www.maledatimes.com ጋዜጠኛ መልካም ሞላ በድጋሚ ተከሰሰች! በአስናቀ ልባዊ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጋዜጠኛ መልካም ሞላ በድጋሚ ተከሰሰች! በአስናቀ ልባዊ

By   /   November 27, 2014  /   Comments Off on ጋዜጠኛ መልካም ሞላ በድጋሚ ተከሰሰች! በአስናቀ ልባዊ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 11 Second

የ‹‹ ቆንጆ ›› መፅሔት ዋና አዘጋጅና የ‹‹ ጃኖ›› መፅሔት ዓምደኛ የነበረችው መልካም ሞላ ሀምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ዜና እወጃ ላይ ‹‹ህገ-መንግሥቱን በኃይል ለመናድ በመንቀሳቀስ፣ ህዝቡን ለዓመፅ ማነሳሳትና የሽብር ስራን ለምስራት ማቀድ ›› በሚል የፍትህ ሚኒስቴር ክስ የመሰረተባት መሆኑን በዜና አቅራቢው ተመስገን በየነ በኩል የተከሰሰች መሆኑን የሰማችና ከዚያም ባሉት ተከታታይ ቀናት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለጥያቄ እንደሚፈልጋት ጥሪ ከደረሳት በኋላ የምትወዳትን ሀገሯን፣ ሙያዋንና ቤተሰቦቿን ትታ ዿግሜ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ከሀገር መሰደዷ ይታወቃል ፡፡
ይሁን እንጂ የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በያዝነው ህዳር ወር 2007 ዓ.ም ከሀገር ከመውጣቷ በፊት በዋና አዘጋጅነት ትሰራበት ለነበረው የ‹‹ቆንጆ›› መፅሔት ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሣን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በማስቀረብ በጥር ወር 2006 ዓ.ም ማለትም ከአንድ ዓመት በፊት ‹‹ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መ/ቤት ምን እየሰራ ነው ? በሚል ርዕስ ሥር በኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማዊነት መስፋፋትን በተመለከተ በፃፈችው ፁሁፍ ‹‹ህዝቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ አድርጋለች ››
በሚል ክስ እንደመሰረተባትና ለጥያቄ እንደሚፈልጋት በመግለፅ ሥራ አሥኪያጁ እንዲያቀርባት ታዟል፡፡
ይሁንና ጋዜጠኛ መልካም ሞላ በሀገር ውስጥ የሌለች በመሆኑ ከዚህ በፊት በሎሚ፣ በጃኖ ፣በአዲስ ጉዳይና በሌሎች የመፅሔት አሳታሚዎች ላይ እንደቀረበው የአሸባሪነት ክስ በቆንጆ መፅሔት አሳታሚ ላይም ይህ የክስ ፋይል እንደሚከፈት የታመነ ሲሆን ለጊዜው ግን ከአንድ ዓመት በፊት በፃፈችው ፁሑፍ ‹‹ ህዝቡን በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ አድርጋለች›› በሚል ክስ የቀረበባት ጋዜጠኛ መልካም ሞላን ካለችበት ቦታ አስሮ እንዲያቀርብ የፌደራል ፖሊስ የከባድ ወንጀል ምርመራ ክፍል የታዘዘ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህንን ሪፖርት ላጠናከረው አስናቀ ልባዊ   ከልብ እናመሰግናለን 

መልካም ሞላ

መልካም ሞላ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on November 27, 2014
  • By:
  • Last Modified: November 27, 2014 @ 4:10 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar