ባለገሩ አይድል በኢትዮጵያ ውስጥ ከተጀምረ ጥቂት አመታትን ማስቆጠሩ ይታወቃል ሆኖም ግን ብዙ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ይዞ መጓዙ ብዙዎቹ ሃሳባቸውንም እንዳይሰነዝሩ የሚያደርጋቸው አንድ ነገር ያለ ይመስለኛል ፣ይሄውም የአብርሃም ወልዴ ከሰው ጋር የመግባባት እና የመልካም ስነ ምግባር ባለቤትነቱ ካለው የሙያ ፍላጎት ጋር ተዳምሮ ማንም ሰው ደፍሮ ይሄን አደረጋችሁ የሚላቸው ሰው መጥፋቱ ስህተታቸውን ለማረም ሊረዳቸው አልቻለም ። በሌላም በኩል ለኛ ያጣነው ነገር እና ሌሎች ያላቸው የሙያዊ አመለካከት ምን ይሆን ብለውም የሌሎችን የውጭ አገር አይድል ሾዎችን ለማየት አለመሞከራቸው ባሉበት እንዲረግጡ አድርጓቸዋል ።
ለምሳሌ ያህል እንጥቀስ ከተባለ ልንጠቅሳቸው የምንችላቸው ብዙ ነገሮች አሉ ለምሳሌ ሱልጣን ኑሪ (ሶፊ) እና አረጋሃኝ ወራሽ የሚሰጧቸው ሙያዊ አስተያየቶች ሙያዊ ክህሎትን እና በቂ እውቀትን ያዳበሩ ሳይሆን በጊዜው የተሰማቸውን ስሜቶች ብቻ የሚያጠነጥን ስሜት ስለሆነ በተመሳሳይ ጊዜያት ተመሳሳይ የሆነ አስተያየት ሲሰጡ ይስተዋላሉ ያ ደግሞ የራሳቸውን ደካማ የሆነ የሙዚቃ እውቀታቸውን በግልጽ የሚያንጸባርቅ መሆኑን ያሳያል ታዲያ እንዲህ አይነቱን የሙያ አጋር በዳኝነት ማስቀመጡ ግን ድርጅቱ ለቆመለት አላማ በቂ የሆነ አሰራር እና አላማ አለመኖሩን የሚጠቁም ሲሆን በአቋራጭ ከተለያዩ ማስታወቂያዎች የሚገኙትን ገንዘብ ሰብስቦ በዋዛ ፈዛዛ ጊዜውን ለማሳለፍ የሚከናወን ጥረት እንደሆነ ያስረዳል ።
ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ባላገሩ አይድል ማድረግ የሚገባው ጥረት ቢኖር በመጀመሪያ ደረጃ ዳኞችን በየ፮ወሩ የመቀየርረና በሙያቸው አንቱ የተባሉ እና በስራቸው ትልቅ ጥበብ ያላቸውን ባለሙያዎችን እድሉን መስጠት ና የሙያቸውን ልምድደ እዲያካፍሉ ማድረግ አለበት ። በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ተወዳዳሪዎች በሙሉ በሚያደርጉት ውድድር ከማንኛውም ነገር በላይ ሊደነቁ የሚገባ ሲሆን ባላቸው ሙያ ላይ ወደ ውድድር ከመግባታቸው በፊት የባላገሩ አይድል የሚወዳደሩበትን የሙዚቃ ቅንብር ካራኦኬ አዘጋጅቶ ማቅረብ ግዴታው መሆን አለበት ይህንን ካላደረገ ግን የሙያዊ ብቃት ያላቸውን ሰዎች የመፍጠር ሆነ የማሳደግ ስራ ሳይሆን የገንዘብ ትኩረት እንዳለው የሚያሳይበት አቋራጭ መንገድ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል ።
በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ በሌሎችም አለማት በጣም ተደናቂነትን የሚያተርፉት የአይድል ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩበትን ሙዚቃ ስራ አስመስለውም ሆነ የመድረክ ስራቸውን በጥራት ጠብቀው ማስኬድ ሲችሉ እና በተለያዩ ካራኦኬዎች ተለማምደው ስራቸውን ለህዝብ ማቅረብ ሲችሉ ብቻ ነው ። ከዚያ ውጭ ግን ከልጅነታቸው ጀምሮ የሙዚቃን ስራ እንደ አንድ የፍላጎት ዓካል አድርገው በፍላጎታቸው መሰረት ቅኝቶችን በማጥናት ለራሳቸው የሚስማማ መንገድ በመሄድ ወደ ስኬት ጎዳና እንዲያቀኑ ያደርጋቸዋል።
በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ አንድም ቀን የሙዚቃ ካራኦኬ ሳይሰራ ፍላጎቱ ያለው ሰው ዘፈናቸውን ብቻ በማድመጥ እና ግጥማቸውን ጽፎ ከሙዚቃው እያጫወተ ከሙዚቃው ጋር አብሮ በመዝፈን የሚያሳድገው ፍላጎት እንጂ እንደ ሌሎቹ ከሙዚቃው ጋር አብሮ አድጎ የሙዚቃውን ቅኝት ሂደት አጥንቶ በልምምድ ድምጹን ገርቶ የገባ ማንኛውም ተወዳዳሪ እንደሌለ ያውቁታል ።ግን ያላዋቂ ሳሚ አይነት ሆኖ የሚሰጧቸው መልሶች ግን ሙያዊ እውቀትን ያማከለ ሳይሆን ስሜታዊ ሂደትን የተከተለ መሆኑ የበለጠ፡ህብረተሰብን ያበሳጫል ።
በትክክል አስመስለው የዘፈኑ የአይድል ተወዳዳሪዎችን ለምን ዘፈናችሁ ተብለው አስተያየት ሲሰጣቸው እንዴት ያሳፍራል? በተለያዩ አለማት ትልቁ ሙገሳ እና ክብር የሚሰጣቸው የባለቤቱን ስራ እንደባለቤቱ አድርገው መስራታቸውን ሲታወቅ እና የስራቸውን ልፋት በግልጽ ማሳየት ሲችሉ ነው ፣ታዲያ የኛገር ተወዳዳሪዎቹ አስልጣኝም ተሰልጣኝ ባልተገኘበት ውድድር ላይ እንዲህ አይነቱ ነገር ሲፈጸም ማየቱ ዝምታን ከማጫሩ ይልቅ ለመናገር አንደበትን እንዲከፈትና ትክክልኛ ያልሆነ ስራቸውን መናገር እንዳለብን ያሻል ። ታዲያ እንዲህ ያለ አስተያየት ሲሰጥ ደግሞ ሰርተህ ብታሳይ የሚሉ አስተያየቶችን ሊደመጡ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም እውነት ገንዘብ ከተገኘ እንደ ኢትዮጵያን አይድል አንድም ሳይሆን አስር አድሎችን በእነ ሶፊ አይነት ዳኞች መምራት ቀላል መሆኑን መግለጽ ያሻል ።በእርግጥ ነው አማራጭ የሌለው የኢትዮጵያ ህዝብ አይድልን እንደመዝናኛ ስለሚያየው ለምን ነካህብን ሊል ይችል ይሆናል አይኑ ሊያለቅስ ይችላል ግን የተሻለ አይድል የሚመጣው ቁንጽል የማይባሉ ግዙፍ ስህተቶችን ያለ እውቀት ከሚጓዝ አይድል ባዶ መሆን ይሻላልና ቢስተካከል አማራጭ ለመስጠት ወይንም የተሻለ ሌላ አይድል መጥቶ ብቃት ያላቸውን ሰዎች በብቃታዊ ሙያ በመታገዝ ስራዎችን መስራት እንዲችል መደረግ አለበት ብለን ስለምናምን ይሆናል ። በእርግጥ በቅርበት ያሉትን የነደቡብ አፍሪካን አይድል ብቻ ማየት በቂ ሊሆንላቸው እና ለወደፊት እድሉን ሊከፍትላቸው የሚችሉት መንገዶች በመከተል ጠቃሚሜና ብቃት ያላቸውን ሙዚቀኞችን ማፍራት እንደሚቻል መዘንጋት የለብንም ።
ይህንን ስንል የተጀመረው ጅማሮ ሙሉ በሙሉ ጥሩ አይደለም ማለታችን ሳይሆን ብቃት ያላቸው የዳኝነትን ሙያ የተካኑ እና የአስተሳሰብ ብስለታቸው በሙዚቃው ደረጃ ያደጉ ሳይሆኑ በለብለብ ስሜታቸው ወጥተው የሚናገሩ ስለሆኑ እነዚህን ሰዎችቻስወግዶ ሌሎች በትምህርቱ እና ብችሎታቸው አንቱ የተባሉ ብዙ ምሁራኖች አሉንነና ቦታውን ለእነርሱ ብናወርሳቸው ከእነርሱ የምናገኘው ልምድ ብቻ በቂ መሆኑን ልናስገነዝብ እንወዳለን ።
Average Rating