አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
************************************************************
******
አንድነት የፀረ ሽብር አዋጁ ተቀብሎትም አያውቅም፤ አይቀበለውም!
************************************************************
*******
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፀረ ሽብሩ አዋጅ እንዲሰረዝ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ከማድረግ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ
እንዳደረገ የሚታወቅ ነው፤ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት እንቅስቃሴም አንዱ አካል የፀረ ሽብር አዋጁ ይሰረዝ የሚል ነው። ለዚህም አባላቱንና በርካታ የተለያዩ
የህብረተስብ ክፍሎች ፊርማ አሰባስቧል። አንድነት ከመጀመሪያው ጀምሮ “ፀረ ሽብር አዋጁ እራሱ አሸባሪ ህግ ነው” ብሎ አቋም ተንቀሳቅሷል፤ በዚህም ሂደት
በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላትና አመራሮች ለእስርና ለእንግልት ተዳርገዋል፡፡
አሁንም ቢሆን ፓርቲያችን አንድነት በሀገራችን አምባገነናዊ ስርዓት እስኪወገድ ድረስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፍል ዝግጁ የሆኑ አባለት ያሰለፈ ፓርቲ ነው፡፡
በመሆኑም፤ ይህ አዋጅ በገዥው ቡድን እየተጠቀሰ ወደ ወህኒ ቤት እየተወረወሩ ያሉት ዜጐች የህሊና እስረኞች ናቸው ብለን እናምናለን። በዚህ ምክንያትም ነው
እነርሱን የሚያስታውስ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች” የሚል የአንድ ሳምንት ዘመቻ አውጀን እየተንቀሳቅስን ነው ያለነው።
በአንዳንድ ወገኖች አንድነት በፀረ ሽብሩ አዋጅ ላይ የተለየ አቋም እንደያዘ ተደርጎ እየቀረበ ያለው አሉታዊ ቅስቀሳ መሰረት የሌለው መሆኑና ፓርቲ በፀረ-ሽብር
አዋጁ ላይ ያለው አቋም አሁንም ያልቀየረ መሆኑን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን።
አንድነት አሁንም ቢሆን በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ ዜጎች በአስቸኳይ መፈታት እንዳለባቸው ያምናል፤ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱና ዴሞክራሲያዊ የሆነ
የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል። አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ አንድነት ፓርቲ
ህዳር 13 ቀን 2007 ዓ.ም.
የግርማ ሰይፉን የአፍ ወለምታ ይቅር በሉት፤ የአንድነት አቋም ይኸውና
Read Time:57 Second
- Published: 10 years ago on November 22, 2014
- By: maleda times
- Last Modified: November 22, 2014 @ 8:12 pm
- Filed Under: Ethiopia
Average Rating