www.maledatimes.com የማለዳ ወግ … በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ / ደ.ህ.ዴ.ን ክብረ በዓል ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ … በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን ክብረ በዓል  !

By   /   November 8, 2014  /   Comments Off on የማለዳ ወግ … በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን ክብረ በዓል  !

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 45 Second

በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ክንፍ የደ.ህ.ዴ.ን ፖለቲካ ፖርቲ አባላት ወዳጆቸ ባደረጉልኝ ግብዣ መሰረት በደ.ህ.ዴ.ንን 22ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተገኝቸ ነበር ።  እንደ ዛሬው የደ.ህ.ዴ.ን በዓል ፍሪዳ ተጥሎ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ድርጅቶች የልደት በዓላቸውን ሲያከብሩ እግር ጥሎኝ ስገኝ በምባረርበት የጅዳ ቆንስል ግቢ በሚገኘው የኮሚኒቲ አዳራሽ ተገኝቸም ኬክ እስኪቆረስና ሙዚቃው እስኪጀመር ያለውን ፕሮግራም ተከታትያለሁ። በልደት ፕሮግራሙ በቀረበው የድርጅቱ የትግልጉዞ “የስምጥ ሸለቆው ታጋዮች ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን የደቡብ የነጻነት ታጋዮች ከህወሃት ጋር ተቀዳጅተው በቅድመ ደርግ ያደረጉትን ትግል ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር  የሰማሁት። በትግሉ ሂደት 57 ብሄረሰብን ይወክላሉ የተባሉት 22 ድርጅቶች አንድ ሆነው ደ.ህ.ዴ.ንን ብለው  አንድ ግንባር መስርተው ለልማት ያደረጉትንም ፋና ወጊ የተባለ ሂደት ሃገሬው ባንድ ድምጽ ባንስማማበትም በቀረበው የበዓሉ መግለጫ ተሞካሽቶ ቀርቦም ነበር  ።

እንዲህ እያለ የቀጠለው መግለጫ በስደቲ እንፈ አሸን የፈሉት የፖለቲካ ድርጅቶች መኖርና እንቅስቃያቸው በዜጎች መብት ማስከበር ዙሪያ እርባና ያለው ለውጥ ስላላመጣ የተባለውን ዲስኩር በማዳመጡ ባልሳብም

ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን የሳውዲውን ስደተኛ መከራ ለመቅረፍ ስላደረገው ጥረት መስማት እንደጓጓሁ በሪፖርቱ የተጠቀሰ  ነገር ባለመኖሩ አልተደሰትኩም። በዚህ ረገድ  ” ለህዝብ ቆምኩ ” የሚለው ድርጅት ለቆመለት ህዝብ አካል ለሆነው  ስደተኛ ዜጋ መብት ማስጠበቅ አልተጋም ብየ ለምሞግተው ዜጋ በስደት በዓሉን የሚያከብረው  ድርጅት ዲስኩር መረጃ አልሰጠኝምና ላወግዝ ፣ ልቃወመው አልልም ። ድርጅቱ በበዓሉ ያሻውን ማለት መብቱ የተጠበቀ እንደመሆኑ እኔም እንደ ዜጋ የሚሰማኝን የመናገር መብቴን ተጠቅሜ የተሰማኝን እንዲህ እጦምራለሁ  ! ፈራጁ ታዳሚው ብቻ ነውና …  !በድግሱ ቁርጡን ጨምሮ ያማረ ምግብ ቀርቦ ፣ በዓሉ በአባላቱ ደምቆ ከሚከበርበት አዳራሹ ሳልወጣ ” ዘንድሮ የአቋም ለውጥ እያመጣህ ነው ፣ ትናንት በአሰራሩ ትኮንነው የነበረውን ቆንስል መስሪያ ቤት የፓስፖርት እድሳት ማስታወቂያ በፊስ ቡክህ መልካም ጅምር ነው በማለት እያሞካሸህ የምትጽፍና የታደሰውን ፖስፖርት ዝርዝር የምታወጣው ጋዜጠኛ ሆነሃል፣ ይባስ ብሎ ዛሬ ደግሞ

ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን በዓል ተጋዥ መሆንህ ተገለባባጭ መሆንክን እያሳየን ነው ” ያሉኝ የኮሚኒቲ ሹሞች ሱፍ ባይደርቡበትም ከሸሚዛቸው ላይ ከረባቷን ጣል አድርገዋል፣ አንዳንዶቹ ደግሞ የዘወትር ልብሳቸውን እንደለበሱ በአሉን እንደኔው ለመከታተል ታድመዋል ። የኢህአዴግ ድርጅቶች በስደት ያለውን የነዋሪ ጩኽትና መከራ በቅረብ እተመለከታችሁ መፍትሔ ስለማታመጡ አልደግፋችሁም ፣ በሚል የሰላ ሂስ በማቅረብ የምሞግታቸው በውይይት የሚያምኑት ግን ለውጥ ማምጣት አልቻሉም የምላቸው ስልጡን የድርጅት አባላት ወዳጆቸም በዓሉን ለማድመቅ ያማረ ሱፍና ከረባታቸውን ቦጫ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን አርማ ያለበት ቢጫ ኮሪያቸውን ደንቅረው ሲያሰተናግዱና ሲስተናገዱ አምሽተዋል። ” ከምንም በላይ የዜጎችን መብት ማስቀደሙ ይቅደም!”  ለምለውና በግል በዘር ለማላምነው ዜጋ የድርጅቱ አባላት ወዳጆቸ ” በሳውዲ ስደተኛ ህይወት ዙሪያ መሻሻልና መብት መጠበቅ ተግተን እንሰራለን! ” ስለሚሉን ስራ በበዓላቸው ማዘከሪያ በቀረበው ሪፖርት አለመገለጹን እንዴት እንደሚያዩት የምሰማው ግን ነገ ከነገ ወዲያ ይሆናል  …


እዚህ ላይ አንድ አፍታም ቢሆን መንፈሴን ስላወከውና ስላልተቀበልኩት ጉዳይ ልጠቁም … ከ
 ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  / ደ.ህ.ዴ.ን ድርጅት  የትግል ሂደት ማስተዋወቂያ ሪፖርት ቀጥሎ በመድረኩ አስተዋዋቂ በአቶ ሰመሩ ርቱዕ አንደበት ተቀሽራ በቀረበች አንድ ግጥም በደቡብ ከታቀፉ ብሔረሰቦች መካከል አንዳንዶቹ ተጠቅሰው በቅድመ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አገዛዝ ” ቀጥቃጭ” እና “ሸማኔ ” እየተባሉ እንደተጨቆኑና እንደተገፉ በአጽንኦት ተገልጿል። ግጥሟ በተስጎድጓጅ ድምጽ በመነበቧ፣ ስንኝ በመምታቷና በተከሸነ ቋንቋ ከመቅረቧ ባሻገር በጥላቻ የታመቀች ጥበብ ነበረችና አልወደድኳትም። ቢያንስ በዚህ የልደት በዓል ባልቀረበች ብያለሁ …ራሴ ለራሴ  !

ከግጥሙ ቀጥሎ በዓሉን ለማድመቅ ሙዚቃና ዳንኪራው ጀመረ ፣ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የድርጅቱ አባላትና ተጋባዦች መድረኩን ተቆጣጠሩት ፣ መድረኩ ሞቅ ሞቅ ሲል ጠሪዎችን አመስግኘ ወደ ቤቴ ስመለስ አንድን ሰሞነኛ ጉዳይ እያውጠነጠንኩ ነበር።  “አቋምህን ትቀያይራለህ ” ስለተባልኩበት ወቀሳ ፣ ከድርጅት አባላቱ ጋር የስደተኛውን ህይወት ታደጉት በሚል ስለማደርገው ሙግት ምክክርና ውይይት ፣ ከልታማውን የጅዳ ኮሚኒቲ “ከማህበረሰቡ ወደ መንግስት ይዞታ ይቀይረዋል ” ተብሎ ስጋት ስለማንዣበቡና በዚያ ዙሪያ ያለኝን ጭብጥ መረጃ በማለዳ ወጌ ለመዳሰስ ነበርሸማሰላሰሌ   ! አዎ የስደተኛው ጉዳይን የሚመለከት ማንኛውኛውም ጉዳይ ያገባኛልና አቅሜ በፈቀደ መጠን እዳስሰዋለሁ ! የስደተኛው ጉዳት ያገባኛልና ዛሬም እጦምራለሁ  !
ሰላም

ነቢዩ ሲራክ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar