www.maledatimes.com ለሰላምና ፍትህ ሰባኪያን የእድሜ ልክ ፤ ለነፍስ ገዳይ የአምስት አመት እስራት! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

  ለሰላምና ፍትህ ሰባኪያን የእድሜ ልክ ፤ ለነፍስ ገዳይ የአምስት አመት እስራት!

By   /   November 8, 2014  /   Comments Off on   ለሰላምና ፍትህ ሰባኪያን የእድሜ ልክ ፤ ለነፍስ ገዳይ የአምስት አመት እስራት!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 15 Second

 

 

ኦስካር ፒስቶሪየስ ዝነኛው አካል ጉዳተኛ አትሌት በ21/ 10/ 2014 በነፍስ ግድያ ወንጀል የአምስት አመት የእስር ቤት ፍርድ ተወስኖበታል። በኢትዮጵያ ከስድስት በላይ መጽሄቶች አዘጋጆች ባለቤቶች እና ጋዜጤኛች የእስራት ቅጣት በወያኔ መንግስት ተወስኖባቸዋል ።በተቸማሪም የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መሪዎች እና  ደጋፊዎች የእስራት የእንግልት የመገለል እንዲሁም የመሰደድ ፍርድ በጨቋኙ የኢህአዲግ መንግስት ተጥሎባቸዋል።በነፍስ ማጥፋት ኦስካር ፒስቶሪየስ 5 አመታት እስራት ከተፈረደበት ለ90 ሚሊዮን የተጨቆነ ህዝብ ነጻነት እኩልነት እንዲሁም ፍትህ የሰበኩት እንዴት የእድሜ ልክ አሊያም የ18 አመታት እስራት ይፈረድባቸዋል?

በ2011 ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛና ብሎገር እስክንድር ነጋ የ18 አመት እስራት በወያኔ መንግስት ተፈርዶበታል።ይህ ጋዜጠኛ በአሜሪካ ከሚገኘው እጅግ ክብር ካለው ፔን አሜሪካስ ፍሪደም ራይተርስ ( Pen Americas Freedom ) የ2011 የአመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ ተብሎ ሽልማት አግኝቷል።በተቃራኒ የኢህአዲግ መንግስት እጅግ አሳፋሪ የሆነ የ18 አመታት እስራት አከናንቦታል በተጨማሪም።የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ (UDJ) ፓርቲ አባልና ቃል አቀባይ አቶ አንዱአለም አራጌ የእድሜ ልክ እስራት በጎጠኛው የአሁኑ የኢትዮጵያ መንግስት ተፈርዶበታል።አቶ አንዱአለም አራጌ የወያኔን ጨቋኝ አገዛዝ በይፋ ስለተቃወመ ለእድሜ ልክ እስራት ተዳርጉዋል።በወያኔ ተጽእኖ ስር ወድቆ የሚሰራው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ለአንዱአለምና ለእስክንድር ይህንን ቅጣት ከሰጠ ኦስካር ፒስቶሪየስ ምን ይቀጣው ነበር ?

የጋዜጠኞች የብሎገርስ እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች እስራት እንግልት ስደት እና ስቃይ ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ እየጨመረ ይገኛል ።በ2014 ብቻ የወያኔ መንግስት በጋዜጠኞች በብሎገሮች እና በአታሚዎች ላይ የወሰደው የእስራትና የቅጣት እርምጃ እጅግ አምባገነናዊና ኋላቀር አስተሳሰብ መሆኑን ያሳያል ።ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ የአዲስ ጉዳይ (Addis Gudaye )  የሎሚ (Lomi) ፋክት (Fact)የአፍሮ ታይምስ (Afrotimes )የጃኖ (Jano) እና የእንቁ (Enku)መጽሄቶች አሳታሚዎች ባለቤቶችና ጸሃፊዎች ወይም ጋዜጠኞች በ2014 በኢህአዲግ መንግስት ክስ የተመሰረተባቸው ናቸው ።

ይህንን አግባብ የሌለውን ክስና ፍርድ በመሸሽ ጋዜጠኞች ከኢትዮጵያ በመሰሰድ ላይ ይገኛሉ ።ከእነዚህም ውስጥ የማራኪ ( Maraki magazine) መጽሄት አዘጋጅ ጋዜጠኛ እና የአንድ ልጅ አባት ሚሊዮን ሹርቤ ከወያኔ ጨቃኝ እስራትና ቅጣት ለመሸሽ ወደ ኬኒያ አገር ለመሰደድ ተገዶ ነበር ።ጋዜጠኛ ሚሊዮን ህይወቱን ከወያኔ ኢፍትሃዊ ፍርድ ለማዳን ቢሰደድም ባለቤቱን ልጁንና አገሩን ዳግም ላያይ ለዘላለሙ በኬንያ ህይወቱ አልፉዋል ።የወያኔ ባለስልጣኖችንና የተሳሳተ ተግባራቸውን በይፋ ሰለ ነቀፈ ወደ ፊት ብዙ የጋዜጠኛ ስራ የመስራት የሚችል እምቅ ችሎታ ያለውን ይህንን ወጣት ጋዜጠኛ ለስደትና ለሞት አብቅተውታል ።ሃሳብን በነጻ በዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ መንገድ ለመገለጽ የሞከረው ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹርቤ የስደትና የሞት ፍርድ እጣው ከሆነ ወያኔ የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ኦስካር ፒስቶሪየስን እንዴት ያለ ፍርድ ይፈርድበት ነበር ?

የወያኔ ባለስልጣናት ትግል ጀመርንብት ከሚሉት ጊዜ ጀምሮ እስክ ዛሬ (2014) በኢትዮጵያ ህዝብ እና አገሪቱ ላይ ከመጠን በላይ አሰቃቂ ድርጊቶችን እየፈጸመ ይገኛሉ።በተቃራኒው ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እኩልነት ብልጽግና እንዲሁም ሰላም ብእራችውን ከወረቀት ጋር ያገናኙት ጋዜጠኞች ብሎገሮች እና ተቃዋሚዎች የስደተና የእስራት ኢፍትሃዊ የሆነ ፍርድና ቅጣት እየተፈረደባቸው ይገኛሉ።ነጻነት ፈላጊዎቹና ሰባኪያኖቹ እየተሰደዱና እየታሰሩ በተቃራኒው ነጻነት ነፋጊፊዎቹ የወያኔ ባለስልጣናት ተደላድለው የሚኖሩበት ጊዜ ማክተም አለበት። ኦስካር ፒስቶሪየስ እራሱ በቃሉ ባመነውና አቃቢ ህግ ባረጋገጠው የነፍስ ግድያ ወንጀል አምስት አመታት እስራት ሲፈረድበት ታዲያ ለሰው ልጅ እንደ መሰረታዊ ፍላጎት አስፈላጊ ለሆኑት እንደ ነጻነት እኩልነት ሰላም ፍቅር መስፈንና መጎልበት በቁርጠኝነት የታገሉት እነዚህ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ፖለቲካ መሪዎች እና አባላት እንዴት የሞትና የረጅም እድሜ እስራት ይፈረድባቸዋል?

በዘርይሁን ሹመቴ

ከ ጀርመን ሆፍ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar