![Girum teklehaimanot walk though the valley of death](https://i0.wp.com/fbcdn-sphotos-h-a.akamaihd.net/hphotos-ak-xpa1/v/t1.0-9/10250277_962858207062595_5648395654431275369_n.jpg?resize=565%2C430&ssl=1)
walk though the valley of death Author by Girum Tekelehaimanot ሊያነቡት የሚገባ እውነተኛ ታሪክ የያዘ ድንቅ መጸሃፍ በገበያ ላይ የሞት ጉዞ በጋዜጠኛ ግሩም ተክለ ሃይማኖት ተጻፈ
በጸሃይ በየነ
ለዚህ ትውልድ ትልቅ ስጦታ
በጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት የተፃፈው ይህ ስለ እራሱና ስለሌሎች ወገኖቻችን የስደት ህይወት በተለይም በባህር በጀልባ ወደ የመን ሲገቡ ባለው የስቃይ ጉዞን የምናበት የስደት ትክክለኛ ገፅታን የምናስተውልበት መፀሐፍ ነው፡፡
በዚህ ስደት ምርጫችን በሆነበት ዘመን እንደ ጉድ እየተሰደድን እንደ ጉድ የምናልቅበት እንደሆነ የማይካድ አውነታ ነው፡፡ ከአኛ አልፎ የአለም ሚድያዎች ተኩረት ሰጥተው የሚወተውቱበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ታድያ ይህ አፍሪካውንን እየጨረሰ ያለው አስከፊው የዘመናችን መቅሰፍት በያንዳንዱ ኢትዮጵየያውን ልብ ውስጥ ትልቅ የማይሽር ጠባሳ ጥሎ አልፋል እያለፈም ነው፡፡
ይህ ወቅታዊ መፀሐፍ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤት መግባት እንዳለበትና ትኩረት ተሰጥቶ መነበብ እንዳለበት አምናለሁ፡፡ ምክንያቱም ስደት የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ቤት አንካኩቶ ልጅ፣ወንድም፣እህት ብሎም አባትን ከእጁ አስገብቶ አላየሁም ብሎ በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ የሀዘን ከል አልብሷል፡፡ የእናት እንባ አልደርቅ ብሏል፡፡
በዚህ እውነተኛ ታሪክን እቅፎ በያዘው መፀሐፍ ውስጥ አንድ ወንድ ልጅዎ ደህና ዋሉ ሳይል እንደ ወጣ የቀረው እንዴትና የት ሄዶ እንደሆነ የሚያገኙበት፣ የናጠጡ ሀብታም ለመሆን ተበድረውም ሆነ የቤት ካርታ አስዘው ወደ አረብ ሀገር የላኳት ልጅዎ ሀብታም ልታደርጎት አይደለም እራሷ መሆን አቅቷት እንደ ወጣች ሳትመለስ የውሃ ሽታ ሆና ለመቅረቷ ትልቁ ሚስጢርም በዚሁ ወቅታዊ በሆነው የሞት ጉዞ መፀሐፍ ላይ ያገኙታ እና እንዳያመልጥዎ፡፡ ለትውልዱ ትልቅ ስጦታ ነውና፡፡
Average Rating