www.maledatimes.com ሰማያዊ-ዎች አልታሰሩም ✿ መልካም ሰላም ሞላ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰማያዊ-ዎች አልታሰሩም ✿ መልካም ሰላም ሞላ

By   /   December 9, 2014  /   Comments Off on ሰማያዊ-ዎች አልታሰሩም ✿ መልካም ሰላም ሞላ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 0 Second

አብዛኛዎቹን የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር እና አባላት በስራ አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ከስራ ውጭ በቅርበት አውቃቸዋለሁ ፡፡ በፖለቲካ አመለካከት የሚመስላቸውን ብቻ ሳይሆን የሚለያቸውን ለማሳመን ከመሞከር ወደ ሁዋላ አይሉም፡፡ በውጭ ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ የሃሳብ አለመስማማት ቢያጋጥማቸው ፀሃይ ሳይመታው ለመፍታት የሚጥሩ በሳል ሰዎች በዙሪያቸው ተከበዋል ፡፡ ሁሉም ጋር ተመሳሳይ ስሜት እልህ እና ወኔ ፡አትንኩኝ ባይነታቸው ጎልቶ የሚወጣው በአንድ ጉዳይ ሲመጣባቸው ብቻ ነው✿✿ የኢትዮጵያ ጉዳይ ✿✿ ሃገራቸውን በምንም ነገር ለድርድር አያቀርቡም፡፡ ህዝቡም አፈሩም ሲነካባቸው ያማቸዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጋር በቅርበት እንተዋወቃለን፡፡ በፖለቲካ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን በግል ባህሪው የሚገርም ነው፡፡ አለመታደል ሆኖ የሃገራችን ፖለቲካ የመጠላለፍና የክፋት ማሳያ ሆኖ እስካሁን ቀጥሎ ሳይ እና የይልቃልን መልካምነት አስተዋይነት የዋህነት ስመለከት ይገርመኛል ፡፡ ክፋት ቂምና ጥላቻ የለበትም ፡፡ያለምንም ማጋነን ኢንጅነር ብልህ እና አስተዋይ መሆኑን የሚያውቁት ይመሰክራሉ፡፡
ኢ/ር ጌታነህ ሰማያዊ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የፌደራል ዱላ ከማያልፉት ፣ የደህንነት ማስፈራሪያ ያልበገሩት ታጋይ ነው፡፡ ይድነቃቸው ከበደ ማውራት ብቻ ሳይሆን መስማት የሚወድ ታሪክ ማንበብ ማስነበብ የሚቀናዉ የህግ ክፍል ሹም ነው፡፡ እያስፔድ ድምፁን አጥፍቶ የ ኢህአዴግን ስርአት የሚታገል ወጣት ነው፡፡ አቤል እምቢ ለሃገሬ ፣ወሮታው፣ ብርሃኑ ፡ ፍቅሬ ✿✿
ምኞት…. ሴቶች የጣይቱ ልጆች ወኔያቸው ይገርመኛል ፡፡
ሰማያዊዎች እርስ በእርሳቸው መተሳሰብን ያውቁበታል፡፡ ወይንሸት ታስራ በነበረበት 1 ወር ውሰጥ ሁሉም ከጎኗ ነበሩ፡፡ ሰብሰብ ? ብለዉ ከተቀመጡ በአብሮነታቸው ውስጥ የወሬያቸው ርእሰ የሀገራችን ጉዳይ የ ህዝባችን & ጉዳይ ነው፡፡
ሰማያዊዎች የሚከተሉት ርእዮተ አለም ትክክል ይ ሁንም አይሁንም፡ ፓርቲው ተፍካካሪ ፖርቲ ይሁንም አይሁንም ፡አባላቱ ለፖለቲካ ይመጥኑ አይመጥኑም ደፍሬ መናገር የሚችለው አንድ ነገር አለ፡፡ እነርሱ ከሁሉም የተሻሉ እና የበለጡ ናቸው ፡፡ ወጣትነታቸውን ለሃገራቸው ገብረዋል፡፡ ራሳቸውን ለሚወዱት ህዝብ ሰውተዋል፡፡ የራሳቸውን ፍላጎት እና ስኬት ለኢትዮጵያ ሸጠዋል ፡፡ ፍላጎታቸውን ለኢትዮጵያ ገድበዋል፡፡ ደማቸውን እያዘሩ ፣እየተቀጠቀጡ፣ እየተገረፉ፣ እየታሰሩ፣ ምራቅ እየተተፋባቸው፣ ስድብ እየተጋቱ፣ ካለማደንዘዣ እየተሰፉ፣ በቤተሰቦቻቸው ፊት እየተሰደቡ፣ እንደ ወንበዴዎች ቤት ቤታቸው በብጫቂ ወረቀት እየተፈተሸ፣ እየተረገጡ ፣ ተለጣፊ ስም ተሸክመው ማጎሪያ ቤት እየታገቱ፣ ጨለማ ቤት በረዶ ክፍል እየታሰሩ ፣ እየተሰቃዩ በመከራቸው ለኢትዮጵያ ብሩህ ዘመን ሊያመጡ ራሳቸውን ለእርድ አቀረቡ፡፡ ይህን ሁሉ መከራ እንደሚደርስ ቀድመው ያውቃሉ፡፡ ግን ለኢትዮጵያ ሲሉ በእነ አጼ ቴዎድሮስ ፣በእነ ዮሃንስ ፣በእነ ምንሊክ መሬት ቆመው ጉዟቸው ቀራኒዮ ሊሆን በደም ማህተም ምለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ያንቺን ክፉ ከማይ ሞቴ ይቅደም ብለው መንገድ ጀምረዋል ፡፡ በኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ምለው በቆመችበት አጥንት ሉአላዊነታችን ይረጋገጥ ራሳቸውን በፌዴራል እያስረገጡ ዛሬም በመንገድ ላይ ናቸዉ ፡፡ ዝም ላለችው ፣ አንገቷን ለደፋችው፣ ጮሆ ለማውራት ላልታደለችው፣ በድህነት ለተዘፈቀችው፣ በረሃብ ለምትማቅቀው ፣መልካም አስተዳደር ለናፈቃት ፣ህዝቦቿ በባህር አውሬ ለተናጠቋት ፣መሬቷ ዳር ድንበሯ ለተደፈረው ህዝቧ ማቅ ለለበሰችው…ኢትዮጵያ ሰማያዊዎች ገንዘባቸውን ያይደለ ወርቃቸውን ያይደለ ራሳቸውን እየገበሩ ነው፡፡ እነርሱ አልታሰሩም! ኢትዮጵያ ናት የታሰረችው ኢትዮጵያ ናት የቆሰለችው ኢትዮጵያ ናት የደማችው ኢትዮጵያ ናት
ኢትዮጵያ ማለት እኔ
ኢትዮጵያ ማለት አንቺ
ኢትዮጵያ ማለት አንተ
ኢትዮጵያ ማለት እናንተ
ኢትዮጵያ ማለት መሬቱ መልከአ ምድሩ ዉሀውው ፍቱልኝ ሃገሬን ፍቱልን ኢትዮጵያን እምዬን ፉቱልን

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on December 9, 2014
  • By:
  • Last Modified: December 9, 2014 @ 7:56 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar