በአዲስ አበባ በአሰቃቂ ሁኔታ የ 17 ዓመቷን ወጣት ለአምስት ቀን ያህል አፍነው ሲደፍሩ የቆዩት ተያዙ። ጉዳዩ አሰቃቂ ነበር። ሃና ትባላለች። የ 17 ዓመት ወጣትና ተማሪ ነች። አየር ጤና ከሚባለው ሰፈር ተነስታ በሚኒባስ ተሳፍራ ወደ ጦር ሃይሎች ለመሄድ ስትሞክር ነው፣ ታክሲ ውስጥ በነበሩ አምስት ወንዶች (ጓደኞች ናቸው) ታፍና ለአምስት ቀን ስትደፈር የቆየችው።
ለአምስት ከደፈሯት በኋላ በመከራ አንዱን አሳምና ደህና መሆኗን ለጓደኛዋ እንድትነግር ስልኩን ትጠይቀዋለች። ይሰጣታል፣ ወዲያው ለጓደኛዋ ደውላ መናገር ስትጀምር፣ ስልኩን ይቀማታል፣ ግን ቁጥሩ መውጣቱ በቂ ነበረና በዚያ ክትትል ሊያዙ ችለዋል። ሃና በደረሰባት የውስጥ አካል ጉዳት (ከፊትም ከኋላም) ፣ ከጥቂት ቀናት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል።
ሃና ፍትህ ልታገኝ ይገባታል – ለወደፊቱ የሚመጣውን ለማስቆም በቂ ፍትህ አሁን !!!
መቼም ለወዳጅ አይታሰብም፡፡ለጠላትም ቢሆንኳ እንደ አፀያፊ በቀል ይቆጠራል፡፡ለሐና ለላንጎ ግን ባገገኘቸው በምን ዕድሏ በሆነ ነበር፡፡ቀንበጥ ነበረች ፣ ደብተሮቿን በቦርሳዋ ተሸክማ ዩኒፎርሟን ለብሳ ሚኒባስ ታክሲ ተሳረች፡፡ከአየር ጤና ሳሚ ካፌ አጠገብ በተሳፈረችው ታክሲ እሰከ ጦር ኃይሎች ከተጓዘች ይበቃታል ፤ቤቷ አካባቢ ደርሳለች ማለት ነው፡፡የጉዞዋ ቅርብነት፣ የተሳፈረችው በይፋና በአደባባይ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመሥጠት ላይ የነበረ ሚኒባስ ታክሲ መሆኑና ሰዐቱም ገና ብራ ከቀኑ 9:30 መሆኑ ለአሥራ ቤቷ ቀምበጥ በሠላምና በጤና አቤት መድረስ እንድንሰጋ የሚያደርገን ምንም ምክንያት አየሰጠንም ነበር፡፡ደግሞም ያለችው ሰው እንደ ጎርፍ በሚተራመስባት የሀገራችን ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ ውሥጥ ነበር፡፡ግን… ይሕ ሁሉ ድርድር ሐና ጅምር የለጋ ዕድሜ አካሏን ፣ስሜቷንና ሕሊናዋን በእኩል የቀረደደ ፣ክብሯንና ልቦናዋን በእኩል ያረከሰና በአሰቃቂ ፍፃሜ ትኩስና አፍላ ነፍሷን የቀማ ጭልጥ ያለ ምድረ በዳ ና 5 ቀንም ተጉዘው በሕይወት የማይወጡበት በረሐ ነበር ፤ፍጹም በርሐ!5 ቀን ሙሉ በ5 በዕፅናበወሲብ የነደዱ ፣በማይታጠብ ገላቸው ልብስና ጫማቸው ትንፋግ የጠነቡ፤ለወንጀላቸው መፈፀሚያ በተከራዩት ‘አይኖርበት’ጎሬ ውስጥ እስረኛ ገላዋን ቁጥር ስፍር ለሌለው ጊዜ ተጫወቱባት፤ቀረደዷት ፤ ማህፀኗ አስኪቆሳስልና ፊንጢጣዋ ቀሳስሎና ተተርትሮ በደም እስክትታጠብ ድረስ ጨፈሩባት፡፡5 ቀን ሙሉ ሲያሰቀዩኣት አህል ውሀስ አቅምሳዋት ይሆን ?ወይስ እራብና ጥማቱም አንዱ የማሰቃያቸው አካል ነበር?ሐና የስቃይሽን መጠን የሰቆቃሽን ርዝማኔና የአሰቃዮችሽን አውሬነት ሳስብ የዛን ቀን የነሱን ታክሲ የተሳፈርሽ ሰዐት ምነው የመኪና ጎማ ውስጥ በገባሽ ኖሮ እላለሁ፡፡ጨከኜና ፈርጄብሽ ሳይሆን ሰቃይሽን ያሳጣርኩ መስሎኞ ነው፡፡ይህ በደለሽ ይህ ራሷ አዲስአባን የሰው ኩላሊት በቁም ከሚዘረፍበት “የሰው ቄራ”ሲናይ በርሀ ጋር በውርደት ያነፃፀረ በደልና መከራሽ ከጎንሽ የሚቆሙና ድምፅ የሚሆኑሽ አነማንን ያስነሳልሽ ይሆን? አዲስ አበባ የምትሰጥው ዳኝነትና የምትበይንልሽ ፍትህ ምን ይሆን?ያን ቀን የትምህርት ቤት ጓደኖችሽ፣የፈረደባቸው ወላጆችሸና አኛም ዬኒፎርምሽንናደብተሮችሽን ከፍ እርገን ይዘን እንገኛለን ፤ሐና ሕይወት ነበራት ፤ሐና ተስፋ ነበራት ፤አሁን የታለ ብለን? ድምፃችንን አናሰማለን፡፡
ሃና ተማሪ ነች። ሃና 17 ዓመቷ ነው። ሃና ለወንድም እህቶቿ ጣፋጭ እህት ነች። ሃና ለወላጆቿ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነች። ሃና ለጓደኞቿ ምርጥ ጓደኛ ነች። ሃና ለኢትዮጵያ አንዲት ዜጋ ነች። ሃና ተስፋ ያላት ፣ አብዛኛው ህይወቷ ወደፊት የሆነ ወጣት ነች።
ሃና ጎበዝ ነች – አምስት ቀን ሙሉ አረመኔዎችን ተቋቁማ ቆይታለች። ሃና ጀግና ነች – እንደምንም ብላ በአንዱ አውሬ ስልክ በመጠቀም ቢያንስ ለመያዛቸው ምክንያት ሆናለች። ሃና ደፋር ነች፣ አምስት ጎረምሶች በተቀመጡበት ታክሲ ደፍራ ገብታለች።
እናም በአምስት ጎረምሶች ለአምስት ቀን ተደፈረች። ሰውነቷ ተበላሸ – ህይወቷም አለፈ። አሁን አገር ሲነጋ ሜክሲኮ አካባቢ ያለ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ፣ በመድፈር ወንጀል የተጠረጠሩት ጎረምሶች ተይዘው ይቀርባሉ ተብሏል። .. ፍትህ እንፈልጋለን። ሃና የሁላችንም እህት የሁላችንም ልጅ ነች።
Average Rating