በሰላማዊ ሰልፉ ዝግጅት ወቅት ከሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ አካባቢ በደህንነት የታፈኑ የሰማያዊና የመኢአድ አባላት እንዲሁም ሌሎች ግለሰቦች በሽብርተኝነት ተከሰሱ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ፍቅረ ማሪያም አስማማውና አወቀ ተዘራ፣ የመኢአድ
አባል የሆኑት ተስፋሁን አለምነህና ሺፈራው ዋለ እንዲሁም ሌሎች አራት ግለሰቦች ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ በመገኘታቸው ብቻ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ ለቀናት የታሰሩበት ሳይታወቅ ቆይቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት ታሳሪዎቹ ኮተቤ ፖሊስ መምሪያ እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹ሽብር በመቀስቀስና ሁከት በመፍጠር›› ወንጀል ተከሰው ተጨማሪ 10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንደተቀጠረባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ ዝግጅት
ወቅት ታፍነው አሁንም ድረስ የት እንደደረሱ ያልታወቁ የ9ኙ ፓርቲዎች በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ ሰላማዊ ሊጀመር ከመጀመሩ በፊት ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ የታፈነችው ወንይሸት ንጉሴ ቤላ 18 ፖሊስ ጣቢያ ታስራ እንደምትገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ በምርመራ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ
(ሶስተኛ) የሚገኙት ታሳሪዎች የፌስቡክና የኢሜል መክፈቻ ቁልፎቻቸውን እንዲሰጡ በግዳጅ እየተጠየቁ እንደሆነ ገልጸዋል፡ከታሳሪዎቹ መካከል የሜሮን አለማየሁን ጨምሮ የሌሎች ታሳሪዎች ፌስ ቡክ ኦን ላይን መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating