በሰሜን ሸዋ በሐገረማርያም ተወልዳ ያደገችው ጠጅ ነሽ የወግ ነህ ለቤተሰቦቿ 5ተኛ ልጅ ስትሆን ከሷ በታች 4 ወንድሞችና እህቶች አሏት፡፡ የ15 አመቷ ጠጅነሽ የ7ተኛ ክፍል ተማሪ እና በቤት ውስጥ ስራም ቤተሰቧን በታታሪነት በመርዳት የቤቱ ዓይን የተባለች ናት፡፡ ጥቅምት 16 ቀን ጠዋት ገበያ ወስዳ የምትሸጠውን በአህያ ጭና ከቤት ትወጣለች፡፡
የምትሸጠውን ሸጣ የገዛቸውን በአህያዋ ጭና ወደቤቷ ስትመለስ መንገድ ላይ 3 ወንዶች ድንገት ይይዟታል ጠጅነሽ ባለ በሌለ ሐይልዋ ብትጮህ ና ብትንፈራገጥም ጠላፊዎቿ አፏን በልብሳቸው አፍነው ለሶስት እግርና እጇን ጠፍረው ወደ ቤታቸው ይወስዷታል
የጠጅነሽ ወላጆች የልጃችውን መዘግየት አሳስቧቸው መምጣቷን ሲጠባበቁ የማታ ማታ አህያዋ ብቻዋን ወደ ቤት ትመለሳለች፡፡
ልጃቸው መንገድ እንደቀረች የተረዱት ቤተሰቦቿ በጨለማ ወጥተው በገደል በተራራው በፍለጋ ሲባዝኑ ቆይተው ሳይሳካለቸው ይመለሳሉ፡፡
ጠጅነሽ ተጠልፋ የተወሰደችበት ቤት ውስጥ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ በዓይኗ ሳይዞር ስትጮህ እና የማምለጥ ሙከራ ለማምለጥ ስታደርግ ታነጋለች ጠላፊዎቿ ወዳ ፈቅዳ ቤታቸው እንደገባች የሚያሳይ ውል አዘጋጅተው እንድትፈርም ያቀርቡላታል ጠጅነሽ አልፈርምም በማለት ትቃወማለች አስገድደው ሊያስፈርሟት ቢሞክሩም አሻፈረኝ በማለቷ ወደ ትልቅ የገደል አፋፍ በመውሰድ ሲያስፈራሯት የሰዎች ድምጽ ስለሰሙ የጠጅነሽ ቤተሰቦች ፖሊሶች ይዘውባቸው የመጡ ስለመሰላቸው ከገደሉ ጫፍ ወደ ገደሉ ወርውረዋት ከአካባቢው ይሰወራሉ፡፡
ጠጅነሽ በዛ በአስፈሪ ገደል ውስጥ ባገጠጡ ድንጋዮች እየተገጫጨች በአሰቃቂ ሁኔታ ወደ ታች ስትምዘገዘግ ገደሉ ላይ የበቀለች ዛፍ ቀሚሷን ይዛ ተፈጥፍጣ ከመሞት ታድናታለች
መንገደኞች የጠጅነሽን የድረሱልኝ ጩኸት ሰምተው በመድረስ ከአካባቢው ሰው ጋር በመተባበር ከገደል ያወጧታል
በልጃቸው መጥፋት ግራ ተጋብተው በፍለጋ ሲማስኑ የነበሩት የጠጅነሽ ቤተሰቦች ከጠዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ስልክ ተደውሎ የልጃቸው ዜና ይደርሳቸዋል
የጠጅነሽ ቤተሰቦች ገስግሰው ሲደርሱ ልጃቸው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት በቃሬዛ ላይ ተኝታ በስቃይ ስትቃትት ይመለከታሉ….
በአስቸኳይ ወደ ሐገረማሪያም ሆስፒታል ያደርሷታል ከሐገረማሪያም ለተሻለ ሕክምና ወደ ደብረብርሐን ይልካቸዋል ደብረብርሐንም ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይልካቸዋል ከከተማ ከተማ ከሆስፒታል ሆስፒታል ሲንከራተቱ የዋሉት እነ ጠጅነሽ ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይደርሳሉ ፡፡
ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ለጠጅነሽ የድንገተኛ አደጋ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ሌሊቱን አሳልፋ በማግስቱ ጠዋት የሚያስፈልጋት ሕክምና እዛ ውስጥ ማግኘት እንደማትችል ተገልጾላቸው ከሆስፒታሉ ይሰናበታሉ የጠጅነሽ ወላጆች ባላቸው አቅም በግል ሆስፒታልም ሕክምና እንድታገኝ ቢሞክሩም በአከርካሪ አጥንቷ ላይ የደረሰው ጉዳት የከፋ ስለሆነ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ሕክምና ማግኘት እንደሚያስፈልጋት ከሆስፒታሉ ተነግሯቸዋል፡፡
ጠጅነሽ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ከተማ ኦሎምፒያ አካባቢ የሚኖሩ አክስቷ ቤት ተጠግታ ከወገብ በታች መንቀሳቀስ ተስኗት በከፍተኛ ስቃይ ላይ ትገኛለች፡፡
ይቺ ታዳጊ ወጣት ህልምዋና እና ሕይወቷ እንዳይቀጭ የእኛ እርዳታ ያስፈልጋታል እርዳታችሁን በባንክ በመላክ ወይም በ0910805732 / 0938934282 በመደወል ጠጅነሽ እና ቤተሰቦቿ ያሉበት ድረስ በመሄድ በአካል ልታደርሱላቸው ትችላችሁ፡፡
0132001059100, Awash bank / olompiya branch , Belayneh teklewold For Tejnesh lewogeneh
ፍትሕ ለሃና እና በአስገድዶ መድፈር በጠለፋ እና በጥቃት ህልማቸው እና ሕይወታቸው ለተቀጨባቸው ሁሉ!
ጠጅ ነሽ የወግ ነህ !
Read Time:1 Minute, 55 Second
- Published: 10 years ago on December 9, 2014
- By: maleda times
- Last Modified: December 9, 2014 @ 2:21 pm
- Filed Under: Ethiopia
Average Rating