www.maledatimes.com ሁሌመታለልአይቻልም (በይግዛው እያሱ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሁሌመታለልአይቻልም (በይግዛው እያሱ)

By   /   September 22, 2012  /   Comments Off on ሁሌመታለልአይቻልም (በይግዛው እያሱ)

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 4 Second

በመሰሪ ስልቱ የታወቀው ወያኔ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም በየጊዜው ራሱን እየቀያየረ በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በደልና ጭቆና ለመቀጠል በሞተው አባቱ እየማለ ለ 21 ዓመት በብቸኝነት ይዞት የነበረውን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረግ ለሁላቸውም እንዲዳረስ በመሚስል በየአስር ዓመቱ እንዲቀየር ገደብ ጣልን ብለው አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሁለት ተርም በላይ እናዳይቆይ ኢሕአዴግ ወስኗል ይሉናል::

ኢሕአዴግ የስልጣን ምደባ ለማድረግ ከመወሰን ባሻገር ስልጣን ለህዝብ እንዳይሆንና ሙጥኝ ያለበት ምክንያት በዴሞክራሲ ካለማመንም ሌላ ለህዝብ ጥያቄ መልስ ለመስጠት አለመፈለጉን ያሳያል:: በዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ተቀባይነት ለማግኘት ብቻ በየስድስት ወሩ ሊቀይረው የሚችለውን የወያኔ የጋራ ስምምነት በኢትዮጵያ ቴሌቨዥን መስኮት ወጥቶ ይተርክልናል::ይህ ውሳኔ ቢያንስ ትክክል ይሆናል ብሎ ህዝብ ለጊዜውም ቢሆን እንዲታለል እንኳ ህገ መንግስቱን አሻሽሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም ሆን የሚኒስትሮችን የቆይታ ጊዜ ከ 2 ተርም በላይ እንደማይሆን የሚያሳይ ቢያሰፍር የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም ከመፈለጉ የተነሳ ቢያንስ ከ 10 ዓመት በኋላ የሚመጣው  የኢሕአዴግ ቡችላ ጥሩ ሊሆን ይችላል ብሎ ስለሚገምት ጊዜ ወስዶ ሊጠብቅ ይችል ነበር::

ይህ ባልሆነበት ሁኔታ የድሮው ጠቅላይ ሚኒስትር የቀኝ እጅ እንደነበር የሚነገርለት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚንስትሩ አቶ በረከት ሰምኦን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሚኒስትሮች የስልጣን ዘመናቸው ከሁለት ጊዜ በላይ እንዳይሆንና እድሜያቸውም ከ 60 እንደማይበልጥ ተወስኗል  ብለው ይደሰኩራሉ::

አቶ መለስም በህይወት ቢቆዩ ኖሮ ከ 60 ዓመት በላይ ስለሚሆናቸው መቀጠል እንደማይችሉ በህይወት እያሉ ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር ይገልጻል::  መቸም አይሰሙኝ ብሎ::

ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሌ መታለል አይቻልም አንዴ ወይም ሁለቴ ሊሆን ይችላል::ስለዚህ ይህን መሰሪ ተግባራቸውን በውል አጢነንና መርምረን በመቃወም ሌላ 21 ዓመት የመከራ ዘመን እንዳይጫንብን የየበኩላችንን ሃላፊነት መወጣት አለብን:: ሓላፊነት ሲባል ከስር ሌላ ለመምራት ብቻ ሳይሆን ራስንም ለመምራት የተስተካከለና የጠራ መስመር ለመያዝ እንዲያስችል ሁኔታወችን ቀድሞ ጠንቅቆ ማወቅ ማለት ነውና ምን እየተፈጸመብን እንደሆነ ለማንም የተሰወረ ስላልሆነ:- ድምጻችንን የሚያሰማው ጋዜጠኛ አሸባሪ ተብሎ ለእስር ሲዳረግና በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መደራጀት መብት ነው ተብሎ የተደራጀው የተፎካካሪ ፓርቲ አመራር አሸባሪ ተብሎ ሲዋከብና ሲታሰር በእምነቱ ዙሪያ ስለመብቱ የጠየቀ አልቃይዳ ተብሎ ሲጨፈጨፍና ሲገደል ከ 10 እና 15 ዓመት በላይ በኖሩበትና ሀብትና ንብረት አፍርተው ከኖሩበት አገር ያለምንም ጥሪት ንብረቱ ተወርሶና ቤቱ ፈርሶ ወደ ምትሔድበት ሂድ ተብሎ ከ 20,000 በላይ የሚገመት የአማራ ተወላጅ ከደቡብ ሲፈናቀል በሶስቱም ማእዘናት መሬቱን ለውጭ ባለሀብት ለመቸብቸብና የግል ካዝናቸውን ለማድለብ ገበሬውን ከማሳውና ከቅየው ሲያፈናቅሉ መሬትን በሊዝ እየሸጡ ለባለስልጣን ሀብት ማፍሪያ ለማድረግ ከተሜውን በመልሶ ግንባታ ሽፋን ቤቱን በዶዘር እያፈራረሱ ከሚኖርበት ሲያፈናቅሉና ሲያሳድዱ ስናይ ኖረን አሁንም ይህንኑ ሊገፉበት ሲሰናዱ አሜን ብለን የምንቀብልበት ጊዜ ማብቃት አለበት::

ይህም ሊሆን የሚችለው የአምባገነኑ አገዛዝ እያሳደረብን ያለውን ጫና በመቋቋም ሙስሊሙ ህብረተሰብ የጀመረውን የመብት ጥያቄ በመደገፍ እንደዜጋ የሃይማኖት ነጻነት ይከበር በሚል ሁሉም ድጋፉን መግለጽና የኦርቶዶክሱንም ፓትሪያርክ ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ምርጫ እንዲያደርግና እየተሳደዱ ያሉት የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ስቃይ ይቁም ገዳሙም እንደተከበረ ይቆይ የጭቁን አርሶ አደሩ መሬት ለውጭ ባለሀብት መሸጥ ይቁም በመጨረሻም አላግባብ የታሰሩ ጋዜጠኞች እነ እስክንድር ነጋ ና ሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ህዝባዊ የሽሽግር መንግስት ይቋቋም በማለት በየተሰማራንበት ድምጻችንን ከፍ አድርገን እናሰማ:: አንድ ሆነንም እንታገል::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 22, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 22, 2012 @ 9:47 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar