www.maledatimes.com የብአዴን አባልነትን ያልተቀበሉ ሰራተኛ “ከተማዋን ለቅቀህ ጥፋ” ተባሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የብአዴን አባልነትን ያልተቀበሉ ሰራተኛ “ከተማዋን ለቅቀህ ጥፋ” ተባሉ

By   /   September 22, 2012  /   Comments Off on የብአዴን አባልነትን ያልተቀበሉ ሰራተኛ “ከተማዋን ለቅቀህ ጥፋ” ተባሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 55 Second

በአማራ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጐንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የአብርሃጅራ ከተማ አስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት እየፈፀሙ እንደሆነ የዜና ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ ምንጮቻችን እንደሚሉት“የቢሮው ኃላፊዎች ራሳቸውን ከህግ በላይ አድርገው ስለሚያስቡ የዜጐችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን እንዲሁም ሰዎች በዜግነታቸው ያገኙትን ህገ መንግስታዊ መብቶች ይጥሳሉ፡፡”  ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀርባሉ፡፡
ምንጮቻችን እንደሚሉት “ኃላፊዎች በማን አለብኝነትና በጀብደኝነት ሰዎችን በአመለካከታቸው ብቻ እንደ ወንጀለኛ በመቁጠር ከህግ አግባብ ውጭ ከሥራ ያግዳሉ ያዋክባሉ፣ ያመናጭቃሉ ያንጓጥጣሉ . . .” በማለት ያስረዳሉ፡፡ ለነዚሁ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ሰለባ ሆነዋል የተባሉትን የቢሮውን ሠራተኛ አቶ አንጋው ተገኝ ጠይቀን በሰጡን መልስ “በእርግጥ ከፍተኛ በደል እየተፈፀመብኝ ነው፡፡ እኔ የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ሠራተኛ ነኝ፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት የብአዴን አባል እንድሆን ተጠየቅኩ፡፡ እኔ እንደ አንድ የመንግስት ሠራተኛ የሞያ ሥራ ከመሥራት ውጪ አባል መሆን እንደማልፈልግ ነገርኳቸው፡፡
አንተ የተቃዋሚ ደጋፊ ስለሆንክ ቢሮ እንዳትመጣ ከሠራተኛ ጋርም እንዳትገናኝ ደሞዝህን ብቻ መጥተህ እንድትወስድ አሉኝ፡፡ እኔ ደሞዝ መውሰድ ያለብኝ ሥራ ሠርቼ ነው፡፡ ሥራዬን ልሥራ ብላቸው ከለከሉኝ፡፡ ምንም ማድረግ ባለመቻሌ አንድ ዓመት ሙሉ ያለ ሥራ ደሞዝ እየተከፈለኝ ቆየሁ፡፡ ተከታትለው ተከታትለው ምንም ጥፋት ሊያገኙብኝ ባለመቻላቸው አሁን ሰሞኑን ደግሞ ሥራውንም ከተማውንም ለቀህ ሂድ የሚል ትዕዛዝ ደረሰኝ፡፡ የተወለድኩትም ሥራዬም ኑሮዬም እዚሁ ነው፡፡ የት ልሂድ ብላቸው ምንም የምናውቀው ነገር የለም ወደ ፈለክበት ሂድ እያሉኝ ነው፡፡ አቤት የምልበት ቦታ አላገኘሁም፡፡ የዜግነት መብቴም ተገፏል፡፡ እባካችሁ የሚሰማ የመንግስት አካል ካለ ጩኽቴን አሰሙልኝ”ሲሉ መልሰውልናል፡፡ በዋናነት የመብት ጥሰቱን እየፈፀሙ ናቸው የተባሉትን የአካባቢውን የአስተዳደር ፀጥታ ሠራተኛ አቶ ገ/መድህን ወንድም እሸትን በስልክ አግኝተን ስለሚባለው ነገር ብንጠይቃቸውም “ዝናብ ስለሆነ አይሰማኝም፡፡ ለማላውቀው ሰው መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለሁም” የሚል መልስ የሰጡን ሲሆን የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ናቸው የተባሉትን አቶ ፋሲል ሰንደቁን በተመሳሳይ ሁኔታ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ አግኝተን ላቀረብንላቸው ጥያቄ በሰጡን መልስ “እኔ
አሁን ያለሁበት ቦታ በረሃ ውስጥ ስለሆነ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለሁም” ብለዋል፡፡ ባገኘነው መረጃ መሠረት ግን በረሃ ነኝ ያሉት አቶ ፋሲል በወቅቱ ቢሮአቸው እንደነበሩ መረዳት ችለናል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 22, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 22, 2012 @ 8:57 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With: ,

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar