ፍትሕ ለሐና!
ገደል ውስጥ ተወርውራ በጀርባ አጥንቷ ላይ ጉዳት የደረሰባት ጠጅነሽ የወግነህ የሕክምና የምርመራ ውጤቷ ብዙም ተስፋ የሚሰጥ አይደለም የህክምና ባለሙያዎች የጀርባ አጥንቷ የተሰበረ ሲሆን ቆማ የመሄድ ተስፋ እንደማይኖራት ገልጸዋል፡፡ እጅግ አሳዛኝ ነው ……ለምን???…. ጠጅነሽ የደሃ ቤተሰብ ናት ተምራ ሰርታ ትልቅ ደረጃ የመድረስ ቤተሰቦቿን የመርዳት ትልቅ ተስፋ የነበራት ታዳጊ ወጣት .. ለምን ??? ………..
ለጠጅነሽ በርካታ ሰዎች እየደወሉ ለመርዳትም ቃል እየገቡ በአካልም እየተገኙ እየጠየቁ ነው በጎ ፍቃደኛ ሐኪም በቀን ሁለቴ እየተመላለሱ የሕክምና እርዳታ የሚሰጧት ነርስ ቀጥሮ አስፈላጊውን እንክብካቤ ና መድሓኒት እያቀረበ ነው፡፡
ሁሌም ከጠጅነሽ ጎን የሆነችው ማርታ ታደሰ ከአሜሪካ ሐገር ለጠጅነሽ የዊልቸር ልገሳ የሚያደርግላት ሰው አግኝታለች፡፡
ጠጅነሽ እና ቤተሰቦቿ እርዳታ እና ድጋፋችን ያስፈልጋቸዋል፡፡ ጠጅነሽ በደረሰባት ጉዳት የጀርባ አጥንቷ ቢሰበርም ሕልሟ እንዳይሰበር ትምህርቷን እንድትቀጥል ትልቅ ደረጃ እንድትደርስ የሚያስፈልጓትን ነገሮች ሁሉ ለማሟላት ሐዘናችን ቁጭታችን ብቻ ሳይሆን ልገሳችን ከምንጊዜም በላይ ያስፈልጋታል፡፡
0132001059100
Awash bank / olompiya branch
Belayneh teklewold For Tejnesh lewogeneh
የበለጠ መረጃ የምትፈልጉ 0910805732 / 0938934282 መደወል ትችላላችሁ
ፍትሕ ለሃና እና በአስገድዶ መድፈር በጠለፋ እና በጥቃት ህልማቸው እና ሕይወታቸው ለተቀጨባቸው ሁሉ!
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating