በሰሜን አሜሪካ የሚደረገው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ነግር ክውስ ጭዋታ በዲሲ እንደሚደረግ ደረሰን መረጃ ያመለክታል ። ከሁለት አመታት በፊት በሜሪላንድ መደረጉ የሚታወስ አሁንም በድጋሚ በዚያው ስታዲየም እንደሚከናወን እና ለፌደሬሽኑ የቅርብ ወዳጅ ለሆነው የአንድ ምግብ ቤት ባለቤትን ለመርዳት ይረዳ ዘንድ የሆቴሎች አገልግሎት የሚሰጡትም የፌደሬሽኑ ፕረዚዳንት በመረጠው ቦታ ብቻ እንዲወሰን መደረጉ ሁሉንም አስደንግⶏአል ። በፌደሬሽኑ የቦርድ አባላት ጋር በመዋቀር ይወሰናል የተባለው ይሄው ጉዳይ ያለማንም ማን አለብኝነት ምርጫውን በእራሱ ስልጣን ሊወስን እንደ ቻለ ታውቇል ። ከዚህ በፊት በነበረው የፌዴሬሽኑ ጨዋታም ላይ ፕረዚዳንቱ ቤተሰቦቹን በማሰማራትታጠቃላይ የገቢ ምንጩንነንዲቆጣጠሩ ማድረጉንነና ከፍተኛውን ገቢ ለግል ጥቅማቸው እንዲደረግ አሰራራቸውን በግላቸው መለወጣቸውን የማለዳ ታይምስ ሪፖርት መዘገቡ ይታወሳል ። በፌደሬሽኑ ይከናወን የነበረውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በመቃወም ወደ ስልጣን የመጣው ይሄው የፌዴረሽኑ ፕረዚዳንት ወደ ስልጣኑ ጎራ ከተቀላቀለ በሁዋላ ግንገራሱ አንባገነናዊ ስርአትን ይዞ የሚንቀሳቀስ አንጃ እንደሆነ ለማወቅ ተችⶀአል ።
በቨርጂኒያ እንዲደረግ የተወሰነውን ይሄንን ጉዳይ የፌዴሬሽኑ ፕረዚዳንት አቶ ጌታቸው የሆቴል አገልግሎቱን ስታዲየም እና የምግቤቶቹን ፋሲሊቲ በሜሪ ላንድ እንዲሆን የወሰነ ሲሆን ፤እንደ ፌደሬሽኑ አሰራ ከሆነ ደግሞ አዘጋጁ ስቴት በሚፈልገው ቦታ ማድረግ እንደሚችል የሚገልጽም አቋም እንዳላቸው ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሌላም በኩል እንዲህ አይነቱ አሰራር በግንቦት ሰባት አባላት እና በኢሳት ቴሌቪዥን ውስጥ መከናወኑ የሚታወቅ ሲሆን የስፖርት ፌደሬሽኑም ሆነ የቴሌቪዥን ጣቢያው ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የጸዳ መሆን ሲገባው በግለሰቦች የመመራትን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው የገዚውም ፓርቲ የሆነው የወያኔ አምባገነናዊ ስርአት ድርጅቶቹን ለመተቸት ረድቶታል ።እንደ ኢሳት የግል መገናኛ የተሰኙት ድርጅቶችም በተወሰኑ ሰዎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው እና የፈለጋቸውን ሰዎች ብቻ በማቅረብ ነጻ መገናኛ መንገድ ነን ብለው ማሰባቸው ተገቢ አለመሆኑን እያወቁት ከግንቦት ሰባት ጎን ተሰልፈው መሄዳቸው ተገቢ አለመሆኑን ከመጠቆም ወደ ኋላ አንቦዝንም ። እንደምሳሌም ለመጥቀስ ከዚህ በፊት በጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ላይ የተከናወኑ ድርብርብ ጉዳዩችን ማንሳት ተገቢ ቢሆንም እንደ አብነት በቴሌቪዥኑ ስቱዲዮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ የግንቦት ሰባትን ደካማ ጎን ለምን ገለጽክ በሚል ሰበብ ከዛሬ ድረስ እንዳይተላለፍ የታገደ ቃለ መጠይቅ ምክንያታዊ ሳይሆኑ የቀሩ ሲሆን በራሳቸውን ስቱዲዮ ጋብዘው እንደ ገና ለህዝብ አይቀርብም ብለው ውሳኔ ማሳለፍ የቆሙለትን አላማ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን በዚህም ጉዳይ ተያያዥነት የጋዜጠኛ ደረጀ ደስታም ክድርጅቱ የመልቀቅ ዋነኛ ጉዳይ ከዚሁ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ነጻ እና ገለልተኛ ሚዲያን ከመፈለግ አንጻር ፣በፍላጎቱ መልቀቁን የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ ።
ነጻ ሚዲያን እና ነጻ የስፖርት ፌደሬሽንን የማቋቋምመና በስራው ጉዳይ ላይ ትኩረት የሚሰጠው ህዝብ መሆን ሲገባው የፓርቲዎች አመራሮች ላይ በመጣሉ ለግል እና ለፖለቲካዊ ጥቅማቸው በሚያገለግል መልኩ እንደፈለጉ ማሽከርከር የሚፈልጉት ለማሽከርከር ይረዳቸው ዘንድ መጠቀሚያ ሲያደርጉ ይታያሉ ።ይህም ግንቦት ፯ ከኢሳት ጋር የሚያደርገውም ጉዞ ሆነ ወያኔ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር አግባብ የሌለው መጠቀሚያ ቢሆንም ጋዜጠኞች ግን ለህሊናቸው ሲሉ እና ሙያዊ ስነ ምግባር ይዘው በመንቀሳቀስ መጓዝ ይገባቸዋል ስንል እጠቁማለን። የፌደሬሽኑም አመራር ከዚህ ጊዜ በሁዋላ አገልግሎት ሊሰጥጠንደማይገባው እና በየ ሁለት አመቱ መደረግ የሚገባው የፕረዚዳንታዊ ምርጫ ተግባራዊ ሆኖ መከናወን ያለበት ሲሆን ለሁለት አመታት ያገለገለ አንድ ግለሰብ በድጋሚ ሊመረጥ የማይችልበት ህግም ማቅረብ ይገባቸዋል ፠አቶ ጌታቸውም ቢሆን የወያኔ መንግስትን ተቃውሞ በማሰማት የምታደርገውን እንቅስቃሴ ዛሬ አንተ በምትመራው ፌዴሬሽን ስር ዲሞክራሲያዊ መንገድን ማስተላለፍ ስትችል ብቻ ሌላውን ብትቃወም ተቀባይነት ልታገኝ ትችላለህ ነገር ግንናንተው ዲክታተር ሆነህ ሌሎችን ዲክታተር ብትል የሚሰማህ የለምመና ቀድመህ ከዚህ ከመጭው የእግር ኳስ ጨዋታ ዝግጅት በፊት መንበርህን ለተተኪዎችህ ብታስረክብ መልካም ነው ።የሰሜን አሜሪካም ስፖርት ፌደሬሽን የህዝብ እንጂ የግለሰብ እንዳልሆነ ልትረዳው ይገባል የሚለው መልእⷍታችን ነው ።
Average Rating