www.maledatimes.com ደኢህዴን በአጼ ምኒልክ ላይ የሰራው ዶክመንተሪ ኢህአዴግ ውስጥ ቅራኔ ፈጠረ * • በርካታ የብአዴን ካድሬዎች በሰንደቅ አላማ በዓል አልተገኙም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ደኢህዴን በአጼ ምኒልክ ላይ የሰራው ዶክመንተሪ ኢህአዴግ ውስጥ ቅራኔ ፈጠረ * • በርካታ የብአዴን ካድሬዎች በሰንደቅ አላማ በዓል አልተገኙም

By   /   October 14, 2014  /   Comments Off on ደኢህዴን በአጼ ምኒልክ ላይ የሰራው ዶክመንተሪ ኢህአዴግ ውስጥ ቅራኔ ፈጠረ * • በርካታ የብአዴን ካድሬዎች በሰንደቅ አላማ በዓል አልተገኙም

    Print       Email
0 0
Read Time:54 Second

 

የደኢህዴን 22ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ተከትሎ በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ‹‹ጮራ ፈንጣቂው ጉዟችን›› በሚል የተሰራውና አጼ ምኒልክ የደቡብ ህዝቦች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንደፈጸሙ የሚሳየው ዶክመንተሪ በዴኢህዴንና በብአዴን መካከል አለመግባባት መፍጠሩን አንድ ከፍተኛ የብአዴን ካድሬ ነገረ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

Minilik

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ዶክመንተሪውን ተከትሎ የብአዴን ፖለቲከኞች ኢህአዴግ በተለይም የዶክመንተሪው አዘጋጅ ደኢህዴን ላይ ተቃውሞ ያስነሱ ሲሆን ‹‹በአንድ በኩል ምኒልክ ይወደሳል፡፡ በአንድ በኩል ደግሞ ይወገዛል፡፡ ፒያሳ ላይ ያለው ሀውልት ምኒልክ መልካም ነገር እንደሰሩ ለማሳየት የተሰራ ነው፡፡ እንዲህ የምታወግዙት ከሆነ ለምን ፒያሳ የሚገኘውን ሀውልቱንስ አታነሱትም?›› በማለት በህዝብ መካከል ግጭት ይፈጥራል ያሉት መቀስቀሻ ዶክመንተሪ ላይ ተቃውሟቸውን ማንሳታቸውን የብአዴን ከፍተኛ ካድሬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የብአዴን ካድሬዎች ዶክመንተሪውን ባዘጋጀው ደኢህዴንም ሆነ ኢህአዴግ ላይ ባላቸው ቅሬታ የዛሬው የሰንደቅ አላማ በዓል ላይ እንዳልተገኙ ተገልጾአል፡፡ በዶክመንተሪው ምክንያት በኢህአዴግ አንዳንድ ፖሊሲዎች ላይ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ለአብነት ያህልም እስካሁን አንስተውት የማያውቁትንና ሰንደቅ አላማው ላይ ያለው ኮከብ ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን የብአዴኑ ካድሬ ገልጾዋል፡፡

በቅርቡ አጼ ምኒልክን በመኮነን ከተላለፈው ዶክመንተሪ በተጨማሪ ተማሪዎች፣ ለሰራተኞችና ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍል በተሰጠው ስልጠና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ታሪክ ነክ ወቀሳዎች የአብአዴን ካድሬዎች በደኢህዴንና ኢህአዴግ ላይ ላነሱት ተቃውሞ በተጨማሪ ምክንያትነት ተነስቷል፡፡

Source/www.zehabhesha.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on October 14, 2014
  • By:
  • Last Modified: October 14, 2014 @ 8:47 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar