ቀልዶ-አደር ክበበው ገዳና ሜሮን ጌትነት ፤ አበበ ተካ ፤
ይህን ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ በቅርቡ በሁሉም ዌብ – ሳይቶች ላይ ማለት ይቻላል ፣ የወጣ አንድ
የአድናቆት ፅሁፍ ነው ። ጽሁፉ አንዲት ገጣሚትን ለማድነቅ የተፃፈ ነው ። የፅሁፉ ርእስ ሐገሬ ፤ ሕዝቤ “
፤ ክብሬ የሚል ሲሆን በእንግሊዝኛ እንዲህ ተተርጉሟል ፤ ” “My Country, My People, My Honor” :: ይህ
የአድናቆት ፅሁፍ የሚያጠነጥነው ፤ ሚሮን ጌትነት በምትባል ኢትዮጵያዊት ዘመናዊ የፊልም ተዋናይ ችሎታና
በግጥሙ ታክኮ ለሃገሯ ያላት ልዩ ፍቅር ላይ ነው ።
ፅሁፉ ገና ሲጀምር ነው “The poet-artist with an “unconquerable soul?” በማለት ተዋናዩዋን
ማንቆለጳጰስ የሚጀምረው ። ፀሃፊዋና አድናቂዋ ደግሞ በእንግሊዝኛ መፃፍ የሚቀናቸው አል ማርያም
ናቸው ። እናም አል ማርያም ናቸው ከላይ እንደጠቀስኩት በሁሉም ዌብ ሳይቶች ላይ አድናቆታቸውን
የናኙት ። የግል አድናቆታቸውን ትክክል ነው አይደለም የሚል ክርክር ወስጥ አልገባም ። ከዚህ በፊትም
ይህቺው ሜሮን ጌትነት የተባለች ተዋናይ የተሳተፈችበትን ድፍረት የሚል ፊልምን ክሊፕ አይቼ በጣም “ ”
ተደነቅኩባት ብለው አሞካሽተዋት ነበር ። ካለፈው ሙገሳቸው ላይ እንዲህ ሲሉ በመጨረሻ ባወጡት ፅሁፍ
ላይም ቀንጭበው አስቀምጠዋል ፡፤
“… The beautiful young actress Meron Getnet sat stunned and speechless. She is visibly shocked and
confused. She looked around in total disbelief trying to get someone to tell her what she has just heard
is not true… In her seat, Meron clasps her palms in the traditional praying position as if to implore
God’s intervention to save her and her country from such cruel public humiliation. An unidentified
interviewer asks her how she feels. (How does one really feel when one’s heart is yanked out before the
entire world!?) Meron is visibly brokenhearted. But she puts on a calm and brave face. She is
struggling to hide her outrage and fury. She is fighting tears; but she does not breakdown though she is
manifestly broken-hearted…”
እንዲህ ይተረጎማል ።
“…..ውቢቱ ወጣት ተዋናይ ሜሮን ጌትነት ፍዝዝ ብላ በዝምታ ተቀምጣለች ፤ እንደሚታየው ደንግጣለች
ግራ ተጋብታለችም ። የሰማችውን ነገር ማመን ስላቃታት ዙሪያዋን እየቃኘች እውነት አይደለም የሚላት
ሰው ፈለገች…… እንደተቀመጠች ሜሮን የእጆቿን መዳፎች በተለመደው የፀሎት አይነት ገጥማ፤ እግዚአብሄር
እሷንና አገሯን ከህዝባዊ ውርደት እንዲያድናቸው ጣልቃ ገብነቱን እንዲያሳያት ተመኘች ። ያልታወቀ ቃለ
መጠይቅ አድራጊ ምን እንደሚሰማት ጠየቃት ። (አንድ ሰው በመላው አለም ፊት ልቡ ቡጥርቅ ብሎ ሲወጣ
ምን ሊሰማው ይችላል ? ) ሜሮን ልቧ እንደተሰበረ ይታያል ። ሆኖም ግን መረጋጋትና ጀግንነት ይታይባታል
። ብስጭትና ንዴቷን ለመደበቅ ትታገላለች። እንቧዋ ይተናነቃታል ፤ ግን እንባዋ አልወረደም ይሁንና ልቧ የተሰበረ መሆኑ በግልፅ ይታይባታል …….”
የትርጉሙ መጨረሻ ።
አል ማርያም ይህን ከላይ የሰጡትን ሙገሳ ያደረጉት የፊልሙን ቅንጫቢ ብቻ አይተው ነው። ሙሉውን
ገና አላዩትም ከፅሁፍዎ እንደተረዳሁት ። እንዴት ነው በቅንጫቢው ብቻ ይህን ያህል ሙገሳ ያፈሰሱላት ።
በፊልሙ ውስጥስ ከሷ ሌላ ተዋናዮች አልነበሩም ፤ የነሱስ ሚና ምን ነበር ? ብየ ልጠይቅ እገደዳለሁ ፤
መቼም አንድ እጅ ብቻውን አያጨበጭብ ። እንደተመልካችና እንደ ውበቷ አድናቂ ቀደምብየ እንዳልኩት
የተዋናይዋ የግል አድናቂዋ ከሆኑ የግል አመለካከትዎ ነውና ነውር የለበትም ። ፍቅር እንደ አፍቃሪው አይን
ነው እንደሚባለው ፤ አድናቂም እንደዚያው ነው ። አድናቂና አፍቃሪ አለምንና ህይወትን እንደሚያይበት
መነፅርም ይለያያል ።
“ድፍረት የሚለውን ፊልም ወያኔ ” /ኢሕዲጎች እንዳይታይ ከለከሉ ። ይህ ዘረኛ አገዛዝ ይህን አደረገ ያን
አደረገ ሲሉ የተቹት ግን አልገባኝም ። ፊልሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊታይ ከነበረበት ቦታ በፖሊሶች መከልከሉ
እሙን ነው ። የፊልሙ ዳይሬክተር ዘረሰናይ መሃሪ እንደተናገረው በፍርድ ቤት ፊልሙ ክስ አለበት ተብለን
ነው እንዳይታይ የተደረገው ሲል በጊዜው ለገባው ታዳሚ ገልጿል ። ዘረሰናይን ለሚያውቀው ደሞ ከማንም
በላይ ለወያኔው ስርአት የተሻለ ቀረቤታ አለው ። እኔ እዚህ ላይ አል ማርያም ወያኒያዊውን አገዛዝ አይተቹ
አይንቀፉ የሚል ፍላጎት የለኝም ።
“ድፍረት ፊልም ግን በታገደ ጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲታይ ተፈቅዶ እየተየ ነው ። የፊልሙ ይዘትም ”
ከወያኔ ስርአት ጋር ፖለቲካዊም ሆነ ማህበራዊ ተቃርኖ የለውም ። ወያኔ ለምን ሲል ያግደዋል ? የጠለፋ
ጋብቻ ከወያኔያዊው ስርአት በፊትም ነበረ ፤ አሁንም አልፎ አልፎ ይኖራል ብዬ እገምታለሁ ። ይህው
ሰሞኑን የሰማነው በታዳጊዋ በሃና ላላንጎ ላይ የተፈፀመ የደቦ አስገድዶ ድፍረት አንዱ ማሳያ ነው ።
“ ” ድፍረት የሚለው ፊልም በራሱ እንዲያውም አገራችን ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ ረገድ በጎ አስተወኦ አለው
ብዬ አላምንም ። ይህ ራሱን የቻለ ሌላ ርእስ ስለሆነ በሌላ ጊዜ ልመለስበት እችላለሁ ።
አሁን ተመልሰን ወደ ተዋናይቷ ሜሮን ጌትነት እንምጣ ። የተዋናይነት ብቃቷንም ሆነ ገጣሚነቷ ላይ
ዛሬ ልተች አልፈልግም ፤ የራሴ አስተያየት ቢኖረኝም ። አል ማርያም ሆይ የሚያደንቋትን የሜሮንን ግጥም
እንደገና ያዳምጡና ወደራስዎ እንዲመለከቱ በዚህ አጋጣሚ ጋብዤዎታለሁ ።
“….መቼም የአሳ ዝላይ መልሶ ከውሃው ነው እመጣለሁ ዞሬ ፣ ስሜን ቀያይሬ ፣
ያኔ ይቀበለኛል ፤ ፍቅር ያጠግበኛል ህዝቤ ፤ አገሬ ፤ ክብሬ ፤ ”.. ….. ይላል አንዱ የገጣሚዋ ስንኝ ። አቶ
አለማየሁ ገ/ማርያም የሚለው ስምዎን አል ማርያም ካሉት ጋር አይገጥም ይሆን ይህ ስንኝ ።
በተረፈ ሜሮን ጌትነት በወያኔው ቴሌቪዥን ላይ የወያኒው የልማት ፕሮግራም ውድድር አዘጋጅነቷንና
አቅራቢነቷን ነው እኛ የምናውቀው ። “The poet-artist with an “unconquerable soul”? የሚለው
ሙገሳዎ አለቦታው የገባ ነው ብየ እከራከርዎታለሁ ፤ የሜሮን ጌትነት ነፍሷ በወያኔ /ኢሓዲጎች conquer
ከተደረገ ከረመ። እንዲያውም ሰሞኑን አሶሳ ወስጥ እየተደረገ ባለው የወያኔ ብሄር ብሄረሰቦች በአል ላይ
ይመልከቷት፤ የህገ/መንግስቱ አወዳሽና ቀዳሽ አስተዋዋቂ ናት ። ይህ ከልክ ያለፈ ሙገሳዎ፤ ይህን እያወቁ ከሆነ እታዘብዎታለሁ ፤ ካላወቁ ደግሞ ይቅርታ አደርጋለሁ ። ወይም የፅሁፍዎ አቢይ አላማ ሜሮን ጌትነትን
የማስተዋወቅ የ PR ስራ ከሆነ ደግሞ ከጋራ አገራችን ፍቅርና ደህንነትና ጋር አይለውሱብኝ ። ኢትዮጵያንና
ሚሮንን አንድ ላይ ሳይለውሱ ኢትዮጵያን ለቀቅ አድርገው ሜሮንን ጠበቅ ያድርጉ ። እዚህ ላይ
እንዲታውቅልኝ የምፈልገው ነገር አለ ። ሜሮን ከወያኔ /ኢሕአዲግ ጋር ሰራች አልሰራች የራሷ ምርጫ ነው ፤
ስሪ ወይም አትስሪ ብዬ ልጫናት መብቱም ሆነ አቅሙ የለኝም ። አል ማርያም ሆይ ፤ እኔ የምመክረዎ ፤
መስታወት ራሱን አያይምና ዘውር ብለው እንደገና ያሞገሱላትን ግጥም “….ህዝቤ ፤ አገሬ ፤ ክብሬ …”
የሚለውን ከራስዎ ጋር አያይዘው እንዲመለከቱ ነው ። ለዛሬው በሜሮን ጌትነት ላይ በዚሁ አበቃለሁ ።
አስፈላጊ ሆኖ ካገኘሁት ደግሞ በግጥሙም ሆነ በተዋናይነት ብቃቷ ላይ እመለስበታለሁ ። ከዚያው ከሜሮን
ጌትነት የግጥም ንባብ ላይ ለወደፊቱ ፅሁፌ ታግዘኝ ዘንድ አንድ ስንኝ ጥዬ ልለፍ ።
“……እድሜህን ቀርጥፈህ ብትሆን ባለ ዲግሪ ፣ ማስትሬት ዶክትሬት ብትደክም ብትለፋ ፤
እውነቱን ልንገርህ በሃገሬ ሂሳብ ፤ ከውጪ የመጣ የሶስት ወር ኮርስ ነው ሚዛን የሚደፋ ፡ …….”
…………………………………………………….
ውድ አንባቢዬ ሆይ እንግዲህ ይህን አጋጣሚ አግኝቻለሁና አንዳንድ ተዋንያንና ድምፃውያን ላይ በየዌብ –
ሳይቱ ተለጥፈው ካገኘኋቸው ዜናዎችና እኒም ከታዘብኳቸው ውስጥ ጥቂቶቹን ላጋራችሁ ።
ከጥቂት ወራት በፊት ነው አበበ ተካ የሚባል ነዋሪነቱን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገ ድምፃዊ ላይ “አበበ
ተካ ለሴት ሲል አገሩን የከዳ ” በሚል ርእስ አንድ ዜና በተወሰኑ ዌብ-ሳይቶች ላይ ተሰራጭቶ ያየሁት ።
ይህ አበበ ተካ የሚባል ድምፃዊ የምን አገር ዜጋ አግብቶ ነው ሙዚቃ ያስተወችው ? የሚል ጥርጣሬ ነው
በውስጤ ያደረው ። ምክንያቱም በአበበ ተካና በአገሩ መካከል ያለውን ግንኙነት ፤ ( በአድናቂዎቹና በሱ
መካከል እንዳለ ግንኙነት አድርጌ በመገመት ) አበበ ተካም ሆነ ባለቤቱ ትዳራቸውን የሚወዱ ባልና ሚስት
አድርጌ ገምቼም ነበር ። ለሚወዳት ባለቤቱ ሲል አንድ ያለችውን ሙያ ትቶ በፍቅር ተሰብስቦ የሚኖር
ግለሰብ አድርጌ ገምቼውም ነበር ። ህይ ዜና በወጣ በጥቂት ወራት ውስጥ አበበ ተካን ባለቤቱ አስገድዶ
ደፈረኝ ብላ ከሰሰችው የሚል ሌላ ዜና ደግሞ በነዚሁ ዌብ -ሳይቶች ላይ ብቅ አለ ። ምንድነው ነገሩ ! ያቺ
ስሙ የጠፋላት ሚስቱ ነች ወይስ ስለሌላ አበበ ተካነው የምሰማው እያልኩ ሳስብ ፡ የአስገድዶ ደፈረኝ ክስ
ተነስቶለት ልጆቹን የማየት እድል እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቀ ተባለ ። ከፍርድ ቤት ሲወጣ ፤ በዩ -ቲዩብ
ላይ አጥር ያለች ቃለ መጠይቅ ቢጤ ሰጥቶ ስለነበር ያችኑ ሳዳምጥ አበበ ከባለቤቱ ጋር የነበረው
አለመግባባት ስር የሰደደ እንደነበር በግልፅ ይታይ ነበር ፤ የወራት ሳይሆን አመታት የተቆጠሩበት
አለመግባባትም ነበር ። ስለዚህ ከወራት በፊት አገሩን የከዳ ሲል የተጻፈው ዜና ከንቱና ባዶ ፈጠራ ሆኖ
አገኘሁት ። እንግዲህ ጉዳዩ የቤተስብ ቢሆንም አንዴ አደባባይ ወጥቷል ፤ በዚህ ላይ አበበ Public Figure
ታዋቂ ግለ-ሰብ ስለሆነ ነው እንጂ ብዙ አበሻ እሱን ከገጠመው በባሰ ሁኔታ ትዳሩ ተፈቷል ፤ መፋታት አዲስ
አይደለም ለማለት ነው ። ይህንና ግን ባለቤቱ እንዲህ አደረገችው እንዲህ በደለችው እየተባለ ነው ወሬው የሚናፈሰው ።ስለዚህ የአንድ ወገን የአበበ ተካን ብሶት ብቻ ከመስማት የባለቤቱን ብሶትም መጠየቅ ተገቢ
ነው። አለዚያ ለፍርድ አይመችም ።
……………………………………..
ሌላው ትዝብቴ ደግሞ ቀልዶ -አደሩን ክበበው ገዳን ይመለከታል ። ክበበው ገዳ ከኢትዮጵያ ቀልዶ –
አደሮች ውስጥ ቁንጮ ነው ብየ ብናገር ማጋነን አይሆንም ። የቀልድ ስራዎቹ ላይ እንደማንኛው ሰው
ችግሮች ሊታዩበት ይችላሉ ።
ተመልካችም በቀልደኛው ንግግር እየሳቀ ሲሰደብ እንኳን መሰደቡ አይገባውም ። ወይም እየገባው ያው
የአበሻ ባህሪይ ሆኖበት ዝም ብሎ ያልፈዋል ። የአበሻ ባህሪይ ያልኩት አንድ የምናደንቀው ሰው ላይ ዛሬ
የምናየውን ስህተት በይሉኝታ ፤ ወይም ይቅርታ እንድናደርግ ሳንጠየቅ በይቅርታ ፤ እናሳልፈውና ነገ በላያችን
ላይ ሲጨፍርብን ፀጉራችንን መነጨት መጀመራችንን ነው ።
ዛሬ በሰለጠነው ዘመን ማንኛውም ሙያ በትምህርት ሲደገፍ ጥቀሜታ አለው ። ሁሉም የቁም ቀልዶ –
አደር Stand-Up Comedian በአሜሪካም ቢሆን እንኳ ፤ የመድረክ ላይ ትምህርት አለው ማለት አይደለም ፤
ሆኖም ግን በሙያው የሰለጠኑ ባለሙያዎች ያማክሩታል ፤ ቀልዶቹን ይመርጡለታል ፡ቃላቱን ይቀርፁለተል
፤ መድረኩን ይመሩለታል ፤ ሰአቱን ያቅቡለታል ። በኛ ሃገር ግን ከፈረንጆቹ በተለይ ከአሜሪካ ሁሉንም ነገር
እየኮረጅን መሟላት ከሚገባቸው ሁነታዎች አንዱን እንኳ ሳናሟላ የምንገባበት ሙያ ላይ ብዙ ስህተቶች
ሲፈጠሩ እንመለከታለን ። ከነዚህ ሙያዎች ውስጥ የቁም -ቀልድ Stand-up comedy ሙያ አንዱ ነው ።
ሌላ ሌላውን እንተወውና ከአስኮራጃችን አሜሪካን ሃገር አንድ የቁም ቀልዶ -አደር ፤ ቢያንስ
ፕሮግራሙን የሚመራለት ዳይሬክተር ብሎም አማካሪ ይፈልጋል ። እንደፈለገና አፉ እንዳመጣለት ያሻውን
አይዘላብድም ። በተለይ ለተመልካቹ ያለው ክብር ከፍተኛ ነው ። ምክንያቱም ኑሮው የተመሰረተው
እንጀራው የሚጋገረው በተመልካቹ ላይ ነውና ። ኒውዮርክ ሾው ላይ የነበረውን ተመልካቹን አትላንታ ሄዶ
አይቀልድበትም ። በሌሎቹ የአውሮፓ አገሮችም እንደዚሁ ነው ።
ቀልዶ-አደር ክበበው ገዳ የታዳሚውን የልብ ትርታ ማዳመጥና አድናቂዎቹ መኖሪያቸው ኢትዮጵያም
ይሁን አሜሪካ ፤ ካናዳም ይሁን ቻይና ማክበር ይገባዋል ። እንደ አለቅላቂ ሴት አንዱ አገር ሲሄድ ቀደም
ብሎ የሄደበትን ከተማ ማንቋሸሽ ወይም መዝለፍ አይገባውም ። ይህን እንድል ያነሳሳኝ ክበበው ገዳ
ከተወሰኑ አመታት በፊት ወደ ኮሎምበስ ኦሃዮ ብቅ ብሎ ነበር ። ከተመልካቹ መሃል ቀልዱ ያላስደሰተው
አንድ ግለ-ሰብ ጋርም መጣላቱን ሰምቻለሁ ። ከዚያ ወደዋሽንግቶን ዲሲ ሲመለስ መድረክ ላይ ወጥቶ “
ኢትዮጵያ እያለሁ አገሬ መራቧን እሰማ ነበር ። አሁን ግን ኦሃዮ ደርሼ ከመጣሁ በኋላ አገሬ ለምን
እንደተራበች ገባኝ ፤ ለካ ገበሬው ሁሉ ተሰብስቦ ኦሃዮ ገብቶ ነው ሲል ቀለደ ። ዋሺንግቶን ዲሲም ኦሃዮ ”
በብዛት የወልቃይት ፀገዴ ተወላጆች እንደሚኖሩበት በማውቅ ለቀልዶ -አደሩ ክበበው ገዳ ሳቀለት አስካካለት ።
የአንተን የቀልዶ-አደሩን ሆድ ለመሙላት ውልቃይት ፀገዴ ማረስ ነበረበት ? ቀልዶ-አደሩ ወንድሜ አገራችን
ረሃብተኛ መባሏን ከሰማህና ገበሬው ሁሉ ኦሃዮ መመጣቱን ከተገነዘብክ ለምን ራስህ ገብተህ አታርስም ነበር ። በዚህ አጋጣሚ አገር የምትለማው በአርሶ አደሮች እንጂ በቀልዶ አደሮች እንዳልሆነ ልገልፅልህ እወዳለሁ ።
ታዲያ ይህን አባባልህን ሳትወቀስበት በዋሽንግተን ተስቆልህ አለፍክ ።
ውድ አንባቢዬ ፤ አሁን በቅርቡ ደግሞ ይባስ ብሎ አውሮፓ አንድ የፋሽን ትርኢት ላይ እንደሟሟያ ሆኖ
ቀርቦ ነበር ክበበው ገዳ ። የአዲስ አበባ ጆክ ነው ብሎ አንድ ቀልድ አወራ ። ጎስቋላዎቹና ማዲያታሞቹ “
ሴቶች ሁሉ አሜሪካና ካናዳ ነው ያሉት ሲል ቀለደ ። ጆኩ እንደጆክ ተወርቶ በዚያ ቢያበቃ መልካም ነበር ”
። ለነገሩ እውነት ነው እኔ ዘወር ዘውር ብየ አይቻለሁ “ ” ማንከሽከሻ ብቻ ናቸው ሲል አሾፈ ። ይህን
አባባሉን ለመመልከት የሚቀጥለውን ሊንክ ይመልከቱ https://www.youtube.com/watch?v=t0-qU60ik3E
።ወይም ክበበው ገዳ ብለው ጉግል ያድርጉና ቆንጆዋን እንካ ግን አትንካ የሚለውን ርዕስ ይጫኑ ። “ ”
ቀደም ብየ እንዳልኩት እንደ አለቅላቂ የመንደር ሴት የኦሃዮን ዲሲ የአሜሪካና ካናዳን አውሮፓ እየወሰደ
ያለቀልቃል ። ቀልዶ አደሩ ወንድሜ ክበበው ! እነዚህ ማንከሽከሻ ፤ ጎስቋላ፤ ያልካቸው የአሜሪካና የካናዳ
ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ሚስቶቻችንና እናቶቻችን ናቸው ። አዎ ማዲያታም ሊሆኑን ይችላሉ
ሊጎሳቆሉም ይችላሉ ። አንተ ኢትዮጵያ ወስጥ ያውም አዲስ አበባ ብቻ እንደምታውቃቸው ፤ ምሽት -አደር
ሴቶች ላይቆነጁ ይችላሉ ። ሰርተው ጥረው ግረው በላባቸው በወዛቸው የሚያድሩ ናቸውና ። በዚህ በፈጣኑ
አለም ውስጥ ልጆች አሳድገው አስተምረው ትዳራቸውን ጠብቀው ከዚያም አልፈው ኢትዮጵያ ወስጥ ቤተ –
ሰብና ዘመድ ረድተው የሚኖሩ ሴቶች ናቸው ፤ ቢጎሳቆሉ ይነሳቸው ፤ ማዲያት ቢወጣባቸው ይብዛባቸው ።
የአንተ የአዲስ አበባ ቆነጃጅት ሴቶች ለፀጉራቸው ሶስት ሰአት ፤ ለጥፍራቸው ሁለት ሰአት
ለቅንድባቸው ሌላ ሁለት ሰአት ለማጥፋት በቂ ጊዜ ያላቸው ናቸው ፤ ምነው አይቆነጁ ። ስለዚህ
ስትቀልድም የምትናገረውን እወቅ ። በአንድ አካባቢ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ስትቀልድም እዚያው እፊታቸው
ላይ ቀልድ ። አንዱን ካንዱ አታምታታ ። አንድ እውነታ ግን ልንገርህ ። ኦሃዮም ካናዳም ሆነ አሜሪካ አንተ
መጣህባቸው እንጂ እነሱ አንተን ብለው አልመጡብህም ። ኦሃዮም ካናዳም አሜሪካም ያላንተ ኖረዋል
መኖርም ይችላሉ ። አስር አመት ቀልደህ ከአዲስ አበባ ቆነጃጅት ሴቶች የማታገኘውን ገንዘብም በአንድ
ትርኢት የምታገኘው ከነዚህ ማንከሽከሻዎች ፤ ማዲያታሞችና ባሎቻቸው ነው ። ዘወር ዘወር ብየ አለምን
አይቻለሁ ብለሀናልና እግርህ ተፍታቶ ክንፍ አውጥተህ ዘወር ዘወር ያልከው ከነዚሁ ከማዲታሞቹ በተገኘ
ገንዘብ እንደሆነ ልትረዳው ይገባል ። ይህ እውነት አይደለም እንዴ ወንድሜ ? መቼም ቀልደኛ ነህና ፤
አይደለም ከአባቴ በወረስኩት ገንዘብ ነው ብለህ እንዳታስቀኝ ።
ውድ አንባቢየ ለዛሬው በዚሁ ላብቃ !
ከአንበሳው ይብራ
እ.ኤ.አ ዲሴምበር 2 2014
Average Rating