www.maledatimes.com የሰበታ ከንቲባና የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ከሀላፊነታቸው ተነሱ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሰበታ ከንቲባና የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ከሀላፊነታቸው ተነሱ

By   /   March 8, 2014  /   Comments Off on የሰበታ ከንቲባና የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ከሀላፊነታቸው ተነሱ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 1 Second

08 March, 2014  Written by  አለማየሁ አንበሴ

የሰበታ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት አቶ የማነ ይገዙ እና የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ኃይሌ በግምገማ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፊንፊኔ ዙሪያ፣ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ከተማ ከንቲባ በመሆን ያስተዳደሩት አቶ የማነ፤ ከሁለት ሳምንት በፊት በሟቹ በአቶ አለማየሁ አቶምሳ በተመራው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ከመሬት አስተዳደር ጉዳዮች ጋር በተገናኘ በዝምድናና በጎሰኝነት በመስራት ኔትዎርክ ፈጥረዋል በሚል የተገመገሙ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ታውቋል፡፡

የከተማው ከንቲባዎች ቶሎ ቶሎ መቀያየር በክልሉ ያለውን የባለስልጣናት ሙሰኝነት ያሳያል ያሉት  ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የከተማው አስተዳደር ፅ/ቤት ሰራተኛ፤ ከ1ሺ በላይ ግለሰቦች ካርታ ይዘው መሬት ሳይረከቡ መቆየታቸው ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የዛሬ ዓመት ከመሬት ሽያጭ ሙስና ጋር በተያያዘ በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ ተመስርቶባቸው ከአንድ ዓመት ላይ በእስር የቆዩ  የቀድሞ የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ሽመልስ ሀሰኖን ጨምሮ ከአስራ አምስት በላይ የፊንፊኔ ዙሪያ  የአስተዳደር ሠራተኞችና መሃንዲሶች በነፃ መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡

በቅርቡ በተካሄደው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ለዘጠኝ ሰዓታት ያህል የተገመገሙት የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ሃይሌም ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ አቶ መስፍን ለአራት ዓመታት የመሩትን ድርጅት በምትካቸው ወክለው እንዲወጡ በተወሰነው መሰረት በኦሮምያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በአስተዳደር ሃላፊነት ሲሰሩ የቆዩትንና በህግ የማስተርስ ምሩቅ የሆኑትን  አቶ ተመስገን ባይሳን ወክለው እንደወጡ ተጠቁሟል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 8, 2014
  • By:
  • Last Modified: November 28, 2014 @ 4:31 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar