www.maledatimes.com ‪‎እጮሃለሁ‬!! Wosenseged Geberekidan - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

‪‎እጮሃለሁ‬!! Wosenseged Geberekidan

By   /   November 22, 2014  /   Comments Off on ‪‎እጮሃለሁ‬!! Wosenseged Geberekidan

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 51 Second

አንድ “ጣፊ ነኝ” ባይ፤ “ሃናን የደፈሩት ((ሰዎች)) ናቸው ሰዎች ብቻ !!” በሚል ርዕስ በቸከቸከው ነገር የተነሳውን የፌስቡክ መንደር ንትርክ ሳነብ አዘንኩኝ፡፡ ከሃዘኔ የተነሳ ምንም ነገር ላለማለት ፈልጌ ነበር፡፡ ግን አልቻልኩም፡፡ ስለዚህም ጥቂት ነገር ማለት ወደድኩ፡፡

ይኼ “ጣፊ” ነኝ ባይ፤ የኢፌዲሪ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር “በሃና ላላንጎ ላይ የቡድን አስገድዶ መድፈር ጥቃት ያደረሱት ግለሰቦች ‹የሰው አራዊቶች› ናቸው -” ማለቱ ከዋናው ጉዳይ በላይ አንገብግቦት የጣፈው ጉዳይ ድሪቷም ሆኖብኝ ለማመን ተቸገርኩ፡፡ ከሁሉ በላይ ወንጀል የተፈፀባትም ሆነ ወንጀል ፈፃሚዎቹ “ሰዎች” መሆናቸውን ሊያስረዳን የቃጣበት ድሪቷም ሃተታ ለጣፊው ለራሱ እንዳዝንለት ነው ያደረገኝ፡፡ ቀድሞ ነገር ከ“ጣፊ” ከዚህ በላይ መጠበቅ ሞኝነት ነውና ወደ ዋናው ጉዳያችን ልለፍ፡፡

ምክንያቱም የሃና ላላንጎ መደፈር ለህልፈተ-ህይወት መዳረግ ከምንም በላይ ያንገበግበኛል፡፡ የተደፈረችበትን መንገድ በሃሳቤ ሳሰላስለው እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሌ አንድ በአንድ ተቆነጣጥቦ እየተቆረጠ እቶን እሳት ውስጥ እንደተጣለ ሲንጨረጨር ይሰማኛል፡፡

እንደውም ይህ ስሜቴ የሃናን ጥቃትና ሞት ቅንጣት እንኳ አይገልፀውም፡፡

በተንተተረከ ፍም ውስጥ የጋመና የነደደ ብረት ይታያችሁ! ያንን የጋመና የፋመ ብረት የሰው ልጅ ገላ ውስጥ መጨመር ይታያችሁ! እስቲ ከዚህ ፅሁፍ ጋር የምትመለከቱን የሃና ላላንጎን ገፅታ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ!? ገራገርነቷን አይታያችሁ፡፡ ዓይነ ውሃዋን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ? አፍለኛውንና ያልጠናውን የልጅነት ገላዋ ገርነት አይታያችሁም?!

እዚች ልጅ ገር ገላ ውስጥ በወሲብ እቶን የነደደና የጋመ “ብረት” እየሰደዱ ማህፀኗን መጠቅጠቅና ወንፊት ሲያደርጉት ይታያችሁ! ማሕፀኗን ብጥቅጥቁን ሲያወጡት ይታያችሁ፡፡ ይህ “አውሬነት” አይደለም ብሎ ለመከራከር መሞከር ነፈዝነት ነው፡፡ ከአውሬነትም በላይ ነው፡፡ አውሬ እንኳን ግዳይ የሚጥልበት የራሱ ስርዓት አለው፡፡ ከአውሬ ባህርይ በባሰ መልኩ የዚችን ታዳጊ “ሙት” ገላ፤ ያውም ለአምስት፤ ያውም ለአምስት ቀን መቀረጣጠፍ ከጭካኔ በላይ ጭካኔ ነው፡፡

እርግጥ ነው፤ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል አዲስ አይሆን ይሆናል፡፡ ከዚህ በፊት ለተፈፀሙ የሴቶች ጥቃት በወቅቱ እና በወጉ አልተጮኸ ይሆናል፡፡ ያኔ ጊዜ፣ ሁኔታ፣ እና አጋጣሚ አልፈቀደ ይሆናል፡፡ ያኔ የሰዎች ንቃተ-ህሊና እና የመረጃ አቅርቦት አለመዳረስ በጉዳዩ ላይ ትኩረት እንዳንሰጥ አድርጎን ይሆናል፡፡ ዛሬ ግን ይህንን እጅግ ሰቅጣጭ ወንጀል ዝም ማለት አይቻልም፡፡ የሚቻልም አይመስለኝም፡፡

ቀደም ሲል እንዳልኩት፤ እኔ የሃና ላላንጎን ስቃይ እና ሞት ሳስብ እያንዳንዱ የስጋዬ አካል እሳት ውስጥ እየወደቀ ሲንጨረጨር ይሰማኛል፡፡ የእናቴ፣ የእህቴ፣ የፍቅረኛዬ ሰውነት እየተቀነጣጠበ እሣት ውስጥ ሲወድቅ ይታየኛል፡፡ ስለዚህም እጨሃለሁ፡፡ ለነገው የሴቶች ህይወት ዋስትና ስል ከወዲሁ እጮሃለሁ፡፡

እጮሃለሁ!

አንድ ነገር በደንብ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ በሃና ላይ ወንጀል በፈፀሙ ሰው-በላዎች ላይ የሚሰጠው ፍርድ ለሃና እንደማይጠቅማት ጥንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ፍርዱ የሃናን ህይወት እንደማይመልስ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

ቢሆንም እጮሃለሁ!

ለእናቶቻችን፣ ለእህቶታችን፣ ለፍቅረኞቻችን፣ ለሚስቶቻችን ህይወት ዋስትና ስል እጮሃለሁ!!

ለሃገራችን የፍትህ ስርአት ስል እጮሃለሁ!! ሃገር የምትመሰለው ወይም የምትጠራው በሴት አምሳል አይደለ!?

ስለዚህ ለፈጣን ፍትህ ስል እጮሃለሁ!!

#እጮሃለሁ!!

/

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on November 22, 2014
  • By:
  • Last Modified: November 22, 2014 @ 8:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar