የማራኪ መጽሄት ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበረው ሚሊዮን ሹርቤ ከሃገሩ የመናገር መብትን መከበር አለበት ጋዜጠኝነት አሸባሪነት አይደለም በማለት የሚዲያን ሃያልነት ለማሳየት ለዘመናት ሲጥር ቆይቶ ከሁለት ወራት በፊት ወደ ኬንያ መሰደዱ ይታወቃል ።ሆኖም ግን ከባለፈው መስከረም ሃያ አንድ ቀን ጀምሮ ጤናው መጓደሉን ለማለዳ ታይምስ ገልጾ ነበር ሆኖም ግን እንደዚህ ለከፍተኛ የሞት ደረጃ ያበቃናል ብሎም አልጠበቀም የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከልም ይህንኑ ሃሳብ ይጋሩት ነበር ።
ከአስራአምስት ቀን የህክምና ቆይታ በኋላ ትላንት ማለዳ ህይወቱን ማለፉ በኬንያ የሚገኝ ጋዜጠና መላኩ አማረ ለማለዳ ታይምስ ገልጾአል አሁንም የሚሊዮን ሹርቤ አስከሬን በሆስፒታል የሚገኝ እንደሆነ እና በወቅቱ በነበረበት የህክምና አገልግሎት የወጣውን ወጭ እስከሚሸፈን ድረስ እንዲሁም ለአስከሬን ማቆያ የሚከፈለው ክፍያ እስከሚጠናቀቅ ድረስ እየጠበቅን ነው ከዚያም ወደ ሃገርቤት አስከሬኑ የሚላክበት መንገድ ደግሞ እናፈላልጋለን ሲል ለማለዳ ታይምስ ገልጾአል ።
በሌላ በኩል የሚሊዮን ህይወትን አስመልክቶ ቤተሰቦቹ ቀድመው ሰምተው ነበር ወይ ብለን ለጠየቅነው መልስ ሲሰጥ ቤተሰቦቹ ከፌስ ቡክ ላይ እንደሰሙ እና በዛሬው እለት ወደ ኬንያ በመደወል ማጣራት እንደቻሉና ሞቱንም እንደ ነገራቸው አክሎ ተናግሮአል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ማሳሰቢያም ይኖረኛል በማለት ለፌስቡክ ወይንም ሌሎች የሶሻል ኔት ወርክ ተጠቃሚዎች እባካችሁ ችግሩ የከፋ እንዳይሆነ ወደፊት እንደዚህ አይነት ነገር ሲፈጸም ምንም ባይለጠፍ ለቤተሰብ ደህንነት ሲባል መልካም ነው ሲል ገልጾአል ።
በዚህ ሁኔታ ላይ የጋዜጠኛውን ቤተሰብም ሆነ ሌሎች የተሰደዱ ጋዜጠኞችን እንዲሁም ለአስከሬኑ መላኪያ መርዳት ለምትፈልጉ ህብረተሰቦች በአድራሻችን ደውሉልን ይህንን ጉዳይ ወደ ሚወክለው አካል እኛ እንመራችኋለን ።
እኛም ለሚሊዮን ሹርቤ ቤተሰቦች መጽናናትን እየተመኘን
ለእርሱም የሰላም እረፍት እንዲሆንለት እና አምላክ በገእት ያኑርልን የሚለው ምኞታችን ነው !
Average Rating