በዛሬው እለት በራስ ሆቴል የሃናን የእልፈተ ህይወትታስመልክቶ ለመታሰቢያ የተደረገው ልዩ ስብሰባ ህብረተሰቦችንናስደምሞ ነበር የተጠበቀውን ያህል ህብረተሰብ ባይገኝም በበቂ ሁኔታ ማስተላለፍ የተፈለገውን ሃሳብ ለማስተላለፍ ሰፊ ሰአት ተሰጥቶት ፕሮግራሙ ተካሂⶌል ። ለጥቃት ምላሽ መሰጠትታለበት የሚሉት እና ወደፊት ሴት እህቶቻችን እናድን የሚለው መፈክራቸው ፣የህግ አስከባሪዎችንም ሆነ ማናቸውም የዚህ ድርጊት ተባባሪ የሆኑ በሙሉ በህግ ስር ተጠያቂ መሆንናለባቸው ሲሉ ጠይቀዋል።
ሃይሌ ገብረስላሴ በሬዲዮ ለተጠየቀው ምላሽ ለነገው ትውልድና ለሶስቱ ሴት ልጆቼ እጨነቃለሁ ዛሬ ሰላም ከሌላቸው ነገ በሰላም አይኖሩም ፣ከሚላን ላይ አሲድ የደፋባት ፩ ሰው ነው አሁን ግን ሃናን ግን የደፈሯት ፭ ሰዎች ናቸው ይሄ ማለት አምስቱም የእንሰሳ ባህርይ እንጂ የሰው አስተሳሰብ የላቸውምን እንዴት እንደሰው የሚያስብ ከአምስቱም አንድ ይጥፋ ሲል ገልጾአል ። በህንድ ብዛት ያላቸው ሰዎችቸንደሚደፈሩ ገልጾ በሃገራችን ደግሞ እንደዚሁ ብዛት ያላቸው ሰዎች በተለያየ የሃገሪቱ ክፍል ክብራቸው እንደሚደፈር ጠቁⶁአል በዚህም የተነሳ ለእነዚህ ሰዎችም ፍርዱ ሞት ቢሆንም አይከብድም ሲልም ጠቅለል አድርጎ ፍርዱን ተናግⶂል ።
በሌላ በኩል አዜብ ወርቁ በራስ ሆቴል የተከናወነውን እንዲህ አጠር አድርጋ ለሶሻል ኔትወርክ ጛደኞችዋ ለማካፈል ሞክራለች እኛም እንዲህ አዘጋጅተነዋል ።
ዛሬ በራስ ሆቴል በተደረገው ስብሰባ ላይ የጠበቅኩትን ያህል ባይሆንም በርከት ያሉ ሰዎች ተገኝተው ነበር
በስብሰባው ላይ ከተባሉት…
የሃና አባት – ሃና ለ5 ቀናት ብቻ ሳይሆን ለ11 ቀናት ነው ጠፍታ የቆየችው
ዶክተር ምህረት – እነሱ አውሬዎች ከሆኑ እኛ ጫካዎች ነን አውሬ የሚደበቀው ጫካ ውስጥ ነው ፡፡ ሃናን የገደሏት ሃናን የደፈሯት እያዩ ያልተናገሩት ጎረቤቶች፣ ሕግ አስፈጻሚ ፖሊሱ፣ በአፋጣኝ ህክምናውን እንድታገኝ ያልረዷት የሕክምና ተቋማትም ጭምር ናቸው፡፡ በማለት በጣም ጥሩ አድርገው ገልጸውታል፡፡
የሀና በግፍ መገደል ዘግናኝ ወሬ ሰዉን ሁሉ ካሳቀቀ በኋላ፡፡ አንዳንድ ወሬዎች እየወጡ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ወሬዎች እንደሚመጡ እጠብቅ ነበር፡፡
ሃና ታፍና አልተወሰደችም ተከትላ ነው የሄደችው ዓይነት ተራ ወሬ………. እና ብትሄድስ ? ተከትሎ መሄድ ይሄን ዓይነት ዘግናኝ እና አሰቃቂ ግፍ ለመፈጸም ምክንያት ነው?
በሕንድ ሐገር ከጓደኛዋ ጋር በባስ ተሳፍራ በነበረች ሴት ላይ በሹፌሩ እና በ4 ተባባሪዎቹ የተፈጸመባት እና ለሞት የዳረጋት አሰቃቂ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ዓለምን ባስደነገጠበት ሰዓት
የተከሳሾቹ ጠበቃ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት- እሷስ ቢሆን ካላገባቸው ወንድ ጋር ከመሸ ውጭ ምን ታደርጋለች ?
በዛ ሰዓት እንዴት ባስ ትሳፈራለች? የሚል ምላሽ ሰጥቶ ዓለምን ጉድ አሰኝቶ ነበር
እኛም ሐገር እንዲህ ዓይነት አስተያየት ይሰጣል ለማለት ሳይሆን ከምሰማቸው አንዳንድ አስተያየቶች በመነሳት እንዲህ አይባል ይሆናል ብዬ ግን ለመገመት እቸገራለሁ
እባካችሁን ሴቶች እራሳችሁን በሐና ቦታ አስቀምጦ እናቶች እራሳችሁን በሐና እናት ቦታ አስቀምጦ
ወንዶች በሐና ወንድም እና በሐና አባት ቦታ አስቀምጡ
ምንም ዓይነት ሰበብ ሴትን በእንዲህ ዓይነተ አሰቃቂ ሁኔታ ደፍሮ ለሞት ለማብቃት ምክንያት ሊሆን አይችልም!፡፡
አስቸኳይ ፍትሕ ለሐን
Average Rating