኑሮ ሲሆን የእርሱ ኑሮ የሌሎችንም በየቤታችን የሚያሳይ ድብቅ ሚስጥር ቅንጨብ አድርጎ ሊያቀብ የተሞከረ እንጂ በጥናታዊ ጽሁፍ የተደገፈ ባለመሆኑ ብዙም ከረር ያሉ ሰነ ጽሁፋዊ አጀንዳዎችን ይዞ አልተነሳም ዋናው ነገር ሊያስገነዝብ የሞከረው በቴዲ ክስ ላይ የተመሰረተው አልባሌ የሆነ ክስ ለምን ዛሬ ሊመሰረት ቻለ በሚለው ዋነኛ ሃይለ ቃል እስከዛሬ ለምን እንደጠበቁት ማብራሪያ ሊያሰጥ የሚችል ሃሳብ ካላቸው በሰነዙሩ በሚል አንደምታ የተተየበ ነው ።
Average Rating