www.maledatimes.com እጅለእጅእንያያይዝ (በይግዛው እያሱ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  POEMS  >  Current Article

እጅለእጅእንያያይዝ (በይግዛው እያሱ)

By   /   September 25, 2012  /   Comments Off on እጅለእጅእንያያይዝ (በይግዛው እያሱ)

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 1 Second

እጅለእጅእንያያይዝ  በ ይግዛው እያሱ

ገበሬው ይዳሰስ ላብ አድሩም ይቃኝ

ምሁሩም ይፈተሽ ዙሪያ ገባው ይታይ

ይደራጅ ሀኪሙ ሁሉም ይነቃነቅ

ተማሪን ብቻ አንበል ከፊት ሆኖ እንዳያልቅ::

ባገር ውስጥም ሆነ ውጭ አገር ያላችሁ

ለነጻነት ትግሉ ግቡ ወስናችሁ::

የወያኔ አገዛዝ ጭቆና እንግልቱ

ከአንዱ አንዱ አያዳላም እኩል ነው ቅጣቱ::

መራብ መጠማቱን ሆዳችን በቻለ

አላረካው ብሎ አላስኖር እያለ

ቤታችንን ሲያፈርስ በቁም ሊቀራመት

እስኪ ምን ይባላል ፀጥ ብሎ ማየት::

ገበሬው ከማሳው ከቦታው ሲጠፋ

ከተሜው ሲሰደድ ዛሬ ቆርጦ ተስፋ

እሱና እሱ ብቻ ለመኖር ሲስማማ

መፍቀድ የለብንም ድምጻችን ይሰማ::

እጅ ለእጅ ተያይዘን እንቁም በጋራ

አገር ሳያጠፋ የወያኔ ሴራ::

መጥፋቱንስ ጠፍቷል ሁሉም ነገር ፈርሷል

መጀመር ነው እንጅ መች መጨረስ ያውቃል::

ግን ባለበት ይቁም ሁሉም ነገር ይብቃ

ሕዝብን አይቁጠሩት እንደገዙት እቃ::

ስልጣኑን ያስረክብ ህዝብ በሚስማማበት

ቀርቦ ይነጋገር ” እውነት” ከቻለበት::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 25, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 25, 2012 @ 5:04 am
  • Filed Under: POEMS

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

አንድዬ

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar